SARE WANA Promotion

SARE WANA Promotion አዝናኝ አስቂኝና አስተማሪ የሀዲይሳና የአማረኛ ቀልዶች ይለቀቃሉ በተጨማሪ
ፖለቲካዊ ፣ማህበራዊ፣ኤኮኖሚያዊ መረጃዎችን እናደርሳለን/Amharic Drama � Also Every day we release photos of Ethiopian artists
(1)

💥የአርሰናል ደጋፊዎች ይህን ፎቶ ዝም ብለው አያልፉትም🤗
11/01/2025

💥የአርሰናል ደጋፊዎች ይህን ፎቶ ዝም ብለው አያልፉትም🤗

❝ አባይ ዳሩ ዳሩ ያበቅላል ጠንበለል ፤ሊጉ የአርሴ ነው ምቀኛ ገለል በል!! ❞ 😆😆😆ታላቁ ክለብ አርሰናል በሚወዱት ደጋፊዎቹ ልብ ላይ ፤ በሚጠሉት ሰዎች ጨጓራ ላይ ለዘላለም ይኑር 🤣🤣😭
11/01/2025

❝ አባይ ዳሩ ዳሩ ያበቅላል ጠንበለል ፤
ሊጉ የአርሴ ነው ምቀኛ ገለል በል!! ❞ 😆😆😆

ታላቁ ክለብ አርሰናል በሚወዱት ደጋፊዎቹ ልብ ላይ ፤ በሚጠሉት ሰዎች ጨጓራ ላይ ለዘላለም ይኑር 🤣🤣😭

💥የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ይህን ፎቶ ዝም ብለው አያልፉትም💪
11/01/2025

💥የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ይህን ፎቶ ዝም ብለው አያልፉትም💪

አዲስ ተከታታይ ድራማ ነው 💥
10/31/2025

አዲስ ተከታታይ ድራማ ነው 💥

Nigist Episode 3 | ንግስት ክፍል 3 – New Ethiopian Drama 2025 Presented by to Art Meda | And Turn ON Notif...

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ መልክአ ምድርን፣ ታሪክን፣ ህጋዊነትንና መብትን መሰረት አድርጎ ምላሽ ማግኘት ያለበት ትክክለኛ ጥያቄ ነው (ሆሳዕና ፤ ጥቅምት 21/2018) ፡- የኢትዮጵያ የባ...
10/31/2025

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ መልክአ ምድርን፣ ታሪክን፣ ህጋዊነትንና መብትን መሰረት አድርጎ ምላሽ ማግኘት ያለበት ትክክለኛ ጥያቄ ነው

(ሆሳዕና ፤ ጥቅምት 21/2018) ፡- የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ መልክአ ምድርን፣ ታሪክን፣ ህጋዊነትንና መብትን መሰረት አድርጎ ምላሽ ማግኘት ያለበት ትክክለኛ ጥያቄ መሆኑን በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የሚሰሩ ምሁራን ገለፁ፡፡

ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነቷን ለማረጋገጥ መንግሥት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ መግለፃቸው ይታወሳል።

በባህር በር ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ሙሉአለም ኃይለማርያም እንደገለፁት ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነቷን የማረጋገጥ ህጋዊም ሆነ ታሪካዊ መብት አላት።

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት የቀጠናውን የልማት ትስስር የሚያጎለብት በመሆኑ በቀናነት ምላሽ ማግኘት እንደሚገባውም ነው የገለጹት፡፡ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ከልማት ትስስር አልፎም የቀጣናውን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ መልክአ ምድርን፣ ታሪክን፣ ህጋዊ መብትን መሰረት አድርጎ ምላሽ ማግኘት የሚያስችል ትክክለኛ ጥያቄ መሆኑንም አስረድተዋል። በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ መምህር ጌታሁን አበራ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት መብት ዓለም አቀፋዊ የህግ ድጋፍ እንዳለው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በጋራ ተጠቃሚነትና አብሮ በመልማት ዲፕሎማሲያዊ መርህ መመራቱንና የበርካቶች ድጋፍ ማግኘቱንም አንስተዋል።ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ ለመንግስት ብቻ የሚተውና የአንድ ወቅት አጀንዳ ባለመሆኑ የዜጎች የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባም ነው የመከሩት።

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በዘላቂነት አስጠብቆ ለማስቀጠል በመንግሥት የሚደረጉ ጥረቶች የተተኪውን ትውልድ ተስፋ ጭምር ያገናዘበ መሆኑንም መምህሩ ተናግረዋል።

የባህር በር ባለቤትነትን የማረጋገጥ ጥያቄው ከቀጠናው ሀገራት ጋር በትብብር ለማደግ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑንም አክለዋል።

የቢሮውን ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት ‼️

📌 በዌብሳይት https://www.cergcab.et/

📌በቴሌግራም https://t.me/CERGCAB

📌 በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100070605291100&mibextid=ZbWKwL

📌 በቲውተር https://twitter.com/CabCerg2678

📌 በቲክቶክ tiktok.com/

📌 በዩቲዩብ https://youtube.com/?si=Ipdg3R3A3hpPQEUV

📌 በኢንስታግራም https://www.instagram.com/cergcab/profilecard/?igsh=MWNseXBlaW05dnM3MA==

አማራጮችን ይጠቀሙ!!

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን !!

ከደቡብ አፍሪካ ለጊምቢቹ የህዝብ ቤተመጻሕፍት ግንባታ የገራድ ፀጋዬ ሄራሮ ልጆች ማለትም:-1.ተስፋዬ ፀጋዬ ሄራሮ 10,000 ብር2. እርስቱ ፀጋዬ ሄራሮ 10,000 ብር3. ሀብቴ ፀጋዬ ሄራሮ...
10/31/2025

ከደቡብ አፍሪካ ለጊምቢቹ የህዝብ ቤተመጻሕፍት ግንባታ የገራድ ፀጋዬ ሄራሮ ልጆች ማለትም:-

1.ተስፋዬ ፀጋዬ ሄራሮ 10,000 ብር

2. እርስቱ ፀጋዬ ሄራሮ 10,000 ብር

3. ሀብቴ ፀጋዬ ሄራሮ, 10,000 ብር በድምሩ 30,000 ብር ለግሰዋል።

እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።

10/31/2025

ከትዝታው ማህደር ከ5 ዓመት በፊት የተሰራ ነው ...🤗
#ጊምቢቹ

💥Habayyi Qaramttito 🎂   መልካም ልደት ለአንተ 🎂🎂
10/31/2025

💥Habayyi Qaramttito 🎂
መልካም ልደት ለአንተ 🎂🎂

10/30/2025

ቆየት ካሉ ሀዲይሳ ድራማዎች መሃል 🤣

የፈለገ ያህል ግዜ ይፍጅ እንጂ ያ የፀለይክበትን ህይወት ትኖረዋለህ!
10/29/2025

የፈለገ ያህል ግዜ ይፍጅ እንጂ ያ የፀለይክበትን ህይወት ትኖረዋለህ!

ለጊምብቹ ህዝብ ቤተ-መጽሐፍት ግንባታ 80,000 ብር ከአሜሪካ 👉በአቶ ቦጋለ ተፈሪ ቤተሰብ ስም ታላቅ ወንድማችን ኮሎኔል ንገቱ ቦጋለ (ከሰሜን አሜሪካ) እና በላቸው ቦጋለ በጋራ ለጊምብቹ ህ...
10/29/2025

ለጊምብቹ ህዝብ ቤተ-መጽሐፍት ግንባታ 80,000 ብር ከአሜሪካ 👉በአቶ ቦጋለ ተፈሪ ቤተሰብ ስም ታላቅ ወንድማችን ኮሎኔል ንገቱ ቦጋለ (ከሰሜን አሜሪካ) እና በላቸው ቦጋለ በጋራ ለጊምብቹ ህዝብ ቤተ-መጽሐፍት ግንባታ 80,000 ብር አበርክተዋል። እናመሰግናለን!

 #ጊምቢቹ  በበጀት እጥረት ምክንያት ግንባታው ቆሞ የነበረው የጊምቢቹ የህዝብ ቤተመጻሕፍት ግንባታ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ግንባታው ተጀመረ። በማህበራዊ ሚዲያዎች በተደረገ ንቅናቄ ...
10/29/2025

#ጊምቢቹ በበጀት እጥረት ምክንያት ግንባታው ቆሞ የነበረው የጊምቢቹ የህዝብ ቤተመጻሕፍት ግንባታ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ግንባታው ተጀመረ።

በማህበራዊ ሚዲያዎች በተደረገ ንቅናቄ ከ1,957,000 ብር በላይ መሰብሰቡን አስተባባሪ ኮምቴ በግንባታው ማስጀመሪያ ገልጿል።

ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም ጊምቢቹ:-

የጊምቢቹ የህዝብ ቤተመጻሕፍት ግንባታ የጊምቢቹ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አየለ ገዴ፣የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ በቀለ ሀብታሙ፣ረዳት የመንግስት ተጠሪዎች አቶ ተመስገን ታምራትና አቶ አማኑኤል ኤርጃቦ፣የቤተመጻሕፍት ግንባታ አስተባባሪዎች ዶክተር ክበሞ ዴታሞ፣ቄስ በየነ ኮብሮ፣አቶ ጥጋቡ አሰፋ፣አቶ ታምሬ ታደሰ፣የጊምቢቹ አጠቃላይ ሁለተኜ ደረጃ ት/ቤት ዋና ርዕሰ መምህር ደነቀ አቦሴ፣ኮንትራክተሮችን ጨምሮ የተለያዩ አካላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ግንባታው በይፋ ተጀምሯል።

በማስጀመሪያው ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጊምቢቹ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በመልዕክታቸው ህዝቡን ይዘን የተለያዩ የልማት ስራዎችን ለመስራትና ከግብ ለማድረስ እንደሚሰራ ገልፀው በማህበራዊ ሚዲያ በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ካላቸው ቀንሰው ገንዘባቸውን የለገሱ አካላትን በከተማ አስተዳደር ስም አመስግነው እኛም የሚጠበቅብንን ኃላፊነት በመወጣት ፕሮጀክቱን ከግብ ለማድረስ ይሰራል ብለዋል።

የመንግስት ተጠሪ አቶ በቀለ ሀብታሙ በበኩላቸው የሁላችንም ተልዕኮ መሆን ያለበት ፕሮጀክት መሆኑን አብራርተው የትውልድ አሻራ በመሆኑ ሁላችንም ተረባርበን ከግብ ማድረስ አለብን ብለዋል።

የፕሮጄክቱ አስተባባሪ ዶክተር ክበሞ ዴታሞ በበኩላቸው በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚገኙ ልማት ወዳድ ወንድሞችና እህቶች አስተባባሪ ኮምቴ ያደረገውን የድጋፍ ጥሪ በመቀበል ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ በአስተባባሪ ኮምቴ ስም ምስጋናቸውን አቅርበው በዚህ ድንቅ የትውልድ አሻራ በሆነው ስራ የበኩላቸውን በመወጣት አሻራቸውን እንድያሳርፉ ጠይቀዋል።

በተጨማሪ ፕሮጀክቱ የሁላችንም በመሆኑ በገንዘብ ፣በአይነትና በጉልበት ጭምር በመሳተፍ ሁሉም የከተማውና የአከባቢው ማህበረሰብ በመሳተፍ ፕሮጄክቱን ለመጨረስ በሚደረገው እርብርቦሽ በመሳተፍ አጋርነቱን ማሳየት እንዳለበት ጭምር ዶክተር ክበሞ አሳስበዋል።

Address

America
Las Vegas, NV

Telephone

+251954743191

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SARE WANA Promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share