
09/24/2025
ይሄን ጀብድ እያዩ አለመኩራት አይቻልም. ወሎ ቤተ አማራ ሁሌም በስራቸው አይታሙም. ከፈተኛ ዝግጅት ያደርጋሉ ከእቅዳቸው በላይ ይፈጽማሉ.
በጠንካራ አደረጃጅቱ እንደ ምሳሌ ሲጠቀስ የነበረውን የምዕራብ አማራ ክፍል ደግሞ በውስጡ በተሰገሰጉ ባንዳዎችና የገንዘባና የዝና ታጋይ እየተፈተነ መመናመኑን ቀጥሎበታል. ጭራሽ ባንዳ ማረክነ እያሉ ሲያደነቁሩን ቆይተው በ1 ሚሊዮን እንደቀየሩት ተነግሯል እንግዲህ ምን ይባላል. ለትግሉ ብለው ህይወታቸውን ያጡን እያሰቡ ከማንባት ሌላ ምን ይደረጋል. ራስን መፈተሽና ግምገማ ፍቱን መድሀኒት ነው.
በነገራችን ላይ ትልቅ ድል ሚገኘው ከልብ ሲታገሉ ነው አንዳንድ ቦታ ድል ሚርቀውም ሳይሞት ለፈንድና ለሪፖርት ሚሆን ጥይት አጩሆ ለመመለስ ሲሞከር ነው. ትግል እንዴት ነው ካልክኝ የዛሬውን የቤተ አምሀራ ተጋድሎና አብይን አቋርጠው ዳሞት የዘለቁ የቢዛሞ ፋኖዎችን ምሳሌ እነግርሀለው. ለነገሩ በሰባሰቡ አንድም በማገት ወይም ለግዳጅ የተሰጠን ጥይት ተሽጦ የተጠራቀመን ብር ሳይበላ ወዴት?😎 ይህን ስል አላስፈላጊ መስዋትነትን መክፈልን እየደገፍኩ አይደለም ቢቻል አንድም የወገን ሀይል አይሙት !!