
09/24/2025
የኢራን ጦር ምክትል አዛዥ : - "እስራኤል ከአሜሪካ እና ከኔቶ ድጋፍ ውጭ እኛ ጋር ጦርነት ማካሄድ አትችልም።"
የኢራን ከፍተኛ አዛዥ እስራኤል ከኔቶ እና ከአሜሪካ ድጋፍ ውጭ ለመዋጋት አቅም እንደሌላት ገልፀው ከዚህ በመቀጠል ሊፈጠር የሚችለው ግጭት “ከዓለም አቀፋዊ እብሪተኝነት” ጋር የሚደረግ ትግል እንደሆነ ገልፀዋል ።
የኢራን ጦር ምክትል አዛዥ ራር አድሚራል ሀቢቦላህ ሳይያሪ በ12 ቀናት ጦርነት ኢራን በአለም አቀፍ ወንጀለኛው መንግስት ላይ “ከፍተኛ ድብደባ” አድርሳለች በመጨረሻም ጠላት ተጨፍልቋል ብለዋል።
ሰኔ 13 ቀን እስራኤል ለ12 ቀናት የፈጀ ጦርነትን በማነሳሳት ወታደራዊ አዛዦችን፣ የኒውክሌር ሳይንቲስቶችን እና ሲቪሎችን ጨምሮ በትንሹ 1,064 ኢራናውያን ሰማዕት ሆነዋል።
አዛዡ ጥቃቱን ተከትሎ ኢራን ከባባድ የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ የሽብር ጥቃቱን በሰኔ 24 በተሳካ ሁኔታ እንዲቆም አስገድዳለች ብለዋል።
አድሚራል ሳይያሪ አክለውም ጠላት (አሜሪካ) አንድ ጊዜ ሳዳምን አንድ ጊዜ ደግሞ የጽዮናውያንን አገዛዝ ተጠቅሞ በውክልና ኃይሎችን በመላክ ወደ እኛ ለግጭት መጥቷል ብለዋል። በተጨማሪም IRGC እና ጦር አለቆች ከዚህ በኃላ በኢራን ላይ ለሚሰነዘረው ትንሽ ጥቃት ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ቃል መግባታቸው ገልፀዋል።
አድሚራል ሳይያሪ " ዛሬም ቢሆን አለም እነዚህ መመሳሰሎች አቀፋዊ እብሪተኝነት ከፊታችን ቆሟል። የምንዋጋው ከትንንሽ ጠላቶች ጋር ሳይሆን እብሪተኞች ጋር በመሆኑ ኩራታችን ነው" ብለዋል።
ለተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎች ቴሌግራም
👇👇👇
t.me/Etmusliminsider