Ethiopia daily News

Ethiopia daily News God's first

01/04/2024

ከቋሚ ሲኖዶስ ነተሰጠ መግለጫ ሙሉ ቃል
እንደሚከተለው ይነበባል፦

| መንፈሰ ሰላም ማዕከለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወማዕከለ ቤተ ክርስቲያን… ውእቱ… የሰላም መንፈስ በኢየሱስ ክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ነው:፡ (መጽሐፈ ምሥጢር)

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በዚህ የሕይወት ቃል አማካኝነት የሰላም መንፈስ በኢየሱስ ክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል በየዘመናቱ ያለና የሚኖር መሆኑን እንመለከታለን፡፡ የዚህም መንፈሰ ኃይል በቤተ ክርስቲያን መኖር ሕማመ ነፍስ በሌለበት ምግባረ ሃይማኖት በፍቅር እንድንኖር ለምንሻው ሁሉ እግዚአብሔር በምልዓት በሚከብርበት ቤተ መቅደስ በኩል የሚሰማው የሰላም ጥሪ በማያቋርጠው የመንፈሳዊ ኑሮ ሂደት ለመንፈስ አንድነት፣ ለአካላዊ ሕብረት የሚጠቅም የሕይወት ምሰሶ ነው፡፡ በመሆኑም ‹‹ወብነ ክሂል ከመ ንቅትል ኅሊና ሰይጣናዌ …ሰላምን የሚያሳጣ ክፉ ሓሳብን በቤተ ክርስቲያናችን መካከል ባለው ሰላም ከእኛ የማራቅ ችሎታ አለን›› ተብሎ እንደተጻፈው ፍጥረተ ሰብእ ሕይወቱን ለበጎ በሚቀርጸው ሥርዓተ ሃይማኖት በመመራት፣ የሰላምን አስፈላጊነት በትምህርት በድርጊት በመግለጽ ባልተዛነፈ ሰብእና በተሟላ ሰላም መኖር የሚችልበት ክሂል ያለው ፍጡር መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ (ዜና አበው)

የሰላም መንፈስ በመካከሏ ሆኖ ከስሕተት የሚጠብቃት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም አመለካከቱ ስሕተት ንግግሩ ሐሰት በሆነው ዓለም የጽድቅና የሰላም ባሕርይ መገለጫ ነው፡፡ ልጆቿ በሰላም በፍቅር በታነጸ ዕለታዊ ሕይወት እንዲኖሩ በማድረግ ሰላም የደግነት ሁሉ አክሊል የመንፈሳዊ ምግባራት ዘውድ መሆኑን ስታውጅ መኖሯን የታሪክ መዛግብት፣ ዕውነትን ለመግለጥ የሚተጉ ጸሐፍት ከመቅድም እስከ ህዳግ ይመሰክሩላታል። መሪዋና አጽናኟ ከሆነው መንፈስ ቅዱስ በተገኘው የሰላም እሴት በእምነታቸው ጸንተው በምግባር በትሩፋት አጊጠው የሚኖሩት ማኅበረ ካህናትና ማኅበረ ምእመናንም የረጅም ዘመናት የቅድስና ታሪክ ጉዞዋ ማሳያዎች ናቸው። የእውነትና የሰላም አምድ እንደመሆኗም በሀገራችን እየተከሰቱ ያሉ አለመግባባቶችንና የእርስ በእርስ ደም መፋሰሶች እንዲቆሙ የሰላም ጥሪ ከማድረግ ጀምሮ ምህላ፣ ጾምና ጸሎት በማወጅ እግዚአብሔር ለሀገራችንና ለሕዝባችን ሰላምን እንዲሰጥ ስትማጸን ቆይታለች። የየዕለት አገልግሎቷም ይህንኑ መሠረት ያደረገ ነው።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላም መንፈስ በመካከሏ እንዲሆን አድርጎ ወኃቤ ሰላም መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት ስለሆነ በዓለም ሁሉ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ የክብር ስፍራውን ይዞ የሚቀጥል ቀዳሚና ዐቢይ ተልእኮዋ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን ።

በመጨረሻም ሰላም የሚጸናው ማንኛውም ማኅበረሰብ እርስ በእርሱ በመተሳሰብና በፍቅር በእውነተኛ መግባባትና በፍትሕ በርኅራሄና በመከባበር አብሮ መኖር ሲቻል ነውና በወንድማማችነት መካከል ጠብን ከሚዘሩ ጥላቻንና መራራቅን ከሚያሰፉ ንግግሮችና ድርጊቶች በመቆጠብ ሁሉም የማኅበረ ሰብእ ክፍል እግዚአብሔር ለሀገራችን ፍጹም ሰላምን ይሰጣት ዘንድ በጸሎት እንዲተጋ ቋሚ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡

ከምን ጊዜውም በላይ ሰላምና ፍቅር በሀገራችን እንዲሰፍን በአንድነት ሆነን የምንሠራበት ወቅት ላይ በመሆናችን በመጪዎቹ ዐበይት በዓላት፣ በዘወትሩ መንፈሳዊ አገልግሎት ሁሉም በየደረጃው ያላችሁ የቤተ ክርስቲያናችን አባቶችና አገልጋዮች "ወፍሬሃኒ ዘጽድቅ በሰላም ይዘራዕ ለእለ ይገብርዋ ለሰላም ... የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉ ሰዎች በሰላም ይዘራል" በሚለው ሐዋርያዊ ቃል መሠረት በየዐውደ ምሕረቱ ሰላምንና እርቅን በመስበክ በሀገራችን ኢትዮጵያ ያለው ችግር እንዲወገድ፣ ማኅበራዊ ሰላም እውን እንዲሆን የበኩላችሁን ጥረት እንድታደርጉ ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል። ያዕ 3÷18

እግዚአብሔር ለሀገራችን ሰላምን ጽድቅን፣ፍቅርንና ፍትሕን ይስጥልን

ታኅሣስ 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ

ለተጨማሪ መረጃ፦
1. ድረገጽ:- https://eotceth.org
2. ፌስ ቡክ ገጽ:- የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation
3. ስልክ፦ +251111262652 | +251111262818
4. ኢሜል፦ [email protected]
5. ፖስታ፦ 1283 አዲስ አበባ

10/24/2023

Ye sewuyewu nigigir le astewayi sewu timirt newu, le mahayim activist degimo agenda newu...

የበረራ ስራዋን ለማቆም ወስና የነበረችዋ ሆስተስ በአየር መንገድ ውስጥ በደረሰባት የመኪና አደጋ ህይወቷ አለፈእግዚአብሔር ከእንዲህ አይነት አሳዛኝ አጋጣሚ ይጠብቀን!የቅርብ ወዳጄ ጓደኛ የሆነ...
08/14/2023

የበረራ ስራዋን ለማቆም ወስና የነበረችዋ ሆስተስ በአየር መንገድ ውስጥ በደረሰባት የመኪና አደጋ ህይወቷ አለፈ

እግዚአብሔር ከእንዲህ አይነት አሳዛኝ አጋጣሚ ይጠብቀን!

የቅርብ ወዳጄ ጓደኛ የሆነችና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአራት አመታት በላይ በበረራ አስተናጋጅነት ስታገለግል የነበረች ቅድስት ከበደ የተባለች ሆስተስ ከትናንት ወዲያ ማለትም በ6/12/2015 ለሊት 12:30 ላይ በበረራ ከሄደችበት ቻይና ሼንካይን ወደ ኢትዮጵያ በሰላም ገብተው ሻንጣዋን እየገፋች ውጪ መኪና ይዘው ወደሚጠብቋት ቤተሰቦቿ እና ጓደኛዋ እየተሻገረች እያለ የሰራተኛ ሰርቪስ በሆነ በራሱ በአየር መንገዱ መኪና ተገጭታ ሕይወቷ አልፏል።

በሰአት ከ15 ኪ ሜ በላይ በማይነዳበት የሰራተኞች ፓርኪንግ ሎት እንዲህ አይነት ያለተጠበቀ ድንገተኛ ሃዘን ማጋጠሙ ለጓደኛዋ፣ለቤተሰቦቿና ለአየር መንገዱ ሰራተኞች ቅስም ሰባሪ ሆኖ አልፏል።

ቅድስት የበረራ ስራዋን ለማቆም ወስና የነበረች፣ እንደውም ይህ የቻይና በረራዋ የመጨረሻዋ እንደነበረና ወደ ትዳር ሕይወት ለመግባት ከጓደኛዋ ጋር ዝግጅት ላይ እንደነበሩ ስሰማ በሕይወት ውስጥ ነገ የሚባል ነገር ትርጉም አልባ ተረት ሆኖ ነው የተሰማኝ።

ተስፋ ሰንቆ ሲጠብቃት ለኖረው ጓደኛዋ፣ለቤተሰቦቿ እና ለወዳጅ ዘመዶቿ ሁሉ መፅናናትን እመኛለሁ።

Via ተስፋሁን ፀጋዬ Nati Manaye

በመዲናዋ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚፈጸምባቸው ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰድ መጀመሩ ተገለጸ   |  የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመተባበር በከተ...
08/10/2023

በመዲናዋ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚፈጸምባቸው ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰድ መጀመሩ ተገለጸ

| የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመተባበር በከተማዋ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚፈጸምባቸው ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ቢሮው ከነባሩ የአገራችን ባህል፣ ወግ፣ የአኗኗር ስርዓት እና ኃይማኖቶች ባፈነገጠ መልኩ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚያስፈጽሙ ሆቴሎች ፣ ሬስቶራንቶች፣ ፔንሲዮኖችና መሰል የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ከኅብረተሰቡ በሚደርሰው ጥቆማ መሰረት ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት አስተማሪ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ነው የገለጸው።

የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የግብረ-ሰዶም ተግባር መፈጸምና ማስፈጸም በኢትዮጵያ በሥራ ላይ ባሉ ሕጎች የተከለከለ መሆኑን ገልጾ፤ “ይህንን አስጸያፊ በሰውም በአምላክም ዘንድ የተጠላ ደርጊት በሚፈጽሙና በሚያስፈጽሙ የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቆማት ላይ ካለ አንዳች ርህራሄ እርምጃ መውሰዱን አጠናክሬ እቀጥላለሁ” ብሏል።

በዚሁ መሰረት፤ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ውስጥ በሚገኝ "አበባ ገስት ሐውስ" በሚባል የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቋም ላይ ከኅብረተሰቡ ለሰላምና ጸጥታ ቢሮ በደረሰ ጥቆማ መሰረት እርምጃ የወሰደ ሲሆን፤ የተቋሙን ኃላፊ በከተማው ፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ በማድረግ ምርመራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተነግሯል።

ከግብረሰዶም ፀያፍ ተግባር ጋር የተገናኘ መረጃ እና ጥቆማ ያለው ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በግንባር በመቅረብ እንዲሁም በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 987 እንዲሁም በ011-1- 11-01-11 እና 011-5-52-63-02 በመጠቀም መረጃና ጥቆማ መስጠት እንደሚችል ከዚህ በፊትም የተገለጸ ሲሆን፤ አሁንም ኅብረተሰቡ ይህንኑ አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል።

ዕጣን ተብሎ ሊሸጥ የተዘጋጀ ከ100 ከረጢት በላይ የተፈጨ እምነበረድ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ***  በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከዕጣን ጋር ተደባልቆ ሊሸጥ የተዘጋጀ ከ100 ከረጢት በላይ የተ...
08/10/2023

ዕጣን ተብሎ ሊሸጥ የተዘጋጀ ከ100 ከረጢት በላይ የተፈጨ እምነበረድ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
***
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከዕጣን ጋር ተደባልቆ ሊሸጥ የተዘጋጀ ከ100 ከረጢት በላይ የተፈጨ እምነበረድ በተለያዩ ቦታዎች በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በክፍለ ከተማው ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ቀበሌ 18 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ እና ፖሊስ በህግ አግባብ ባከናወነው ፍተሻ በአነስተኛ የቆርቆሮ ቤት ውስጥ የተቀመጠ 57 ከረጢት የተፈጨ ዕምነበረድ ከቀናት በፊት በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚሁ አካባቢ በተመሳሳይ በሌላ የቆርቆሮ ቤት ውስጥ ተዘጋጅቶ የተቀመጠ የተፈጨ ዕምነበረድ መኖሩ ከህዝብ ጥቆማ የመጣ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ እና ማስረጃ ለማሰባሰብ ሲባል ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ዕለትና ሰዓት ድረስ ቤቱ ታሽጎ በፖሊስ አባላት እየተጠበቀ ይገኛል፡፡

ትናንት ነሃሴ 3 ቀን 2015 ዓ/ም ለፖሊስ በመጣ ጥቆማ መነሻነት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ዕጣን ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተመሳሳይ መልኩ ለገበያ ሊቀርብ የተዘጋጀ 52 ከረጢት በቆርቆሮ ቤት ውስጥ በብርበራ ሊያዝ ችሏል፡፡

የተፈጨ ዕምነበረድን ዕጣን አስመስሎ ለመሸጥና ህብረተሰቡን ለማታለል በተፈፀመው በዚህ ህገ ወጥ ተግባር የተጠረጠረ አንድ ግለሰብ ተይዟል፡፡ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋልም የምርመራ ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ለውጤቱ መገኘት የህብረተሰቡ ሚና የጎላ መሆኑን ያስታወሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ የከተማችንን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ በመደበኛነት የሚከናወኑ የፖሊስ ተግባራትን በመደገፍ መላው የከተማችን ነዋሪ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ዘገባ፦ዋና ሳጅን ዘላለም አበበ
*
ለፈጣን መረጃዎች:
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
*
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
***

አማካሪ ኮሚቴው ለምክር ቤቱ የቀረበውን የአስቸኳይ ግዜ አጀንዳ አፀደቀ ።(ዜና ፓርላማ)፤ ነሐሴ 03 ቀን 2015 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበውን የሚኒስትሮች ምክ...
08/09/2023

አማካሪ ኮሚቴው ለምክር ቤቱ የቀረበውን የአስቸኳይ ግዜ አጀንዳ አፀደቀ ።

(ዜና ፓርላማ)፤ ነሐሴ 03 ቀን 2015 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበውን
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የምክር ቤቱ አማካሪ ኮሚቴ አጀንዳውን በሙሉ ድምፅ አፀደቀ ።

ሠሞኑን በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ የፌዴራል መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀፅ 1 (ሀ) መሠረት ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 መደንገጉ ይታወሳል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካሪ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ የቀረበውን የአስቸኳይ ግዜ አጀንዳ በተመለከተ የጉዳዩን አሳሳቢነት በጥልቀት አይቶና በሰፊው ተወያይቶ ለምክር ቤቱ ቀጣይ አስቸኳይ ጉባኤ እንዲቀርብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአጀንዳነት በሙሉ ድምፅ ማፅደቁ ታውቋል ፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ https://www.youtube.com/

በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ

ወደ ባህር ዳር እና ጎንደር መደበኛ በረራ ነገ ይጀምራል!   | ወደ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር ...
08/09/2023

ወደ ባህር ዳር እና ጎንደር መደበኛ በረራ ነገ ይጀምራል!

| ወደ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ

አየር መንገዱ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን አስታውቋል።

መንገደኞችም በአቅራቢያቸው በሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮዎች ወይም ወደጥሪ ማዕከል (6787/+251116179900) በመደወል መስተናገድ የሚችሉ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል።

የግብረ ሰዶም ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ  |  በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሶስት ህፃናት ላይ የግብረ ሰዶም ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ  በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተላልፎበ...
08/08/2023

የግብረ ሰዶም ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

| በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሶስት ህፃናት ላይ የግብረ ሰዶም ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተላልፎበታል፡፡

የ43 ዓመት ዕድሜ ያለው ተከሳሹ ወንጀሉን የፈፀመው በክፍለ ከተማው ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ማር ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ግለሰቡ የጎረቤቱ ልጆች የሆኑ የ5፣ የ6 እና የ10 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህፃናትን በተለያዩ ቀናት ከረሜላ እየገዛ በማታለል መኖሪያ ቤቱ ውስጥ አስገብቶ ወንጀሉን ፈፅሞባቸዋል፡፡

ወንጀሉ ከተፈፀመባቸው ህፃናት መካከል የ6 ዓመቱ ህፃን ስለሁኔታው ለወላጅ እናቱ በመናገሩ ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

ይህንን ተከትሎ ሌሎቹ 2 ህፃናትም ተመሳሳይ ድርጊት እንደፈፀመባቸው በመግለፃቸው በሶስት የምርመራ መዝገቦች ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል፡፡

መዝገቡን ሲመረምር የቆየው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የተከሳሹን ጥፋተኝነት በሰው እና በህክምና ማስረጃ በማረጋገጡ በ19 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡

ህብረተሰቡ ከህግና ከማህበራዊ እሴቶች ያፈነገጡ ህገ-ወጥ ተግባራት ሲያጋጥሙ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡

ሀገራችን በህብረ ብሄራዊነቷ የምትታወቅና የተለያዩ ባህሎችና ወጎች ያላት ሀገር ነች፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከማክበረሰቡ ወግና ባህል ያፈነገጡ ድርጊቶች እያጋጠሙ መሆኑን የተመለከተ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑንየአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡

ግብረሰዶማዊነት በሀገራችን ህግ ፍፁም የተከለከና በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር በመሆኑ ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘ መረጃ እና ጥቆማ ያለው ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በግንባር በመቅረብ እንዲሁም በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 987 እንዲሁም በ011-1- 11-01-11 እና 011-5-52-63-02 በመጠቀም መረጃና ጥቆማ መስጠት እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ዘገባ ፡- ዋና ሳጅን ዘላለም አበበ

Fano zirfia be Debre Markos
08/04/2023

Fano zirfia be Debre Markos

የአርሲ ዩኒቨርሲቲ  በዛሬው እለት ለአትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የክብር ዶክትሬት  ዲግሪ ይሰጣል
07/22/2023

የአርሲ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት ለአትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ይሰጣል

ኢትዮጵያ ዛሬ የምታስመርቀው የሳይንስ ሙዚየም በውስጡ ምን ምን ነገሮችን ይዟል?************በመዲናችን አዲስ አበባ አስደናቂ የቀለበት ቅርጽ ያለው ህንጻ እና ማራኪ የጉልላት ቅርጽ ያለ...
10/04/2022

ኢትዮጵያ ዛሬ የምታስመርቀው የሳይንስ ሙዚየም በውስጡ ምን ምን ነገሮችን ይዟል?
************

በመዲናችን አዲስ አበባ አስደናቂ የቀለበት ቅርጽ ያለው ህንጻ እና ማራኪ የጉልላት ቅርጽ ያለው ተደርጎ የተገነባው ማዕከል በአይነቱ አዲስ የሆነው የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም በዛሬው እለት ይመረቃል ::

ሙዚየሙ በ7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በኪነ-ህንጻ ንድፍ ውስጥ ያካተተው ክብ ቅርጽም በማያቋርጥ እድገት ውስጥ ያለን እድገትና የሰው ልጆችን ጥበብ የሚያመለክት ነው።

በተጓዳኝም ኢትዮጵያ በአስገራሚ ፍጥነት በማደግ ላይ ካለው ቴክኖሎጂ ጋር ለመጣመር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይም ነው።

የስነ ጥበብና የሳይንስ ሙዚየሙን አስደናቂ የሚያደርገው ምንድነው ?

👉 ሁለት ግዙፍ ህንጻዎችን በተንጣለለ ስፍራ ላይ ቢያሳርፍም 80 በመቶ የሚሆነው ክፍሉ ከ4ሺህ በላይ በሆኑ ሀገር በቀል ዛፎች፣ እጽዋትና ባሸበረቁ አበቦች የተሸፈነ ስፍራ በመሆኑ አረንጓዴነቱ ጎልቶ ይታያል።

👉 ሙዚየሙ በጥንቃቄ የተዘጋጁ የመኪና ማቆሚያዎች በተጨማሪ በዙሪያው ካሉ የከተማችን ፓርኮች ጋር የሚያገናኘው ውብ የእግረኛ መንገዶች ያሉት ነው።

👉 የአትክልት ስፍራዎቹ ጎብኚዎች አረፍ ብለው ንፋስ የሚቀበሉባቸው ምቹ መቀመጫዎችን እንዲሁም በጥበብ ስራዎች የሚዝናኑባቸውን የስነ ጥበብና የመዝናኛ ቦታዎችን የያዙ ናቸው።

👉 ትልቁ ህንጻ ከ15ሺህ ሜትር ካሬ በሚበልጥ መሬት ላይ ያረፍ ሲሆን አጠቃላይ ስፋቱ 132 ሜትር ያህል ነው።

👉 ከተፈጥሮ ስርዓት ጋር ተስማሚ በሆነ መንገድ ሃይል ከሚያመነጩ የውሃ ግድቦቻችን እንዲሁም በጣሪያው ላይ ከተገጠሙ የጸሀይ ብርሃን ሰብሳቢ መሣሪያዎች የሚያስፈልገው የኤሌክትሪክ አቅርቦት የሚያገኘው ይህ ሙዚየም ተፈጥሮአዊ የሃይል ማስተላለፊያዎችንና ሃይል ቆጣቢ የተፈጥሮ ብርሃንን የሚጠቀም ነው።

ይህ የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም ትላንታችንን፣ ዛሬያችንን እና ነገአችንን በአንድ ላይ አሰናስኖ ሳይንስን ጥበባዊ በሆነ መንገድ፤ ጥበብን ደግሞ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያስቃኝ በመሆኑ አስደማሚ ተሞክሮዎችና አዳዲስ እውቀቶች የሚቀሰሙበት ነው።

09/04/2022

Hasab Journal

08/27/2022

Ethiopian case 😢

Congratulations to all Ethiopians
08/11/2022

Congratulations to all Ethiopians

ከዓለም 3ኛ 🇪🇹 ኢትዮጵያ በኮሎምቢያ ካሊ  ላለፋት ስድስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ በሰነበተው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮናኢትዮጵያ በ6ወርቅ፣ በ5ብር እና 1የነሃስ በድምሩ...
08/07/2022

ከዓለም 3ኛ 🇪🇹 ኢትዮጵያ

በኮሎምቢያ ካሊ ላለፋት ስድስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ በሰነበተው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና
ኢትዮጵያ በ6ወርቅ፣ በ5ብር እና 1የነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎች ከዓለም ሃገራት አሜሪካንን እና ጃማይካን ተከትለን 3ኛ ደረጃን ይዘን አጠናቅቃለች።

እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪካችን ዘንድሮ የተመዘገበው ውጤት ከፍተኛው መሆኑም ተገልጿል።

🥇🥇🥇🥇🥇🥇
🥈🥈🥈🥈🥈
🥉
አትሌቶቻችን ኮርተንባችኋል!!!

መላው የሃገራችን ህዝቦች እንኳን ደስ አለን አላችሁ።

🥇የ5000ሜ. የሴቶች የሜዳልያ አሰጣጥ ስነስርዓት
08/06/2022

🥇የ5000ሜ. የሴቶች የሜዳልያ አሰጣጥ ስነስርዓት


ሰበር ዜናየአባይ ግድብ ሶስተኛው ሙሌት የግድቡን ከፍታ አልፎ ውሀው መፍሰስ ጀምሯል። ሶስተኛው ሙሌታችን በስኬት ተጠናቋል ኢትዮጵያዬ እንኳን ደስ አለሽ!Breaking News ‼️🇪🇹 Ethio...
07/31/2022

ሰበር ዜና

የአባይ ግድብ ሶስተኛው ሙሌት የግድቡን ከፍታ አልፎ ውሀው መፍሰስ ጀምሯል። ሶስተኛው ሙሌታችን በስኬት ተጠናቋል ኢትዮጵያዬ እንኳን ደስ አለሽ!
Breaking News ‼️
🇪🇹 Ethiopia just completed the 3rd round filling of the GERD dam. Congratulations Ethiopia 🇪🇹 👏🏽
ታላቁ_የኢትዮጵያ_ህዳሴ_ግድብ
ዓባይ ዓባይ ዓባይ... ያገር🇪🇹ሲሳይ
🇪🇬🇸🇩ጫጫታ አያስፈልግም 🤨 ከእንግዲህ ራሱ "ሀይድሮጂን ቦምብ" ሆኗል😁😁😁

Address

2905 Preston Road
Madison, WI
53719

Telephone

+16082173785

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia daily News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopia daily News:

Share