10/14/2025
📝ተጀመረ ፦
👉አጠቃላይ መደበኛ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በየዓመቱ በጥቅምት ወር ፣ በሀገርም ፣በውጭም የሚገኙ የየአህጉረ ስብኩቱ ተዋካዮች የሚሳተፉበት ልዩ ጉባኤ ነው ።
👉ይህ ጉባኤ የጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ከመደረጉ በፊት ቀድሞ መደረጉ ፣ አጠቃላይ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ ተልዕኮ እና ተግዳሮት ላይ በግልጽ ተወያይቶ ፣ ሕግ አውጭው እና ሕግ አጽዳቂው የቤተክርስቲያን የመጨረሻው ብይን ሰጪ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ሊቀርቡ የሚችሉ አጀንዳዎች የሚለዩበት ፣
👉በበጀት ዓመቱ የተሰሩ የሥራ አፈጻጸም የሚገመገሙባቸው ፣ ይህንን ጉባኤ ያዘጋጁ የቀደሙ ብሩህ አይምሮ ያላቸው አባቶች ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴውፍሎስ ፣ ከዛም ይህንን መምሪያ ዛሬ ላለበት ደረጃ እንዲደርስ ፈር ከቀደዱ ብርቅዬ የቤተክርስቲያን አባት ሊቀ ጉባኤ አበራ ታሪክ የማይረሳቸው ፣ ስማቸው በደማቅ ቀለም ዛሬም ድረስ የተከተበ ነው ።
👉ከጉባኤው ምን እንጠብቅ ፦ ዛሬም እንደትላንቱ የመምበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መደበኛ ሰበካ መምፈሳዊ ጉባኤ በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ ፣ ተደረገ ፣ ተጀመረ እና አበቃ ብለን እንለፈው ።
👉የብዙዎች እምነት የተለመደ በውዳሴ ከንቱ ያሽቆጠቆጠ ፣ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱን የሚያወድስ ፣ ያልሰሩትን ሰሩ ፣ ያላጠመቁትን አጠመቁ ፣ ያልተፈጸ ሐዋርያዊ ጉዞ ከአራት ኪሎ በርቀት ተከናወነ ተብሎ ብቻ ይነገርበት።
👉 ለምን እንዲህ ሆነ ሲባል ግልጹን ስንነጋገር በዚህ መምሪያ ለአራት ዓመት በዋና ጸሐፊነት እኔ ቀሲስ ሳሙኤል አገልግያለው ፣ መምሪያው ልዑካን እንዲመጡ ደብዳቤ ይጽፋል ፣ የሪፖርት አቀራረብ መርህን ተከትሎ እንዲቀርብ መረጃ ይልካል ፣
👉ይሁን እንጂ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሚመደበው በዋናው መስራቤት በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ቢሆንም ፣ ለሀገረስብከቱ ሊቀጳጳስ ግን እንደፈለጉ የሚያንቀሳቅሱት ሻንጣ ነው ፣ አድርግ የተባለው ያደርጋል ፣ በል የተባለውን ይላል ፣ ከዛም በላይ ዕድሜውን ለማርዘው ሙሉ ሪፖርቱ በጳጳሱ ውዳሴ ፣ ምስጋና አገልግሎት ይከናወናል ፣
👉ይህ የማይካዳው እውነታ ነው ፣ በዚህ መልእክ ለዕድምተኞቹ ሊቀ ጳጳሱን በደንብ ካልገለጠ ሊቀ ጳጳሱ በገዛ ፈቃዳቸው በምትኩ ሌላ ሰው መመደብ ይችላሉ ፣ እውነት ሀሰት ብልን ብንጠይቅ ዛሬ ጠቅላይ ቤተክህነቱን ያጨናነቁት ከሀገረስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው አንዳንዶች በግፍ ፣ አንዳንዶች ለመሸጋገሪያ ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩ ሊመሰክሩ ይችላሉ ።
👉ከሪፓርቱ አቀራረብ መሰልቸት የተነሳ ከሚያዳምጠው የማያዳምጠው የጉባኤው ዕድምተኛ ይበልጣል ፣ አንዳንዱም ሳይጨርስ ወደ ገንዘቡ ሪፓርት ይባላል ፣ አንብቦ ሲጨርስ ፐርሰንት ያስገባበትን ደረሰኝ ለሀገረስብከቱ ጳጳስ ሰጥቶ ለዋናው ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ጳጳሱ ያቀብላሉ ።
👉ዉዉይት የሌለው ፣ መሠረታዊ በቤተክርስቲያን ወቅታዊ ችግር ላይ ትኩረት ያልሰጠ፣ የበሰሉ ሀሳቦች የማይንሸራሸሩበት ፣ ግልጽ ድጋፍ እና ውዳሴ እጅ ከፍ አድርጎ በማጨብጨብ የሚገለጽበት ፣ ተቃውሞ እና ትችት መግለጫው በእግር መሬት የሚደበደብበት አስልቺ ስብሰባ ነው በየወቅቱ የሚደረግበት፦
👉 ሌላው ለብዙዎች ግርምታ የሚፈጥረው ከውጭ የሚላኩ ሪፓርቶች ፣ ተወካይ ከመጣ በተወካዮቻቸው ፣ ካልመጣም እዛው በሀገረስብከቱ ጳጳስ በተሰየመ አንድ ሰው ይቀርባል መቸስ የውጭውን አገልግሎት እና የቤተክርስቲያን ምስረታ ያላወቀ አፉን ከፍቶ ሊሰማ ይችል ይሆናል እኔም እዛ ሆኜ ምልከተዬ እንደሱ ነበር እና ፣
👉ግርም የሚለው ግን እንዴት ፐርሰንት አያስገቡም እል ነበር ፣ ለካ ጥርስ የሌላቸው አንበሳ መሆናቸውን እዚህ የመጣ ነው የሚያውቀው ፣ የቤተክርስቲያኑ ባለቤት ወይም ባለ መብት የቤተክርስቲያን መስራቾች ናቸው በተለይ በአሜሪካ ፦ ብቻ ጉድ ይታያል ፣ ብሎም ይሰማል ።
በመጨረሻም በመምሪያ የተዘጋጀ የሽልማት አሰጣጥ የሚካሄድበት ፣ ያልተሸለመ ሀገረስብከት በሰልፍ ቀርቦ መምሪያውን በጥያቄ ኩርፊያውን የሚገልጽበት ፣ ከዛም የጋራ አቋም መግለጫ ተነቦ፣ የራት ግብዣ በመመሪያው እና በማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ ፣ የስብሰባው ፍፃሜ ይሆናል ።
📌ዘንድሮስ ከዚህ የተለይ ምን እንጠብቅ ፦
👉ስለቤተክርስቲያን ውስብስም የውስጥም የውጭም ችግር ይወሳ ይሆን ፦ ለችግሮቹ መፍትሔ በጋራ ይፈለግ ይሆን ?
👉 ሀገር ሰላም አጥታ በእርስ በእርስ ጦርነት የወገን ደም እንጅረት ወንዝ በየቀኑ እየፈሰሰ መቀጠል አለበት ወይ? ወይስ በየዓመቱ እንደሚደረገው የሰላም ኮሚቴ ተሰየመ እየተባለ ይታለፍ ይሆን ?
👉 ለቤተክርስቲያን ከባድ ፈተና የሆኑት የሐሰት አጥማቂያን በየጊዜው መፈብረክ ፣ ብሎም ሰንሰለታቸውን እስከ ውጭ ድረስ አድርገው በጳጳሳት ድጋፍ እየተሰጣቸው በግለቻው ቤተክርስቲያን እስከመክፈት በደረሱት ምንደኞች ዉይይት ተደርጎ ብይን ይሰጥ ይሆን ?
👉 የቤተክርስቲያኒቱ የመልካም አስተዳደር እጦት ፣ ሙስናው ፣ ምዝበራው ፣ ቅጥፈቱ እረ ስንቱ ተነስቶ በአጥፊዎች ላይ ከታች እስከ ላይ ብይን ይሰጥ ይሆን ?
👉 ብዙ ልጽፍ አልኩኝ እና ልቤ ተወው ሲለኝ እኔ ተውኩት እስኪ ጨምሩበት***************** ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,?
📍ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም ድምፅ