Banking Matters

Banking Matters Personal Blog on Ethiopian Financial Matters https://www.facebook.com/BankingMATERS/
(1)

የወደቁትን ማንሳት እና ሕይወትን ማዳን — የጋራ ተልዕኮ! ‼️Commercial Bank of Ethiopia CBE NOOR የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ፣ መቄዶንያ የበጎ አድ...
09/06/2026

የወደቁትን ማንሳት እና ሕይወትን ማዳን — የጋራ ተልዕኮ! ‼️

Commercial Bank of Ethiopia CBE NOOR
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ፣ መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ሰው ተኮር ተልዕኮውን አጠናክሮ እንዲቀጥል መግለጻቸውን አስታውቀዋል።

በፕሬዚዳንቱ የተመራ የባንኩ የሥራ መሪዎች በአዲስ አበባ አያት 49 የሚገኘውን የመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት ማህበሩ በማስገንባት ላይ ያለውን ሕንፃና ሌሎች የሥራ እንቅስቃሴዎች ተመልክተዋል።

አቶ አቤ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣ መቄዶንያ በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍ የሚያከናውነው ሰው ተኮር ተግባር ከፍተኛ ማህበራዊ እሴት አለው። ለዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የባንኩ ሰራተኞችና የሥራ መሪዎች ከመቄዶንያ ጎን እንደቀድሞው ሁሉ በመቆም ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል።

የመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው፣ “ከብዙ ማህበራዊ ጉዳዮች መቄዶንያን በማስቀደም በእረፍት ቀናችሁ ስለጎበኛችሁን እናመሰግናለን” በማለት ለባንኩ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል። አቶ ቢኒያም እንዳስታወቁት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የባንኩ ሰራተኞች በየጊዜው የሚያደርጉት ድጋፍና ጉብኝት ለማህበሩ የሥራ አቅም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ማህበሩ ጳጉሜን 1ን “የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀን” ብሎ መሰየሙንም አስታውሰዋል።

በመገባደድ ላይ ያለው የማህበሩ ሕንፃ እንዲሁም በማህበሩ የሚከናወኑት የበጎ አድራጎት ሥራዎች፣ የባንኩን ጨምሮ የተለያዩ ቅን አሳቢ ተቋማትና ዜጎች ያደረጉት የጋራ ድጋፍ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

---

ይህ ጉብኝት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከባንኪንግ አገልግሎት በላይ በመሄድ የሚያከናውነውን ሰፊ የማህበራዊ ኃላፊነት (CSR) ሥራ አንዱ መገለጫ ነው። ባንኩ “**Banking with Purpose, Impacting Lives**” በሚል መርህ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ይከተላል። “ኃላፊነታችን ከባንኪንግ በላይ ነው። በሰዎች ላይ ኢንቨስት እናደርጋለን፣ ማህበረሰቦችን እናነሳለን፣ ዘላቂ ልማትንም እንደግፋለን” በማለት ይገልጻል።

ባንኩ የCSR ሥራዎቹን በዋናነት በሚከተሉት ዘርፎች ያከናውናል፡-

- አካባቢ ጥበቃ — ለGreen Legacyና ለClean Ethiopia ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ
- በጎ አድራጎትና ድጋፍ — ለበጎ አድራጎት ማህበራት፣ ለአደጋ ተጎጂዎችና ለማህበረሰብ ልማት
- ስፖርት — የራሱ የእግር ኳስ ክለብ እና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስፖንሰርሺፕ
- ጤናና ሰብአዊነት — የጤና ተቋማትና የሕክምና ድጋፍ
- የገንዘብ ማካተት — የሴቶች፣ የወጣቶችና የልጆች ቁጠባ ምርቶች እንዲሁም CBE Noor አገልግሎት

ባንኩ በአንድ የበጀት ዓመት ብቻ ለተለያዩ ድርጅቶችና አረንጓዴ ተነሳሽነቶች ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል። በእሴቶቹ ውስጥም “Corporate Citizenship” በግልጽ ተካቷል።

የመቄዶንያ ጉብኝትም የዚህ ተከታታይ የጋራ ተልዕኮ አካል ነው። የወደቁትን ማንሳትና ሕይወትን ማዳን የጋራ ሥራ መሆኑን በተግባር የሚያረጋግጥ ነው።

#መቄዶንያ #የኢትዮጵያንግድባንክ #የጋራተልዕኮ #በጎአድራጎት

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) በዓመታዊ የአፈጻጸም ውይይቱ ዘጠነኛ ቀን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ጋር ገመገመ።Commercial Bank of Ethiopia CBE NOOR...
09/05/2026

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) በዓመታዊ የአፈጻጸም ውይይቱ ዘጠነኛ ቀን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ጋር ገመገመ።
Commercial Bank of Ethiopia CBE NOOR
በ 2018 የተገኘው ጊዜያዊ መረጃ ባንኩ አስደናቂ ውጤት ማስመዝገቡን ያሳያል፦

አዲስ የደንበኛ ሂሳቦች፡ 3.1 ሚሊዮን (አጠቃላይ 48.1 ሚሊዮን)
ተጨማሪ ተቀማጭ፡ ETB 707.5 ቢሊዮን (አጠቃላይ ተቀማጭ ከ ETB 2.4 ት በላይ)
የብድር ሰብሳቢነት፡ ETB 521.9 ቢሊዮን (82.7% እድገት)
የብድር ክፍያ፡ ETB 645.8 ቢሊዮን — ከዚህ ውስጥ 91.3% ለግል ዘርፍ
ከታክስ በፊት ትርፍ፡ ከ ETB 84 ቢሊዮን በላይ

ባንኩ በግል ዘርፍ ላይ ያለውን ትኩረት እያሳደገ መሆኑን መረጃው ያረጋግጣል። EIH ደግሞ ዲጂታላይዜሽንን ማስፋት፣ የደንበኛ አገልግሎትን ማሻሻል፣ የብድር ሂደቶችን ማቀላጠፍ፣ የአደጋ አስተዳደርን ማጠናከር እና ወጪን መቀነስ እንደሚያስፈልግ ጠቁሟል።

በማንኛውም ጊዜ ቢሆን እንጀምረው @ ===============የአንበሳ ባንክ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ሰይፈ ተስፋዬ ካሕሳይ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላመጡት ውጤት የባንኩ ሥራ አመራር የእንኳን...
08/29/2026

በማንኛውም ጊዜ ቢሆን እንጀምረው @
===============
የአንበሳ ባንክ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ሰይፈ ተስፋዬ ካሕሳይ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላመጡት ውጤት የባንኩ ሥራ አመራር የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክቱን እያስተላለፈ አቶ ሰይፈ ተስፋዬን የሚያበረታታ ስጦታዎችን አበርክቷል፡፡
በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ሰለዋ ወረዳ ደላ ከተማ በሚገኘው ቅርንጫፋችን ላለፉት ሰባት አመታት በጥበቃ ስራ እየሰሩ የሚገኙ ሰራተኛችን አቶ ሰይፈ ተስፋይ ካሕሳይ በ46 አመታቸው የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቅያ ፈተና ተፈትነው 320.25 ነጥብ በማምጣት ወደ ዩንቨርስቲ በማለፋቸው የባንካችን የዳይሬክቶሮች ቦርድ አባላት ፣ ማኔጅመንት እና ሰራተኞች በሙሉ የተሰማንን ደስታ ለመግለፅ እንወዳለን።
በዚሁ መሰረት የባንካችን ማነጅመንት በዚሁ የባንካችን ሰራተኛ በሆኑት አቶ ሰይፈ ተስፋይ ካሕሳይ የተሰማው ደስታና ኩራት ከፍተኛ መሁኑን እየገለጸ ለአቶ ሰይፈ ተስፋይ ካሕሳይ እና ለመላው ቤተሰባቸው እንዃን ደስ አላችሁ እያለ ለአቶ ሰይፈ ተስፋዬ የሚከተሉትን ማበረታቻዎች ለመስጠት ውሳኔ አስተላልፏል፤
1. አቶ ሰይፈ ተስፋይ ካሕሳይ ወደ ዩንቨርስቲ ለመግባት እና ለመማር የሚያስፈልጋቸው ማንኛውም ወጪ የዩንቨርስቲ ቆይታቸው እስከሚያጠናቅቁ ድረስ ሙሉ ወጪያቸውን ባንኩ ይሸፍንላችዋል።
2. አት ሰይፈ ተስፋይ ካሕሳ ወደ ዩንቨርስቲ ከገቡበት ወር ጀምሮ አሁን የሚከፈላቸ ወርሃዊ ደመወዝ ሙሉ በሙሉ በየወሩ ለቤተሰቦቻቸው እንዲከፈል ይደረጋል።
3. አቶ ሰይፈ ተስፋይ ካሕሳይ የዩንቨርስቲ ትምህርታቸው ካጠናቀቁ በኋላ ባንኩ በተገቢው የስራ ዘርፍ በመመደብ በቋሚነት ቀጥሮ የሚያሰራቸው ይሆናል።

#እንጀምረው

ኢትዮ-ፖስት 3,000 ቅርንጫፎቹን ወደ የባንክ ወኪልነት እየቀየረ ነው ‼️  National Bank of Ethiopia Commercial Bank of Ethiopia ✅️ በ700 ቅርንጫፎች የሙ...
08/17/2026

ኢትዮ-ፖስት 3,000 ቅርንጫፎቹን ወደ የባንክ ወኪልነት እየቀየረ ነው ‼️

National Bank of Ethiopia Commercial Bank of Ethiopia
✅️ በ700 ቅርንጫፎች የሙከራ /ፓይለት አገልግሎት አስጀምራል ::

✅️ኩባንያው ቅርንጫፎቹ ገንዘብ እንዲቀበሉ ፣ ክፍያዎችን እንዲከፍሉ እና ማንኛውንም ባንክ እንዲያገለግሉ ይፈልጋል::

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት/ ኢትዮ-ፖስት በመጀመሪያ በ700 ቅርንጫፎች የሙከራ ፕሮጀክት በማካሄድ 3,000 ቅርንጫፎቹን ወደ የባንክ ወኪሎችነት ለመቀየር እያዘጋጀ ነው። በአንድ ወር ውስጥ በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚጀምር ይጠበቃል።

በኢትስዊች ሲስተም አማካኝነት የማንኛውም የንግድ ባንክ ደንበኞች በፖስታ ቢሮዎች ገንዘብ ማስገባትና ማውጣት፣ የመገልገያ ክፍያዎችን መክፈል እንዲሁም የባንክ ሂሳቦቻቸውን ማግኘት ይችላሉ።

132 ዓመት እድሜ ያለው ይህ ተቋም የደብዳቤ አገልግሎት እየቀነሰ በመምጣቱ አዲስ የገቢ ምንጭ ለማግኘት ይህን እርምጃ እንደወሰደ ነው የተነገረው።

ሙሉ የAddis Fortune ዘገባውን በተቀመጠውሊንክ ይመልከቱ
https://addisfortune.news/ethio-post-turns-branches-into-banks-as-banks-close-theirs

ክቡር አቶ አቤ ሳኖ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት “CEO of the Year” ሽልማትን አሸነፉ!*************Congratulations ‼️ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ...
08/12/2026

ክቡር አቶ አቤ ሳኖ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት “CEO of the Year” ሽልማትን አሸነፉ!
*************
Congratulations ‼️

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በፋይናንስ ዘርፍ ባሳዩት የላቀ አመራር የዓመቱ ምርጥ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ (CEO of the Year) ሽልማትን አሸነፉ።

ሽልማቱ የተበረከተው ዓለም አቀፉ የስትራቴጂክ ጥምረት ማዕከል (ICSA) በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል ባካሄደው 29ኛው “Connected Banking Summit – Innovation & Excellence Awards 2026” መድረክ ላይ ነው።

ይህ ታላቅ እውቅና አቶ አቤ ሳኖ በፋይናንስ ዘርፍ ባሳዩት የላቀ አመራር፣ በተለይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ግዙፍ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና የፈጠራ ጉዞ በበላይነት ለመምራት ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

አቶ አቤ ሳኖ ይህንን ክብር ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት ማግኘታቸውም በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አልሰን አሰፋ ፕሬዚዳንቱን በመወከል ሽልማቱን ከተቀበሉ በኋላ፣ “ይህ እውቅና የባንካችንን ጠንካራ አመራር የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ፣ ለመላው የባንካችን ሠራተኞችና ደንበኞች የተበረከተ የጋራ ስኬት ነው” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማኅበራዊሚዲያገፁ Commercial Bank of Ethiopia " ይህ ሽልማት በራዕይ፣ በፈጠራ፣ በዲጂታል ለውጥና በጠንካራ ቡድናዊ አመራር የተገነባ የCBE የጋራ ስኬት ነው!" ብሏል።
Alsen Assefa Ararso

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአቶ ይህንዓለም አቅናውን የአማራ ባንክ የዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሹመት አፀደቀ ❗️National Bank of Ethiopia Amhara Bank S.C.     በኢትዮጵ...
08/11/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአቶ ይህንዓለም አቅናውን የአማራ ባንክ የዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሹመት አፀደቀ ❗️

National Bank of Ethiopia Amhara Bank S.C.
በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ የባለአክሲዮኖች ቁጥር በማስመዝገብ የሚታወቀው አማራ ባንክ ቀደም ሲል ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. አቶ ይህንዓለም አቅናውን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት መሾሙን ማስታወቁ የሚታወቅ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ደግሞ ይህንን የቦርዱን ውሳኔ በዛሬው ዕለት በይፋ አጽድቆታል።

ይህ ሹመት አማራ ባንክ በገበያው ውስጥ ያለውን ከፍተኛ የሕዝብ መሠረት ወደ ተጨባጭ የፋይናንስ ትርፋማነት እና ተወዳዳሪነት ለመቀየር አዲስ ስትራቴጂያዊ መዋቅር እየዘረጋ ባለበት ወሳኝ ወቅት ላይ የተደረገ ነው። የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አዲሱን ሹመት ሲያጸድቅ፣ አቶ ይህንዓለም ባንኩ የያዘውን ግዙፍ የባለአክሲዮኖች ቁጥር እና ያላቸውን ከፍተኛ የትርፍ ጥበቃ ማስተናገድ የሚችል የአመራር ብቃት አላቸው በሚል እምነት ነው። አዲሱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ ባንኩ በቅርቡ ያደረጋቸውን የሌሎች ከፍተኛ መኮንኖች ሹመት በማስተባበር ተቋሙን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ የማሸጋገር ከባድ የቤት ሥራ ይጠብቃቸዋል።

አቶ ይህንዓለም አቅናው በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከሩብ ምዕተ ዓመት በላይ የዘለቀ ሰፊ ልምድ አላቸው። በዳሸን ባንክ ከጀማሪ ባለሙያነት ጀምሮ እስከ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ፣ የብድር መምሪያ ዳይሬክተር፣ የስትራቴጂ መምሪያ ዳይሬክተር፣ የስትራቴጂ እና የደንበኞች አገልግሎት ዋና መኮንን፣ የሪቴይል እና ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ዋና መኮንን፣ እንዲሁም በመጨረሻም የኢንቨስትመንት ባንክ አማካሪ በመሆን በተለያዩ የኃላፊነት እርከኖች አገልግለዋል።

የትምህርት ዝግጅታቸውን በተመለከተ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሒሳብ አያያዝ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። በተጨማሪም ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ በኢንፎርሜሽን ሲስተምስ በ2005 እ.ኤ.አ. ሁለተኛ ዲግሪያቸውን፣ እንዲሁም በሥራ አመራር በ2014 እ.ኤ.አ. የማስተርስ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል። ከዚህም ባሻገር በዩናይትድ ኪንግደም፣ ለንደን ከሚገኘው ዓለም አቀፍ የሒሳብ ባለሙያዎች ማኅበር በ2013 እ.ኤ.አ. የላቀ የሙያ ማረጋገጫ አግኝተዋል።

ባንኩ አሁን ላይ እየተገበረ ካለው አዲስ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ አንጻር፣ የአቶ ይህንዓለም ጠንካራ የፋይናንስ እና የስትራቴጂ አመራር ዳራ፣ የተቋሙን ቀጣይ ጉዞ ለማቃናት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል። ዳይሬክተሮች ቦርዱ እና የባንኩ ሠራተኞች ለአዲሱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የእንኳን ደህና መጡ መልእክት እና የስኬት ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

Banking Matters Banking Matters

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ተጠባባቂ  CEO  ሾመ ❗️❗️Global Bank Ethiopia Global Bank Ethiopia Appoints Banking Industry Veteran Mr. Sahlem...
08/08/2026

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ተጠባባቂ CEO ሾመ ❗️❗️

Global Bank Ethiopia

Global Bank Ethiopia Appoints Banking Industry Veteran Mr. Sahlemichael Mekonnen as Acting Chief Executive Officer

Banking Matters

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን ቦርድ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ❗️❗️National Bank of Ethiopia Global Bank Ethiopia Ethiopian Reporter ...
08/07/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን ቦርድ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ❗️❗️

National Bank of Ethiopia Global Bank Ethiopia Ethiopian Reporter
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጥረዋል የተባሉ ችግሮችን ሲመረመር ቆይቶ፣ የባንኩ ፕሬዚዳንት በየትኛውም የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ እንዳይሠሩ ማገዱና የባንኩን የቦርድ አባላት ለአስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ታወቀ፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠሩ የተለያዩ ችግሮችን ሲመረምር የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ባገኘው የምርመራ ውጤት ላይ ተመሥርቶ ውሳኔ ማሳለፉ የታወቀ ሲሆን፣ ከውሳኔዎቹም አንዱ የባንኩ ፕሬዚዳንት በሆኑት ተስፋዬ ቦሩ (ዶ/ር) ላይ የጣለው ዕግድ ተጠቃሽ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሰኞ ሐምሌ 27 ቀን 2ዐ18 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ተስፋዬ ቦሩ (ዶ/ር) በየትኞቹም የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ለአምስት ዓመታት እንዳይሠሩ ዕግድ የተጣለባቸው መሆኑን ለግለሰቡ አሳውቋል።

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጥረዋል ለተባሉ ችግሮች በዋናነት ተጠያቂ ናቸው ተብለው ከተዘረዘሩት የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መካከል አንዱ የባንኩ ፕሬዚዳንት ተስፋዬ (ዶ/ር) ናቸው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በግለሰቡ ላይ የአምስት ዓመት ዕግድ ከመጣሉ አስቀድሞም የግሎባል ባንክ ቦርድ ግለሰቡን ከባንኩ ፕሬዚዳንትነት በማንሳት የራሱን ዕርምጃ ወስዶ እንደነበር ታውቋል።

ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ በአሁኑ ወቅት በአገር ውስጥ የሌሉ መሆኑን የጠቆሙት የሪፖርተር ምንጮች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በባንኩ ውስጥ ተፈጥረዋል የተባሉ ችግሮችን ለማጥራት ረዘም ላለ ጊዜ ምርመራ ሲያካሄድ የቆየ በመሆኑ፣ ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪ በሌሎች የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች ላይም ዕርምጃዎችን ይወስዳል ተብሎ ሲጠበቅ እንደነበር ገልጸዋል። ይሁን እንጂ እስካሁን ባለው ሁኔታ ከባንኩ ፕሬዚዳንት ውጪ ተጠያቂ የተደረጉ ሌሎች አመራሮች አለመኖራቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል።

ነገር ግን የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ቦርድ በባንኩ ውስጥ ተፈጥረዋል ለተባሉት ችግሮች ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን የባንኩን ፕሬዚዳንትን ጨምሮ 17 ከፍተኛ አመራሮችን ከሥራ በማገድ በምትካቸው አዳዲስ አመራሮችን መመደቡን ምንጩቹ ተናግረዋል። ከዚህም ባሻገር፣ አንድ የባንኩ የቦርድ አባል ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡

በብሔራዊ ባንክ ባካሄደው ምርመራ ያገኛቸውን ጥሰቶች መሠረት በማድረ፣ ከባንኩ የማኔጅመንት አባላት በተጨማሪ፣ የቦርድ አባላትንም ተጠያቂ ሊያደርግ እንደሚችል የጠቆሙት ምንጮቹ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቦርድ አባላትን ለአስቸኳይ ስብሰባ መጥራታቸውንም ገልጸዋል።

የብሔራዊ ባንክ አመራሮች ከባንኩ የቦርድ አባላት ጋር በሚኖራቸው ስብሰባ፣ በቀጣይ በባንኩ ሊወሰዱ የሚገቡ ዕርምጃዎችን የተመለከተ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ገልጸዋል።

በባንኩ ውስጥ ተፈጠሩ የተባሉትና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምርመራ የተለዩት ችግሮች በርካታ መሆናቸውን የሚጠቁሙት የሪፖርተር የምንጮቹ፣ ከእነዚህም መካከል የረዥም ጊዜ ተቀማጭ ገንዘብ (ታየም ዲፖዚት) ጋር በተያያዘ ተፈጠረ የተባለው ችግር አንዱ ነው፡፡ ባንኩ ከተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ለሰበሰበው ለረዥም ጊዜ የማይንቀሳቀስ ተቀማጭ ገንዘብ፣ ከባንኩ አሠራር ውጪ ያልተገባ ከፍተኛ የወለድ ምጣኔ ለመክፈል መስማማቱና በስምምነቱ መሠረትም ወለድ ክፍያውን በመፈጸም በባንኩ ጥቅም ላይ ጉዳት ድርሷል መባሉን ምንጮቹ ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ፣ ከአስቀማጭ ደንበኞች ጋር በመመሳጠር አስቀማጮች ሊከፈላቸው ከሚገባው የተቀማጭ ገንዘብ ወለድ ምጣኔ በላይ በመክፈል ጭምር ሕገወጥ ተግባር መፈሙን ምንጮቹ አስረድተዋል።

ባንኩ ለረዥም ጊዜ ተቀማጭ ገንዘብ የተጋነነ የወለድ ክፍያ ሲከፍል የነበረ ከመሆኑ ባሻገር፣ አንድ የባንኩ ደንበኛ በዚህ ያልተገባ መንገድ ሲያገኝ የነበረውን የተጋነነ የወለድ ለብድር ዕዳ መክፍያነት ማዋሉ እንደተደረሰበትና ይህንንም የሚያስረዳ የሰነድ ማስረጃ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መቅረቡን ምንጮቹ ጠቁመዋል።

ባንኩ ላይ ተገኘ የተባለው ሌላው ችግር የተሳሳተ ሪፖርት ከማቅረብ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ እንደ ምሳሌ የተጠቀሰውም የባንኩ የተበላሸ የብድር መጠን ወደ 20 በመቶ አካባቢ ደርሶ፣ በባንኩ ሪፖርት የተደረገው ግን ከዚያ በታች ሆኖ መገኘቱን ምንጮቹ ገልጸዋል።

ባንኩ ለአንዳንድ ግለሰቦች የሰጠው ብድር የተበላሸ ብድር ውስጥ ገብቶ ሳለ፣ ብድሩ ጤናማ እንደሆነ አድርጎ ሪፖርት ሲያደርግ መቆየቱን የሚጠቁም መረጃ፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀርቦ ምርመራ ሲደረግበት እንደነበርም ገልጸዋል።

ይህንንም ተከትሎ ባንኩ ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ የረዥም ጊዜ ተቀማጭ ገንዘብ እንዳይቀበል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደተወሰነበት ምንጮቹ አስረድተዋል።

በባንኩ ቦርድ የታገዱትና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክም ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በማንኛውም የፋይናንስ ተቋሞች ውስጥ እንዳይሠሩ ውሳኔ የተላለፈባቸው ተስፋዬ ቦሩ (ዶ/ር) ከአገር ከመውጣታቸው በፊት ተወካይ ሰይመው የነበረ ቢሆንም፣ ቦርዱ ግን የፕሬዚዳንቱን ተወካይ በመሻር ሌላ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት እንደሾመ ከምንጮቹ ለመረዳት ተችሏል። ቦርዱ የሰየማቸው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንትነት አቶ ሳህለሚካኤል መኮንን ናቸው።

አቶ ሳህለሚካኤል ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሆነው ከመሰየማቸው በፊት የባንኩ ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር በመሆን ሲሠሩ ነበር፡፡

ተሰናባቹ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አቶ ተስፋዬ ቦሩ (ዶ/ር) ባንኩን ከአሥር ዓመታት በላይ በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የነበሩ ሲሆን፣ ወደ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት በዘመን ባንክ ውስጥ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲሱ ማኔጅመንት የተመራው ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ፣ የባንኩን የ2018 ሒሳብ ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ከሰሞኑ መገምገሙን ባንኩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ባንኩ በሒሳብ ያስመዘገባቸው ውጤቶች በዚህ መድረክ ላይ ከመገምገማቸው ባሻገር፣ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የአሠራር ክፍተቶች በግልጽ ተለይተው ተግባራዊ የመፍትሔ አቅጣጫዎች እንደሰተጠባቸው አስታውቋል።

በመርሐ ግብሩ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ የሥራ አመራሮችና የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች መሳተፋቸውን የሚገልጸው ይሄው የባንኩ መረጃ፣ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ደንበኞቹንና ባለድርሻ አካላትን ማዕከል ያደረገ ዘመናዊ፣ ተደራሽና ጥራት ያለው የባንክ አገልግሎት በማቅረብ፣ በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ ያለውን ተወዳዳሪነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚሠራውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያትታል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የተከፈለ ካፒታሉን ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑን የባንኩ መረጃ ያመለክታል፡፡ ባንኩ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን የቅርንጫፎቹን ቁጥር ከ240 በላይ ያደረሰ ሲሆን፣ አጠቃላይ የሀብት መጠኑም ከ35 ቢሊዮን ብር በላይ እንደደረሰ የባንኩ መረጃ ያመለክታል፡፡

Banking Matters

የብሔራዊ ባንክ የቀድሞ የግሎባል ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ቦሩን ለአምስት ዓመታት አግዷልNational Bank of Ethiopia  Global Bank Ethiopia የኢትዮጵያ ብ...
08/01/2026

የብሔራዊ ባንክ የቀድሞ የግሎባል ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ቦሩን ለአምስት ዓመታት አግዷል

National Bank of Ethiopia Global Bank Ethiopia
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE) የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ (GBE) የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበሩትን ተስፋዬ ቦሩን ተደጋጋሚ የቁጥጥር ጥሰቶችን በመጥቀስ በማንኛውም የፋይናንስ ተቋም ውስጥ ለአምስት ዓመታት ከፍተኛ የአመራር ቦታዎችን እንዳይይዙ ከልክሏቸዋል።

ማዕከላዊ ባንኩ በጁላይ 29 በጻፈው ደብዳቤ፣ ተስፋዬ የGBE ልዩ ምርመራ ከተደረገ በኋላ ከስልጣናቸው መባረራቸውን አረጋግጧል። ግምገማው የባንኩን የኮርፖሬት አስተዳደር፣ የብድር እና የብድር አስተዳደር ልምዶች፣ የሰው ኃይል አስተዳደር፣ የውጭ ምንዛሪ ስራዎችን እና አጠቃላይ የፋይናንስ አስተዳደርን ገምግሟል።

እንደ ብሔራዊ ባንክ ገለጻ፣ ምርመራው በርካታ የቁጥጥር መመሪያዎችን እና የባንኩን የውስጥ ፖሊሲዎች መጣስ እና የተቋሙን ጤናማ አሠራር እንዳዳከመ ገልጿል።

“ግኝቶቹ በመቀጠልም ከባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ተደርጎባቸዋል፣ በተለዩት ጉዳዮች ላይ ሰፊ ስምምነት ላይ ተደርሷል” ሲል ማዕከላዊ ባንኩ ገልጿል።

GBE በኋላ ላይ ተለይተው የታወቁትን ጉድለቶች የሚዳስስ የእርምት እርምጃ ዕቅድ ይዞ ዝርዝር ምላሽ አቅርቧል። ሆኖም፣ ብሔራዊ ባንክ የግኝቶቹ ክብደት፣ ከተስፋዬ ቀደም ሲል ከነበረው የቁጥጥር መዝገብ ጋር ተዳምሮ፣ የበለጠ ጠንካራ የማስፈጸሚያ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ተናግሯል።

ማዕከላዊው ባንክ በግንቦት 2021 እና ህዳር 2024 ቀደም ሲል የወጡ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያዎችን በመጥቀስ፣ የባንክ ንግድ አዋጅ ቁጥር 1360/2025 አንቀጽ 20(1) እና (2) እና የመመሪያ ቁጥር SBB/89/2024 አንቀጽ 10ን ተጠቅሞ ውሳኔውን አጸደቀ።

“በዚህ መሠረት፣ በምርመራው ግኝቶች እንዲሁም ቀደም ሲል በተጻፉት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያዎች ላይ በመመስረት… ከጁላይ 28፣ 2026 ጀምሮ ከGBE ዋና ሥራ አስፈፃሚነትዎ ይወገዳሉ” ሲል ደብዳቤው ተነቧል።

ተስፋዬ ከስልጣን ከመባረሩ በተጨማሪ ከሐምሌ 28፣ 2026 ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀስ በማንኛውም የፋይናንስ ተቋም ውስጥ የቦርድ አባል፣ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይም ከፍተኛ ሥራ አስፈፃሚ ሆኖ እንዳያገለግል ተከልክሏል።

የቁጥጥር እርምጃው ባለፈው ሳምንት የጂቢኢ የዳይሬክተሮች ቦርድ ከስራ መባረሩን ተከትሎ ነው።
Capital Banking Matters

የአቢሲንያ ባንክ የ2025/26 ዓመታዊ ጉባዔ እየተካሄደ ነው ‼️Bank of Abyssinia የአቢሲንያ ባንክ ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ጉባዔ የመጀመሪያ ቀን አቢሲንያ ባንክ ዓመታዊ የ...
07/31/2026

የአቢሲንያ ባንክ የ2025/26 ዓመታዊ ጉባዔ እየተካሄደ ነው ‼️

Bank of Abyssinia
የአቢሲንያ ባንክ ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ጉባዔ የመጀመሪያ ቀን አቢሲንያ ባንክ ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ጉባዔውሎ የባንኩ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለተሰብሳቢው አቅርበው ውይይት ሲደረግባቸው ውሏል።

በ ዓመታዊ ጉባዔዉ የመጀመሪያ ቀን ውሎ የባንኩ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ሪፖርታቸውን አቅርበው ውይይት ተካሄደባቸው

ዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው የአቢሲንያ ባንክ ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ጉባዔ የመጀመሪያ ቀን ውሎ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለተሰብሳቢው አቅርበው ውይይት ሲደረግባቸው ውሏል።

የአቢሲንያ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ በቃሉ ዘለቀን የመክፈቻ ንግግር ተከትሎም የባንኩ የስትራቴጂና ሪሰርች መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ታምራት የ2025/26 በጀት ዓመት ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው በተሰብሳቢዎቹ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በዚህ ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት፣ የዲፓርትመንት ዳይሬክተሮች፣ የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች፣ በአ.አ የሚገኙ ቅርንጫፍ ስ/አስኪያጆች እና የዲቪዥን ስ/አስኪያጆች እየተሳተፉ ይገኛል።

ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ጉባዔው በነገው ዕለትም ቀጥሎ የሚውል መሆኑን ተገልጿል ።
Banking Matters

Address

100 Business Park Lane, Unit E
Milton, DE
19968

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Banking Matters posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Banking Matters:

Shortcuts

Share