DONGA MEDIA NETWORK HADERO

DONGA MEDIA NETWORK HADERO Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from DONGA MEDIA NETWORK HADERO, Media/News Company, New York, NY.

10/11/2025

ከጠምባሮ አብራክ የተገኘው አርቲስት Ashenafi sahle የጠምባሮ ዶንጋ እና ከምባታ ወንድማማች ሕዝቦችን ሙዚቃ በቅርብ ቀን ጠብቁ ብሏል፡፡

ህመምሽ ምን ነበር ?        አንች ውብ ከተማ አንች ደማቅ ሀገር ፣       ተምሳሌት የሆንሽው መገኛ የሰው ዘር ፣       ሳትከፋፍይን በኃይማኖት በዘር ፣        ሰብስበሽ ያኖር...
10/10/2025

ህመምሽ ምን ነበር ?

አንች ውብ ከተማ አንች ደማቅ ሀገር ፣
ተምሳሌት የሆንሽው መገኛ የሰው ዘር ፣
ሳትከፋፍይን በኃይማኖት በዘር ፣
ሰብስበሽ ያኖርሽን ሚስጥሩ ምን ነበር ?
ህንፃው ምን ቢረዝም ቢፀዳ ውበቱ ፣
ምንገዱ ቢፀዳ ቢንጣለል አስፋልቱ ፣
ተከብሮ ካልኖረ ሰው በማንነቱ ፣
ከተበለሻሸ ከታች መሰረቱ ፣
ስላገር አንድነት ደጋግሞ ማውራቱ ፣
ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድን ነው ? ውበቱ ።
ድንጋይ ቤት አይሆንም ህንፃው ቢደረደር ፣
ምንገድ ተዘጋግቶ ቢበጅለት አጥር ፣
በፍቅር በጋራ ተሳስቦ የሚኖር ፣
የሰው ልጅ ልብ ነው የሌለው ዳር ደንበር ፣
ታዲያ እንድህ ከሆነ እውነት ለመናገር ፣
ካለ ሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል ሀገር ።
ምስቅልቅልሽ ጠፍቶ ችግርሽ በርትቶ ፣
ስቅታ በዝቶብሽ ሀዘንሽ በርትቶ ፣
ቁጥሮችሽ ላልተው፧ ማሰሪያሽ ተፈቶ ፣
ህልምሽ እውን ሆኖ የጎደለሽ ሞልቶ ፣
ያኑርሽ ፈጣ የሰውን ልብ ገዝቶ ፣
አንች ውብ ከተማ አፍሪካዊት ምድር ፣
ማንም ያልደፈረሽ ልዕዋላዊት ሀገር ፣
ለብዙ ሺ አመታት ያኖርሽን በፍቅር ፣
ተጋብተን ተዋልደን ሳንቆጥር የሰው ዘር ፣
ዛሬ ተከፋፍለን በኃይማኖት በዘር ፣
ተቆጭና ገልማጭ የሌለባት ሀገር ፣
ተብሎ ስማችን በዓለም ላይ ሲነገር ፣
ለብዙ ዘመናት የተለየሽ ፋቅአር ፣
ሁሉም ያልተረዳው ህመምሽ ምን ነበር ።


መልካም አዳር !!

ምንም እንኳን ከተማ የነዋሪዎች ብትሆንም በተደጋጋሚ ሀደሮ ከተማ ላይ የሚሰራው አደረጃጀት ነዋሪዎቿን ሆነ ህዝብን መሰረት ያደረገ አይደለም።በተለይ የዶንጋ ብሄረሰብ በከተማዋ ከለው ታሪክ አን...
10/10/2025

ምንም እንኳን ከተማ የነዋሪዎች ብትሆንም በተደጋጋሚ ሀደሮ ከተማ ላይ የሚሰራው አደረጃጀት ነዋሪዎቿን ሆነ ህዝብን መሰረት ያደረገ አይደለም።
በተለይ የዶንጋ ብሄረሰብ በከተማዋ ከለው ታሪክ አንፃር የከተማው ወይም የቦታው አራሽ እና ነበር ህዝብ እንደሆነ ግልጽ ነው።

የአደረጃጀት ስብጥር ምልመለ ነዋሪ እና ህዝብ ከሆነ ሀደሮ ከተማ ላይ 80% ያህል የከተማዋ ነዋሪ የዶንጋ ብሄረሰብ መሆኑ እየታወቀ በከተማው አደረጃጃት ላይ አንድም ጊዜ ከንቲባ ወይም ብልፅግና ፖርቲ ሲሆን እና በሚገባው ልክ በከተማው ሀላፊነት ሲሰጥ አይታይም። ምክንያትስ ምንድነው?
አደረጃጃቱ ሀደሮ ከተማ ላይ ያለውን የዶንጋ ብሄረሰብ ተወላጆች የከተማውን ህዝብ ያለማከለ አደረጃጃት ስለሆነ አደረጃጀቱን በመቃወም ለመብተችን እንታገል። ለመብትህ ቆርጠህ ካልታገልክ ማንንም አምጥተው ይጭኑብሃል እየሆነ ያለውም ሀቅ ይህ ነው።
1,ታምሬ ታደሰ ሀድያ
2,አደነ ፍቅሬ ዶንጋ
3,አበረ ተፈሰ ከምባታ
4,ተፈራ ማቴዎስ ከምባታ
ሀደሮ ከተማ ላይ ያለችሁ ምሁራን፣ ነገዴዎች፣ ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች ሆይ ለህዝባችሁ ተነሱ! ለመብታችሁ ታገሉ!

ከፍ አድርገን ድምፃችንን ያሰማነው፤ ክብር የሆነውን የሰው ልጅ ያጣነው፤ አካለ ጎዶሎ የሆነው፤ ሰላማዊ ወጣቶች አካባቢውን ለቀው የተሰደዱበት፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን በማረሚያ የታጎሩበት፤...
10/09/2025

ከፍ አድርገን ድምፃችንን ያሰማነው፤ ክብር የሆነውን የሰው ልጅ ያጣነው፤ አካለ ጎዶሎ የሆነው፤ ሰላማዊ ወጣቶች አካባቢውን ለቀው የተሰደዱበት፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን በማረሚያ የታጎሩበት፤ ዝቅ ብለን ለሕዝባችን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንዲኖር ነው።
አንድ ክፍለ ዘመን የተሻገረውን የዶንጋን ህዝብ መዋቅራዊ በደል የተጠየፍነው፣ ከሸዋ ክፍለሀገር እስከ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እናም እስከዛሬው ማዕከላዊ እትዮጵያ ክልል ድረስ ከከምባታ እና ሀዲያ አውራጃ እስከ ከምባታ ዞን የምንታገለው እንደ ሀገር በኢትዮጵያ ውስጥ የዶንጋን ሕዝብ እኩል ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ለማስቻል እንጂ ከዚህ ቀደም በከሸፈው መዋቅር ያለፍላጎቱ ህዝቦችን ተደራጅቶ ባህሉ ቋንቋው እንድሞት፤ እንደጠፋ፤ እንዲንገላታ ፤ እንዲገፋ ፤ አልፎም ተርፎ እንዲሰቃይ አልነበረም፤ አይደለምም።

ስለሆነም የዶንጋ ሕዝብ በሰላማዊ መንገድ ሲያነሳቸው የነበሩ እና እስካሁን የሚያነሳቸው ፍፁም ሕጋዊ የሆኑ በልዩ ወረዳ የመደራጀት፤ የምርጫ ክልል ሌሎችም የልማት ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል።

ፍትህ ለዶንጋ ብሔረሰብ ⚖️

ጥያቄዎች ሕጎችንና አሰራሮችን በመከተል ወንድማማችነትና አንድነትን በሚያጠናክር አግባብ ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ እንዲያገኙ በትኩረት እንደሚሠራ ተገለጸ***************************...
10/06/2025

ጥያቄዎች ሕጎችንና አሰራሮችን በመከተል ወንድማማችነትና አንድነትን በሚያጠናክር አግባብ ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ እንዲያገኙ በትኩረት እንደሚሠራ ተገለጸ
************************************************
(ዜና ፌዴሬሽን) መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣

የሚቀርቡ ጥያቄዎች ሕጎችንና አሰራሮችን በመከተል ወንድማማችነትና አንድነትን በሚያጠናክር አግባብ ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ እየሰጡ መሄድ ተጠናክሮ አንደሚቀጥል የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

በፌዴሬሽን ምክር ቤት የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰን የሰላም ግንባታ ቋሚ ጸሐፊ የተከበሩ አቶ ፍቅሬ አማን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ቋሚ ኮሚቴው በበጀት ዓመቱ በርካታ አንኳር ጉዳዮችን ማከናወኑን በዋናነትም ከግጭት መከላከልና ከሰላም ግንባታ አንጻር በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነት ስር እንዲሰድ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ሰነድ በመፈራርም ትኩረት ሰጥቶ መሥራትን ጨምሮ በህዝበ ውሳኔ የምርጫ ስርዓት መሰረት ራሳቸውን መልሰው ያደራጁ አዳዲስ ክልሎች በውስጣቸው በሚገኙ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መካከል ህብረ-ብሔራዊ አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ መድረክ በማዘጋጀት የተሳካ ሥራ መሠራቱን ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም ከሚመለከታቸው የቀርቡ አቤቱታዎች በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት፣ በአዋጅ ቁጥር 1261/2013 እንዲሁም በደንብ ቁጥር 3 አማካኝነት ጥናቶችን በማድረግ ሕገመንግሥታዊ ምላሽ እንዲያገኙ የማድረግ ስራ ትኩረቱ እንደነበር የጠቀሱት የተከበሩ አቶ ፍቅሬ እስከ ክልል ጭምር በመሄድ የድጋፍና ክትትል ሥራ በማጠናከር ወደ ምክር ቤቱ የሚመጡ አቤቱታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሱ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጥላሁን ከበደ ቋሚ ኮሚቴው ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ሕገ መንግሥቱንና ሌሎችን አሠራሮች በመከተል ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ እንዲያገኙ ጥልቅ ምርመራ በማድረግ የውሳኔ ሃሳቦችን ለም/ቤቱ በማቅረብ እያስወሰነ ሲሠራ መቆየቱን በማስታወስ በቀጣይም የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ሕጎችንና አሠራሮች በመከተል ወንድማማችነትንና አንድነትን በሚያጠናክር አግባብ ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ እየሰጡ መሄድ እንዲሁም ከግጭት መከላከልና ከሰላም ዕሴት ግንባታ አንጻር ከሚመለከተው ጋር ተቀናጅቶ መሥራት የቋሚ ኮሚቴው ትኩረት እንደሚሆን ገልፀው የቋሚ ኮሚቴውን ያለፈውን መደበኛ ቃለ ጉባዔ እና የዕለቱን የመወያያ አጀንዳዎች በማጸደቅ ውይይቱን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

የ2017 በጀት ዓመት አፈጻፀም ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ በዝርዝር ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሄዷል፡፡ ሪፖርቱና ዕቅዱ ለተከበረው ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ እንደሚጸደቅ ይጠበቃል፡፡

የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 62፣48 እና 39 እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር በድጋሚ ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ ቁጥር 1261/2013 መሰረት የሕዝቦች ጥያቄ ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ እንዲያገኝ ጥልቅ ምርመራ በማድረግ የውሳኔ ሃሳቦችን ለም/ቤቱ እንደሚያቀርብ ይታወቃል::

09/25/2025

እንኳን ለ2018ዓ.ም የዶንጋ ብሔረሰብ የዓመት መለወጫ ለሆነው ዶንጊ መሳላ አደረሳችሁ አደረሰን ፡፡

አዲሱን ዓመት የሰላም የጤና የፍቅር እንድሁም የብልጽግና ያድርግልን፡፡

በዓሉን ሲናከብር የተቸገሩትን በመርዳት እና ካለን ላይ አከፍሎ በማጉረስ ይሁን፡፡

መላው የሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ እና አጎራባች ወረዳዎች እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!!የጡንጦ ከተማ ማዘጋጃ የጡንጦ ከተማ ገበያ ከዛሬ መስከረም 15 2018ዓ.ም ጀምሮ በየሳምንቱ...
09/25/2025

መላው የሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ እና አጎራባች ወረዳዎች እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!!

የጡንጦ ከተማ ማዘጋጃ የጡንጦ ከተማ ገበያ ከዛሬ መስከረም 15 2018ዓ.ም ጀምሮ በየሳምንቱ ሐሙስ ሐሙስ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

የጡንጦ ከተማ ማዘጋጃ ከዛሬ ጀምሮ በየሳምንቱ ሐሙስ ሐሙስ የሚውለውን የከብት÷የፍየል ÷ የበግ እና የአህያ ተራን አስመርቆ ለገበያተኛው ክፍት አድርጓል ፡፡

በመሆኑም የአከባቢው ነዋሪዎች እና ነገዴዎች በዛሬው ዕለት የተመረቀውን የከብት÷የፍየል ÷ የበግ እና የአህያ ተራን በየሳምንቱ ሐሙስ በነፃ መጠቀም እንደምችሉ አብስሯል ፡፡

የዶንጋ ብሄረሰብ የልዩ ወረዳ መዋቅር ህገ መንግስታዊ መብት ተጠቃሚ ባለመሆኑ ምክንያት አሉታዊ ጫና እየደረሰበት ነው ሲል የዶንጋ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስ...
09/24/2025

የዶንጋ ብሄረሰብ የልዩ ወረዳ መዋቅር ህገ መንግስታዊ መብት ተጠቃሚ ባለመሆኑ ምክንያት አሉታዊ ጫና እየደረሰበት ነው ሲል የዶንጋ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

የዶንጋ ብሔረስብ በሰፈረበት ጂዮግራፊ ወይም አካባቢ በሚገኘዉ ወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅር ፍትሃዊ አገልግሎት የማግኘት መብት ተነፍጓል ያለው ዶንጋ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት የብሔረሰቡን ባህል ልብስ ለብሶ የመንቀሳቀስ ነጻነት ተነፍጓል፣ የዶንጋን ባህል ልብስ በመስቀል በዓል የለበሱ ወጣቶች የመታሰር በደል ደርሰባቸዋል ብሏል።

የመስቀል በዓል (ዶንግ መሳለ) በራስ መዋቅር የማክበር መብት ተነፍጓል የተባለ ሲሆን የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ተጠቃሚ እንዳይሆን ተደርጓል ሲሉ የፓርቲው ኃላፊዎች በመግለጫው ገልጿል።

ብሔረሰቡ በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ-መንግሥት አንቀጽ 39 (3) የተደነገገዉንና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህገ-መንግሥት አንቀጽ 48 (3) የተደነገገዉን ህገ-መንግሥታዊ መብት እንዳላገኘ ነው የተናገሩት።

ስለሆነም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ህገ-መንግስቱን የመተርጎም ኃላፊነት ተጠቅሞ የዶንጋ ብሔረሰብ በልዩ ወረዳ የመደራጀት ህገ-መንግሥታዊ መብት ተጠቃሚ እንድያደርግ በአጽኖት እናሳስባለን ሲል የዶንጋ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

የዶንጋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት  ብሔረሰቡ የመስቀል በዓልን እንዳያከብር ተደርጓል በማለት የክልሉን መንግስት ከሰሰየዶንጋ ብሔረሰብ በሌሎች ብሔሮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን የመስቀል ...
09/24/2025

የዶንጋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ብሔረሰቡ የመስቀል በዓልን እንዳያከብር ተደርጓል በማለት የክልሉን መንግስት ከሰሰ

የዶንጋ ብሔረሰብ በሌሎች ብሔሮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን የመስቀል በዓል እንዳያከብር ስለመደረጉ ተነግሯል። የዶንጋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ዶህዴድ) ከፍተኛ አመራሮች በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የዶንጋ ብሔረሰብ የራሱን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ተጠቃሚ ስላለመሆኑ ገልጿል።

የዶንጋ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ዶህዴድ) ሊቀመንበር አለሙ ከበደ፣ ምክትል ሊቀ መንበሩ አቶ ለገሰ ልመንጎ እና የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ደነቀ ዲጀጎን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተገኝተዋል። ሊቀ መንበሩ አቶ አለሙ ከበደ እንደተናገሩት፣ ዶንጋ የቀድመው ከምባታ፣ ሀላባ እና ጠምባሮ ዞን መስራች ከሆኑ ብሔረሰቦች አንዱ መሆኑን አውስተው፣ በአዲሱ ክላስቴራዊ አደረጃጀት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስራች ብሔረሰብ ስለመሆኑ አመልክተዋል።

ይሁንና እንደመስራች ብሔረሰብነቱ፣ በሕገ መንግስቱ የተሰጡትን መብቶች ሊጠቀም "አልቻለም" ያሉት ሊቀ መንበሩ፣ የዶንጋ ብሔረሰብ እያቀረበ ያለው የልዩ ወረዳ አደረጃጀት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጠው ጠቁመዋል። በአካባቢው ይህን ጥያቄ የሚያነሱ ወጣቶች እና ፖለቲከኞች ዱራሜ ከተማ በሚገኘው ማረሚያ ቤት በእስር ላይ እንደሚገኙ እና ፓርቲው ሃደሮ ከተማ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱን እንደተነፈገ ገልጸዋል።

"[የብሔሩ ተወላጆች] የብሔረሰቡን ባህል ልብስ ለብሰው ሃደሮ ከተማ ውስጥ የመንቀሳቀስ መብታቸውን ተነፍገዋል" ሲሉ የተደመጡት አቶ አለሙ፣ ባህላዊ አልባሳቱን የመስቀል በዓል በሚከበርበት ወቅት ለብሰው የተንቀሳቀሱ ወጣቶች "ራቁታቸውን የመታሰር በደል ደርሶባቸዋል" ብለዋል። አያይዘውም፣ የመስቀል በዓል (ዶንግ መሳለ) በራስ አስተዳደራዊ መዋቅ እንዳያከብር የዶንጋ ብሔር "መብቱን እንደተነፈገ" አስረድተዋል።

በመሆኑም፣ መንግስት የዶንጋ ብሔረሰብን "ፍትሐዊ ጥያቄ" በመረዳት፣ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ አቶ አለሙ ጥሪ አቅርበዋል።
Via #ድሬቲዩብ

መላው የሀዲያ ወንድም ህዝብ እንኳን ለ2018ዓ.ም ያሆዴ በዓል አደረሳችሁ/አደረሰን ፡፡
09/22/2025

መላው የሀዲያ ወንድም ህዝብ እንኳን ለ2018ዓ.ም ያሆዴ በዓል አደረሳችሁ/አደረሰን ፡፡

09/22/2025
09/22/2025

መላው የከምባታ ሕዝብ እንኳን አደረሳችሁ

Address

New York, NY

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DONGA MEDIA NETWORK HADERO posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share