AM Info.

AM Info. “A whole stack of memories never equal one little hope.” — Charles M. Schulz

06/04/2026

ፎቶውን እርሱት!!
በግፍ የተጨፈጨፈውን ምስኪንና እና የተቃጠለውን ቤተክርስቲያን አስቡት!!

አርሲ የደም ምድር!
06/02/2026

አርሲ የደም ምድር!

 !!የአማራ ህዝብ በምርጫ ካርድ መርጦ ፓርላማ ያስገባቸው ተወካዮችን የመንደሩ ሰው እንኳን አንድ ድምፅ ያልሰጠው ጋሻው መርሻ በድብቅ ሲያደርግባቸው የነበረውን ሴራ ዛሬ በአደባባይ ተናግሮታል...
02/26/2026

!!
የአማራ ህዝብ በምርጫ ካርድ መርጦ ፓርላማ ያስገባቸው ተወካዮችን የመንደሩ ሰው እንኳን አንድ ድምፅ ያልሰጠው ጋሻው መርሻ በድብቅ ሲያደርግባቸው የነበረውን ሴራ ዛሬ በአደባባይ ተናግሮታል።
!!

በነገራችን ላይ ጋሻው መርሻ ክርስቲያን ታደለን እንዲታሰር ከማቃጠር ጀምሮ ከመጋረጃ ጀርባ የውሸት ምስክርነት ተሰጥቶበታል። ጊዜ ደኛ ነው!!

አገኘሁ ተሻገር 🙂የፌዴሬሽን ምክርቤት አለቃ ናቸው😏
01/31/2026

አገኘሁ ተሻገር 🙂
የፌዴሬሽን ምክርቤት አለቃ ናቸው😏

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የወልቃይት ፥ ራያ እና ጠገዴ የምርጫ ወረዳዎችን በአማራ ክልል ቢያካትታቸው ኖሮ የአማራ ክልል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚኖረው የወንበር ብዛት 147 እንጅ 143...
01/31/2026

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የወልቃይት ፥ ራያ እና ጠገዴ የምርጫ ወረዳዎችን በአማራ ክልል ቢያካትታቸው ኖሮ የአማራ ክልል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚኖረው የወንበር ብዛት 147 እንጅ 143 አይደለም ።
ወደ አማራ ክልል ሳይካተቱ የቀሩትን የምርጫ ወረዳዎችን ስም ልዘርዝር

ራያ 1ኛ- አላማጣ ወረዳ
2ኛ- አላማጣ ከተማ
3ኛ- ኮረም

ወልቃይት ጠገዴ
1ኛ- ቃፍቲያ ሁመራ
2ኛ- ሰቲት ሁመራ
3ኛ- ወልቃይት
4ኛ- ጠገዴ
5ኛ- ማይካድራ
ጠለምት
1፥ ጠለምት። ናቸው ።

እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት፣ የአማራ ክልል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለው 138 ወንበሮች ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ አልተደረገም።

ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ዝግጅት እያደረገ ቢሆንም፣ አዳዲስ የወንበር ድልድሎችን ወይም ጭማሪዎችን በተመለከተ ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም። የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 54(3) የፓርላማ ወንበሮች ብዛት በየአሥር ዓመቱ በሚካሄድ የሕዝብ ቆጠራ መሠረት ሊሻሻል እንደሚችል ቢደነግግም፣ በሀገሪቱ ላለፉት 20 ዓመታት ገደማ አዲስ የሕዝብ ቆጠራ ባለመካሄዱ የድሮው ድልድል እንደቀጠለ ነው። አብይ አህመድ ለአማራ ክልል "አዝኖ" (😂) በፓለቲካዊ ውሳኔ 5 የፓርላማ ወንበር ጨምሯል እንዳይባል የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበሮች ከ550 እንዳይበልጡ በህገ መንግስቱ በአስገዳጅ ሁኔታ ( shall not exceed 550) በሚል ህገ መንግስታዊ ገደብ ተቀምጦበታል ። ታዲያ ከአዲስ አበባ ወይስ ከኦሮሚያ ተቀንሶ ነው ለአማራ ክልል የፓርላማ ወንበር የተጨመረው?

የወንበር ብዛት የሚወሰነው በሕዝብ ቁጥር ላይ ተመሥርቶ በሚደረግ የምርጫ ወረዳዎች የድንበር ክለላ (Constituency delimitation) ነው።
​የኢትዮጵያ የምርጫ ወረዳዎች የድንበር ክለላ ከ1987 ዓ/ም (ከመጀመሪያው ምርጫ) ጀምሮ እስካሁን ድረስ በሲዳማ ክልል ከተደረገው መጠነኛ ማስተካከያ በስተቀር ለውጥ አልታየበትም።
​ለማጠቃለል፦ የአማራ ክልል በፌዴራል ፓርላማ የሚወክሉት የምርጫ ክልሎች (Constituencies) አሁንም 138 ናቸው።

የምርጫ ወረዳዎችን የማስፋት ወይም ጭማሪ ካለ በይፋ ህዝብ እንዲያውቃቸው ይደረግ ነበር ።

©️ኤልሻዳይ የጊዮን ልጅ

01/31/2026

ተከዜ ወንዝ ላይ ልብሳቸውን አውልቀው ፎቶ የተነሱት የሰሊጥ ነጋዴዎች ዘመቱ ወይ?

01/30/2026

ወልቃይት ላይ ስልጣን የያዛችሁ ፣መሬት የምታሳርሱ እና ሰሊጥ የምትነግዱ እንዲሁም በዚህ መዋቅር ተጠቃሚ የሆናችሁ ሁሉ አማራ አማራ እያላችሁ ባትፅፉ ጥሩ ነው። አማራን ስሙን ጠራችሁት አንጂ ወልቃይትን ይዛችሁ ለአማራው ምን አበረከታችሁለት? ይልቁንም ወደቀልባችሁ ብትመለሱ እና ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት በመፍጠር ሰላም ብትሰጡት ይሻላል።

❌ለትግሬውም ይህ ንግግሬ ይሰራል!!

12/12/2025

የአማራ ባንክ ባለፉት አምስት ወራት 1 ነጥብ 15 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዘገበ።

የአማራ ባንክ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ከታክስ በፊት የ1 ነጥብ 15 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታውቋል።

አፈጻጸሙን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዮሐንስ አያሌው (ዶ.ር) የተመዘገበው ትርፍ በ2017 በጀት ዓመት ከተመዘገበው የ910 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አምስት ወራት 3 ነጥብ 55 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስመዝገብ እንደተቻለም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጠቅሰዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለውም በእነዚህ አምስት ወራት ውስጥ የተመዘገበው አፈጻጸም በጠንካራ የሃብት ማሰባሰብ፣ በዲጅታል ትራንስፎርሜሽን እና በብድር አስተዳደር ላይ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ላይ አተኩሮ መሥራት በመቻላቸው የመጣ ነው ብለዋል።

የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን እስከ ኅዳር 2018 ዓ.ም 35 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ደርሷል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዕድገቱ 82 በመቶ መኾኑንም ጠቁመዋል። ይህም በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ የ4 ነጥብ 29 ቢሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል ነው ያሉት።

በውጭ ምንዛሪ 76 ነጥብ 58 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ በመሰብሰብ የላቀ አፈጻጸም አሳይቷልም ብለዋል። ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ313 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ነው ያሉት።

አማራ ባንክ ከተመሠረተ ጀምሮ ያቀረበው አጠቃላይ ብድር እና የቅድሚያ ክፍያ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረበት በ53 ነጥብ 8 በመቶ በማሳደግ 31 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር አበድሯል ብለዋል።

ብድር ማስመለስ በኅዳር 2017 ዓ.ም ከነበረበት 12 ነጥብ 9 በመቶ ያልተከፈለ ብድር ጥምርታን ወደ 4 ነጥብ 06 በመቶ እንዳወርድ ርብርብ ተደርጓል ነው ያሉት።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው በመግለጫቸው ኅዳር 20/2018 ዓ.ም የባንኩ 4ኛ ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ጉባዔ በስኬት ተካሂዶ መጠናቀቁን ጠቁመው ለተሳታፊዎቹ ምስጋና አቅርበዋል። በተጨማሪም ከሕዝቡ፣ ከመላው ባለአክሲዮን እና ደንበኞች ጋር ኾነው በየጊዜው የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን እየተወጡ መኾናቸውንም ጠቁመዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/
Ticktock: https://www.tiktok.com/?_t=ZM-8uQMisH1Hd7&_r=1
Website: https://www.amharacomm.gov.et

 ?በፕሬዘዳንቱ አማካኝነት የአማራ ባንክ ጉዳይ መነሳቱ ካልቀረ ባንኩ አንድ የአማራ ህዝብ የፋይናስ ተቋም በመሆኑ ዘለቅ አድርገን ስለ ባንኩ   የቦርድ አባላት ማንነት ማወቁ የመላው አማራ ሕ...
12/11/2025

?

በፕሬዘዳንቱ አማካኝነት የአማራ ባንክ ጉዳይ መነሳቱ ካልቀረ ባንኩ አንድ የአማራ ህዝብ የፋይናስ ተቋም በመሆኑ ዘለቅ አድርገን ስለ ባንኩ የቦርድ አባላት ማንነት ማወቁ የመላው አማራ ሕዝብ በተለይ በባንኩ ካፒታል ላይ የባለቤትነት ድርሻ ላላቸው ባለአክሲዮን (Shareholders) ለሆኑ ሰዎች ጠቃሚ መረጃ ነው የሚል እምነት አለኝ ።

የአማራ ባንክ የቦርድ አባላት የሚከተሉት ናቸው ፡-

1. ጋሻው ደበበ _ቦርድ ሰብሳቢ _ጎንደር
2. እውነቴ አለነ- ጎንደር
3. ብርሃኑ ጣምያለው-ጎንደር
4. ዶ/ር ኤደን አሸናፊ-ጎንደር
5. ሃይለማርያም ተመስገን- ጎንደር
6. ቢያድግልኝ- (የደብረታቦር ከንቲባ የነበረ)- ጎንደር
7. አባቡ እምሩ_ወሎ
8. መሰንበት ሸንቁጤ-ሸዋ
9. ብርሃን ሃይሉ_ ሸዋ
10. ዶ/ር ሙሉነሽ አበበ -ጎጃም ::

በቀጣይ የሌሎችን የአማራ ህዝብ የፋይናስ ተቋማትን ለምሳሌ የአባይ ባንክ እና የሌሎች የቦርድ አባላት ስብጥር እና አመራሮችን ማወቅ ትፈልጋላችሁ?

እንኳን ደስ አለን!!
09/08/2025

እንኳን ደስ አለን!!

Address

New York, NY

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AM Info. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category