
10/12/2025
ወጣቷ በሰዉ እጅ ተገ""ድላ ተገኘች 😭
እናንዬ ትባላለች ወጣትና የአንድ ልጅ እናት ስትሆን በጎንደር ከተማ ማራኪ ክፍለከተማ ነዋሪና ህይወትን ለማሸነፍ ምግብና መጠጥ በመሸጥ ራሷን ታስተዳድር ነበር ።
ከወራት በፊት ግን ለወትሮው እለት ከእለት ተዘግቶ የማያዉቀዉ የእናንንዬ ቤት ድንገት ለቀናት ሳይከፈት ይሰነባብታል ። ይህን የታዘቡ አከራዮች ለቤተሰቦቿ ይደዉላሉ ። ቤተሰቦቿም ያለችበትን ለማወቅ እንዳልቻሉና ለእነሱም ደብዛዋ እንደጠፋባቸዉ ይነግሯቸዋል ቤቷ እንደተዘጋ ይሰነብታል ።
ቀናት ቀናትን እየተኩ ሲሄዱ ቤተሰብ መጨነቅ ና ማፈላለግ ይጀምራሉ ። ከዚህ መካከልም ለቀናት ዝግ በነበረው የእጅ ስልኳ ተከፍቶ ለቤተሰቡ ደህና ነኝ አዲስአበባ በድንገት ስለሄድኩ ገንዘብ ስለቸገረኝ ላኩልኝ የሚል አጭር መልዕክት ለሟቿ ወንድም ይደርሳል ።
ወንድምዬዉም መጀመሪያ ክፉ ነገር ይፈጠራል ብሎ አልተጠራጠረም ነበርና ገንዘቡን ይልካል ። ብሩ እንደደረሳት ለማረጋገጥ ሲደዉል ግን ስልኩ መልሶ ተዘግቷል ለቀናት ለማግኘት ሙከራ ሲያደርግም በፅሁፍ መልዕክት ደህና እንደሆነችና በቅርቡ ወደ ጎንደር እንደምችመለስ በመፃፍ እንጂ በድምፅ ማግኘት አልቻለም ። ይሄኔ በመጠራጠር ማፈላለግ ይጀምራል ሆስፒታል እና ሌሎች ቦታዎች በሚያፈላልግበት ወቅት ይህቺው እናንዬ የተባለችው ወጣት አየሁኝ ሰማሁኝ የሚል በመጥፋቱ ጉዳዩን ወደ የህግ አስፈፃሚዎች በመዉሰድ በስልኳ አማካኝነት በተደረገ ክትትል የሟቿ የእጅ ስልክ እንደተባለው አዲስአበባ ሳይሆን ጎንደር እንደሆነ በጅፒኤስ አማካኝነት ይታወቃል ።
ፖሊስ ክትትሉን በመቀጠል የስልኩን አድራሻ ፈልጎ ሲያገኘዉ ግን እንደተባለው ግለሰቧ ሳይሆን ስልኩን የያዘው ሌላ ግለሰብ መሆኑን ያረጋግጣል ። ይህን ግለሰብም በቁጥጥር ስር በማዋል ምርምራ ይጀመራል ።
በምርመራ ወቅትም ይህ የድሮ ደንበኛዋ የነበረዉ ግለሰቡ እናንዬን መግደሉንና አስከሬኑንም ከከተማ ወጣ ባለ አቡነሐራ አካባቢ በተባለ ሰዋራ ስፍራ መጣሉን ያምናል ። ፖሊስም ወደስፍራው በመሄድ ማጣራቱን ሲቀጥል ከወር በፊት አንዲት ግለሰብ አስከሬን መገኘቱንና ምንም አይነት ማንነቷን የሚገልጽ መረጃ ባለመገኘቱ በመዘጋጃ ቤት አማካኝነት መቃብሯን ያረጋግጣል ።
በዚህ መልክ ተገድላ የተገኘችው የእናንዬ አስከሬን በማዘጋጃ ቤት ቤተሰብ ከሌላቸው መቀበርያ ቦታ ወጥቶ ወደ ትዉልድ ከተማዋ ደባርቅ መወሰዱንና በአስከሬን ምርመራ ወቅትም በሰዉ እጅ በአሰ""ቃቂ ሁኔታ መገደሏን ያረጋገጠው ፖሊስ ተጠርጣሪውን በህግ ጥላ ስር በማዋል የክስ ሂደት ላይ እንደሆነ ከጎንደር ካሉ የመረጃ ምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።