
06/22/2025
#በጣናነሽ
ክፍል 1
ጊዜዉ 2004/5 ይመስለኛል የግንቦት ወር ሐሙስ ማለዳ ከተንጣለለዉ የጣና ሃይቅ ፊት ለፊት ከግዙፏ ጣናነሽ መርከብ ስር ተገኝቻለሁ አልፎ አልፎ በጣና ሃይቅ ና በሃዋሳ ፍቅር ሃይቅ በባቡጋያ መሰል ሃይቆች ከማደርገዉ የጀልባ ሽርሽር ባለፈ ረጅም ርቀት የባህር ጉዞ አድርጌ ስለማላዉቅ የአዲስ ነገር የመሞከር ጉጉትና በባህር ዉስጥ ምን ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት እንደ ሸበበኝ ከጧት እንቅልፍ ጋር እየታገልኩ የጣናንና የጨረቃን ጉርብትና እያደነኩ እያለ የመርከቧ የመጨረሻ የመንገደኞች ጥሪ ጡሩንባ ነፍታ ጣናነሽ ለጉዞ መንገደኞች ደግሞ ወደ መርከቧ ሆድ ለመግባት እንቅስቃሴ ተጀምሮ በተደበላለቀ ስሜት ወደ 3ኛ ደረጃ የመንገደኞ መቀመጫ(ቴራስ)ከጓደኞቸ ጋር ተሳፈርኩ::
ስለ የባህር ጉዞ ካነሳሁ አይቀር የባህርን ዉበትና የመርከበኛን ሕይዎትን በተመለከተ የማወቅ ጉጉት የፈጠረብኝ የተሰኘ መፅሐፍ ነዉ:: አንብባችሁት ይሆን?
በመርከብ ስለመጓዝ crazy ሃሳብ ያመጣዉ ማን እንደሆነ ባላስታዉስም ከጣና ዳር ከቀድሞዉ ጊዮን ሆቴል ጎን መርከቦች ድርጅት ቢሮ ከጉዞዉ ሁለት ቀን በፊት ተገኝተን ለጉዞ በ3ኛ ማዕረግ ደረጃ 137 ብር ከፍለን ትኬት እንደቆረጥን አስታዉሳለሁ:: ዕለተ ሐሙስ እስኪደርስ በጉጉት መጠበቃችን ከጉዞ እንዳንዘገይ በየሩማችን በየ ደቂቃዉ እንቅልፍ እንዳይጥለን እየተደዋወልን ቸክ ስንደራረግ ከቆየን በኋላ ልክ ከለሊቱ 11:00 ከሆቴላችን ዉጥተን በነፋሻማዉ ዓየር ታጅበን ወደ ተንጣለለዉ የጣና ሃይቅ ወደ የሐይቁ ሞገስ ጣናነሽ የደረስን።
👉🏼ሐሙስ ማለዳ በሰዓቱ የደረሰዉተሳፋሪዉ ሁሉ ወደ መረከቧ ሆድ ገብቶ ካበቃና ጣናነሽ የመጨረሻ ጡሩንባዋን ካሰማች በኋላ መልህቋን ሰብስባ ጉዞ ጎርጎራ
Tip ጎርጎራ ለመድረስ በርከት ያሉ ደሴቶችና የባህር ላይ የተለያዩ ትዕይንቶችን ያለፍን በመሆኑ የባህር ላይ የጉዞ ትወስታየን በሚቀጥለዉ ክፍል እተርካለሁ::