Ethiopia Today

Ethiopia Today Stay Informed and Join our Community of Active, Concerned Citizens.

እንኳን ወደ Ethiopia Today-የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ገጽ በደህና መጡ። በኢትዮጵያ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች ላይ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት Ethiopia Today መድረሻዎ ይሁን። ተልዕኳችን ሀገራችን የተመለከቱ ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃዎችን እና ትንተናዎችን ማቅረብ ነው። ይቀላቀሉን እና መረጃ ያግኙ።

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ የአርሴማ ቤተክርስቲያን ካህናት ሌሊቱን መታጣቂዎች ተገደሉ::+++++++++++++++++++++++++++++++++በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ የመካ...
10/05/2023

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ የአርሴማ ቤተክርስቲያን ካህናት ሌሊቱን መታጣቂዎች ተገደሉ::
+++++++++++++++++++++++++++++++++

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ የመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች በጥይት መገደላቸው ተገለጸ፡፡

ድርጊቱ የተፈጸመው መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ ሲሆን ከተገደሉት አንድ ካህን እና ዲያቆን በተጨማሪ ሁለት ካህናትና አንድ ምእመን በታጣቂ ኃይሎቹ ታግተው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል፡፡

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ በተደጋጋሚ ጊዜ ካህናትና ምእመናን ላይ ጥቃቶች እንደሚደርሱ የሚታወቅ ነው ። በዚህም ምክንያት በርካታ ምእመናን አካባበቢውን እየለቀቁ መሰደዳቸውም ይነገራል፡፡

10/02/2023

በአርሲ ሀገረ ስብከት በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ቤተ ክህነት የቦሌ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደሪ ባለቤት እና ልጃቸውን ጨምሮ ሰባት ምእመናን በታጣቂዎች ተገደሉ::
+++++++++++++++++++++++++++++++

መስከረም 15/2016 ዓ.ም በኦሮምያ ክልል አርሲ ሀገረ ስብከት በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ቤተ ክህነት ከምሽቱ 4 እስከ 5 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ 7 ኦርቶዶክሳውያን መገዳላቸውን ከጣቢያችን ቆይታ ያደረጉ የአካባቢው ምእመናን ተናግረዋል።

ድርጊቱን የፈጸሙት አካላት በሀገረ ስብከቱ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ቤተ ክህነት የቦሌ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደሪ በሆኑት ካህን ላይ መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በመሄድ ግድያ ለመፈጸም ቢሞክሩም አስተዳደሪው በኋላ በር አምልጠው ሕይወታቸውን አትርፈዋል።
ይሁን እንጂ በዚህ በቃኝ ያላሉት ጥቃት ፈጻሚዎች ቤት ውስጥ ያገኙዋቸውን የአስተዳደሪውን ባለቤት ከእነ ልጃቸው በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ደብድበው መግደላቸውን የአካባቢው ምእመናን ተናግረዋል።
በዚህ ጥቃትም ወንበር ዘርገተው የሚስተምሩ እንድ የአብነት ትምህረት ቤት መምህር ጨምሮ በአጠቃላይ 7 ኦርቶዶክሳውያን የተገደሉ ሲሆን 5 ምእመናን ካባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ለጣቢያችን ተናግረዋል።

ምእመናኑ በተደጋጋሚ በአካባቢው ላይ ኦርቶዶክስ ተኮር በሆነ መልኩ ለሚፈጸም ጥቃት መንስኤ የሆነው በአካባቢው በሕገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎችን መቆጣጣር ባለመቻሉ መሆኑንን ጠቅሰዋል። አሁን በደረሰው ጉዳት ምክንያትም በአካባቢው ቤተክርስቲያን የምትሰጠው አገልግሎት መቋረጡን ገልጸዋል።

በዚህም የአካባቢው ምእመናን የመኖር ህልውናቸው አደጋ ላይ መሆኑን በመጥቀስ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስጋታችንን ተረድቶ ጥቃቱ እንዲቆም ከሚመለከተው አካል ጋር ተገቢውን ስራ ካልከወነ ዛሬ በአባቶቻችን፣ ወንድም እና እህቶቻችን ላይ የደረሰው ዕጣ ነገ በእኛ ላይ እንደማይደርስ ምንም ዋስትና የለንም ብለዋል።

08/27/2023

France 24 የዜና ጣቢያ በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ ስላለው ግፍ የዘገበው ዘገባ
=========================================================================
#ሳውዲአረቢያ #ኢትዮጵያ

የአማራ ክልል በአምስት ዓመት ውስጥ ስድስተኛውን ርዕሰ መስተዳድር ሾመ===================================የአማራ ክልል ምክር ቤት አርብ ነሐሴ 19፤ 2015 ባካሄደው አስ...
08/26/2023

የአማራ ክልል በአምስት ዓመት ውስጥ ስድስተኛውን ርዕሰ መስተዳድር ሾመ
===================================

የአማራ ክልል ምክር ቤት አርብ ነሐሴ 19፤ 2015 ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አቶ አረጋ ከበደን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾመ። አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የተሾሙት ላለፉት ሁለት ዓመታት ገደማ ክልሉን የመሩት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ያቀረቡት የስልጣን መልቀቅ ጥያቄ በምክር ቤቱ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ነው።

አቶ አረጋ ከበደ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው እስከተሾሙበት ዕለት ድረስ የአማራ ክልል የስራ ፈጠራና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በልማት አስተዳደር የሰሩት አቶ አረጋ፤ ወደ ክልል የኃላፊነት ቦታ የመጡት፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ረዳት የህዝብ ተሳትፎ አማካሪ በመሆን ነው። ከዚያ በመቀጠልም የክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል።

ከአራት ዓመታት በፊት በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ከተፈጸመው ጥቃት በኋላ አቶ አረጋ፤ የክልሉን ሚሊሺያ ጽህፈት ቤት በኃላፊነት እንዲመሩ ተሹመዋል። ነገር ግን በዚህ የኃላፊነት ቦታ ላይ የቆዩት ለአንድ ዓመት ያህል ብቻ ነው። በሐምሌ 2012 የክልሉ ቴክኒክ ሙያ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ በመሆን፤ የወቅቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ካቢኔ ተቀላቅለዋል።

አቶ አረጋ ከስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በኋላ በአማራ ክልል አዲስ መንግስት ሲመሰረት፤ የክልሉ የስራ ፈጠራ እና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። አቶ አረጋ ወደ ክልል ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት፤ በምስራቅ ጎጃም ዞን በወረዳ እና በዞን አመራርነት ሰርተዋል። አዲሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የምስራቅ ጎጃም ዞንን በምክትል አስተዳዳሪ እና በዋና አስተዳዳሪነት መርተዋል።

የአቶ አረጋ ሹመት የአማራ ክልልን ባለፉት አምስት ዓመታት በርካታ የርዕሳነ መስተዳድር ሹም ሽር የተካሄደበት ክልል አድርጎታል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን ካመጣው የፖለቲካ “ለውጥ” በኋላ፤ አቶ አረጋ ክልሉን ለማስተዳደር ሲሾሙ አምስተኛው ርዕሰ መስተዳድር ናቸው።

08/21/2023

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ ባለዉ ውጊያ ከክልሉ መንግሥት መዋቅር ውጪ ናቸው ያላቸውን ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች አሳወቀ
===========================================================

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከስር የተዘረዘሩ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ከመንግሥት መዋቅር ውጪ ስለሆኑ ምንም አይነት ገንዘብ ዝውውር እንዳይፈፀም እገዳ ደብዳቤ ፅፏል።

ከእነዚህ ውስጥ!

▪ከሰሜን ሸዋ ወረዳዎች:-ሚዳ፣መርሃቤቴ፣ አለም ከተማ ፣እነዋሪ፣ መንዝ ቀያ፣ መንዝ ላሎ፣መንዝ፣ ማማ፣መንዝ ሞላሌ፣ መንዝ ጌራ፣ ሲያደብር፣ ዋዩ፣ እንሳሮ ፣ምረትና ጅሩ ወረዳዎች

▪ሰሜን ወሎ ወረዳዎች:- ግዳን ወረዳ ፣እስታይሽ፣ ቡግና እና ሙጃ ወረዳዎች

▪ከደቡብ ወሎ ወረዳዎች:- ወግዲ ወረዳ፣ ከለላ፣ መካነሰላም ፣ቦረና እና ዋድላ ደላንታ ወረዳ

▪ከምዕራብ ወሎ ወረዳዎች:- አማራ ሳይንት

▪ከደቡብ ጎንደር ወረዳዎች:- ደብረታቦር ከተማን ጨምሮ ሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች

▪ከጎጃም:- ሰሜን ጎጃም፣ ምስራቅ ጎጃም እና ምዕራብ ጎጃም ሁሉም ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች

▪ማዕከላዊ ጎንደር ወረዳዎች:- ምዕራብ ደንብያ ወረዳ፣ጣቁሳ፣አለፋ፣ምስራቅ ደንብያ፣ሻውራ፣ቆላድባ ወረዳዎች

▪ከምዕራብ ጎንደር ወረዳዎች:- ቋራ ወረዳ

▪ከሰሜን ጎንደር ወረዳዎች:- ጃናሞራ ወረዳዎች ከመንግሥት መዋቅር ውጪ ናቸው ብሏል። በእነዚህ ወረዳዎችም ምንም አይነት የገንዘብ ዝውውር እንዳይኖር የክልሉ ገንዘብ ቢሮ አግዷቸዋል።

አቶ  #ዮሐንስቧያለው በጸጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወሰዱ======================================የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው...
08/15/2023

አቶ #ዮሐንስቧያለው በጸጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወሰዱ
======================================

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው ዛሬ ከባህር ዳር በጸጥታ ኃይሎች መወሰዳቸውና ተሰማ።

ባለፈው ስምንት ታፍነው እንደተወሰዱት የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ሁሉ አቶ ዮሐንስ ቧያለውም የምክር ቤት አባል በመሆናቸው ያለመከሰስ መብት ያላቸው መሆኑ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲዊ ሪፐብሊክ ህገ- መንግስት እና የክልል ህገ-መንግስታት ያለመከሰስ መብት ከሰጣቸው ወገኖች መካከል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የክልል ምክር ቤት አባላት ተጠቃሽ ናቸው።

አቶ ዮሐንስ ቧያለው በምን የህግ ማእቀፍ በቁጥጥር ስር መዋላቸው እስካሁን ከክልሉም ሆነ ከፌደራል አካላት የተገለጸ ነገር የለም::

08/14/2023

የቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በምክር ቤቱ ያደረጉት የተቃውሞ ንግግር
============================================

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን ያመጣውን “ለውጥ” ከመሩ ባለስልጣናት አንዱ መሆናቸው የሚነገርላቸው አቶ ገዱ፤ በዋነኛነት በአማራ ክልል ተፈጻሚ የሚሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ከመጽደቁ በፊት ባስደመጡት አስተያየት ነው፤ በክልሉ በአሁኑ ወቅት ያለውን ችግር ለመፍታት መፍትሔው “የፖለቲካ ውይይት፤፡ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። “ይህን ችግር በቅንነት ለመፍታት ከተፈለገ መፍትሔው፤ እስካሁን በአማራ ክልልም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ሲሞከር ከርሞ ሀገርን ወደ ከፋ ጥፋት ያመራው ወታደራዊ ኃይል መጠቀም ሳይሆን፤ የፖለቲካ ውይይት ነው የሚል እምነት አለኝ” ብለዋል አቶ ገዱ።

ከጥቂት ቀናት በፊት የአብይ መንግስት የአማራ ክልላዊ መስተዳድር ምክርቤትን በማፍረስ ጊዜያዊ አስተዳደር ሊያቋቁም ምክር ላይ እንደሆነ አፈትልከው የወጡ ወሬዎችን መሰረት በማድረግ የዛሬው የአቶ ገዱ ንግግር አጀንዳ ለማስቀየር የተደረገ ነው የሚሉ የተለያዩ አስተያየቶችም እየተደመጡ ነው::

08/13/2023

የኢትዮጵያ መንግስት በፍኖተ ሰላም የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት አደረሰ።
=====================================================

የኢትዮጵያ መንግስት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን #ፍኖተ ሰላም መሀል ከተማ ላይ የድሮን ድብደባ ፈፀመ፡፡ በዚህ በኢትዮጵያ አየር ሃይል በተፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የበርካታ ንፁሃን ዜጎች ህይወት በአሳዛኝ ሁኔታ አልፏል። የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ከአዲስ አበባ 376 ኪ.ሜ ርቀት እንዲሁም ከክልሉ ርእሰ ከተማ ባህር ዳር 180 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ የምዕራብ ጎጃም ዞን መቀመጫ ናት፡፡

የአንድ ሐገር ሰራዊት ቀዳሚ ሚና ሀገርንና ህዝብን መከላከል ሲሆን መሰል ድርጊቶች በመንግስት እና በዜጎች መካከል አለመተማመንን መፍጠር ብቻ ሳይሆን የዜጎችን መብት ለማስጠበቅ የተነደፉትን አለም አቀፍ ህጎችንም ይጥሳል። በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች በመንግስት እየተፈጸሙ ስላሉት የድሮን ጥቃቶች እና በንጹኃን ላይ ስለደረሰው ጉዳት ከክልሉም ሆነ ከፌደራል መንግስት አካላት የተሰጠ ማብራርያ እስካሁን የለም።

The Ethiopian government launched a attack in Selam.
================================================
The government carried out a drone strike on the city center of Fnote Salam in the West Gojam zone of the Amhara region. The attack, executed by the Ethiopian Air Force, has resulted in the tragic loss of many innocent lives. The primary role of a country's military is to protect the nation and its citizens. These recent drone attacks raise serious questions about the relationship between the Ethiopian government and its people and potential violations of international laws designed to safeguard civilian rights.

As of now, there has been no official explanation from either the state or the federal government regarding the drone attacks being carried out in various cities in the Amhara region. The lack of transparency and accountability adds to the growing concern over the harm done to innocent people.

OOHCHR AAmnesty International

አቶ  #ክርስቲያን ታደለ በጸጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወሰዱ======================================የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ ...
08/05/2023

አቶ #ክርስቲያን ታደለ በጸጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወሰዱ
======================================

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ ትላንት ማምሻውን ከመኖሪያ ቤታቸው በፌደራል ፖሊስ መወሰዳቸውና ድብደባ እንደደረሰባቸው ተሰማ።

አቶ ክርስቲያን የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል በመሆናቸው ያለመከሰስ መብት ያላቸው መሆኑ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲዊ ሪፐብሊክ ህገ- መንግስት እና የክልል ህገ-መንግስታት ያለመከሰስ መብት ከሰጣቸው ወገኖች መካከል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የክልል ምክር ቤት አባላት ተጠቃሽ ናቸው። ለአብነት የህዝብ ተወካዮችን በሚመለከተው የአፌዲሪ ህገመንግስት አንቀፅ 55 (6) ላይ የአለመከሰስ መብትን እና መብቱ የሚነሳበትን አግባብ እንደሚከተለው ደንግጓል።

«ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል ከባድ ወንጀል ሲፈፅም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም፣ በወንጀልም አይከሰስም።»

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ በምን የህግ ማእቀፍ በቁጥጥር ስር መዋላቸው የታወቀ ነገር የለም::

በጠ/ሚ ዓብይ አህመድ የሚመራው የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ወሰነ======================================ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ...
08/04/2023

በጠ/ሚ ዓብይ አህመድ የሚመራው የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ወሰነ
======================================

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ በ #አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ያጋጠመው ችግር በመደበኛው የህግ ማስከበር ሥርዓት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጅ ስላለበት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህገመንግስቱን መሰረት በማድረግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወስኗል ብሏል::

እንደሚታወቀው የፌዴራል መንግስት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ የሚገባበትን ሁኔታ የሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 359/2003(95) ሲሆን በዚህ አዋጅ መሰረት የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ወሰኑ እስከምን ድረስ እንደሆነ በግልፅ ተደንግጓል፡፡ በአዋጁ አንቀፅ 14(2)(ለ) ስር እንደተደነገገው የፌዴራሉ መንግሥት የክልሉን ምክር ቤትና የክልሉን ከፍተኛ የህግ አስፈፃሚ አካል በማገድ/በማፍረስ ለፌዴራል መንግስቱ ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም የመወሰን ስልጣን ጭምር አለው፡፡ ይህንንም ህግ ከዚህ ቀደም የፌደራል መንግስቱ በሶማሌ ክልል ላይ ተግባራዊ ማድረጉ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው:: አሁንም የአብይ መንግስት ይህንን ተመሳሳይ ዘዴ በመከተል የአማራ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤትን በማፍረስ እና የራሱን ሰዎች በመሾም ክልሉን ወደ ለየለት የጦርነት አውድማ የሚቀይር ውሳኔ እንዳይወስን የብዙዎች ፍራቻ ነው::

08/02/2023

ቅዱስ ሲኖዶስ በአክሱም የተፈጸመውን ሕገ ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሢመት፣ ፈጻሚዎቹንና የተፈጸመላቸውን ሁሉ አወገዘ
==========================================

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሔደው አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ፣ ባለፈው ሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም.፣ በርእሰ ገዳማት ወአድባራት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ በአራት የትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት መሪነት የተፈጸመውን ቀኖና አፍራሽ ሕገ ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሢመት በመቃወም፣ ሿሚዎቹንና ተሿሚዎቹን አወገዘ፡፡

የቅዱስ ሲኖዶሱን ስብሰባ በርእሰ መንበርነት የሚመሩት ብፀዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ሕገ ወጦቹ ኤጲስ ቆጶሳት፣ “በሕዝባቸው ተመርጠው ለሕዝባቸው የተሾሙ ናቸው፤” ሲሉ፣ በውግዘቱ እንደማይተባበሩ በመግለጽ ውግዘቱን ተቃውመዋል፡፡ ድርጊቱን ማውገዝ ስሕተት እንደኾነ፣ ጉዳዩም በሽምግል እና በይቅርታ ታይቶ በዕርቀ ሰላም እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡ ለዚኽም፣ ከኹሉም አካባቢዎች የተውጣጡ ባለሞያዎች እና ገለልተኛ ሽማግሌዎች እንዲሠየሙ አመልክተዋል፡፡

በቅዱስ ሲኖዶሱ እንዲወገዙ ከስምምነት የተደረሰባቸው የአራቱ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ (የመቐለ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)፣ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ (የማዕከላዊ ትግራይ-አኵስም ሀገረ ስብከት)፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (የሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ-ሽረ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት) እና ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ (የምሥራቃዊ ትግራይ ዓዲግራት ሀገረ ስብከት) ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡ ከእነርሱም ጋራ፣ ሐምሌ 16 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ ሳይስማማበት እና ሳይወስን ቀኖናንና ሕግን በመተላለፍ ኤጲስ ቆጶስነት የሾሟቸው ዘጠኝ መነኰሳት አብረው ተወግዘዋል፡፡

ከተሾሙትና ከሾሙት በተጨማሪ በዕጩነት የቀረቡትና የነገሩ ሠሪና አቀናባሪ የሆኑት አባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል እና የሕገ ወጡ ቡድን ቃል አቀባይ የሆኑት መምህር ተስፋዬ ሀደራ አብረው ተወግዘዋል፡፡

07/22/2023

ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ ሕገወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት በአክሱም ተፈጸመ።
================================================

እኒህ መነኮሳት እና አባቶች በቅዳሴ እና በጸሎት ወቅት የሚናገሩት ነገር ግን በተግባር ለማድረግ ካልቻሏቸው ኃይለ ቃል መሃከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፦

➡ “ከወንድሙ ጋራ የተጣላ ቢኖር ይተውለት” ቅዳሴ
➡“ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም እንዲሁ ይቅር ተባባሉ፡፡” ቆላ 3፥13።
➡“በደላችንን ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል” የዘውትር ጸሎትት (አባታችን ሆይ)
➡“ተቆጡ አትበድሉም፤ጸሐይ ሳይጥልቅም ቁጣችሁን አብርዱ፤ መልካም ነገር እንጂ ክፉ ነገር ሁሉ ከአፋችሁ አይውጣ” ኤፌ 4፦26_27
➡“እናንተ የበደሏችሁን ኃጢአት ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ ደግሞ እናንተን ይቅር ይላችኋል፤ነገር ነገር ግን የሰዎችን ኃጢአት የቅር የማትሉ ከሆነ አባታችሁም ኃጣታችሁን ይቅር አይላችሁም”፡፡ ማቴ 6፦14_15
➡“እምከመኬ ታበውዕ መባዓከ ውስተ ምስዋዕ ወበህየ ተዘከርከ እኁከ ዘተኃይስክ ኅድግ ህየ መባዓከ ውስተ ምስዋዕ ሑር ወተኳነን ምስለ እኁከ” ለአምልኮት ተዘጋጅተህ ለአገልግሎት ከመቅረብህ በፊት የበደልከው (ቂም የያዝክበት)ወንድምህ ቢታሰብህ መበዓኽን አስቀምጠኽ ክወንድምህ ጋር ታረቅ ከዚያ በኋላ መበዓኽን አቅርብ”
➡“በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ ጌታ ሆይ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበላየው?እስከ ሰባት ጊዜ ነውን? አለው፡፡ ኢየሱስም “ እስከ ስባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ ብቻ አልልህም” ማቴዎስ 18:21‭-‬22

ምሕረትና ይቅርባይነት ከእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘብ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው:: የእግዚአብሔር ምሕረትና ይቅርታ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡ ከሰው በደል ይልቅ እጅግ ስለበዛው ምሕረቱ «ከማስተዋል በላይ ነው፡፡» በማለት ብዙ ቅዱሳን አባቶች መስክረዋል። አባቶቻችን እንዳስተማሩን እግዚአብሔር በክፉ በደል ሆነን እንኳን ሳለን አይቶ እንዳላየን በይቅርታው የሚያልፈን ጊዜያት ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ ይህንን ከልብ የተገነዘበ ከርስቲያን ሰው ቢበድለው እግዚአብሔር እርሱን እንደማረው እያሰበ ይቅርታን ያደርጋል፡፡ እኒህ በትግራይም ሆነ በአዲስ አበባ ያሉ ቀሳውስት ይህ መሰረታዊ እውነታ እንዴት ተሰወራቸው? ለምንስ ክርስቶስን ሳይመስሉ ብጽዕ ተብለው፣ በቂም እና በቁጣ ተሞልተው እኛን በጎቻቸውን አሳዘኑ?

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ልቡን በማስጨከን ለይቅርታ እንቢተኛ ስለነበረ አንድ ባሪያ እንዲህ በማለት አስተምሯል። ባሮችን ሊቆጣጠር የጀመረ አንድ ንጉሥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን ሰው በፊቱ አመጡለትና ዕዳውን ጠየቀው:: ባሪያውም የሚከፍለው ባጣ ጊዜ በፊቱ ወድቆ ተወኝ በማለት ለመነው፡፡ ጌታውም እጅግ አዘነለትና ዕዳውን ሁሉ በመተው አሰናበተው፡፡ ምሕረትን ያገኘ ያ ባሪያም መቶ ዲናር ያበደረውን ሌላውን ባልንጀራውን አገኘና አንቆ ክፈለኝ በማለት አስጨነቀው:: ባልንጀራውም በፊቱ ወድቆ ጥቂት ታገሠኝ እከፍልሃለሁ በማለት ለመነው፡፡ እርሱም ጨከነበት ዕዳውንም ሊተውለት አልፈቀደምና ወደ ወህኒ አወረደው፡፡

ይህም ነገር በጌታው ዘንድ ተሰማ ይህንም ክፉ ባሪያ አስጠራውና እኔን በለመንኸኝ ጊዜ ሁሉን እዳህን ትቼልህ አልነበረምን? አንተስ ስለምን የባልንጀራህን እዳ አልተዉህለትም? ልትምረው ይገባህ ነበር። አንተ ግን አልወደድህም በማለት ወንድሙን በይቅርታ ዓይን ሊያየው ያልቻለውን አሳልፎ ለሚያሰቃዩት ሰዎች እዳውን እስኪከፍል ድረስ በወህኒ አቆዩት ብሎ በቊጣ ቃል አዘዛቸው። ማቴ 18፥23-35፡፡

በትግራይ ክልል የሚኖሩ ጳጳሳት እና ቀሳውስት ቅዱስ ሲኖዶሱ ይሁን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በትግራይ ሕዝብ እና የእምነት ቦታዎች ላይ ጉዳት ሲደርስ አላወገዙም በሚል ማዘናቸው ተገቢ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ግን ሃይማኖታችን እንደሚያስተምረን የበደለኛን ሰው በደል እያስቡ ልቡናን በማስጨከን ይቅርታ አለማድረግ መንፈሳዊነት አይደለም::

በልቦና ቂም፣ ጥላቻ፣ ተንኮል፣ ቅንዓትን ይዞ የፍቅር ሰው በመምሰል በእግዚአብሔር ቤት በመንፈሳዊ አገልግሎት ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን እየተካፈሉ መመላለስ ይቻል ይሆናል፡፡ነገር ግን ረቂቊን ኅሊና በሚመረምር በእግዚአብሔር ፊት ውስጣዊ ማንነታችን የተገለጠ ነው፡፡ ልብን በሚያውቅ በእግዚአብሔር ፊት የተጣላና የበደለን ሰው በይቅርታ ልብ ሳይመለከቱ ወደ ጌታችን ሥጋና ደም መቅረብ ድፍረት ከመሆኑም ባሻገር ለድኅነት ሳይሆን ለፍርድ ይሆናል፡፡

በዚህ በከፋ ዘመን በእድሜም በእውቀትም የበሰሉ የምንላቸው እና በሥሥት የምንመለከታቸው አባቶች በቂም በበቀል ልቦናቸው ዳምኖ፣ በሹመት ፍቅር ታውረው ማየት ለእኛ ለምእመናኑ ክፉኛ የሚያሳዝን እና ፈተና ውስጥ የሚጥል ነው፡፡ ሆኖም እኒህ በሁለቱም ወገን ያሉ ጥቂት አባቶች አውቀውም ሆነ ሳያውቁ የቅድስት ቤትክርስቲያንን አንድነት ለመናድ ቢተጉም፤ እውነተኞቹ ገዳማውያን አባቶችን ተንሥኡ ለጸሎት፣እኛ ደካሞችን እና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስቡ፤ርሑቀ መዓት ወብዙኀ ምሕረት፤መዓቱ የራቀ ምሕረቱም የበዛ አምላካችን ለሀገራችን ምሕረቱን ለቤተክርስቲያናችን አንድነቱን፤ፍቅሩን እንዲልክልን ጸልዩ እያልንን እንማጸናለን።

Address

San Francisco, CA

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Today posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share