Amanual Gebremariam Yfter

Amanual Gebremariam Yfter Peace for East Africa ✌️ ሰላም ለመላው አለም
Peace for the whole world
(5)

እየተጓዝን ነው ለገሰ ቱሉ ...."ወደ ቀይ ባህር (ዓሰብ) የምናረገውን ጉዞ ከግማሽ መንገድ በላይ ተጉዘናል። የቀረውን በጥቂት ግዜ እናገባድዳለን"።
08/14/2025

እየተጓዝን ነው ለገሰ ቱሉ ....
"ወደ ቀይ ባህር (ዓሰብ) የምናረገውን ጉዞ ከግማሽ መንገድ በላይ ተጉዘናል። የቀረውን በጥቂት ግዜ እናገባድዳለን"።

አንጀሊና ጆሊ የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታልን ጎበኙዝነኛዋ አሜሪካዊት ተዋናይት ፣ የፊልም ባለሙያ እና የሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢ የሆኑት አንጀሊና ጆሊ በዛሬው ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስ...
08/11/2025

አንጀሊና ጆሊ የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታልን ጎበኙ

ዝነኛዋ አሜሪካዊት ተዋናይት ፣ የፊልም ባለሙያ እና የሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢ የሆኑት አንጀሊና ጆሊ በዛሬው ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎብኝተዋል።

ተዋናይቷ ያደረጉት ጉብኝት በዋነኝነት ሆስፒታሉ እየሰጠ በሚገኘው መድሃኒቱን የተላመደ ቲቢ (ኤም.ዲ.አር ቲቢ) ህክምና ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ፣ የሚታዩ ለውጦችን እንዲሁም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ቦታዎች መለየት ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።

በጉብኝቱ ላይ አንጀሊና የሆስፒታሉን የቲቢና መድሃኒቱን የተላመደ ቲቢ (ኤም.ዲ.አር ቲቢ) ህክምና አገልግሎት መስጫ ዋርድ ፣ ላብራቶሪ እንዲሁም ታካሚዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

አንጀሊና ወደ ሆስፒታሉ ከረጅም ጊዜያት በፊት መጥተው እንደነበር ያስታወሱ ሲሆን በአሁኑ ጉብኝታቸው ላይ ሆስፒታሉ ዘርፈ ብዙ ለውጦች አምጥቶ በመመልከታቸው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አክለውም ሆስፒታሉ ድጋፍ ቢደረግለት በቀጣይ የተሻለ
አገልግሎት ለታካሚዎች መስጠት በሚያስችለው አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንዳለ በጉብኝቱ ላይ መገንዘባቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም በሆስፒታሉ በቲቢ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተገኘው እድገት በእጅጉ የሚደነቅ እና የሚያስተማምን ስለሆነ በቀጣይ በጂ.ኤች.ሲ (Global Health Committee (GHC)) በኩል ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሃም እሸቱ በበኩላቸው ቲቢን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተዋናይቱ ላሳዩት ዘላቂ ቁርጠኝነት ፣ ልግስና እና በቀጣይ ለሚያደርጉት ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አንጀሊና ጆሊ ከፊልም ስራ ባሻገር በአለምዓቀፍ ደረጃ ለስደተኞች እና ለሰብአዊ መብቶች ጥብቅና በመቆም በ UNHCR (United Nations High Commissioner for Refugees) የበጎ ፈቃድ አምባሳደር እንዲሁም ልዩ መልዕክተኛ በመሆን ከ20 ዓመታት በላይ በማገልገል በሰሩት ሰፊ የሰብዓዊነት ስራ ይታወቃሉ።

(መሰጃው የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ነው)

በአንድ ስሟ ባልተጠቀሰ ሀገር ውስጥ የሠራዊት አባል የነበር አንድ ወጣት በእግዚአብሔር ፈጽሞ ያምን ስለነበር ባልደረቦቹና ኃላፊዎቹ ሌሎች ሰዎችም ያለማቋረጥ ክብሩን ያዋርዱት ነበር።አንድ ቀን...
08/11/2025

በአንድ ስሟ ባልተጠቀሰ ሀገር ውስጥ የሠራዊት አባል የነበር አንድ ወጣት በእግዚአብሔር ፈጽሞ ያምን ስለነበር ባልደረቦቹና ኃላፊዎቹ ሌሎች ሰዎችም ያለማቋረጥ ክብሩን ያዋርዱት ነበር።

አንድ ቀን መቶ አለቃው በወታደሮቹ ፊት ሊያዋርደው ፈለገና ጠርቶ እንዲህ አለው፦
"ወደዚህ ና! ቁልፉን ይዘህ ሄደህ ያን የሰራዊት መኪና ነድተህ አምጥተህ እዚህ ከፊታችን አቁመው"።

ወጣቱ ወታደር እንዲህ ሲል መለሰ፦ " መኪና መንዳት እንደማልችል ታውቃለህ እኮ ጌታዬ!"

አለቃውም፡-
"እንግዲህ የምታመልከው አምላክህ ይረዳህ እንደሆነ ጠይቀውና አሳየን!"

ወጣቱ ቁልፉን ተቀብሎ ወደ ተሽከርካሪው ሄደና መጸለይ ጀመረ። ከዚያም ተሽከርካሪውን አስነስቶ አለቃው በፈልገው ቦታ ላይ አቆመው።

ወጣቱ ከተሽከርካሪው ሲወርድ ሲጠባበቁ የነበሩት አዛዦቹና ሌሎች ሰዎች ሁሉ ሲያለቅሱ አያቸው። ሁሉም በአንድነት እንዲህ አሉት፡- "አምላክህን ማገልገል እንፈልጋለን!"።

ወጣቱ በሁኔታቸው ተገርሞ ምን እየሆነ እንዳለ ጠየቀ።
አለቃውም እያለቀሰ መኪናው ምንም ሞተርም ሆነ ነዳጅ የሌለው አሮጌ ተሽከርካሪ መሆኑን ኮፈኑን ከፍቶ ለወጣቱ አሳየው።

ወጣቱም አምላኩን እያመሰገነ አለቃውን እንዲህ አለው፡-
"አየህ? ይህ የማመልከው አምላክ፣ ምንም የማይሳነው ጌታ፣ ለባዶው ነገር ሕይወት የሚሰጥ አምላክ ነው። አሁንም የማይቻሉ ነገሮች እንዳሉ ታስብ ይሆናል። ነገርግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉም ነገር ይቻላል።"

የማይቻል የሚመስለው ነገር በፈጣሪ ዘንድ ሁሉም ይችላል። አምላክን በንጽህና ከጠየቅነው የሚሆነንን መርጦ ያሟላልናል።

(ከዚሁ መንደር የተገኘ)

08/07/2025
እዚህ ቤት ውስጥ ያለው እምነትና በረከት በእያንዳንዳችሁ ቤት ይግባ🙏
08/07/2025

እዚህ ቤት ውስጥ ያለው እምነትና በረከት በእያንዳንዳችሁ ቤት ይግባ🙏

የተሰጠንን እድል በአግባቡ እንጠቀም‼️***********************እንግሊዛዊው ማይክል ካሮል ህይወትን ለማሸነፍ ፡ የሚረዳውን ስራ ሲፈልግ ፡ ሲወጣ ፡ ሲወርድ ቆየ ። ግን ለሱ የሚሆ...
08/06/2025

የተሰጠንን እድል በአግባቡ እንጠቀም‼️
***********************
እንግሊዛዊው ማይክል ካሮል ህይወትን ለማሸነፍ ፡ የሚረዳውን ስራ ሲፈልግ ፡ ሲወጣ ፡ ሲወርድ ቆየ ። ግን ለሱ የሚሆን ስራ የለም ።
ለሱ የሚሆን ስራ ያለው አንድ ቦታ ብቻ ነው ። የእንግሊዝ መዘጋጃ ቤት ።
እና የሎንዶን ከተማ ፡ መዘጋጃ ቤት. . የፅዳት ሰራተኞች እንደሚፈልግ ያወጣውን ክፍት የስራ ቦታ አይቶ ሄዶ ተመዘገበ ።
ከቀናት በኋላም ተቀጠረ ።.............
ማይክል ይህንን ስራ በመስራት ላይ እያለ ፡ አንድ ቀን ካገኛት ገንዘብ ላይ ቆጥቦ ሎተሪ ቆረጠ ።
ፈጣሪ በ19 አመትህ የለንደን ከተማ ፅዳት ሰራተኛ ሆነህ አትቅር ሲለው ፡ የቆረጠው ሎተሪ ደርሶት. .. የ18 .4 ሚሊዮን ዶላር አሸናፊ ሆነ ።............
ማይክል ካሮል ፡ ከፅዳት ሰራተኝነት ፡ በአንድ ጊዜ ሚሊየነር ሆነ ። ህይወት ሳቀችለት ።
ቤት ገዛ ፡ መኪኖች ኖሩት ።

ከዚያን እለት ጀምሮም ፡ ስራ የሚባል ነገር አለርጂኩ ሆነ ።

ጠዋት ይነሳል ፡ ሲጠጣ ይውላል ፡ ከብዙ ሴቶች ጋር መዋል ፡ ድራግ መጠቀም ጀመረ ።
አኗኗሩ ቅጥ አጣ ።................
በተለያዩ ወንጀሎች እየተከሰሰ ፡ ፍርድ ቤት መቅረብ ስራው ሆነ ። በዚህም ከሰላሳ ያላነሱ ጊዜያት በተለያዩ ትናንሽ ወንጀሎች ተከሶ ፍርድ ቤት እየቀረበ. .. ፡ በገንዘብ እና በቀላል እስር ይቀጣ ነበር ።

ማይክል የአልኮል ሱሰኝነቱ ከመብዛቱ የተነሳ በቀን ፡ ሁለት ጠርሙስ ቮድካ ይጠጣ ነበር ።...........
በአንድ ወቅት የለንደን ከተማ ፅዳት ሰራተኛ ሆኖ ድህነትን እንዳላጣጣማት ያሳለፈውን መጥፎ ጊዜ ረስቶ ፡ 24/7 ገንዘቡን መርጨቱን ቀጠለበት ።....
በዚህ ሁኔታ ጥቂት አመታት ካለፉና ፡ በእጁ የነበረው ገንዘብ እንዳልነበር ሆኖ ፡ ቤት ፡ መኪና ፡ ንብረቱን ሁሉ ከሸጠ በኋላ ማይክል ስራ መስራት እንዳለበት አሰበ ። ለአመታት ስራ የሚባል ነገር ትቶ መኖሩ ቆጨው ።
እና አንድ ቀን ጠዋት ተነስቶ ወደ አንድ ቢሮ ሄዶ አንኳኳ.....
ሃላፊው እንዲገባ ፈቀዱለት
እንዴት ኖት አላቸው ።
ሰውየው ምቾት የለወጠውን ማይክልን በቶሎ ማስታወስ አልቻሉም ።......
እርግጥ ነው ጊዜው ስለቆየ ረስተውኝ ይሆናል ። እኔ ማይክል ካሮል እባላለሁ ። ከአመታት በፊት እናንተ ጋር እሰራ ነበር ።

ሰውየው አላስታወሱትም ።

ምን ነበር የምትሰራው ብለው ጠየቁት
ፅዳት ሰራተኛ ነበርኩ
ሰውየው ትዝ አላቸው ፡ ጥቂት ካወሩት በኋላ እና አሁን ምን ልርዳህ አሉት
የበፊት ስራዬን ፡ ለመጀመር ማለት . .. የከተማ ፅዳት ሰራተኛ ፡ ከፈለጋችሁ

ሰውየው ማይክልን ቀጠሩት ።

እና አሁን በለንደን ጎዳና ላይ ፡ አንድ ወፍራም ሰውዬ. .. የፅዳት ስራ ሲሰራ ካያችሁት ፡ ያ ሰው ፡ በአንድ ወቅት ሚሊየነር የነበረውና ፡ ህይወት የሰጠችውን እድል ሊጠቀምበት ባለመቻሉ ፡ ተመልሶ ፅዳት ሰራተኛ የሆነው ማይክል ካሮል እንደሆነ እወቁ።

 💔Texas በጎርፍ ኣደጋ ምክንያት89 ሰዎች ሂወታቸው እንዳለፈ እየተነገረ ይገኛል:: ኣብዛኞዎቻቸው ህፃናት መሆናቸው ተነግሯል::
07/07/2025

💔
Texas በጎርፍ ኣደጋ ምክንያት89 ሰዎች ሂወታቸው እንዳለፈ እየተነገረ ይገኛል::
ኣብዛኞዎቻቸው ህፃናት መሆናቸው ተነግሯል::

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!ገብርኤልና አባቱ ዘካርያስ ትንቢት የተናገሩለት፤ ከሕፃንነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን ያገለገለ፤ በፍጹም ልቡ ዓለምን የናቀ፤ ...
07/07/2025

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!

ገብርኤልና አባቱ ዘካርያስ ትንቢት የተናገሩለት፤ ከሕፃንነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን ያገለገለ፤ በፍጹም ልቡ ዓለምን የናቀ፤ ከተድላዋና ከደስታዋም የተለየ፤ አምላክን ለማጥመቅ የታደለ ሐዋርያ፣ መምህር፣ ሰማዕት፣ ባሕታዊ፣ ነቢይ፣ ጻድቅ ነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅዱስ፡፡ ዮሐንስ ማለት እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው፡፡ በሉቃስ 1÷14 እንደተጻፈው ቅዱስ ወንጌልም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን ተድላና ደስታ ይለዋል፡፡ ወላጆቹ በእርሱ መወለድ ተደስተዋልና፡፡ በዚህ የወንጌል ክፍል ካህኑ ቅዱስ ዘካርያስና ሚስቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ በመፈጸም ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ፡፡ ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ ይሰጣቸው ዘንድም እግዚአብሔርን ዘወትር ይማጸኑት ነበር፡፡ ካህኑ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ዕጣን በማሳረግ ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ጸሎቱ እንደ ተሰማ ነገረው፡፡

ሚስቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ እንደምትወልድ፣ ስሙንም ዮሐንስ እንደሚለው፤ በመወለዱም ብዙዎች እንደሚደሰቱ፤ ልጁም በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ እንደሚኾን፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ እንደማይጠጣ፤ እንደዚሁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሞላበት ነገረው፡፡ ካህኑ ዘካርያስም መልአኩን “እኔ ሽማግሌ ነኝ፤ ሚስቴም አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ?” አለው፡፡ መልአኩም “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፡፡ እነሆም በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ ይህ ነገር እስከሚኾን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ፤ መናገርም አትችልም” አለው፡፡ ከውጪ ቆመው ጸሎት ሲያደርጉ የነበሩት ሕዝብም ዘካርያስን ከቤተ መቅደስ እስኪወጣ ይጠብቁት ነበር፤ በመዘግየቱም ይደነቁ ነበር፡፡

ከቤተ መቅደስ በወጣም ጊዜ ሊያናግራቸው ባለመቻሉ ይጠቅሳቸው ነበር፡፡ በሁኔታውም በቤተ መቅደስ ራእይ እንዳየ አስተዋሉ፡፡ እርሱም ድዳ ሆኖ ኖረ፡፡ የማገልገሉም ወራት ሲፈጸም ወደ ቤቱ ሔደ፤ ከሁለት ቀን በኋላም አረጋዊቷ ቅድስት ኤልሳቤጥ ፀነሰች፡፡ ቅድስት ኤልሳቤጥም በመካንነቷ ከሰዎች የሚደርስባት ሽሙጥ ተወግዷላታልና “እግዚአብሔር በዚህ ወራት ከሰው ስድቤን ያርቅ ዘንድ እንዲህ አደረገልኝ” ስትል ለአምስት ወራት ተሸሸገች፡፡ ጌታችን ሊወለድ ስድስት ወራት ሲቀረው፣ ሰኔ 30 ቀን ንዑድ፣ ክቡር የሆነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ፡፡ ዘመዶቹ ስሙን በአባቱ መጠርያ ዘካርያስ ሊሉት ቢወዱም እናቱ ግን “ዮሐንስ ይባል” አለች፡፡ የመልአኩን የብሥራት ቃል ባለመቀበሉ አንደበቱ ተይዞ የነበረው ካህኑ ዘካርያም ስሙ “ዮሐንስ” ይባል ብሎ ሲጽፍ አፉ ተከፈተ፤ አንደበቱም ተፈታ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶም “… አንተ ሕፃን ሆይ! የልዑል ነቢይ ትባላለህ፤ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና… ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል፤ እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል፤” በማለት የቅዱስ ዮሐንስን ነቢይነትና አጥማቂነት፣ እንደዚሁም የክርስቶስን የማዳን ትምህርት አብሣሪነት የሚመለከት ትንቢት አስቀድሞ ተናገሯል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ሰኔ 30 ቀን የተወለደበት፤ መስከረም 1 ቀን ቃል ኪዳን የተቀበለበት፤ መስከረም 2 ቀን በሰማዕትነት ያረፈበት፤ ጥር 11 ቀን ጌታችንን ያጠመቀበት፤ ሰኔ 2 ቀን ደግሞ ዐፅሙ የፈለሰበት በዓል በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ ይከበራል፡፡

ከባሌ ጋር የሀሳብ ልዩነት ሲፈጠር ተያይዘን ወደ መኝታ ቤት ነው የምንገባው!በትዳር ላይ ባል መከበር አለበት  ምክንያቱም ፈጣሪም አክብሮ ነው የሰጠን😍 ባከበርከው ቁጥር ምላሹ ክብር እንደሆነ...
07/07/2025

ከባሌ ጋር የሀሳብ ልዩነት ሲፈጠር ተያይዘን ወደ መኝታ ቤት ነው የምንገባው!

በትዳር ላይ ባል መከበር አለበት ምክንያቱም ፈጣሪም አክብሮ ነው የሰጠን😍 ባከበርከው ቁጥር ምላሹ ክብር እንደሆነ ስለማውቅ በመደፋፈር ፣ አላምንም እላፊ ነገር በመነጋገር አላምንም።
እኔ ከምከተለው ሃይማኖት አንጻር ወንድ የቤት ራስ ነው።ወንድን እንዳከብር ነው የተሰጠኝ ሳከብረው እንደሚያከብረኝ ስለማምን እና ትዳርን የሚያቆየው መከባበር ነው ብዬ ስለማስብ።❤❤

የዓለማችን ቢሊየነር ፓርቲ ተመሠረተ‼አሜሪካዊው ቢሌነር  ኤሎን መስክ "የአሜሪካ ፓርቲ" የተሰኘ ፓርቲ ማቋቋሙን  አስታውቋል።መስክ የብዙሃኑ ዜጎች የፖለቲካ ለውጥ ፍላጎት ምላሽ ነው በማለት ...
07/06/2025

የዓለማችን ቢሊየነር ፓርቲ ተመሠረተ‼

አሜሪካዊው ቢሌነር ኤሎን መስክ "የአሜሪካ ፓርቲ" የተሰኘ ፓርቲ ማቋቋሙን አስታውቋል።

መስክ የብዙሃኑ ዜጎች የፖለቲካ ለውጥ ፍላጎት ምላሽ ነው በማለት አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መመስረቱን አሳውቋል።

በኤክስ ፔጁ ላይ በለጠፈው መግለጫ፣ ዛሬ የአሜሪካ ፓርቲ የተመሰረተው ነፃነታችሁን ሊመልስላችሁ ነው ብሏል።

በአሜሪካ የአንድ ፓርቲ ሥርዓት ብሎ የገለጸውን፣ "ሀገራችንን በብክነት እና በሙስና የምንከስር ከሆነ፣ በዴሞክራሲ ውስጥ አንኖርም። የምንኖረው በአንድ ፓርቲ ሥርዓት ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ብቻ ነው" ሲሉ ነቅፈዋል።

አክለውም "የአሜሪካ ፓርቲ" የመመስረት አላማ "የአሜሪካን ህዝብ ነፃነት መመለስ" እና ከባህላዊ የፖለቲካ ተቋማት እውነተኛ አማራጭ መፍጠር ነው ብሏል።

መልካም ሰንበት 🙏
07/06/2025

መልካም ሰንበት 🙏

" የቡድን ጓደኞች ይመጣሉ፤ ይሄዳሉ በዚህ መልኩ ግን አይደለም"- መሀመድ ሳላህ መሀመድ ሳላህ በዲያጎ ጆታ ህልፈት ቃላት እንዳጣ የገለፀበትን የሀዘን መግለጫ ከደቂቃዎች በፊት በማህበራዊ ትስ...
07/05/2025

" የቡድን ጓደኞች ይመጣሉ፤ ይሄዳሉ በዚህ መልኩ ግን አይደለም"- መሀመድ ሳላህ

መሀመድ ሳላህ በዲያጎ ጆታ ህልፈት ቃላት እንዳጣ የገለፀበትን የሀዘን መግለጫ ከደቂቃዎች በፊት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስፍሯል:

" ቃላት የለኝም። ከእረፍት በኋላ ወደሊቨርፑል ለመመለስ እንዲህ የሚያስፈራኝ ነገር ይኖራል ብዬ አስቤ አላውቅም። የቡድን ጓደኞች ይመጣሉ፤ ይሄዳሉ በዚህ መልኩ ግን አይደለም። ከእረፍት ስንመለስ ዲያጎ እዛ አለመኖሩን መቀበል እጅግ ከባድ ነው። ለባለቤቱ፣ ለልጆቹ እንዲሁም በድንገት ልጆቻቸውን ላጡ ወላጆች መፅናናቱን እመኛለሁ። ለ ዲያጎ እና ለወንድሙ አንድሬ ቅርብ የሆኑ ሁሉ አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል። ዲያጎ እና አንድሬ መቼም አንረሳችሁም።"

Address

Oakland, CA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amanual Gebremariam Yfter posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amanual Gebremariam Yfter:

Share