Amanuel Yfter

Amanuel Yfter ሰላም ለሀገራችን ✌️ ሰላም ለመላው አለም
Peace for the whole world
(6)

እርግጠኛ ነኝ ብዙ እምንባ አይታችሁ ሊሆን ይችላል እንደዚህች ልጅ ጎርፍ የሆነ እንባ ግን አይታችሁ አታውቁም😢ይህች ልጅ እንደዚህ እምታለቅሰው አባቷ በእናቷ ላይ ስላደረሰው ክህደት እያወራች ...
05/25/2026

እርግጠኛ ነኝ ብዙ እምንባ አይታችሁ ሊሆን ይችላል እንደዚህች ልጅ ጎርፍ የሆነ እንባ ግን አይታችሁ አታውቁም😢
ይህች ልጅ እንደዚህ እምታለቅሰው አባቷ በእናቷ ላይ ስላደረሰው ክህደት እያወራች ነው
አባቷ በበረሃ እንደሞተ ለእናቷ አስወርቶ ለ 16 አመት ተደብቋት ኖሯል
እናቷም እሱ ከሞተ ጀምሮ ጥቁር ለብሳ ሌላ ወንድ ሳታገባ ይህችን ልጅ አሳድጋለች።
ከ16 አመት በኅላ ግን እናቷ ስራ ልትፈልግ አንድ ድርጅት ውስጥ ስትገባ ሞተ የተባለው ባሏን ታገኘዋለች
ሴትዮዋም ባሏን እንዳገኘችው ምን በድላው እንደሆነ ይሄን እንዳደረገ ብጠይቀውም ውጭልኝ ትዳሬን ልታፈርሽ ነው የመጣሽው በማለት ያስወጣታል። ይህ ታሪክ የምታለቅስዋ እናት ታሪክ ነው።
እምታለቅሰውም ይሄንኑ የእናቷን ታሪክ እያወራች ነው።
እኔ እምለው እንባ አይደርቅም እንዴ? እንዴት ለ1 ሰዓት ሰው እንደዚህ እንባው ሳይደርቅ ያለቅሳል??? ህመሙ ከባድ ነው!

የእናትየው ፅናት እና የታማኝነት ልክ፣ በአንጻሩ ደግሞ የተፈጸመባቸው ክህደት ለማመን ይከብዳል። ልጇ እንዲህ ባለ መሪር ሁኔታ ማልቀሷ የደረሰባቸውን ስነ-ልቦናዊ ስብራት በግልጽ ያሳያል።

እናቷ ባሁን ሰዓት ይህችን አለም በቃኝ በማለት እግዚአብሔር ን መርጠው መንኩሰው በገዳም ይገኛሉ።

The most beautiful smile, radiant and genuine, lighting up the face with warmth and joy. 😁
04/23/2026

The most beautiful smile, radiant and genuine, lighting up the face with warmth and joy. 😁

በ NASA - National Aeronautics and Space Administration የተነሳው ኣዲሱ የምሬታችን ምስል ይሄን ይመስላል::
04/03/2026

በ NASA - National Aeronautics and Space Administration የተነሳው ኣዲሱ የምሬታችን ምስል ይሄን ይመስላል::

ነቢያቱም ሐጌና የአዶ ልጅ ዘካርያስ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለነበሩ አይሁድ በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩላቸው።በዚያን ጊዜ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ ተነሥተው ...
03/08/2026

ነቢያቱም ሐጌና የአዶ ልጅ ዘካርያስ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለነበሩ አይሁድ በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩላቸው።
በዚያን ጊዜ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ ተነሥተው በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመሩ፤ የሚያግዙአቸውም የእግዚአብሔር ነቢያት ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
በዚያም ዘመን በወንዝ ማዶ የነበረው ገዥ ተንትናይ፥ ደግሞ ሰተርቡዝናይ፥ ተባባሪዎቻቸውም ወደ እነርሱ መጥተው። ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ፥ ይህንኑም ቅጥር ታድሱ ዘንድ ያዘዛችሁ ማን ነው? አሉአቸው።
ደግሞም። ይህንስ ሥራ የሚሠሩት ሰዎች ስም ማን ነው? ብለው ጠየቁአቸው።
የአምላካቸው ዓይን ግን በአይሁድ ሽማግሌዎች ላይ ነበረ፥ ይህም ነገር ወደ ዳርዮስ እስኪደርስ ድረስ፥ መልሱም በደብዳቤ እስኪመጣ ድረስ አልከለከሉአቸውም።
በወንዙ ማዶ የነበረው ገዥ ተንትናይ ደግሞ ሰተርቡዝናይ ተባባሪዎቹም በወንዙ ማዶ የነበሩት አፈርስካውያን ወደ ንጉሡ ወደ ዳርዮስ የላኩት የደብዳቤው ግልባጭ ይህ ነበረ።
እንዲህም የሚል ደብዳቤ ላኩለት። ለንጉሡ ለዳርዮስ ሙሉ ሰላም ይሁን፤
ወደ ይሁዳ አገር ወደ ታላቁም አምላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እርሱም በትልቅ ድንጋይ ተሠራ፥ በቅጥሩም ውስጥ እንጨት ተደረገ፥ ያም ሥራ በትጋት ይሠራል፥ በእጃቸውም ይከናወናል።
እነዚያንም ሽማግሌዎች። ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ፥ ይህንስ ቅጥር ታድሱ ዘንድ ያዘዛችሁ ማን ነው? ብለን ጠየቅናቸው።
ደግሞም እናስታውቅህ ዘንድ፥ በእነርሱም ያሉትን ሹሞች ስም እንጽፍልህ ዘንድ ስማቸውን ጠየቅን።
እንደዚህም ብለው መለሱልን። እኛ የሰማይና የምድር አምላክ ባሪያዎች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረውን፥ ታላቁም የእስራኤል ንጉሥ ሠርቶ የፈጸመውን ቤት እንሠራለን።
አባቶቻችንም የሰማይን አምላክ ካስቈጡ በኋላ በከለዳዊው በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ እርሱም ይህን ቤት አፈረሰ፥ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ።
ነገር ግን በባቢሎን ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ንጉሡ ቂሮስ ይህን የእግዚአብሔርን ቤት ይሠሩ ዘንድ አዘዘ።
ናቡከደነፆርም በኢየሩሳሌም ከነበረው መቅደስ የወሰደውን፥ ወደ ባቢሎንም መቅደስ ያፈለሰውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቅንና የብርን ዕቃ ንጉሡ ቂሮስ ከባቢሎን መቅደስ አውጥቶ ሰሳብሳር ለተባለው ለሹሙ ሰጠውና።
ይህን ዕቃ ይዘህ ሂድ፥ በኢየሩሳሌምም ባለው መቅደስ አኑረው፤ የእግዚአብሔርም ቤት በስፍራው ይሠራ አለው።
በዚያ ጊዜም ይህ ሰሳብሳር መጣ፥ በኢየሩሳሌምም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሠረተ፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እየተሠራ አልተጨረሰም።
አሁንም ይህ ነገር በንጉሡ ዓይን መልካም ቢሆን ይህ የእግዚአብሔር ቤት በኢየሩሳሌም ይሠራ ዘንድ ከንጉሡ ከቂሮስ ታዝዞ እንደ ሆነ በባቢሎን ባለው በንጉሡ ቤተ መዛግብት ይመርመር፤ ስለዚህም ነገር ንጉሡ ፈቃዱን ይላክልን።

 #ተስፋየሰው ልጅ ሲወለድ እራቆቱን ምንም ሳይኖረው ይወለዳል ልጅ ሁነን ህልም ይኖረናል ይሃን ህልም ለመድረስ በተስፍ ግዜው እሲኪ ደርስ እንጓዛለን::  #ሁሉም ይድርሳል ተስፍ ብቻ ይኑረን🙏...
03/04/2026

#ተስፋ
የሰው ልጅ ሲወለድ እራቆቱን ምንም ሳይኖረው ይወለዳል ልጅ ሁነን ህልም ይኖረናል ይሃን ህልም ለመድረስ በተስፍ ግዜው እሲኪ ደርስ እንጓዛለን::

#ሁሉም ይድርሳል ተስፍ ብቻ ይኑረን🙏


02/25/2026

🙏

ብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ፤ቡራኬዎ ይድረሰን🤲
02/25/2026

ብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ፤
ቡራኬዎ ይድረሰን🤲

እነሆ ጠባቡ ደጅ!ለስም አጠራሩ ምስጋና የሚገባው እውነተኛው መምህር ኢየሱስ ክርስቶስ እንድንገባበት ያመላከተን በር ጠባቡን በር ነው። ሰፊው በር ወደ ሞት የሚወስድ በመሆኑ የእርሱ የሆኑት ሁ...
02/25/2026

እነሆ ጠባቡ ደጅ!

ለስም አጠራሩ ምስጋና የሚገባው እውነተኛው መምህር ኢየሱስ ክርስቶስ እንድንገባበት ያመላከተን በር ጠባቡን በር ነው።

ሰፊው በር ወደ ሞት የሚወስድ በመሆኑ የእርሱ የሆኑት ሁሉ በሰፊው በር እንዳይገቡ ከለከለ።

“በጠበበው ደጅ ግቡ። ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና። ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው” ማቴ. 7፥13-14 ብሎናል።

የጠበበው ደጅ፣ የቀጠነው መንገድ የትኛው ነው?
በዚህ ላይ የሚሄዱስ እነማን ናቸው?

ወደ ሕይወት የሚያደርሰውን መንገድ ያገኙ በሕይወት በሮችም መግባት የቻሉ ሰዎች ንዑዳን ክቡራን ናቸው።

ወደ ሕይወት የሚወስደው መንገድ ክርስቶስ ነው።

በዚህ በር የሚገቡ ሁሉ ይድናሉ፤ ማረፊያ፣ መሰማሪያ ያገኛሉ ዮሐ. 10፥9

ወደ ጥፋት የሚያደርሰው ሰፊ ደጅ የተባለውም ዲያብሎስ ነው። ምንም እንኳን ወደ ሞት የሚያደርስ ቢሆንም የሚመርጡት ግን ብዙዎች ናቸው።

ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ያልተመዘገቡት ሁሉ የሚገቡበት ደጅ ነው። ለጊዜው ሰፊ ሆኖ ስላገኙት መጨረሻው ዕረፍት መስሏቸው ይጓዛሉ፤ ነገር ግን በሞት ያጠናቅቃሉ። በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ሰዎች በዚህ ደጅ መመላለስ ነፍስን የሚያስጨንቅ ነው።

የጠበበው ደጅ የሚገኘው በጾምና ጸሎት ነው፤ በሙሴ እጅ ላይ እንደነበረችው በትር ተአምር የምናደርግባት እጃችን ላይ ያለች በትራችን የተቀደሰችው የጌታ ጾም ናት።

ፈርዖን የትኛውንም ያኽል ቢበረታ የትዕቢቱ ማስታገሻ የምትሆነን ከዚህች ጾም በቀር ሌላ ምንም የለንም።

መብል መጠጥን ማሰናዳት መብል መጠጥን ከመተው ይልቅ አስጨናቂ የሚሆነው ለምንድነው?
ይገርማል!
መብል መጠጥን በብዙ ድካም እንሰበስበዋለን፤ ከግንባራችን በሚፈሰው ወዝ እናገኘዋለን። መብል መጠጥን መተው ግን ከዚህ ይልቅ ቀላል ነበር፤ ታዲያ “ጠባብ ደጅ፣ ቀጭን መንገድ” የተባለው ጾም ሳይሆን
መብል መጠጥ መሆን አልነበረበትም ትላላችሁ?
አወ!
እውነት ነው የሚያስጨንቅስ ምግብ ፍለጋ የምንደክመው ድካም ነበር ነገር ግን መብል መጠጥን መተው ፈቃድን መተው ስለሆነ “ጠባብ ደጅ፣ ጭንቅ መንገድ” ተብሎ ተጠራ።

ሰው ሊተዋቸው የሚቸገርባቸው ሦስት ፈቃዳተ ሥጋ አሉት፤ ምግብ መሻት፣ ከሴት ጋር/ከወንድ ጋር መገናኘት እና ማንቀላፋት ናቸው።

እነዚህን ስለ እግዚአብሔር ብሎ መተው እጅግ አስጨናቂ ስለሆነ “ጸባብ አንቀጽ፣ ጽዕቅት ፍኖት” ተባለች።

ዛሬ የተጠራነው በዚህ መንገድ እንድንሄድ ነው፤ በጠባቡ ደጅ በጭንቁ መንገድ።

መብል መጠጥ ፍለጋ ያደከመው ሰው ምግብ በማግኘት ደስ ይለዋል።
በጾም ሰውነቱን ያደከማትም ሰው ክርስቶስን በማግኘት ደስ ይለዋል።

ደጁ የጠበበ፣ መንገዱ የቀጠነ ቢሆንም በመዳረሻው ግን ቀንበሩ ልዝብ ሸክሙ ቀላል ነው።

አስተውሉ ክርስቲያኖች!
የሚከብደን ዛሬ ነው፤ ነገ ለኛ ቀላል ነው። የሚጎረብጠን ዛሬ ነው፤ ነገ ለእኛ ልዝብ ነው። በሕገ እግዚአብሔር መኖር ለሰዎች ቀንበር ቢመስልም ልዝብ ቀንበር ነው።

ከሕገ እግዚአብሔር ውጭ መኖርም ቀንበር የሌለው ቢመስልም መልካም አይደለም።
እንደ ፈቃዳችን እየተመላለስን ነጻነት በሚመስል ባርነት ውስጥ ለምን እንወድቃለን?

የብልጣሶር መንግስት ያበቃችው በግብዣ ቤት መሆኑን አልሰማችሁምን? ዳን. 5፥30።
ዳንኤልንስ በዳርዮስ ፊት ኑሮውን ያቃናችለት ጾሙና ጸሎቱ እንደሆነች አታውቁምን? ዳን. 6፥28።

ጾም ኑሮን ያቃናል፤ መብልና መጠጥን ማብዛት ግን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል።

እነሆ ጾም ተጀምሯል፤
ጠባቡ ደጅ ተከፍቷል!
ወደ ሕይወት የሚያደርሰውን መንገድ አግኝተነዋል። ማንም ወደ ኋላ የሚመለስ ሊኖር አይገባም።

የበረከት ጾም ያድርግልን

ስምዓኮነ መልአከ / Simakone Melak

መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የልባችንን መልካም መሻት ይሙላልን፤ ረድኤቱ እና ምልጃውም አይለየን🙏መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የዙፋን መልእክተኛ ነውና መልአክ ወይም መልእክተኛ ይባላል፡፡ ዳግመኛም በቅ...
02/20/2026

መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የልባችንን መልካም መሻት ይሙላልን፤ ረድኤቱ እና ምልጃውም አይለየን🙏

መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የዙፋን መልእክተኛ ነውና መልአክ ወይም መልእክተኛ ይባላል፡፡

ዳግመኛም በቅድስናው ቅዱስ ይባላል፡፡ ገብርኤል ማለት አምላክ ሰው ሆነ፣ ሰው አምላክ ሆነ” ማለት ነው፡፡ የሠራዊት አዛዥ ነውና ሊቀ መላእክት ይባላል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል አብሳሬ ትስብዕት ነው፡፡ እመቤታችን አምላክን እንደምትወልድ ታላቁን የምሥራች ይዞ የደረሰው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ የሰው ልጆችን መዳን ታላቁን የምሥራች ይዞ በመምጣቱ መጋቤ ሐዲስ ይባላል፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ ስማቸው ከገነኑ መላእክት ከቅዱስ ሚካኤል ቀጥሎ የሚጠራው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡

እግዚአብሔርን የሚያመለኩና የሚገዙ እንዲሁም ለእርሱ ከብርን የሚሰጡ ሁሉ ከነገር እንኳን አንዳች እንደማይጎድላቸው በዘመናት መካከል ተመልክተናል፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚወዱት የሚሆን ጠባቂ በዙሪያቸው ያቆማል። በባቢሎን ምርኮ ሆኖ ስለሕዝቡ የሚያለቅሰውን የነቢዩ ዳንኤልን የጸሎት መልስ ይዞ የመጣው፣ ራእዩንም ያብራራለት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆች ወዳጆች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ወዳጆቻችን፣ ፈጥኖ ደርሶ የሚያድነን አንዱ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

ህጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን እንዲሁም ሦስቱ እግዚአብሔር የመረጣቸው ጠቢባን ሕጻናት አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤልን ከእሳት ሲያድን ተመለክተነዋል፡፡

ዛሬም ገዳማውያን እናቶችና አባቶቻችን የኃጢአት እቶን፣ የስጋ ፈተና፣ የዲያብሎስ ውጊያ በበረታቸው ጊዜ የሚረዳቸው በመከራቸው ሁሉ ጽናት የሚሰጣቸው እርሱ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እነርሱም በጸሎታቸው ሰዓት ሁሉ ተግተው ይጠሩታል፡፡ የጸሎታቸው በረከት ተካፋይ እንድንሆን ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
🙏🙏🙏

ቅዱስ ሚካኤል 🙏እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር ሾመው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሁሉ ልዕልና ላይ ትሕትናን ደርቦ የያዘ በጸሎቱ ተማ...
02/19/2026

ቅዱስ ሚካኤል 🙏

እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር ሾመው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሁሉ ልዕልና ላይ ትሕትናን ደርቦ የያዘ በጸሎቱ ተማጽኖ በተራዳኢነት አምኖ ለሚለምነው ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ከአጋንንት ሠራዊተ ተንኰል የሚያድን ነው፡፡ ሚካኤል የሥሙ ትርጓሜ በዕብራይስጥ “ማንነው እንደ እግዚአብሔር?” ማለት ነው፡፡

በክርስትና በአይሁድ፣ እንዲሁም በመላዕክት አማላጅነት በሚያምኑ ሃይማኖቶች የመላዕክት ሁሉ አለቃ ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህም የከበረ መልአክ ክብር ይገባውና በጌታችን ፊት ስለ ሰው ልጆችና ስለ ፍጥረትም ሁሉ ይለምናል፤ ይማልዳልም፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ተአምራቱ ብዙዎች ናቸው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ለቅዱስ ሚካኤል የተሰጠውን ክብርና ባለሟልነት እንዲሁም የሠራቸውን ሥራዎች በስፋት እንመለከታለን፡፡

በኢያሱ 5÷13 እንዲህ ይላል፡፡ “እንዲህም ሆነ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፡፡ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፡፡ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን አለው፡፡ እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ፡፡ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው አለው፡፡ የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃም ኢያሱን አንተ የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን በፊቱ አውልቅ አለው፡፡ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ” ይላል፡፡ ኢያሱ ከኢያሪኮ ጀምሮ ታላላቅ አሕዛብን አጥፍቶ እግዚአብሔር ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ የማለላቸውን የተስፋይቱን ምድር ለልጆቻቸው ያወረሳቸው በዚህ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ በተገለጸለት የእስራኤል መሪ በቅዱስ ሚካኤል እገዛ ነው፡፡ መልአኩ በሰው አምሳል ስለተገለጸለት አላወቀውም ነበር፡፡

ከቃሉ እንደምንረዳው ከራሱ ወገን ወይም ከጠላቶቹ ወገን የሆነ አንድ ወታደር መስሎት ነበር፡፡ ያነጋገረውም ያለ ፍርሃት ያለ ጭንቀት ያለድንጋጤ ወታደሮቹን እንደሚያነጋግር ዘና ብሎ ነው፡፡ ሆኖም “ከወገኖችህ ወይም ከጠላቶችህ አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ” ሲለው ኢያሱ በፊቱ የቆመው ከሙሴ ሳይለይ እስራኤልን የሚጠብቅ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን ሲረዳ ለመልአኩ ክብር መስጠት ስለሚገባ የአክብሮት ስግደት ሰገደለት፤ “ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድነው” በማለት በትህትና ጠየቀ፡፡ ጌታዬ ማለቱ የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡር መስጠቱ አይደለም፣ መላእክት የጸጋ ጌቶች ስለሚባሉ እንጂ፡፡ ኢያሱ መልአኩን ጌታዬ ብሎ ከጠራው እኛም ጌታዬ፤ ቅዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ጸልይልኝ መጥተህ አድነኝ በማለት የአክብሮት የጸጋ ስግደት በመስገድ ብንለምነው፣ ብንታዘዘው ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አልወጣንም፡፡

መላእክትን ማክበርና መታዘዝ እንደሚገባ እግዚአብሔርም ነግሮናል፡፡ በዘጸ.23÷20-22 “በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ሥፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክህን በፊትህ እሰዳለሁ፤ በፊቱ ተጠንቀቁ፤ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት፤ አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፣ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፣ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፣ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ፣ መልአኬ በፊትህ ይሄዳል” በማለት ለሙሴ ተናግሯል፡፡ ይህ ቃል ለሙሴና ለሕዝቡ ብቻ ተነግሮ ያበቃ ሳይሆን ዛሬም ያለ ወደፊትም የሚቀጥል ነው፡፡

ገዳማውያንም ይህን ቃል ታምነው ሌሊትና ቀን ሚካኤል ሆይ አማልደን ይሉታል፡፡ ከጸሎታቸው በረከት እንድንካፈል ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡



02/18/2026

Address

Oakland, CA
694601

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amanuel Yfter posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amanuel Yfter:

Share