MANKIRA MEDIA

MANKIRA MEDIA please follow our page for more info.

Mankira media's latest Ethiopian breaking news online video-sharing website providing Ethiopian News, Music videos, movies, Drama series, Comedy, politics, and fun culture.

ለአንዱአለም ጎሳ የተሰጠው ሽልማት ተነጥቋል።  የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ለአርቲስት አንዷአለም ጎሳ የሰጠውን ሽልማት ከሕዝቡ ከፍተኛ ተቃውሞ በመምጣቱ ምክንያት መንጠቁን በማህበራዊ ሚዲያ ገ...
07/05/2025

ለአንዱአለም ጎሳ የተሰጠው ሽልማት ተነጥቋል።

የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ለአርቲስት አንዷአለም ጎሳ የሰጠውን ሽልማት ከሕዝቡ ከፍተኛ ተቃውሞ በመምጣቱ ምክንያት መንጠቁን በማህበራዊ ሚዲያ ገፅ አሳውቋል።


06/12/2025

የሕንድ አውሮፕላን ተከሰከሰ🥲🥲🥲

242 ሰዎችን ከአሕመዳባድ አሳፍሮ ወደ ለንደን በመብረር ላይ የነበረ የሕንድ አውሮፕላን ተከሰከሰ፡፡

ቦይንግ 787- 8 የሚል ስያሜ ያለው አውሮፕላኑ በምዕራብ ሕንድ አሕመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ ምድር እንደለቀቀ በቅጽበት መከስከሱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከመንገደኞች ውስጥ 169 የሕንድ፣ 53 የብሪታንያ፣ 7 የፖርቹጋል ፣ አንድ የካናዳ እና የሌሎች ሀገራት ዜጎች እንደነበሩ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ቲክቶከሯ"  ጃኒ" በፀጥታ ሃይሎች ተይዛለች 🥹🥹🥹ቲክቶከር ጃኒ ( ስመኝ ገብሩ ) በድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች ላይ በሰነዘረችው ዘለፋ በፀጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መያዟ ታውቋል ። ስመኝ ገብሩ...
06/07/2025

ቲክቶከሯ" ጃኒ" በፀጥታ ሃይሎች ተይዛለች 🥹🥹🥹

ቲክቶከር ጃኒ ( ስመኝ ገብሩ ) በድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች ላይ በሰነዘረችው ዘለፋ በፀጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መያዟ ታውቋል ።

ስመኝ ገብሩ ከቀናት በፊት በቀጥታ በሚተላለፍ የቲክቶክ ላይቭ ላይ በድሬዳዋ ሴቶች ከአለባበሳቸው ጋር በተያያዘ በተናገረቸው አፀያፊ ንግግር አብዛኛውን የድሬዳዋ ማህበረሰብ በማስቆጣቱ ክስ ቀርቦባት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከሳሽነት በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውላለች ።

ገብሩ
የይቅርታ ቪድዮ ሰርታ ቢሆንም ይቅርታዋ ግን ተቀባይነት አላገኘም።

06/03/2025

Ethiopian traffic police fight with driver

ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አዲስ ሊቀ ጳጳስ መረጠች Roberto Prevost of the United States is named POPE Leo XIVCongratulations!
05/08/2025

ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አዲስ ሊቀ ጳጳስ መረጠች Roberto Prevost of the United States is named POPE Leo XIV
Congratulations!

በየመን የስደተኞች ማዕከል ላይ በአሜሪካ ተፈጸመ በተባለው ጥቃት የተጎዳ ኢትዮጵያዊ እንዳለ ተሰማ አሜሪካ በሁቲ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ባለው የሰሜን ምዕራብ የየመን ክፍል ውስጥ ኢትዮጵያውያንን...
04/29/2025

በየመን የስደተኞች ማዕከል ላይ በአሜሪካ ተፈጸመ በተባለው ጥቃት የተጎዳ ኢትዮጵያዊ እንዳለ ተሰማ

አሜሪካ በሁቲ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ባለው የሰሜን ምዕራብ የየመን ክፍል ውስጥ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ አፍሪካውያን ስደተኞች ተይዘው በሚገኙበት ማዕከል ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 68 ሰዎች መገደላቸውን የታጣቂ ቡድኑ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገበ።

በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሚኖሩባት የመን ዛሬ ሰኞ ማለዳ በተጸመው ጥቃት ቆስለው በአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ከቦታው ከወጡት ሰዎች መካከል ቢያንስ አንድ ኢትዮጵያዊ እንዳለ እየተገለጸ ነው።

አል ማሲራህ የተባለው የሁቲ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንዳለው ሳዓዳ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ማዕከል ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከሞቱት በተጨማሪ አብዛኞቹ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው 47 ሰዎች ቆስለዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመበት የማቆያ ማዕከል ውስጥ የነበሩት ስደተኞች አፍሪካውያን መሆናቸው ከመገለጹ ውጪ የየት አገራት ዜጎች እንደሆኑ ለጊዜው የወጣ ዝርዝር መረጃ የለም።

04/24/2025

Yared Negu: በማረሚያ ቤት የፋስካ በዓል እንድህ ነበር።

Pope Francis died on Monday, April 21, 2025, at the age of 88 at his residence in the Vatican's Casa Santa Marta. RIP
04/21/2025

Pope Francis died on Monday, April 21, 2025, at the age of 88 at his residence in the Vatican's Casa Santa Marta. RIP

      ከኢትዮጵያውያን ባህል፣ ኃይማኖትና ወግ ተቃራኒ የሆነ በርካታ ድርጊቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሰራጨ ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ...
04/16/2025


ከኢትዮጵያውያን ባህል፣ ኃይማኖትና ወግ ተቃራኒ የሆነ በርካታ ድርጊቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሰራጨ ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
***
ግለሰቡ ሚሊዮን ድሪባ የሚባል ሲሆን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሚለቃቸው ተንቀሳቃሽ ምስል በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታቸውን ያነሱበት ጉዳይ ሆኗል።

በአንዳድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ አንዳንድ ምስሎች ተገቢነታቸውን የሳቱና ያፈነገጡ እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ ገልፆ ህገ ወጥ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በሚለቁ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

04/09/2025

አሜሪካ ከኢራን ጋር በቀጥታ የኒውክሌር ድርድር እያደረገች መሆኑን ትራምፕ ተናገሩ

 ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ
04/09/2025


ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

04/09/2025

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የሆኑት አቭራም ንጉሤ ሰኞ ዕለት በአፍሪካ ኅብረት የሩዋንዳውን የዘር ጭፍጨፋ ለማሰብ ከተዘጋጀ ስብሰባ ላይ ተገድደው እንዲወጡ ተደረጉ።🤔🤔🤔

Address

San Francisco, CA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MANKIRA MEDIA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to MANKIRA MEDIA:

Share

MANKIRA MEDIA


  • Mankira Media is an Ethiopian Online Video Sharing site. It has been providing Ethiopian News, Music, Video, Movie, Drama series, Comedy & Fun culture for diaspora community all over the world. please follow our page for more information. https://www.facebook.com/mankiramedia/ #mankira