Gateway to Heaven St. John Monastery in California

Gateway to Heaven St. John Monastery in California ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ የኢ.ኦ.ተ. አንድነት ገዳም በካሊፎርኒያ
St. John the Baptist & St. Arsema Ethiopian Orthodox Tewohedo Monastery in California

09/17/2026

Our Monastery Gift Shop offer a selection of unique religious gifts, books, and handcrafted items. We specialize in high-quality clergy apparel and custom choir uniforms, expertly tailored to meet the needs of your church.

09/15/2026

ምትረተ ርእሱ ለዮሐንስ በዓለ ንግሥ ስብከት በቀሲስ ዲበኩሉ በላይ

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ 2019 ዓ.ም አደረሳችሁ ፣ አዲሱ ዓመት የሰላም የፍቅር የጤና የደስታ ይሁንላችሁ።
09/15/2026

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ 2019 ዓ.ም አደረሳችሁ ፣ አዲሱ ዓመት የሰላም የፍቅር የጤና የደስታ ይሁንላችሁ።

09/15/2026

ምትረተ ርእሱ ለዮሐንስ በዓለ ንግሥ ማህሌት

የመጥምቁ ዮሃንስ ክብረ በዓል
09/15/2026

የመጥምቁ ዮሃንስ ክብረ በዓል

09/12/2026


መስከረም ፪

ማቴዎስ ፲፬፥፩
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
"በዚያ ዘመን የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ የኢየሱስን ዝና ሰማ፥
ለሎሌዎቹም፦ ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው፤ እርሱ ከሙታን ተነሥቶአል፥ ስለዚህም ኃይል በእርሱ ይደረጋል አለ።
ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና፤
ዮሐንስ፦ እርስዋ ለአንተ ትሆን ዘንድ አልተፈቀደም ይለው ነበርና።
ሊገድለውም ወዶ ሳለ፥ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስለ አዩት ፈራቸው።
ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤
ስለዚህም የምትለምነውን ሁሉ እንዲሰጣት በመሐላ ተስፋ አደረገላት።
እርስዋም በእናትዋ ተመክራ፦ የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በዚህ በወጭት ስጠኝ አለችው።
ንጉሡም አዘነ፥ ነገር ግን ስለ መሐላው ከእርሱም ጋር ተቀምጠው ስላሉት ሰዎች እንዲሰጡአት አዘዘ፤
ልኮም የዮሐንስን ራስ በወህኒ አስቆረጠው።
ራሱንም በወጭት አምጥተው ለብላቴናይቱ ሰጡአት፥ ወደ እናትዋም ወሰደችው።
ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው በድኑን ወሰዱና ቀበሩት፥ መጥተውም ለኢየሱስ አወሩለት"

እንኳን አደረሳችሁ!


አሜሪካ

🔶  🔶    የዮሐንስ መጥምቅ አባቱ  ዘካርያስ እናቱ ኤልሳቤጥ  ይባላሉ፡፡ መጽሐፍ  ቅዱስም እንዲህ ይላል ስለወላጆቹ  “ወክልኤሆሙ ጻድቃን እሙንቱ በቅድመ እግዚአብሔር ፤ሁለቱም በእግዚአብሔ...
09/12/2026

🔶 🔶

የዮሐንስ መጥምቅ አባቱ ዘካርያስ እናቱ ኤልሳቤጥ ይባላሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል ስለወላጆቹ “ወክልኤሆሙ ጻድቃን እሙንቱ በቅድመ እግዚአብሔር ፤ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ”( ሉቃ. 1÷6) ሁለቱም ልጅ ሳይወልዱ መካን ሁነው ሲኖሩ ከዐረጁ በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል “ዘካርያስን ቤተ መቅደስ ሲያጥን ልጅ ትወልዳላችሁ ስሙንም ዮሐንስ ትሉታላችሁ “አለው፡ ፡ዘካርያስም “ዘር ከአለቀ ደም ከደረቀ እንደምን ሁኖ ያቻላል? ”አለው፡፡ መልአኩም "እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር ፤ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም አለው ”ይላል ( ሉቃ.1÷37)

👉 ዘካርያስም አላምን ብሎ የመልአኩን ቃል ስለተጠራጠረ መልአኩ ገብርኤል እንዲህ አለው፡ ”ሕፃኑ እስኪወለድ ድረስ አፍህ ይዘጋ ዲዳ ይሁን “አለው፡፡ ዘካርያስም ዲዳ ሆነ ፡፡ዮሐንስም በብስራተ መልአክ መስከረም ፳፮ ቀን ተጸነሰ፡፡ ዮሐንስ ከተጸነሰ በኋላ ፮ ወር ሲሆነው ወበሳድስ ወርኀ ተፈነወ ገብርኤል መልአክ እምኀበ እግዚአብሔር ኀበ አሐቲ ሀገር ዘገሊላ እንተ ስማ ናዝሬት ኀበ ድንግል (በስድስተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል የገሊላ ክፍል ወደ ምትሆን ወደ ናዝሬት ወደ አንዲት ድንግል ተላከ ማርያም ውኃ ቀድታ ስትመለስ መልአኩ በአምሳለ ዐረጋዊ ትጸንሲ አላት ፫ ጊዜ ትጸንሲ (፫) አላት ማርያምም ይህንን ነገር ወደ ቤተ ክርስቲያን ሂጄ ልረዳው ብላ ወደ ቤተ መቅደስ ገባች ከድናግል እስራኤል የተከፈለችውን ጥጥ ስትፈትል ትጸንሲ አላት እሷም “ወንድ ሳላውቅ እንደምን ሁኖ ይቻላል“ አለችው፡፡መልአኩም “ እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር ፤ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም አላት”(ሉቃ.1÷37)

👉መልአኩም እነሆ ከዘመዶችሽ መካን የምትሆን ኤልሳቤጥ ደሟ ከደረቀ ዮሐንስን ፀንሳ ፮ ወር ሁኗታል አላት፡፡ ማርያምም እልፋ ብላ ለመረዳት ወደ ኤልሳቤጥ ሄደች፡፡ በደረሰችም ጊዜ ዮሐንስ ከሆድ ሁኖ ከሆድ ላለው ለአምላክ ሲሰግድ ለኤልሳቤጥ ታውቋታል፡፡ እመቤታችን ከኤልሳቤጥ ቤት ፫ ወር ተቀምጣለች፡፡ በተወለደ ጊዜ አባቱ ዘካርያስ ዘመዶቹ በሙሉ ተሰብስበው ስሙን ማን እንበለው እያሉ ሲጨነቁ ስሙን በወረቀት ጽፎ እንዲሰጣቸው ብዕርና ክርታስ ሰጡት፡፡ ዮሐንስም ስሙን ዮሐንስ ብሎ ጽፎ አንደበቱ ተፈትቶለት ተናግሯል፡ ፡ወዲያውም “ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል ዘተሣሃለነ ወገብረ መድኀኒተ ለሕዝበ ዚአሁ “ብሎ ጌታን አመስግኗል፡፡

👉መልአኩ ገብርኤል እንዳለው ዮሐንስ ይባል ብሎ በሰሌዳ ጽፎ ሰጥቷቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ጌታን ለመግደል ባሰበ ጊዜ ሲፀነስ የአባቱን አፍ (ልሳን ) የዘጋ ሲወለድ የአባቱን አፍ የከፈተ ሰው አለ እሱ ይሆናል፡ ብለው ለሄሮድስ ነገሩት፡፡ ሄሮድሰም ሰራዊቱን በላከ ጊዜ መልአኩ ገብርኤል ይህን ቃል ለኤልሳቤጥ ነገራት፡፡
በነገራት ጊዜ ወደ ሰራጵታ ይዛው ሸሸች ሰራዊቱም ዮሐንስን በአጡት ጊዜ ዘካርያስን ልጅህን አምጣው አሉት እሱም እንቢ ቢላቸው ከቤተ መቅደስ ቆርጠውት ሂደዋል፡፡ የዘካርያስ ደም ናሁ ተቀትለ በግፍ ወልደ ዘካርያስ ወልደ በራክዩ እያለች ፸ ዓመት ጩኻላች ከዚህ በኋላ ጥጦስ የሚባል የኢየሩሳሌም ንጉሥ ነበር ስትጮህ ሰምቶ ይህቺ ደም ምን ሁና ነው የምትጮኸው ?ብሎ ቢጠይቅ ዘካርያስ በግፍ ስለሞተ ነው አሉት ያን ጊዜ ከእነርሱ ወገን ፯ ሰው ቢያርዱ ዝም ብላለች፡፡በኋላ ኤልሳቤጥ በስደት ሙታለች ፡፡

👉ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ከዱር አግኝተው ቀብረዋታል፡፡ ዮሐንስንም አጋዘን (ቶራ) የምትባል አውሬ በገዳም ጡት እንደ እናት እያጠባች አሳድጋዋለች ፡፡በአደገ ጊዜም ሊያስተምር ወደ ገሊላ ወጣ ሄሮድስ የወንድሙን ሚስት የፊልጶስን አግብቶ ነበር፡፡ ዮሐንስም ዋርሳ አትውረሱ ደንበር አታፍርሱ እያለ ሲያስተምር ወደ እስር ቤት አስገቡት፡፡
ከጥቂት ቀናት በኋላ አሕዛብ የተወለዱበትን ቀን ያከብሩ ነበርና ሄሮድስ የተወለደበትን ቀን እያከበረ ግብዣ አድርጎ ሳለ ወለተ ሄሮድያዳ ከሄሮደስ ፊት ዘፈነች (ወከዊኖ ዕለተ ልደቱ ለሄሮድስ ዘፈነት ሎቱ ወለተ ሄሮዳያዳ በማዕከሎሙ) (ማቴ 14÷6) ፡፡ እሱንና ሕዝቦችን አስደሰተች፡፡ ሄሮድስም ከደስታው ብዛት የተነሣ የመንግሥቱን ዕኩሌታ እንደሚሰጣት ቃል ገባላት (ወበእንተዝ መሐለ ላቲ ከመየሀባ ዘሰአለቶ በዚህም የለመነቺውን እንደሚሰጣት ማለላት (ማቴ፣፲፬÷፯) ሂዳም ለእናቷ ነገረቻት፡ እናቷም የዮሐንስን አንገት ቆርጠህ ስጠኝ በይው አለቻት ፡፡
እናቷ የነገረቻትን ሂዳ ነገረች ፡፡ሄሮድስም ዮሐንስን በጣም ይወደው ነበርና አዘነ (ወተከዘ ንጉሥ በእንተ መሐላሁ ፤ንጉሱም ስለመሐላው አዘነ ማቴ ፲፬÷፱) ለነገርግን ቃል ገብቶላታልና አስቆርጦ ሰጣት እሷም ራሱን በጻሕል ይዛ ወደ እናቷ ሄደች፡፡ በዮሐንስ ራሰ የማይሰራ ክፉ ሥራ ሲሰሩ የዮሐንስ ራሱ ክንፍ አውጥታ ሄሮዳያዳን በጥፊ መታ ወደ ሰማይ ዐርጋለች፡፡ እናቷንም ምድር ተከፍታ ውጣታለች፡፡ ዮሐንስ ጌታውን ለማጥመቅ የታደለ ጌታም አማን እብለክሙ ኢተንሥአ እምትውልደ አንስት ዘየዐብዩ ለዮሐንስ (ማቴ ፲፩÷፲፩) ብሎ የተናገረለት የቅዱሳን ርእስ ነው። በተስፋው ያመነውን በቃል ኪዳኑም የተማጸነውን እስከ50 ትውልድ ሊምርለት ጌታ ቃል ኪዳን ገብቶለታል። የዮሐንስ ስብከት ከሞት በኋላ ያልቆመ ስብከት ነው።
የዮሐንስ ራስም ፲፭ ዓመት ወንጌልን ከአስተምራለች በኋላ ሚያዚያ ፲፭ ቀን ዐረቢያ ከምትባል ሀገር ዐረፈች ነጋድን አግኝተው ቀብረዋታል፡፡ የዩሐንስ ራስም ጌታ በደብረ ዘይት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሳለ ሄዳ ሰገደችለት። ዕረፍቱ የካቲት ፴ ቀን ሲሆን በንጉሥ ሄሮድሰ ሰማዕት የሆነው መስከረም ፪ ቀን ነው ።መስከረም ፪ በሊቃውንቱ ዘንድ ምትረተ ርእሱ ለዮሐንስ መጥምቅ ትባለልች ፡፡ሰኔ ፴ ቀን ዕለተ ልደቱ ነው፡፡
በመምህር ተመስገን ዘገየ

እንኳን አደረሳችሁ!
@ኆኅተ ሰማይ ገዳም ሚዲያ አሜሪካ!

09/11/2026
ብፁዕ አባታችን እንኳን ለአዲሱ  ፳፻፲፱ የምሕረት ዓመት ቸር እግዚአብሔር በጤና ጠብቆ በመንበረ ጵጵስናዎ አጽንቶ በሰላም አደረሰዎ።በረከትዎ አይለየን!  _አሜሪካ
09/11/2026

ብፁዕ አባታችን እንኳን ለአዲሱ ፳፻፲፱ የምሕረት ዓመት ቸር እግዚአብሔር በጤና ጠብቆ በመንበረ ጵጵስናዎ አጽንቶ በሰላም አደረሰዎ።
በረከትዎ አይለየን!

_አሜሪካ

  ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በክብር ያረፉት ነሐሴ ፳፬ ቀን ነው። በዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ታከብረዋለች።አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከአባ...
08/30/2026


ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በክብር ያረፉት ነሐሴ ፳፬ ቀን ነው። በዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ታከብረዋለች።

አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብ እና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኃረያ ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ፲፪፻፲፪ ዓ.ም በቡልጋ አውራጃ ኢቲሳ በሚባል ቦታ ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን እሑድ ከጠዋቱ በሦስት ሰዓት ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ፤ አንዱ አብ ቅዱስ ነው፤ አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው፤ አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው››በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ በተወለዱ በ፲፭ ዓመታቸው መዓርገ ዲቊናን፤ በ፳፪ ዓመታቸው ደግሞ መዓርገ ቅስናን ከግብጻዊው ጳጳስ አባ ጌርሎስ (ቄርሎስ) ተቀብለዋል፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በመጀመሪያ በወላጆቻቸው የወጣላቸው ስም ‹ፍሥሐ ጽዮን› ነበር፡፡

በአንድ ወቅት በሕፃንነታቸውም ወደ ጫካ ለአደን በሔዱበት ጊዜ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦ ጸጋ መንፈስ ቅዱን አሳደረባቸው፡፡ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወንጌል ወዳልተዳረሰበት ቦታ እንደሚልካቸውም አስረዳቸው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ከአውሬ አዳኝነት ሰውን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመመለስ እንደ ተመረጡ፤ አጋንንትን የማውጣት፣ ተአምራትን የማድረግ ሥልጣን እንደ ተሰጣቸው፤ ስማቸውም ‹ተክለ ሃይማኖት› እንደሚባል፤ ትርጓሜውም ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት እንደሆነ አበሠራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ያላቸውን ንብረት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ሰጥተው ‹‹አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደ ተከፈተ ተውኹልህ›› በማለት ቤታቸውን ትተው ወንጌልን ለማስተማር ፈጥነው ወጡ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምረው በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክና ተአምራትን በማድረግ ብዙ አሕዛብን ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፤ ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሰዋል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳንጸዋል፡፡

በደብረ ሊባኖስ ገዳምም (ገዳመ አስቦ) ዋሻ በመግባትም ሁለቱን በፊት፣ ሁለቱን በኋላ ሁለቱን በቀኝ፣ ሁለቱን በግራ ስምንት ጦሮችን ተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማም፣ ሞትና ነገረ መስቀል በማሰብ በተመስጦ ሌሊትና ቀን ያለ ማቋረጥ በጾም፣ በጸሎት ተወስነው ሲጋደሉ፤ ከቊመት ብዛት የተነሣ በ፺፪ኛ ዓመታቸው ጥር ፬ ቀን ፲፪፻፹፱ ዓ.ም አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራለች፡፡ ደቀ መዛሙርቱም የመንፈሳዊ አባታቸውን ስባረ ዐፅም (የዐፅም ስባሪ) አክብረው በሥርዓት አኑረዋታል፡፡ እግራቸው እስኪሰበር የቆዩባቸው ዓመታትም ፳፪ ናቸው፡፡ ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ያለ ምግብና ያለ ውኃ በትኅርምት ሌሊትና ቀን እንደ ምሰሶ ጸንተው በትጋት ለሰው ዘር ዅሉ ድኅነትን ሲለምኑ ኖረዋል፡፡ ከሰባቱ ዓመታት ውስጥ ጥቂት ውኃ የቀመሱት በአራተኛው ዓመት ብቻ እንደ ነበረ መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል፡፡

አቡነ ተክለሃይማኖት ምድራዊ ሕይወታቸውን በተጋድሎና በሐዋርያዊ አገልግሎት ከፈጸሙ በኋላ ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድ የሚያልፉበት ቀን ተቃረበ፡፡ በዚህ ጊዜ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን መላእክት፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ከቅዱሳን ሐዋርያት ጋር ወደ እርሳቸው በመምጣት የሚያርፉበት ዕለት መድረሱን ነገራቸው፡፡ የተጋድሏቸውን ጽናት አድንቆ በስማቸው መታሰቢያ ለሚያደርጉ፣ ለነዳያን ለሚመጸዉቱ ቤተ ክርስቲያን ለሚያሠሩ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ስለ ተጋድሏቸው ጽናትም ‹‹በሰው እጅ የማይለካውን ይህንን የመንግሥት አዳራሽ ውሰድ›› በማለት የመለኮትን ነገር የሚናገር የእሳት አንደበት ያለው የጸጋ ልብስ አልብሷቸዋል፤ በመስቀል ምልክት ያጌጡ ሰባት የሕይወት አክሊላትንም አቀዳጅቷቸዋል፡፡

ጻደደቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው ጊዜ መቃረቡን ባወቁ ጊዜ የመንፈስ ልጆቻቸውን ጠርተው ጌታችን የነገራቸውን ሁሉ አስረድተው አባታዊ ምክርና ተግሣፅ ከሰጧቸው በኋላ ነሐሴ ፳፬ ቀን ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል፡፡ የመንፈስ ልጆቻቸውም ለአንድ ቅዱስ አባትና ካህን በሚገባ ሥርዓት በማኅሌት፣ በዝማሬና በምስጋና ቀብረዋቸዋል፡፡ ጌታችንም ከእመቤታችንና ከቅዱሳን መላእክት ጋር ተገልጾላቸዋል፤ነፍሳቸውንም ‹‹የጠራሽ፣ ንጽሕት ነፍስ ሆይ ወደ እኔ ነዪ›› ብሎ በክብር ተቀብሏታል፡፡

አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዚህ ዓለም የኖሩበት ዕድሜ ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከዐሥር ወር ከዐሥር ቀን ነው፡፡ በእናት አባታቸው ቤት ፳፪ ዓመት፤ በከተታ ፫ ዓመት፤ በይፋት ፱ ወር፤ በዳሞት ፲፪ ዓመት፤ በአማራ ፲ ዓመት፤ በሐይቅ ፲ ዓመት፤ በደብረ ዳሞ ፲፪ ዓመት፤ በትግራይና በኢየሩሳሌም ገዳማት ፩ ዓመት፤ ዳዳ በሚባል አገር ፩ ወር፤ በደብረ አስቦ ገዳም ፳፱ ዓመት ከ፲ ቀን መቆየታቸውን መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል (ገ.ተ.ሃ ፶፱፥፲፬-፲፭)፡፡

ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕይወታቸውን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣ እንደ ገበሬ ታጥቀው ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና ከመኖራቸው ባሻገር እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የሰበኩ፤ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሐዋርያ ናቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያችንም ነሐሴ ፳፬ ቀን የዕረፍታቸውን በዓል በትላቅ ደስታ ታከብራለች፤ የጻድቁ በረከት አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ከማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ የተወሰደ!

ምንጭ፡–መጽሐፈ ስንክሳር፣ ነሐሴ ፳፬ ቀን፣ገድለ ተክለ ሃይማኖት፡፡
-አሜሪካ
እንኳን አደረሳችሁ
የጻድቁ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ረድኤት በረከት ይደርብን!

Address

69300 Vineyard Canyon Road
San Miguel, CA
93451

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gateway to Heaven St. John Monastery in California posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gateway to Heaven St. John Monastery in California:

Shortcuts

Share

Category