ቀለም Kelem

ቀለም Kelem ከቀለም እውነትንም ዕውቀትንም ይቅሰሙ፡፡ Kelem means Color, explore realty and knowledge Informing the realities around the world focusing Ethiopian Issues

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአሜሪካ ፓርኪንግ ሲሰሩ ያሳያል በሚል ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተጋራ የሚገኘዉ ምስል በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተፈበረከ ነው /ኢትዮጵያ ቼክ/- በርካታ የፌስቡክ...
10/14/2025

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአሜሪካ ፓርኪንግ ሲሰሩ ያሳያል በሚል ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተጋራ የሚገኘዉ ምስል በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተፈበረከ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- በርካታ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶች “አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአሜሪካ ፓርኪንግ ሲሰሩ ያሳያል” በሚል በስክሪን ቅጂው (screenshot) ላይ የሚታየውን ምስል እያጋሩ ይገኛሉ።

ይህን መረጃ እና ምስል ካጋሩ የፌስቡክ ገጾች መካከል ‘Arada Times’ የሚል ስም ያለው እና ከ44 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ አንዱ ነው። ይህ ገጽ ያጋራዉን ጽሁፍ እና ምስል ከ130 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰዉ ያጋሩት ሲሆን ከ1,600 በላይ ሰዎች ሀሳብ እና አስተያየት ሰጥተዉበታል።

በተጨማሪም 'Ethio Times' የተባለ ከ1 ሚልዮን በላይ ተከታይ ያሉት የፌስቡክ ገፅም ምስሉን አጋርቷል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገዉ ማጣራት ምስሉ ትክክለኛ ያልሆነ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተፈበረከ መሆኑን አረጋግጧል።

የምስሉን ትክክለኛነት ለማጣራት በጉግል ኤአይ (Google AI) የተሰሩ ምስል፤ ድምጽ እና ቪዲዮዎችን ለማጣራት የሚያገለግለው እና በጉግል የተበለጸገዉን ‘SynthID Detector’ የተጠቀምን ሲሆን ምስሉም በጉግል ኤአይ ምርት የተሰራ መሆኑን ተመልክተናል።

ጉግል በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰሩ ምስሎች፤ ድምጾች እና ቪዲዮዎች አማካኝነት የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል ‘SynthID Detector’ የተሰኘዉን መገልገያ ያበለጸገ ሲሆን መገልገያዉም በGemini፣ Imagen፣ Lyria እና Veo ሞዴሎች የተመረቱ ምስሎች፣ ድምጾች እና ቪዲዮዎችን ለማጣራት ይረዳል።

ከዚህም በተጨማሪ በምስሉ ላይ የሚታዩት የድሮ ሞዴል ፎርድ ስሪት የሆኑ ቢጫ ታክሲዎች ከጥቂት አመታት ወዲህ ከአሜሪካ መንገዶች ላይ እንደማይታዩ መረጃዎች ያሳያሉ።

በአሁኑ ወቅት ከሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መስፋፋት እና መርቀቅ ጋር በተያያዘ ትክክለኛ የሚመስሉ እና ለመለየት አዳጋች የሆኑ የድምጽ፣ ምስል እና ቪዲዮ ይዘቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በመስራት ማሰራጨት በጣም ቀላል ሆኗል።

በመሆኑም በማህበራዊ ትስስር ገጾች የምንመለከታቸዉን እና ታማኝ ባልሆኑ የመረጃ ምንጮች የሚሰራጩ የምስል እና ቪዲዮ ይዘቶችን ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

የማዳጋስከር ሕዝባዊ አመጽ ሥልጣን ለወታደሩ አስረከበ፡፡በአፍሪካ ትልቋ ደሴት ማዳጋስከር ከሰሞኑ በሕዝባዊ አመጽ እየተናጠች ሰንብታለች፡፡ ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆይሊና ለደኅንነታቸዉ በመስጋት ...
10/14/2025

የማዳጋስከር ሕዝባዊ አመጽ ሥልጣን ለወታደሩ አስረከበ፡፡

በአፍሪካ ትልቋ ደሴት ማዳጋስከር ከሰሞኑ በሕዝባዊ አመጽ እየተናጠች ሰንብታለች፡፡ ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆይሊና ለደኅንነታቸዉ በመስጋት ከቤተ መንግሥታቸዉ አካባቢ መሸሸታቸዉን ገልጸውም ነበር፡፡ ዛሬ በወጣ መግለጫም ኮሎኔል ሚካኤል ራንድሪያኒሪና የተባሉ የጦር መኰንን ሀገራዊ ተቋማትን ማፍረሳቸዉን እና የታችኛዉ ምክር ቤት በሚል የሚታወቀው የመንግሥት አካል ብቻ እንደቀረ አስታውቀዋል፡፡ ኮብላዩ ፕሬዝዳንት በሕግ እንደሚጠየቁም ተናግረዋል፡፡

አቶ ሳንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።****************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አ...
10/14/2025

አቶ ሳንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።
******************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ሳንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ ደንብ ዛሬ መጽደቁ ይታወሳል።

የዳሞት እግር ኳስ አባት ጋሽ ዘነበ አሰፋ ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል።በፍኖተሰላም ከተማና አካባቢዋ ከ1971 ጀምሮ በአሰልጣኝነት የአካባቢው እግርኳስ በራስ ተነሳሽነታቸው እንደሻማ ቀልጠው ያ...
10/14/2025

የዳሞት እግር ኳስ አባት ጋሽ ዘነበ አሰፋ ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል።

በፍኖተሰላም ከተማና አካባቢዋ ከ1971 ጀምሮ በአሰልጣኝነት የአካባቢው እግርኳስ በራስ ተነሳሽነታቸው እንደሻማ ቀልጠው ያቆሙት የእግርኳሱ ቅኔ ጋሽ ዘነበ አሰፋ በተወለዱ በ82 ዓመታቸው በዛሬ ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ጋሽ ዘነበ አሰፋ ማናቸው?
አሰልጣኝ ዘነበ አሰፋ ከአባታቸው ከአቶ አሰፋ ገብረ ስላሴና ከእናታቸው ከወ/ሮ ጥሩ መሸሻ በ1936 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቡልቡላ ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ተወለዱ:: በቤተሰቦቻቸው የሥራ ዝውውር ምክንያትም ፍቅር ከሆነዉ ቤተሰባቸው ፍቅርን እና መተሳሰብን ባህል ባደረጉት ታሪካዊ ከተሞች በሆኑት ናዝሬት፣ ሐረር እና ድሬዳዋ ኖረዋል::
በታዳጊነት ዕድሜያቸው ለብሄራዊ ቡድን ለመጫወት ከበቁት እና ስመ ጥር ከሆኑት ኢታሎ ቫሳሎ፣ ሉቺያኖ ቫሳሎ እንዲሁም ከአስራት ኃያሌ ጎራዴዉ ጋር በድሬዳዋ ኮተኒ እና ምድር ባቡር የእግር ኳስ ቡድኖችን በመመልከት፣ ብሎም በመጫወት የኳስ ሕይወትን እንደጀመሩ ይናገራሉ። ከድሬዳዋ ክለብ በተጨማሪ ቀይ ኮከብ ከሚባል አንድ የጣሊያን ቡድን ጋር እግር ኳስ ተጫውተዋል፡፡
ትምህርታቸውን ድሬዳዋ የተከታተሉ ሲሆን በ1971 ዓ.ም ወደ ጎጃም ክፍለ ሀገር ብር ሸለቆ እርሻ ልማት በማምራት ሥራ ጀምረዋል።

አሰልጣኝ ዘነበ አሰፋ በስራ ምክንያት ወደ ጎጃም ብር ሸለቆ ከተዛወሩ በኋላ በሚፈልጉት ልክ ምኞታቸውን ማሳካት ባይችሉም ከልጅነታቸው ጀምሮ ለእግር ኳስ ያላቸው ፍቅር ከፍ ያለ በመሆኑ በ1971 ዓ.ም ወደ ጎጃም ብር ሸለቆ እርሻ ልማት ውስጥ ለነበረው አረንጓዴው ብር ለሚባል የእግር ኳስ ቡድን በተጫዋችነት እና ለመጀመሪያ ጊዜ በአሰልጣኝነት የወቅቱ የጎጃም ክፍለ ሃገር ሻምፒዮን እስከመሆን ደርሰዋል::

ከዚያም ለአስር ዓመታት ያክል ያገለገሉበትን የብር ሸለቆ እርሻ ልማትን በመልቀቅ ወደ ፍኖተ ሰላም ከተማ አመሩ፤በዚያም በ1969 ዓ.ም የተቋቋመውን የቀድሞውን ገራይ የአሁኑን ዳሞት ከነማ የእግር ኳስ ቡድንን ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት አስርት ዓመታት በታላቅ ፍቅር እና ወኔ በማሰልጠን ቡድኑንም ሆነ ተጨዋቾችን ታላቅ ደረጃ ላይ ማድረስ ችለዋል::
በአሰልጣኝነት ጊዜያቸው በርካታ ተጨዋቾችን እና አሰልጣኞችን ማፍራት ችለዋል። በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተለያዩ ክለቦች ውስጥ ከተጫወቱ ተጫዋቾች አድማሱ አንተነህ፣ አብርሃም ብርሃኔ፣ ገበያው ሽፈራው፣ ሰለሞን ተስፋዬ የመሳሰሉትን አፍርተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አሰልጣኝ ገብረ መድህን ኀይሌ እና አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለም በዘነበ አሰፋ ስር ሰልጥነዋል።
ለዳሞት ከነማ እግር ኳስ እድገት ዕውቀታቸዉን፣ገንዘባቸውን፣ ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን እና ሁሉንም ነገራቸውን የሰጡ ጀግና ተብለው የሚመሰከርላቸዉ ታላቅ ሰው ለመባልም በቅተዋል፡፡
አሰልጣኝ ዘነበ አሰፋ ከበኲር ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ እግር ኳስ ሲናገሩ፣ “ሙያዬ ብቻ አይደለም፤ ብዙ መስዋእትነት የከፈልኩበት ህይወቴም ጭምር ነው” ይላሉ፤ ከተጨዋችነት እስከ አሰልጣኝነት ብዙ ዓመታትን በእግር ኳስ ጨዋታ ማሳለፋቸውን በመግለጽ። “ለዚህ ደግሞ ከእኔ ይልቅ ዛሬ የተሰጠኝ እውቅና ምስክር ነው” ሲሉም ያነሳሉ።
አሰልጠኝ ዘነበ አሰፋ ከስፖርቱ ዘርፍ በተጨማሪ በንግድ እና በሆቴል ስራ፣ በቤት እንዲሁም በቢሮ ዕቃዎች አምራችነት፣ በዳቦ ቤት እና በከብት እርባታ ላይ በመሰማራት ለበርካታ ዓመታት በውጤታማነት የዘለቁ ሰው ናቸዉ፡፡
በዚህም በስፖርቱም ሆነ በንግድ ስራዎቻቸው በታማኝነት እና በሃቀኝነት እንዲሁም ዘመን ተሸጋሪ የሆኑ ስራዎችን በማበርከት በፍኖተ ሰላም ማህበረሰብ ዘንድ የተከበሩ ናቸው፡፡

አሰልጣኝ ዘነበ አሰፋ በልጆቻቸዉ እና በሚያሳድጓቸዉ የልጅ ልጆቻቸዉ የሞቀ እና የደመቀ የትዳር ሕይወት የሚመሩ፤ ከራሳቸዉ አልፈዉ ለሌሎች የተረፈ የሀብት ባለቤት ነበሩ፡፡ በርካታ አድናቂዎቻቸው፣ ወዳጆቻቸው እና አለፍ ሲሉም የስፖርት ወዳዱ ማህበረሰብ ለዳሞት ከነማ ላደረጉት ነገር ሁሉ ምስጋናን ችሯቸዋል።
ዳሞት ከነማ የእግር ኳስ ክለብ ከምስረታው ጀምሮ ከፍተኛ ሊግ እስኪደርስ ድረስ ሚናቸው ግንባር ቀደም ነበር። በክለቡ ባበረከቱት አስተዋጽኦ እና ባሳዩት ብቃትም በአካባቢው ስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ “የእግር ኳሱ ንጉሥ” እስከመባልም ደርሰዋል።
ዳሞት ከነማ የእግር ኳስ ክለብን ከምስረታው ጀምረው ጠንክረው በማሰልጠናቸው በአንድ ዓመት ብቻ ከወረዳ እስከ ክልል በተደረጉ ውድድሮች ሶስት ዋንጫዎችን በማንሳት ክለቡን ሻምፒዮን በማድረግ አንቱታን አትርፈዋል።
በአጠቃላይ አሰልጣኝ ዘነበ አሰፋ ከ1971 ዓ.ም እስከ 2008 ዓ.ም ድረስ በብር ሸለቆ የእርሻ ልማት ውስጥ የአረንጓዴው ክለብን እና ዳሞት ከነማን በአሰልጣኝነት ጊዜ ቆይተዋል። የዳሞት ከነማ የእግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ለነበሩት ዘነበ አሰፋ በክለቡ ለነበራቸው አበርክቶ በክለቡ ተጨዋቾች እና የአካባቢው ስፖርት አፍቃሪያን እውቅና ተሰቷቸው ነበር።

ምንጭ:- በኲር ጋዜጣ ሚያዝያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም

ጋሽ ዘነበ አሰፋ ነፍስ ይማር!

ባለሙያዎች በአፍሪካ አፋጣኝ የእዳ ስረዛ እንዲደረግ ጠየቁ።ከ30 በላይ መሪ ኢኮኖሚስቶች እና ባለሥልጣናት፣ የአፍሪካ ሀገራት በአማካይ 17% ዓመታዊ ገቢያቸውን ዕዳ ለመክፈል ማዋላቸውን በመቃ...
10/14/2025

ባለሙያዎች በአፍሪካ አፋጣኝ የእዳ ስረዛ እንዲደረግ ጠየቁ።

ከ30 በላይ መሪ ኢኮኖሚስቶች እና ባለሥልጣናት፣ የአፍሪካ ሀገራት በአማካይ 17% ዓመታዊ ገቢያቸውን ዕዳ ለመክፈል ማዋላቸውን በመቃወም፣ አፋጣኝ የእዳ ስረዛ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የኖቤል ተሸላሚው ጆሴፍ ስቲግሊዝን ጨምሮ ባለሙያዎቹ፣ ይህ ከፍተኛ የዕዳ ጫና መንግስታት ለመሰረታዊ አገልግሎቶች የሚሰጡትን ድጋፍ እየገታ እንደሆነ አስጠንቅቀዋል።

ይህም ሆኖ 32 የአፍሪካ ሀገራት ከጤና፣ እና 25 ሀገራት ከትምህርት ይልቅ ለዕዳ እንዲከፍሉ እየገፋፋ ነው።

ባለሙያዎቹ፣ የዕዳ ቅነሳ ከተደረገ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ንፁህ ውሃ ማቅረብ እና በሺዎች የሚቆጠሩ የሕፃናትን ሞት መከላከል እንደሚቻል አስታውቀዋል።

ጥሪው የቀረበው በአፍሪካ የጤና ሥርዓት የመድኃኒት እጥረት እና የሰራተኞች ችግር በገጠመበት ወቅት ነው።

በሚቀጥለው ወር በአለም ባንክ እና በአይኤምኤፍ አመታዊ ስብሰባዎች ላይ ሀገራት ይህንን ጉዳይ እንዲፈቱት ጥያቄው ቀርቧል።

በሲሸልስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚው መሪ አሸነፉ።በአፍሪካዊቷ ደሴት ሲሸልስ በተካሄደ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲዉ ዕጩ ፓትሪክ  ኸርሚኔ 52.7% ድምፅ በማግኘት አሸነፉ።በሥልጣን ...
10/12/2025

በሲሸልስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚው መሪ አሸነፉ።

በአፍሪካዊቷ ደሴት ሲሸልስ በተካሄደ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲዉ ዕጩ ፓትሪክ ኸርሚኔ 52.7% ድምፅ በማግኘት አሸነፉ።

በሥልጣን ላይ የቆዩት ዋቫል ራምካላዋን 47.3% ድምፅ በማግኘት መሸነፋቸው ተሰምቷል።

አሳዛኝ የአደጋ ዜና በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በጨፋ ሮቢት በደረሰ የመኪና አደጋ በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል።በጨፋ ሮቢት ከተማ ልዩ ስሙ ጃራ ድልድይ አከባቢ  ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ...
10/12/2025

አሳዛኝ የአደጋ ዜና

በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በጨፋ ሮቢት በደረሰ የመኪና አደጋ በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል።

በጨፋ ሮቢት ከተማ ልዩ ስሙ ጃራ ድልድይ አከባቢ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ ሲጓዝ የነበረ ታታ ባስ እና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ ተሳቢ መኪና ተጋጭተው በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ለግዜው ቁጥራቸዉ ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በርካቶች የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በጨፋ ሮቢት ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ።

በጥንቃቄ ማሽከርከር ከዚህ መሰል አደጋ ይታደጋል።

ለሞቱት ነፍሰ ዕረፍትን፣ ለቆሰሉ ፈውስን፣ ለወገኖቻቸዉ መጽናናተትን እንመኛለን።

https://youtu.be/kSpJkC4YA4k
10/12/2025

https://youtu.be/kSpJkC4YA4k

በግእዝ ቋንቋ ጉዳይ ከዶ.ር በድሉ ዋቅጅራ እና መምህር ይኩኖአምላክ መዝገበ ጋር በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የተደረገ ውይይት ላይ የቀረበ

https://youtu.be/I_gKcsxHaag
10/12/2025

https://youtu.be/I_gKcsxHaag

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

ባለስልጣኑ አደገኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ 2 ድርጅቶችን 600 ሺህ ብር መቅጣቱን አስታወቀ።   የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አደ...
10/11/2025

ባለስልጣኑ አደገኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ 2 ድርጅቶችን 600 ሺህ ብር መቅጣቱን አስታወቀ።


የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አደገኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ 2 ድርጅቶችን እያንዳንዳቸውን 300 ሺህ ብር በድምሩ 600 ሺህ ብር መቅጣቱን አስታወቀ ።

ድርጅቶቹ ሮያል ከረሚላ ፋብሪካ እና ዲኤም ሲ ሪል እስቴት ሲሆኑ ባልተገባ መንገድ ከፋብሪካ አደገኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ሲለቁ በመገኘታቸው ቅጣቱ ተላልፎባቸዋል ።

በክፍለ ከተማው የኮሪደር ልማት እየለማ በሚገኝበት ጀሞ ወረዳ ፣ለቡ ወረዳ እንዲሁም ወረዳ 12 መዳረሻውን ያደረገው በተለምዶ አርሴማ ወንዝ አካባቢ የተለቀቀ አደገኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ፈሳሽ መሆኑ ተመላክቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለትን ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት ተቀጥተዋል ።

ባለስልጣኑ አሁን ላይ በወንዞች ዳርቻ ልማት መርሃ ግብር መሰረት የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማት ለከተማዎ ነዋሪዎች ምቹና ሳቢ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሆነ ማስታወቁን
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

ሦስት ከበድ ያሉ የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዘገቡ።በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል መቀሌ አካባቢ ዛሬ ምሽቱን ሦስት የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል። ከፍተኛው 5.68 ሬክተል ስኬል ተመዝግቧል።
10/11/2025

ሦስት ከበድ ያሉ የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዘገቡ።

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል መቀሌ አካባቢ ዛሬ ምሽቱን ሦስት የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል። ከፍተኛው 5.68 ሬክተል ስኬል ተመዝግቧል።

ሲኖ ትራክ ችግሩን ፈትቷል፤ እንዲገባ ይፈቀድለታል?የሲኖትራክ ኩባኒያ የቴክኒክ ችግር ያለባቸውን የሲኖትራክ መኪኖች በተለይም ገልባጮችን ስታንዳርዳቸውን ለማሟላት ቃል በገባዉ መሠረት ማስተካከ...
10/11/2025

ሲኖ ትራክ ችግሩን ፈትቷል፤ እንዲገባ ይፈቀድለታል?

የሲኖትራክ ኩባኒያ የቴክኒክ ችግር ያለባቸውን የሲኖትራክ መኪኖች በተለይም ገልባጮችን ስታንዳርዳቸውን ለማሟላት ቃል በገባዉ መሠረት ማስተካከል ጀመረ። የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ባረኦ ሀሰን በቦታው ተገኝተው የማስተካከያ ሥራዉን ዐይተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ከዚህ በፊት በተለይ ፍሬናቸው አካባቢ ባለባቸው የቴክኒክ ችግር ምክነያት የትራፊክ አደጋ ሲያደርሱ የነበሩ እና ይህም በጥናት የተደረሰበት እና መስተካከል የነበረበት ችግር እንደነበር አስታውሰው ኩባንያው ለማስተካከል በተስማማዉ መሠረት የማስተካከል ሥራ መጀመሩን አረጋግጠዋል።

ምርቶቹ በዋናነት ያላሟሏቸውም የውስጥ እና ውጪ 360 ድግሪ የሚያሳዩ ካሜራዎች፣ የፍሬን ጥንካሬ፣ ከተፈቀደ ክብደት በላይ ሲጫን የሚያሳውቅ ማንቂያ፣ ጭነት በየቦታው እንዳይፈስስ የሚከላከል የጣሪያ ክዳን እና ሌሎች ክፍሎች መስተካከላቸው ተሰምቷል።

ይሁን እንጅ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ዐዲስ መመሪያ በነዳጅ የሚሠሩ ከባድ መኪኖች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ከልክሏል። ሲኖ ችግሩን ቢያስተካክልም የመግባት ዕድሉ ዝቅተኛ ነው። ሚንስትር ድኤታውም ወደ ቻይና ያቀኑት ለዚህ ጉዳይ ብለው ከነበረ ድካማቸው ውኃ በልቶታል።

Address

Seattle, WA
1000

Telephone

+13609419683

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቀለም Kelem posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ቀለም Kelem:

Share

ከየትም ቦታ የሥራ ማስታወቂያ ወሬ አያልፈንም፤ እናደርሳችኋለን፡፡

Informing the realities around the world focusing Ethiopian Issues