Arega kassa media

Arega kassa media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Arega kassa media, Media/News Company, Silver Spring, MD.

የእግር ኳስ አፍቃሪም አይደለሁ።  ነገር ግን Lamine Yamal የተባለ ይህ ስፔናዊ ተጨዋች ከዕድሜው በላይ የበሰለ ቴክኒካዊ እና ታክቲካዊ ብቃቱ አንቱ የተባሉ ሁለትም ይሁኑ ሶስት የተጋጣ...
07/28/2026

የእግር ኳስ አፍቃሪም አይደለሁ። ነገር ግን Lamine Yamal የተባለ ይህ ስፔናዊ ተጨዋች ከዕድሜው በላይ የበሰለ ቴክኒካዊ እና ታክቲካዊ ብቃቱ አንቱ የተባሉ ሁለትም ይሁኑ ሶስት የተጋጣሚው ቡድን ተጨዋቾች ሲያቅታቸው በእጃቸው ለመያዝ ግብግብ ቢሞክሩም እንኳን ሚዛናቸውን አስቶ ግብ የማስቆጠር ብቃቱ እጅግ አስገራሚ የ2026 የአለም እግር ኳስ ጨዋታ ክስተት ነበረ።

የኔ ወንድም  አቶ ይበሉ ካሴ  ከቤተሰቦቻችን  ሁሉ  አንተ የተለየህ እና የላቀ ስነምግባር የነበረህ፤ እጅግ ሲበዛ ደግ፤ ታዛዥ እና ለእውነት ብቻ የኖርህ ልብህም  ልክ እንደመልክህ  ንፅህ ...
07/11/2026

የኔ ወንድም አቶ ይበሉ ካሴ ከቤተሰቦቻችን ሁሉ አንተ የተለየህ እና የላቀ ስነምግባር የነበረህ፤ እጅግ ሲበዛ ደግ፤ ታዛዥ እና ለእውነት ብቻ የኖርህ ልብህም ልክ እንደመልክህ ንፅህ ነበረ።

ለወላጆቻችን እና ለእኔ የዋልከውን ውለታ ለመመለስ ባልችልም በሌላ መንገድ ውለታህን ለመመለስ ሞክሬለሁ። እንደታሰበው ባለመሳካቱ ከስህተቱ ታርሜ ከወንድሞቼ እና እህቶቼ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት በማድረግ የተጀመረው ወዳጅ ዘመድ ጥየቃ አንተጋ ሳይደርስ በድገተኛ አደጋ መረፍህን ሰማሁ። እጅግ በጣም አዝኜለሁ፤ ነፍስህ በሰላም ትረፍ ወንድሜ!!
እኔ ግን እስከወዲያኛው አልረሳህም፤

05/18/2026
እጅግ ታታሪው እና ጎበዙ ተማሪ  የነበው የማከብረው ፣ የምወደው  እና የቀድሞ ጓደኛ  የአሁኑ የዩንቨርስቲ መምህር ዶ/ር ኢንጅነር  አረጋ ሙሉ  አዳል ፊዚክሱን፣ ኬሚስትሪውን እና ሂሰቡን አ...
05/09/2026

እጅግ ታታሪው እና ጎበዙ ተማሪ የነበው የማከብረው ፣ የምወደው እና የቀድሞ ጓደኛ የአሁኑ የዩንቨርስቲ መምህር ዶ/ር ኢንጅነር አረጋ ሙሉ አዳል ፊዚክሱን፣ ኬሚስትሪውን እና ሂሰቡን አኝኮ ውጦታል። ነገር ግን ታሪክ እና ጂኦግራፊን ስለማይመለከተው እምብዛም ነው። እና በማትሪክ የ እንግሊዝኛ ፈተና ተፈተን እና PASSAGE የሚናገረው ስለ አንዲት ኤዥያዊት ሀገር ቢሆንም እሳቸው ምንቢሉኝ ጥሩ ነው ፈሊፒንስ ግን ምንድናት እይለኝም? አይመለከታቸውማ!!

እናም ጂኦግራፊም በመማራችን የአገሮችን መገኛ እና ተያያዥ ጉዳዮችን እንዲሁም ታሪክ በመማራችንም ደግሞ ስለአለም ጥንታዊ ፤ መካከለኛ እና ዘመናዊ ታሪካቸውን ለመረዳትም ለማስረዳትም በተለይ በታላቋ የአለም ህዝቦች ሁሉ በሚኖሩባት አገር ሰዎች ጋር ስንገናኝ ሳንደናገር ለመግባባት እየተጠቀምንበት ነው።

ነገር ግን ሙያዊ ትምህርት እና እውቀት ላይ ትውልዱ እንዲያተኩር እመክራለሁ። አልተጠቀምሁበትም እንጂ ብሰራበት ኖሮ ለ6 አመታት ታሪክ እና ጂኦግራፊን በዲፕሎማና በዲግሪ በማጥናት ከሰበሰብሁት ‘A’ ይልቅ በጥቂት ወራት የተገኙት ሰርቲፊኬቶች እና ሙያዊ ስልጠናዎች ህይወትን ይቀይራሉ። ይህችን ትንሿን ትራክ የራሴን ጉዳይ ለመፈፀም የተጠቀምሁበት ነው። በጣም ደስ አይልም?

ሙያው ላይ አተኩሩ፣
ሀብታም ያደርጋል ኩሩ።

ወይ  ክቡር አረጋ ካሳ  እንግዳዬ ትገርማለህ ብዙ ምታካፍለው ሀሳብ አለህ ለካ፣ ተመስገን። ሱዳን እያለሁ አርቲስቱንም ፣ ንጉሱንም  ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘኋቸው  ከዛሬ አስር አመት በፊት በታ...
04/18/2026

ወይ ክቡር አረጋ ካሳ እንግዳዬ ትገርማለህ ብዙ ምታካፍለው ሀሳብ አለህ ለካ፣ ተመስገን።

ሱዳን እያለሁ አርቲስቱንም ፣ ንጉሱንም ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘኋቸው ከዛሬ አስር አመት በፊት በታላቋ ሱዳን ካርቱም ከተማ ነበር።
ለዛሬው ስለ ሙዚቀኛው ንጉስ ላውራና ስለሎቹ ነገስታት በሚቀጥለው እንዴት እና በምን ሁኔታ እንዳወቅናቸው እነሰነሳለን።

አርቲስት ቴወድሮስ ካሳሁን (TEDE AFRO) በ1990ዎቹ መጀመሪያ አጋማሽ አከባቢ ደምበጫ ወረዳ እያለሁ አቡጊዳን ጨምሮ ባወጣበት ወቅት ሙዚቃ ድምፅ ይሰማል፣ ሰውም ቴዲ እያለ ያደንቀዋል። እኔ አልገባኘም ሰምቼ የጠየቅሁትም የለም።

ነገር ግን በታላቁ የሙዚቃ ንጉስ አርቲስት መሐመድ ዋርዲ(MOHAMMED WARDI) ታላቅ አገር ሱዳን ካርቱም እያለሁ ቴዲ አፍሮ እ.ኤ.አ. 1914 ኮንሰርት ተዘጋጅቶ በ$50,000 (ሃምሳ ሺ የአሜሪካ ዶላር) ሱዳናዉያን አድናቂዎቹ ውል ፈፅመው እንዳመጡ እና አትርፈው ሳይሆን ከኪሳቸው አውጥተው ጭምር በካርቱም የሙዚቃ ድግስ ተዘጋጅቶ ነበር እና ወሬው እና ዜናው ስለአርቲስቱ አድናቆት ነበረ። ሱዳናውያን ደግሞ እንኳን ለቴዲ ይቅር እና ለተረ እንግዳም ቢሆን የፍቅር እና ክብር አሰጣጥን ያውቁበታል። እኔም ገባኝ ታላቅነቱ እና ተዋቂነቱ ገባኝ፤ በደንብ ገባኝ።

አርቲስቱ ስታደንቀውም፣ ብትከሰውም ፣ ብታስረውም የማይሞቅ የማይቀዘቅዝ የአገሩ ክብር እና ፍቅር ስላለው ከአገሩ ውጪ ለኮንሰርት አለምን ሲዞር ከሳምንታት ላልበለጠ እድሜ ስራውን ከውኖ ተመልሶ ምታገኘው እዚያው በአገሩ ነው። ታላቁን የሙዚቃ ንጉስ ቴዲ አፍሮን ከሁሉም አርቲስቶች ልዩ ከሚያደርጉት በርካታ ጉዳዮች በእኔ እይታ ይኽ እውነታ የልዩ ልዩ ያደርገዋል።

ልክ እንደወትሮው በአዲሱ አልበሙም አለምን አነጋግሮበታበታል፤ ህዝቡም፣ፓለቲከኛውም፣ ሙዚቀኛውም....ሁሉም ሁሉም እንደየተሰማራበት የስራ እና የሙያ ዘርፍ ወዘተ እየተነተነ እተነጋገረበት ነው።

ብልህ የሆን ሰውም ይሁን ድርጅት በራሱ ወጪ አርቲስቱ ያቀረበውን ሙዚቃዊ የምርምር ስራ ከአዝናኝነቱ እና ከመተቸት ባሻገር የሚጠቅመውን ትምህርት እና ጥቆማ ወስዶ የቤት ስራውን በመከወን ይጠቀምበት እንላለን።

የዚህ ዘመን በሙዚቃው ንጉስ በቴዲ አፍሮ በድፍረት የተሰራው ስራ እጅግ በጣም ተወዶለታል እና እንኳን ደስ አለው እንላለን፤ እግዚያብሔ ከክፉ ይሰውርው ፣ ይጠብቅው ለማለትም እንውዳለን።

AK & AKM

በሺዎች የሚቆጠሩ  የሚያማምሩ ውሸቶች እና ማስመሰሎችን ደረበህ ደረርበህ፣ ጀቡነህ ጀቧቡነህ ተንከባክበህ ሰማይ ብታስነካት ፤ ኮስማናዋ እውነት   ወቅቱን ጠብቃ የሆነ ቀን ፈንቅላ በመውጣት ራ...
04/17/2026

በሺዎች የሚቆጠሩ የሚያማምሩ ውሸቶች እና ማስመሰሎችን ደረበህ ደረርበህ፣ ጀቡነህ ጀቧቡነህ ተንከባክበህ ሰማይ ብታስነካት ፤ ኮስማናዋ እውነት ወቅቱን ጠብቃ የሆነ ቀን ፈንቅላ በመውጣት ራቁቷንም ቢሆን ቁማ አምራና ተውባ መቆሟን የሚያስቀር ምድራዊ ሐይል የለም።
እውነት እውነት ስለሆነች ነዋ!!!

እጅግ በጣም ሲበዛ በማራኪ አንደበታቸው፣  ስለታላቁ ምሁር ክቡር ወሌ ቸኮል ምርምር የሰሩት እውቁ ተመራማሪ እና የታሪክ መምህር አዳሙ መንግስቴ ጋር የተደረገውን ረጅም ውይይት ልክ እንደ አዲ...
03/28/2026

እጅግ በጣም ሲበዛ በማራኪ አንደበታቸው፣ ስለታላቁ ምሁር ክቡር ወሌ ቸኮል ምርምር የሰሩት እውቁ ተመራማሪ እና የታሪክ መምህር አዳሙ መንግስቴ ጋር የተደረገውን ረጅም ውይይት ልክ እንደ አዲስ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው አዳመጥሁት፤ ኮራሁባቸው። ነገር ግን ነፃ ትምህርት እና ማብራሪያ በመሆኑ የሚገባው ክብር እና ትኩረት አልተሰጠውም። ለምን? እኔ እንጃ ነው መልሴ። ለምን ይሆን?

ለማነኛውም በAKM ጋር ከተሰናዱት ዝግጅቶች እና በሚዲያችን ግንባር ቀደም ተብለው ከተመረጡት የምርምር ስራዎች አንዱ የታላቁ አዳሙ መንስቴ ተጠቃሽ ስለሆኑ ክብር ይገባቸዋል፤ እንኮራባቸዋለን።

AK & AKM

WOLIE CHEKOL,ETHIOPIAN PROMINENT ECONOMIST, BY ADAMU MENGISTIE, HISTORIAN AND RESEARCHERromo_ola_belay_manaye_bekalu_alamirew_zena_merja_wekitawi_abiy_pp_tpl...

Address

Silver Spring, MD

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arega kassa media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share