Sebez media - ሰበዝ ሚዲያ

Sebez media - ሰበዝ ሚዲያ What Sebez Media does is touches all forms of events like politics, social life, social media, Ethiopian history, health issues and to bring Ethiopian communities together.
(2)

With the help of our greatest Ethiopian journalists.

Operating as usual

የመደመር መንገድ!— — — —- — —የዶ/ር ዐቢይ አህመድ የመደመር ተከታይ “የመደመር መንገድ” መፅሐፍ ዛሬ ተመርቋል። የቀድሞው የመደመር መፅሐፍ አብራሪና አጋዥ ይሆናል የተባለው የመደመር ...
03/06/2021

የመደመር መንገድ!
— — — —- — —
የዶ/ር ዐቢይ አህመድ የመደመር ተከታይ “የመደመር መንገድ” መፅሐፍ ዛሬ ተመርቋል።

የቀድሞው የመደመር መፅሐፍ አብራሪና አጋዥ ይሆናል የተባለው የመደመር መንገድ መፅሐፍ በሶስት ክፍል በአስራ አንድ ምእራፍ ተከፍሎ ለንባብ ቀርቧል።

በወዳጅነትፓርክ በተሰናዳው ዝግጅት ላይ መፅሐፉ በአራት ፀሐፍትና ምሁራን አስተያየት ተሰጥቶበታል።

መፅሐፉ እንደ መጀመሪያው የመደመር መፅሐፍ ሀሳቡ እንደወረደ ያልተገለፀበት በትረካ አይነት መንገድ ከበድ ያሉ ሃሳቦች ቀለል ብለው በተረት አባባልና በግጥም ታጅበው የቀረቡበት መፅሐፍ ነው ተብሏል።

ዝክረ ጥላሁን የሙዚቃ ኮንሰርት በሸገር ወንድማማቾች ፓርክ
03/04/2021

ዝክረ ጥላሁን የሙዚቃ ኮንሰርት

በሸገር ወንድማማቾች ፓርክ

በዘንድሮው ምርጫ የሚሳተፉ እጩዎችን ያስመዘገቡ ፓርቲዎች እስካሁን 15 ብቻ ናቸው— — — — — — — —በ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ እስካሁን እጩዎችን ያስመዘገቡ ፓርቲዎች ቁጥር 1...
03/03/2021

በዘንድሮው ምርጫ የሚሳተፉ እጩዎችን ያስመዘገቡ ፓርቲዎች እስካሁን 15 ብቻ ናቸው
— — — — — — — —

በ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ እስካሁን እጩዎችን ያስመዘገቡ ፓርቲዎች ቁጥር 15 ብቻ መሆኑ ተነገረ።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር በምርጫው ዙሪያ እየመከረ ነው።

ፓርቲዎች በፀጥታ ስጋት በበጀት እጥረት በቂ ቢሮዎች ባለመከፈታቸውና በሌሎችም ምክንያቶች እንደ ልብ ተንቀሳቅሰው እጩ ማስመዝገብ እንዳልቻሉ ተናግረዋል ።

ነገ የሚጠናቀቀው የእጩዎች ምዝገባ ጊዜም ይራዘምልን ሲሉ ጠይቀዋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የፀጥታ ችግር አለባቸው የተባሉ ቦታዎች ላይ ተጨማሪ ጥበቃን በመመደብ በሃገር ደረጃ 673 ቢሮዎችን ከፍተናል ያሉ ሲሆን ያልተከፈቱ ቢሮዎች ካሉ ግን ማጣራት አድርገን እንዲከፈቱ እናደርጋለን ብለዋል።

እስካሁን 15 ፓርቲዎች ብቻ እጩዎችን ያስመዘገቡበትና ነገ የሚጠናቀቀው የምዝገባ ጊዜን በድጋሚ ማራዘም ከባድ እንደሚሆን ተናግረዋል።

በፀጥታና በሌላም ችግር ምክንያት የተለየ መጓተት የታየባቸውን ቦታዎች ብቻ በመለየት ግን የተወሰነ ማራዘሚያ ሊደረግ እንደሚችል ጠቁመዋል።

በትራንስፖርት ዋጋ ላይ የታሪፍ ጭማሪ ተደረገ— — — — — — — —የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ እንዳሳወቀው በሚኒባስና በሚዲባስ ትራንስፖርት ላይ ከ50 ሳንቲም እስከ 3ብር የታሪፍ ...
02/17/2021

በትራንስፖርት ዋጋ ላይ የታሪፍ ጭማሪ ተደረገ
— — — — — — — —

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ እንዳሳወቀው በሚኒባስና በሚዲባስ ትራንስፖርት ላይ ከ50 ሳንቲም እስከ 3ብር የታሪፍ ጭማሪ ተደርጓል።

እስከ 8 ኪ/ሜ ርቀት የሚሸፍነው የሚዲባስ ታሪፍ 3ብር የነበረ ሲሆን ባለቤት እንዲቀጥል ተወስኗል።

እስከ 2.5 ኪ/ሜ የሚሸፍነውን 2ብር ታሪፉ የነበረው ዝቅተኛው የሚኒባስ ታሪፍም ባለቤት ይቀጥላል ተብሏል።

ከዛ ውጪ ባሉ ርቀቶች ግን ከ 50 ሳንቲም እስከ ሶስት ብር የታሪፍ ጭማሪ ተደርጓል።

በሚኒባስ ታክሲ 17 ብር ታሪፍ ወቶለት የነበረው ከ20.1 እስከ 22.5 ኪ/ሜ ርቀት መንገድ ሶስት ብር ጭማሪ ተደርጎበት 20 ብር ተደርጓል ።

የነ አቦይ ስብሃት የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ— — — — — — — —መርማሪ ፖሊስ እስካሁን የ 113 ሰዎችን የምስክርነት ቃል መቀበሉን ተናግሯል። በርከት ያሉ ማስረጃዎችንም መሰብሰቡን እና ተ...
02/12/2021

የነ አቦይ ስብሃት የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ
— — — — — — — —

መርማሪ ፖሊስ እስካሁን የ 113 ሰዎችን የምስክርነት ቃል መቀበሉን ተናግሯል።

በርከት ያሉ ማስረጃዎችንም መሰብሰቡን እና ተጨማሪ መረጃና ማስረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ የ 14 ቀን ጊዜን ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ ስራውን እየሰራ አይደለም ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በተለያየ ህመም ምክንያት መድሃኒት እንደሚወስዱና በተለይ በመጀመሪያው መዝገብ የመጀመሪያ ተጠርጣሪ ሆነው የቀረቡት አቦይ ስብሃት በከፍተኛ ህመም ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ህክምናቸውንም በአዲስ ህይወት ሆስፒታል በግል ሀኪማቸው በኩል እንዲከታተሉ ጠይቀዋል።

መርማሪ ፖሊስ የመጀመሪያው ተጠርጣሪ ህመም ከአቅም በላይ እንዳልሆነና ህክምና እያገኙ እንደሆነ ጠቅሶ ህመማቸው ከአቅም በላይ ሳይሆን የግል ሀኪም ይየኝ ማለት ተገቢ አይደለም ብሏል።

በዛሬው የፍ/ቤት ውሎ በሶስት መዝገብ የቀረቡት የህውሓት ከፍተኛ አመራሮች በቁጥር 21 ናቸው።

ዳኛው በሶስቱም መዝገቦች የቀረበውን ክርክር ከሰማ በውሃላ በሶስቱም መዝገብ ተጨማሪ የአስራ አራት ቀን የምርመራ ጊዜን ፈቅዳል።

መዝገቡም ለየካቲት 19 ተቀጥሯል።

በምስራቅ ሐረርጌ በተሽከርካሪ አደጋ የ36 ሰዎች ህይወት አለፈ— — — — — — — —በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ36 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።...
02/03/2021

በምስራቅ ሐረርጌ በተሽከርካሪ አደጋ የ36 ሰዎች ህይወት አለፈ
— — — — — — — —

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ36 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ዲቪዥን ሃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ ለኢዜአ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው በወረዳው በዱሴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ዛሬ ከረፋዱ አምስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ላይ ነው።

ከወረዳው ዱሴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ወደ ጨለንቆ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ…አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ በመገልበጡ አደጋው መድረሱን ተናግረዋል ።

በአደጋው በተሽከርካሪው ላይ ተጭነው የነበሩ የ36 ሰዎች ህይወት ወድያው ማለፉን ገልጸዋል።
የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በደደር፣ ጨለንቆና ድሬዳዋ ከተማ በሚገኘው ድልጮራ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስከሬን ለየቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ መሆኑን አመልክተዋል።

የአደጋው መንስዔ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር እንደሆነ ያመለከቱት ኢንስፔክተሩ ፖሊስ አሽከርካሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ምንጭ: ኢዜአ

01/31/2021

ኮልፌ የገበያ ማእከል አካባቢ ማምሻውን የእሳት ቃጠሎ ተከስቷል።

የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች ከቦታው ደርሰው እሳቱን ለማጥፋት ሙከራ እያደረጉ ነው።

ከተራ በጃንሜዳ
01/18/2021

ከተራ በጃንሜዳ

መከላከያ ሰራዊት በሰጠው መግለጫ  የተደመሰሱት አመራሮች ፦1. አቶ ስዩም መስፍን፣ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ እንዲሁም ውጊያውን የመሩና ሰራዊቱ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ያዘዙ...
01/13/2021

መከላከያ ሰራዊት በሰጠው መግለጫ

የተደመሰሱት አመራሮች ፦

1. አቶ ስዩም መስፍን፣ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ እንዲሁም ውጊያውን የመሩና ሰራዊቱ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ያዘዙ፣ በመጨረሻም በሰራዊቱ ላይ ውጊያ እንዲከፈት ትዕዛዝ የሰጡ፣

2. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ፣ የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ

3. አቶ አባይ ፀሃዬ፣ የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ

4. ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎስ ከመከላከያ የከዱ ከነጥበቃዎቻቸው ተደምስሰዋል።

በሌላ በኩል በቁጥጥር ስር የዋሉ ወታደራዊና የክልል አመራሮች ፦

1. ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረ ኪዳን፣ ከመከላከያ የከዱ
2. ኮሎኔል ፍስሃ ብርሃኔ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
3. ኮሎኔል ዘረአብሩክ ታደሰ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
4. ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም የልዩ ሀይል ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረ
5. አቶ መብራህቶም ክንዴ ሀይሉ፣ የክልሉ ውሃ ስራዎች ድርጅት ፋይናንስ ሀላፊ የነበረ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የመከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሀላፊ ብ/ጀነራል ተስፋዬ አያሌው እንደተናገሩት።

እርጋታና ጥንቃቄ አይለየን!— — — — — — — —ከአዲስ አበባ ሰሜን በር መውጫ ከሱሉልታ እስከ ደብረ ሊባኖስ ባለው መንገድ ዛሬ የደረሱና በካሜራዬ ያስቀረዋቸው የትራፊክ አደጋዎች ናቸው። ...
01/12/2021

እርጋታና ጥንቃቄ አይለየን!
— — — — — — — —

ከአዲስ አበባ ሰሜን በር መውጫ ከሱሉልታ እስከ ደብረ ሊባኖስ ባለው መንገድ ዛሬ የደረሱና በካሜራዬ ያስቀረዋቸው የትራፊክ አደጋዎች ናቸው።

ጥንቃቄ ጥንቃቄ

ሀዋሳ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል
12/28/2020

ሀዋሳ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል

ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የጁንታው ቡድን መሪዎች የሚጠቀሙባቸውና በአሻራ የሚከፈቱትን ጨምሮ ከ40 በላይ ተሽከርካሪዎች ተያዙቡድኑ ሰራዊቱን መቋቋም ተስኖት ወደ ገጠራማ ስፍራ በእግር መጓዝ ሲጀምር...
12/07/2020

ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የጁንታው ቡድን መሪዎች የሚጠቀሙባቸውና በአሻራ የሚከፈቱትን ጨምሮ ከ40 በላይ ተሽከርካሪዎች ተያዙ

ቡድኑ ሰራዊቱን መቋቋም ተስኖት ወደ ገጠራማ ስፍራ በእግር መጓዝ ሲጀምር በታጣቂዎቹ በኩል ለማጥቃት ቢሞክርም እንዳልተሳካለት የ32ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ ተናግረዋል።

ፅንፈኛው ቡድን የመንገድ መሰረተ ልማት በሌለበት ከማይጨው 60 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ዴላ ወረዳ ከ40 በላይ የመንግስት እና በርካታ የግል ተሽከርካሪዎችን ይዞ ለመደበቅ ያደረገው ሙከራም መክሸፉን ነው ኮሎኔል ደጀኔ የተናገሩት።

ተሽከርካሪዎቹን ከፅንፈኛው ቡድን ሀይሎች አስጥሎ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰራዊቱ ባደረገው ፍተሻ በተሽከርካሪዎቹ ውስጥ መታወቂያ እና ፓስፖርቶች ተገኝተዋል።

የተለያዩ ሰነዶቻቸውን ጥለው ከሸሹት መካከል የቀድሞው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት፣ የማይጨው አስተዳዳሪ የነበረው ሀፍቱ ኪሮስ እና ሌሎች የወረዳ አመራር የነበሩ ሰዎች ሰነድ ይገኝበታል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ጥቆማ መሰረት ጌታቸው ረዳ በዴላ በኩል ከሸሸው ቡድን ውስጥ እንደሚገኝበትም ነው ኮሎኔል ፀጋዬ የገለጹት፡፡

በመከላከያ ሰራዊቱ ከተያዙት ተሽከርካሪዎች መካከል ስድስቱ በአሻራ የሚከፈቱ እጅግ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ሲሆኑ አራቱ ለኮሮና ወረርሽኝ መከላከል ስራ ከፌደራል መንግስቱ ለትግራይ ክልል የተበረከቱ አምቡላንሶች ይገኙበታል።

ፅንፈኛው ቡድን ሲጠቀምባቸው የነበሩ የጭነት ተሽከርካሪዎች እና ቦቴዎችንም ሰራዊቱ ወደ ማይጨው ከተማ እንዲገቡ አድርጓል ብለዋል።

በአሻራ የሚከፈቱትን ተሽከርካሪዎችም ከሞኤንኮ ጋር በመነጋገር ከአካባቢው ለማንሳትና ፍተሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አውስተዋል።

FBC

በቆላ ተንቤን የመጨረሻው ምሽግ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደ ነው— — — — — — — — በቆላ ተንቤን የሚገኘው የጁንታው የመጨረሻ ምሽግ በሀገር መከላከያ ሰራዊት በሶስት አቅጣጫ ተከቦ እርምጃ ...
12/06/2020

በቆላ ተንቤን የመጨረሻው ምሽግ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደ ነው
— — — — — — — —

በቆላ ተንቤን የሚገኘው የጁንታው የመጨረሻ ምሽግ በሀገር መከላከያ ሰራዊት በሶስት አቅጣጫ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደበት እንደሚገኝ ተገለጸ።

በቆላ ተምቤን የጁንታውን አመራር ለመያዝ የሚ ደረገውን ዘመቻ እየመሩ ያሉት በመከላከያ ሰራዊት የ31ኛ ክፍለ ጦር ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ኮሎኔል ሻምበል በየነ እንደገለጹት፤ ከመቀሌ ቢሮው ለቆ የሸሸው የጁንታው አመራር በቆላ ተንቤን የመጨረሻ ምሽጉ ላይ ይገኛል።

የመከላከያ ሰራዊትን የጁንታውን የመጨረሻ ምሽግ በተለያዩ አቅጣጫዎች ከቦ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል።

ቆላተምቤን ወርቅ አምባ ከተማ ላይ የመጨረሻ ምሽጉን ያደረገውን የጁንታውን አመራር ለመያዝ አሊያም ለመደምሰስ መከላከያ ሰራዊት በመረጃ የተደገፈ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ያሉት ኮሎኔል ሻምበል፤ ከአድዋ መስመር የመጣው ሰራዊት አካባቢውን ለመቆጣጠር እየገሰገሰ እንደሆነ እና ከሃውዜን እና መቀሌ መስመር ያለውም ወደ ቦታው በከፍተኛ ወኔ እየተጠጋ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

መከላከያ ሰራዊቱ ወርህ የሚባል ትልቅ ወንዝ መሻገር አይችልም በሚል አካባቢ የጁንታው ታጣቂዎች ማጥቃት ቢፈጽምም ሰራዊቱ ወደ አካባቢው ተጠግቶ ከወርቅ አምባ 10 ኪሎ ሜትር ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

እንደ ኮሎኔል ሻምበል ከሆነ፤ በቆላ ተምቤን ወርቅ አምባ አካባቢ የመሸገው ጁንታው በምድር ከሚወሰድበት እርምጃ ባለፈ በአየር ጭምር እርምጃ ተወስዷል።

በአየርና በድሮን አውሮፕላኖች በተወሰደ እርምጃ ወርቅ አምባ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ሰባት የጁንታው ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ወድመዋል።

ምንጭ: የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

ነብስ ይማር!ኢትዮጵያዊቷ ታዳጊ በአሳዛኝ ሁኔታ ከጎረቤት በተተኮሰ ጥይት ህይወቷ አለፈ— — — — — — — —ኢትዮጵያዊቷ የ 12 ዓመት ታዳጊ ከጎረቤት በተተኮሰ ጥይት በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወቷ...
12/05/2020

ነብስ ይማር!

ኢትዮጵያዊቷ ታዳጊ በአሳዛኝ ሁኔታ ከጎረቤት በተተኮሰ ጥይት ህይወቷ አለፈ
— — — — — — — —

ኢትዮጵያዊቷ የ 12 ዓመት ታዳጊ ከጎረቤት በተተኮሰ ጥይት በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወቷ አለፈ።

በአሜሪካ ኮሎምበስ ነዋሪ የሆነችው ታዳጊ ሊዲያ ከቤተሰቧ ጋር በምትኖርበት አፓርትመንት ውስጥ እንዳለች በድንገት ከጎረቤት ቤት የተተኮሰ ጥይት አንገቷን መቶ ለሞት እንዳበቃት ፖሊስ ተናግሯል።

የመሳሪያው ባለቤት ተገቢውን ጥንቃቄ ባለማድረጉ አሳዛኙ ድርጊት መፈፀሙን የተናገረው ፖሊስ ጠበቅ ያለ የመሳሪያ ቁጥጥር የሚያስፈልገው እንዲህ አይነቱን አደጋ ለመከላከል ነው ብሏል።

ሊዲያና ቤተሰቧ ወደዚህ አፓርትመንት ገብተው ኑሮ ከጀመሩ ገና አንድ ወራቸው እንደሆነ ተወርቷል።

ታዳጊዋ ሊዲያ በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወቷ ማለፉን ተከትሎ ለቀብር ስነ ስርዓት ማስፈፀሚያ በተከፈተው የ GoFundMe አካውንት ገንዘብ እየተሰበሰበ ነው።

ሰበር መረጃየህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሒም እጃቸውን ሰጡ!— — — — — — — —የአስኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማእከል እንዳስታወቀው ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሒም ለፌዴራል መን...
12/01/2020

ሰበር መረጃ

የህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሒም እጃቸውን ሰጡ!
— — — — — — — —

የአስኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማእከል እንዳስታወቀው ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሒም ለፌዴራል መንግስት ሃይል እጃቸውን ሰጥተዋል።

ወ/ሮ ኬሪያ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤነት ስራቸውን ለቀው ከወራት በፊት ወደ መቀሌ ማቅናታቸው የሚታወስ ነው።

በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ዘመቻውን አስመልክቶ እና በቀጣይ ሁኔታ ላይ ከጄኔራል አበባው ታደሰ ጋር በመቀሌ ከተማ መግለጫ እንሰጣለን።የጁንታው ርዝራዦች የጦር መሪዎችን ማርከናል እያሉ የሚነዙት ...
11/29/2020

በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ዘመቻውን አስመልክቶ እና በቀጣይ ሁኔታ ላይ ከጄኔራል አበባው ታደሰ ጋር በመቀሌ ከተማ መግለጫ እንሰጣለን።

የጁንታው ርዝራዦች የጦር መሪዎችን ማርከናል እያሉ የሚነዙት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ስለ ጦርነት አውድ ያላቸው እውቀት አናሳነት የሚያሳይ ነው።

ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ

የትግራይ ሕዝብ ከስግብግቡ ጁንታ ጋር እንዳልሆነ በተግባር አስመስክሯል - ጠቅላይ ሚኒስትርዶ/ር ዐቢይ አህመድ— — — — — — — —የመከላከያ ሠራዊት በድል በገሠገሠባቸው የትግራይ አካባቢዎ...
11/28/2020

የትግራይ ሕዝብ ከስግብግቡ ጁንታ ጋር እንዳልሆነ በተግባር አስመስክሯል - ጠቅላይ ሚኒስትር
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
— — — — — — — —

የመከላከያ ሠራዊት በድል በገሠገሠባቸው የትግራይ አካባቢዎች ሁሉ የትግራይ ሕዝብ ለሀገሩ ያለውን ፍቅርና ለመከላከያ ሠራዊቱ ያለውን ክብር አሳይቷል።

ጁንታው ካስታጠቃቸው ጥቂት የክፋት ኃይሎች ውጭ ያለው የትግራይ ሕዝብ መቀሌ እስኪገባ ድረስ ለመከላከያ ሠራዊቱ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ሁሉ አድርጓል።

ይህም የሠራዊቱን ድልና የጁንታውን ሽንፈት አፋጥኖታል።

ስግብግቡ ጁንታ በየትኛውም መመዘኛ ለትግራይ ሕዝብ አይመጥነውም። የትግራይ ሕዝብ ከእውነት ጋር በመቆምና የጁንታውን እኩይ ዓላማ በመፃረር ከቀበሌ ቀበሌ፣ ከዞን ዞን መቀሌ እስኪገባ ድረስ ተመሳሳይ ድጋፍ ለሠራዊቱ ሰጥቷል። ለዚህም ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ጁንታው በሸሸበት ከተማና አካባቢ ሁሉ የጤና ተቋማትን፣ ተ/ቤቶችን፣ ድልድዮችን፣ መንገዶችን፣ መሥሪያ ቤቶችን እያወደመ ሄዷል። በዚህም የገዛ ወገኑ ጠላት መሆኑን አሳይቷል። ጁንታው እኔ ከሞትኩ ብሎ ያፈረሳቸውን መሠረተ ልማቶች በፍጥነት በመገንባት የትግራይ ሕዝብ ወደ ሰላማዊ ኑሮው እንዲመለስ ለማድረግ የቻልነውን ሁሉ እንደምናደርግ ቃል እገባለሁ።

በዚህ ዘመቻችን ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ፣ ከተሞቻችንና ቅርሶቻችን ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት ተችሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

11/27/2020

የአገር መከላከያ ሰራዊት መቐለን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን ስትራቴጂክ ቦታዎች መያዙን አስታወቀ

በማይካድራ ተጨማሪ የጅምላ መቃብሮች ተገኙ— — — — — — — —የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቦታው በመገኘት ባደረገው ጥናት እና  ይፋ ባደረገው መረጃ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 እን...
11/27/2020

በማይካድራ ተጨማሪ የጅምላ መቃብሮች ተገኙ
— — — — — — — —

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቦታው በመገኘት ባደረገው ጥናት እና ይፋ ባደረገው መረጃ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 እንደሆነ ገልጾ ነበር።

ግድያውም ዘርን መሠረት ያደረገና በተለይም የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ጭፍጨፋ መሆኑን ገልጿል።

ይሁን እንጂ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 ነው ተብሎ የተገለጸው በማይካድራ ከተማ በየቤቱ ህይወታቸው አልፎ የተገኙ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ የተቀበሩትን ብቻ መሠረት ያደረገ ነው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጥናት አድርጎ ከተመለሠ በኃላ ከማይካድራ ከተማ ወጣ ባሉ የገጠር አካባቢዎች በርካታ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ጋዜጠኞች በቦታው በመገኘት አረጋግጠዋል።

በአንድ ቦታ 18 ሰው በጉድጓድ ውስጥ በጅምላ የተጣሉ ሲሆን በሌላ የገጠር አካባቢ ደግሞ 57 ሰዎች በጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ውስጥ በጅምላ ተገድለው እና ተጥለው ተገኝተዋል።

በዛሬው ዕለትም በማይካድራ ሌላ የገጠር ቀበሌ ውስጥ 17 ሰዎች በጅምላ ተገድለው በጉድጓድ ውስጥ ተጥለው ተገኝተዋል።

አሁንም ሴንትራል፣ ዶሮ እርባታ፣ በረኸት በሚባሉ አካባቢዎች ላይ አሠሳ እየተደረገ እንደሚገኝ እና ቁጥሩ እንደሚጨምር የማይካድራ ነዋሪዎች ገልጸውልናል።

በዚህ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳታፊ ናቸው የሚባሉት ተጠርጣሪዎች በብዛት ሱዳን ሐሻባ በሚባል የስደተኞች መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ ይነገራል።

ከዚህ በተጨማሪ በማይካድራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ ተሳታፊ ናቸው በሚል ተጠርጥረው ከተያዙት 60 ግለሠቦች ውስጥ 17ቱ በቀጥታ የወንጀሉ ተሳታፊ መሆናቸውን የማይካድራ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ገልጾልናል።

ትህነግ በወልቃይትና አካባቢው ተወላጆች ላይ በአስር ሽህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ገድሏል፤ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ደግሞ ከአካባቢያቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል፡፡

ምንጭ: አብመድ

የእግር ኳሱ ኮከብ አረፈ!— — — — — — —አርጀንቲናዊው የዓለም የእግር ኳስ ኮከብ ዲዬጎ አርማንዶ ማራዶና ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። በቅርቡ 60ኛ ዓመቱን የያዘው የእግር ኳስ ኮከቡ ...
11/25/2020

የእግር ኳሱ ኮከብ አረፈ!
— — — — — — —

አርጀንቲናዊው የዓለም የእግር ኳስ ኮከብ ዲዬጎ አርማንዶ ማራዶና ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

በቅርቡ 60ኛ ዓመቱን የያዘው የእግር ኳስ ኮከቡ ማራዶና ከሳምንታት በፊት የጭንቅላት ውስጥ የደም መርጋት አጋጥሞት ሀኪሞቹ እንዳሉት የተሳካ የቀዶ ህክምና ተደርጎለታል።

በሆስፒታል የነበረውን ህክምና ጨርሶ በመኖሪያ ቤቱ በክትትል ላይ እንዳለ በድንገተኛ የልብ እክል ዛሬ ህይወቱ ማለፉ ተወርቷል።

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫStatus update on #COVID19Ethiopia
11/23/2020

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ

Status update on #COVID19Ethiopia

በትግራይ ክልል የተጀመረው ህግን የማስከበር ዘመቻ ወደ ሶስተኛውና የመጨረሻው ምዕራፍ መሸጋገሩን ጠ/ሚ ዐቢይ ተናገሩ— — — — — — — —የተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች፣በትግራይ ክልል የጀ...
11/22/2020

በትግራይ ክልል የተጀመረው ህግን የማስከበር ዘመቻ ወደ ሶስተኛውና የመጨረሻው ምዕራፍ መሸጋገሩን ጠ/ሚ ዐቢይ ተናገሩ
— — — — — — — —

የተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች፣

በትግራይ ክልል የጀመርነው ሕግን የማስከበር ርምጃ ሁለተኛ ምእራፍ ተጠናቅቋል። አሁን በመጨረሻውና በሦስተኛው ወሳኝ ምእራፍ ላይ እንገኛለን።

እየወሰድን ያለነው ሕግን የማስከበር እርምጃ ሦስት ምእራፎች እንዳሉት ቀደም ብለን የገልጸን ሲሆን፤ የመጀመሪያው ምእራፍ፥ በገዛ ወገኑ የተጠቃውን የመከላከያ ሠራዊታችንን አሰባስበንና አጠናክረን፣ ተቋርጦ የነበረውን የእዝ ሰንሠለቱን ወደ ቦታው መልሰን ግዳጁን እንዲወጣ ማስቻል ነበር። በዚህም መሠረት ሠራዊቱ በከፍተኛ እልህ፣ ቁጭትና ወኔ ከገጠመው አደጋ በፍጥነት አገግሞ፣ የሕዝቡን ከፍተኛ ድጋፍ በልቡ ይዞ የሀገር ክህደት የፈጸመውን የሕወሐት ቡድን ለሕግ ለማቅረብ በተለያዩ አቅጣጫዎች ተንቀሳቅሷል።
የርምጃው ሁለተኛ ምእራፍ ዋና ዓላማ፥ የሕወሐትን ጁንታ ከየአካባቢው እያስለቀቀ፣ ዐቅሙንም ከጥቅም ውጭ እያደረገ፣ ሕዝቡን ከዚህ የክህደት ቡድን ይዞታ ነጻ በማድረግ፣ የመሸገበትን የመቀሌ ከተማ መክበብ ነበር። ከመቀሌ ውጭ ያለውን ሕወሃት የያዘውን ቦታ ነጻ በማውጣት፤ የተዘረፉ ትጥቆችንና ካምፖችን መልሶ በመያዝ፤ የክህደት ቡድኑ የዘረፋቸውን ስትራቴጂያዊ የሆኑ መሣሪያዎችን ለውድመት ሳያውላቸው በፊት ከጥቅም ውጭ ማድረግ፤ በግዳጅ የያዛቸውን የሠራዊታችን አባላት ማትረፍ፤ የተሠውትን መቅበር እና አደጋ የሚደርስባቸውን ዜጎች መታደግ የሁለተኛው ምእራፍ እርምጃ ዝርዝር ዓላማዎች ነበሩ።

በዚህ መሠረት በዳንሻ፣ በሑመራ፣ በሽሬ፣ በሽራሮ፣ በአክሱም፣ በአድዋ፣ በአዲግራት፣ በአላማጣ፣ በጨርጨር በመሖኒ፣ በኮረምና በሌሎችም ቦታዎች በተወሰደ ርምጃ ሠራዊታችን ሕዝብ እየታደገና ድል እያደረገ ተጉዟል። ሕዝብ ለመታደግ በነበረው ዓላማ በተቻለ መጠን ሕግ የማስከበር እርምጃው በከተሞች አካባቢ ጥፋት እንዳያስከትሉ እና ሰላማዊ ዜጎች ዒላማ እንዳይሆኑ፤ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የሃይማኖት ቦታዎች፣ የሕዝብ መገልገያዎች፣ መሠረተ ልማቶች፣ የተፈጥሮ ሀብቶችና የመሳሰሉት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳይደርስባቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል። ምንም እንኳን የክህደት ቡድኑ የጥፋቱ ደረጃ ሰፊ እንዲሆን ቢፈልግም፥ በሕግ ማስከበር እርምጃችን ወቅት፥ የአየር ኃይል አውሮፕላኖቻችን ለሕዝቡ በነበራቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ፣ ወደ ዒላማዎቻቸው የቀረበ አንድም ሰው እንኳን ከገጠማቸው የታጠቁትን ትጥቅ ይዘው እስከ መመለስ ደርሰዋል።

በዚህም፥ ምንም ዓይነት ኃላፊነት የማይሰማው ቡድኑ በሃይማኖት ተቋማትና በቅርሶች አካባቢ ተኩስ እንዲኖር የነበረውን ፍላጎት፣ በሠራዊቱ ተልዕኮን በጥበብ የማከናወን ችሎታ አማካኝነት የቡድኑ ፍላጎት ሊመክን ችሏል። ነጻ በወጡ አካባቢዎች በሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት ሕዝቡን መልሶ እንዲደራጅ፣ በመከላከያ ሠራዊቱ አማካኝነት የተጎዱ ወገኖቻችን እንዲደገፉ፣ ሕዝቡ የተፈጸመውን ነገር በትክክል እንዲረዳና ራሱን የሂደቱ አካል ለማድረግ ተችሏል። የተበላሹና የተበጣጠሱ ማኅበራዊ ተቋማትን፣ የመገናኛና የትራንስፖርት መሠረተ ልማቶችን በመጠገን፣ ሕዝቡ የሰላም አየር መተንፈስ ጀምሯል።
ሁለተኛው የርምጃው ምእራፍ ሕዝቡን የታደገ፣ የጁንታውን አከርካሬ ሰብሮ አቅሙን ወደ መቀሌ ማጥበብ ተችሏል።

አሁን የቀረው ጉልበት መቀሌ ላይ ያደራጀው ምሽግ እና አልፎ አልፎ የሚያሰማው ከንቱ ፉከራ ነው። በዚህ ሕግን የማስከበር እርምጃ ወቅት ሕዝባችን ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን መሆኑን በግልጽ አሳይቷል። ሕወሃት ስለ መከላከያ ሠራዊቱ የነዛው ፕሮፓጋንዳም ስሕተት መሆኑን የትግራይ ሕዝብ በዓይኑ ለማየት ችሏል። የሠራዊቱን ደግነትና ከጥፋት ለመታደግ የከፈለውን መስዕዋትነት ሕዝቡ ራሱ መመስከር ጀምሯል። በየአካባቢው ከዕለት ጉርሱ እየቀነሰ ለሠራዊቱ በማብላት፣ የክህደት ቡድኑ የሚሄድባቸውን መንገዶች በመጠቆም፤ የተደበቁ መሣሪያዎችንና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን በማጋለጥ ከሠራዊቱ ጎን ሆኖ የሚያስደንቅ ተጋድሎ ፈጽሟል። በዚህም የትግራይ ሕዝብ ቀድሞም በሕወሃት የጥፋት መንገድ ምን ያህል እንደተንገሸገሸ በግልጽ አሳይቷል።

ሠራዊቱ ሽሬ በገባበት ጊዜ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ በሆታ ከመቀበሉም በላይ፣ ጁንታው ያስታጠቀውን ከ200 በላይ መሣሪያ ሰብስቦ ለመከላከያ አስረክቧል። ሠራዊታችን አክሱም በደረሰም ጊዜ ሕዝቡ ራሱ በክህደት ቡድኑ ቁጥጥር ሥር የዋሉ የሠራዊት አባላትን ነጻ አድርጎ፣ የቆሰሉትን አክሞና ተከባክቦ፣ በክብር ለመከላከያ ሠራዊቱ አስረክቧል። የአክሱም ሕዝብ የመከላከያ ሠራዊቱ ከእርሱ ጋር እንዲሆን ከመጠየቁም በላይ አብሮ ተሠልፎ የሕግ ማስከበሩ ዳር እንዲደርስ ቁርጠኝነቱን አሳይቷል። በተመሳሳይ ሠራዊታችን አዲግራት ሲገባ፣ ሕዝቡ ራሱ የተደበቁትን የልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት እየያዘ ለመከላከያ አስረክቧል።

በተቃራኒው የቆመው የክህደት ቡድን ስንትና ስንት የሀገር ሀብትና ጉልበት የፈሰሰባቸውን መሠረተ ልማቶችን እያፈረሰ፣ ትምህርት ቤቶችንና የጤና ተቋማትን ከጥቅም ውጭ እያደረገ፣ መንገዶችና ድልድዮችን እየደረማመሰ ሸሽቷል። የታሪካዊቷ አክሱም የአውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጭምር ውድመት በማድረስ የቀጣይ ዓመታት የቱሪዝም እንቅስቃሴያችን ላይ ከፍተኛ ጠባሳ ጥሎ አልፏል። የክልሉ ነዋሪ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ የሚያደርግባቸውን መንገዶች በዶዘር ማፈራረሱ ሳይበቃው፥ የመቀሌ ከተማን ልክ እንደ ጦርነት አውድማ ለማድረግ በመዛት ቅንጣት ታህል ኃላፊነት የማይሰማው መሆኑን በግልጽ አሳይቷል።

ውድ ኢትዮጵያውያን፣
አሁን ሕግ የማስከበር ርምጃው ወደ ሦስተኛውና ወሳኙ ምእራፍ ተሸጋግሯል። ሦስተኛው ምእራፍ በመቀሌ የሚካሄደውና የክህደት ቡድኑን ለሕግ ለማቅረብ የሚደረግ የመጨረሻው እርምጃ ነው። የዚያኑ ያህል ከፍተኛ ጥበብ፣ ጥንቃቄና ትእግሥት የሚፈልግ እንደሆነ ግልጽ ነው።

ይህ የክህደት ቡድን ለምንም ነገር ደንታ እንደሌለው፥ ለሕዝቡ፣ ለታሪኩ፣ ለባህሉ፣ ለቅርሱና ለእምነቱ ቅንጣት ርኅራሄ እንደሌለው በግልጽ አሳይቷል። ሁሉም ነገር ጠፍቶ እርሱ ብቻ ቢተርፍና ከሕግ ቢያመልጥ ደስተኛ ነው። በዚህም የተነሣ በመቀሌ ከተማ ውስጥ የሃይማኖት ተቋማትን፣ ሆቴሎችን፣ የመንግሥት ተቋማትን፣ የሕዝብ መኖሪያ መንደሮችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ቅርሳ ቅሶችንና መካነ መቃብሮችን ሳይቀር እንደ ምሽግ ተጠቅሞባቸዋል። መጥፋቱ ላይቀር ብዙዎችን ይዞ ለመጥፋት ተዘጋጅቷል። ልክ በአንዳንድ ሀገራት እንደሚታዮት የሽብር ቡድኖች፣ ለሕዝብና ለሀገር ምንም ደንታ የሌላቸው አሸባሪዎች እንደሚያደርጉት ሁሉ፣ ይሄ የጥፋት ቡድን መቀሌን እንደ ሕዝብ መኖሪያነት ሳይሆን እንደ ጦር አውድማነት ቆጥሯታል።
በዚህ ቡድን ምክንያት እንዲሞቱ የተገደዱት ነዋሪዎች ዜጎቻችን እንደመሆናቸው መጠን እና የሚወድመውንም ከተማ ነገ መልሶ ለመገንባት ዞሮ ዞሮ የእኛው ኃላፊነት እንደመሆኑ መጠን በመቀሌ የሚኖረን የሕግ ማስከበር ርምጃችን፥ ጉዳትን እጅግ በቀነሰ መልኩ መከናወን እንዳለበት እናምናለን። ስለዚህም፥ የመቀሌ ከተማን ከከፋ ጉዳት ታድገን ዘመቻውን በድል የምናከናውንበትን መንገድ እንደምንከተል ለመግለጽ እወዳለሁ። መንግሥት ይሄንን የሚያደርገው በዚህ የክህደት ቡድን የተነሣ ሕዝብና ሀገር እንዳይጎዳ ከመፈለግ ነው።

በመሆኑም፤
አንደኛ፡- የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች፥ በጀመርነው ሕግን የማስከበር እርምጃ ቁልፍ ተዋናዮች እንድትሆኑ፣ ከሠራዊታችን ጎን በመቆም ይሄንን የክህደት ቡድን አባላት ለፍርድ በማቅረብ ወሳኝ ሚናችሁን እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን። ለጥቂት ስግብግብ ጁንታዎች ሲባል አንድም ሰው መሞት፣ አንዲትም ንብረት መውደም የለበትም።
ለዚህም የእናንተ ትብብር አይተኬ ሚና የሚጫወትና ብዙ ጉዳቶችን እንደሚያቀል እሙን ነው።

ሁለተኛ፡- የክህደት ቡድኑን ዓላማ በማስፈጸም ላይ ያላችሁ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት፥ አሁንም ቢሆን እጃችሁን በሰላም ለመስጠት ጊዜው አልረፈደም። ሕግ የማስከበር እርምጃው የመጨረሻ ምእራፍ ላይ መሆናችንን ተረድታችሁ የማያዳግመውን ዕድል እንድትጠቀሙበት፤ ከአሁኗ ሰዓት ጀምሮ ባለው በ72 ሰዓታት ውስጥ እጃችሁን በሰላም ለመንግሥት እንድትሰጡ የመጨረሻ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።

ሦስተኛ፡- የጁንታው አባላት፥ የጥፋት ጉዟችሁ ጀንበሯ እየጠለቀች መሆኑን አምናችሁ፣ ከማትወጡበት ቅርቃር ውስጥ መግባታችሁን ተገንዝባችሁ በቀጣይ 72 ሰዓታት ውስጥ እጃችሁን በሰላም እንድትሰጡ እንጠይቃችኋለን። የመጨረሻዋን ዕድል ተጠቀሙበት። ተጨማሪ የሕዝብ እልቂት ከመፍጠርና ከተማ ከማውደም ተቆጥባችሁ ከታሪክ ውግዘት እንድትድኑ ጥሪ እናቀርባለን።

በመጨረሻም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲረዳው የምንፈልገው ነገር ቢኖር ሦስተኛውን ምዕራፍ የሕግ ማስከበር እርምጃ ከማከናወን ጎን ለጎን በጥፋት ቡድኑ ምክንያት ቀያቸውን ጥለው ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሸሹ ወገኖቻችንን ለመመለስ፤ የተፈናቀሉትን መልሶ ለማቋቋም፤ መሠረተ ልማቶችን ለመጠገን፤ ነጻ የወጡ አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ዜጎች ወደ መደበኛ የሕይወት እንቅስቃሴያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ በሁሉም ረገድ ዝግጅት አድርገናል። ወደ ትግበራ ስንገባ ከእጃችን እንዳያጥር እና ዐይናችንን ወደ ሌሎች እንዳናማትር ሁሉም ኢትዮጵያዊ የበኩሉን ድጋፍ ለማድረግ እንዲነሳ ጥሪ እናቀርባለን። እኛ ኢትዮጵያውያን የቆየና የዳበረ እርስ በእርስ የመረዳዳት ባህል ስላለን፣ የማንንም የውጭ እጅ ሳንጠብቅ ወገኖቻችንን እኛው ልናቀዋቁማቸው ይገባል። ለዚህም በመንግሥትና በተለያዩ የማኅበረሰብ አንቀሳቃሾች አማካኝነት የተጀመረውን እንቅስቃሴ እንድትቀላቀሉ ስል ጥሪ አቀርባለሁ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራ፣ ተከብራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ኅዳር 13 ቀን 2013 ዓ.ም

ከህዳር 22 ጀምሮ በአሮጌው የብር ኖት ግብይት መፈፀም ይቆማል— — — — — — — —የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።...
11/19/2020

ከህዳር 22 ጀምሮ በአሮጌው የብር ኖት ግብይት መፈፀም ይቆማል
— — — — — — — —

የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።

ከህዳር 22 ጀምሮ ደግሞ በአሮጌው የብር ኖት ግብይት መፈጸም አይቻልም ብሏል።

ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት በሚቀረው 25 ቀን ውስጥ ወደ ባንክ በመሄድ አሮጌውን ብር በአዲስ መቀየር የሚቻል ሲሆን ከህዳር 22 ጀምሮ ግን በአሮጌው ብር ግብይት መፈፀም ይቆማል ተብሏል።

11/18/2020

የማምለጫ መንገዱ ሁሉ የተዘጋጋ ነው

“ስደተኛ መስለው በእግር መውጣቱን ደግሞ ሽማግሌዎች ስለሆኑ አይችሉትም”

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ

የአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ 76 ጄነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እና የበታች ሹማምንቶች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጣ— — — — — — — —ምንጭ: ኢቢሲ
11/18/2020

የአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ 76 ጄነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እና የበታች ሹማምንቶች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጣ
— — — — — — — —

ምንጭ: ኢቢሲ

11/13/2020

ዛሬ ምሽት 5:00 ሰዓት ገደማ በባህር ዳር መኮድ እና በጎንደር አዘዞ አካባቢ በተቀራራቢ ሰአት መለስተኛ ፍንዳታ እንደተፈፀመ የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ሰአት ሁሉም ነገር ሰላም ነው።

የጠላት ኃይል ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ የሽብር ስራ እየሰራ ስለሆነ ጦርነት ውስጥ ያለን መሆኑ ታውቆ ህብረተሰቡ ተረጋግቶ እራሱንና አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ የክልሉ መንግስት አሳስቧል፡፡

በቀጣይም ተመሳሳይ ድርጊቶች ሊፈፀሙ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ በሁሉንአቀፍ መንገድ ራሱን እና አካባቢውን እንዲጠበቅ የክልሉ መንግስት ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

Source: Amhara Mass Media Agency

በፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት በትግራይ ብሔራዊ ክልል የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ማጽደቁ ይታወሳል። በጸደቀው ደንብ መሠረት ዶ/ር ሙሉ ነጋ...
11/13/2020

በፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት በትግራይ ብሔራዊ ክልል የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ማጽደቁ ይታወሳል። በጸደቀው ደንብ መሠረት ዶ/ር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሰይመዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል ሆነው፣ የክልሉን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትን የሚመሩ ኃላፊዎችን፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመመልመል ይሾማሉ።

ከጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የፌስቡክ ገፅ

11/12/2020
PM Abiy Ahmed

We are confident!

In a relatively short period of time,we will accomplish our objectives.

በሕገ-ወጥ ተግባር ውስጥ በመገኘታቸው እንዲታገዱ የተወሰነባቸው የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች— — — — — — — —የኢፌዴሪ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳለው አንዳንድ የግል የጥበቃ ኤጀንሲዎች የተቋቋሙበትን...
11/12/2020

በሕገ-ወጥ ተግባር ውስጥ በመገኘታቸው እንዲታገዱ የተወሰነባቸው የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች
— — — — — — — —

የኢፌዴሪ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳለው አንዳንድ የግል የጥበቃ ኤጀንሲዎች የተቋቋሙበትን የመንግሥት እና የግል ተቋማትን የመጠበቅ ዓላማን ወደ ጎን በመተው ከቀጠሯቸው የጥበቃ አባላት መካከል ለሌላ እኩይ ተግባር የመረጧቸውን በመመልመል፣ ለተቋም ጥበቃ የተሰጣቸውን የጦር መሣሪያ በማስታጠቅ እና በማሰማራት በሕዝብ እና በመንግሥት ተቋማት እንዲሁም በተለያዩ አካላት ላይ ጥቃት ለመፈፀም እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተደርሶበታል።

ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎቹ በቀጠሯቸው የጥበቃ አባላት እና ተባባሪዎቻቸው ባንኮችን እና የተለያዩ ድርጅቶችን ሲዘርፉ እና ሲያዘርፉ መቆየታቸውንም በአብነት ጠቅሷል።

በዚህም ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ እና ንብረት መዝረፋቸውን እና እንዲዘረፍም ማድረጋቸውን ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም ተቋማቱን እንዲጠብቁበት የታጠቁትን በርካታ የጦር መሣሪያ ይዘው እንደጠፉም ተረጋግጧል ብሏል።

እነዚህ ከተልዕኮአቸው ውጭ እንደሚንቀሳቀሱ የተደረሰባቸው የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች ይህም አልበቃ ብሏቸው አሁን ባለው ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ በህወሓት የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈፀም የተለያዩ ግለሰቦችን ወደ ኤጀንሲዎቹ አስርገው በማስገባት እና የጦር መሣሪያ በማስታጠቅ በኅብረተሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እያሴሩ መሆኑ ነው ፌዴራል ፖሊስ የገለጸው።

በመሆኑም ከታች የተዘረዘሩት የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች፦

1. ንስር የሰው ሃይል እና የጥበቃ አገ/ሃ/የተ/የግ/ማ

2. አጋር የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ

3. ስብኃቱና ልጆቹ የንብረት አስ/ጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ

4. ሰላም ሴኩሪቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማ

5. ኃይሌ ተክላይ እና ጓደኞቻቸው የጥበቃ አገልግሎት ህ/ስ/ማ

6. ክፍሌ ጎሳዬ ሃጎስ እና ወ/ገብርኤል የጥበቃ አገልግሎት ሽርክና /ማ

7. ዮናስ፣ ሮዛ እና መብርሂት የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሽ/ማ

8. ሃየሎም እና ብርሃኔ የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሸ/ማ

9. ደመላሽ፣ ሃፍቱ እና ጓደኞቻቸው የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሸ/ማ

10. ህሉፍና ሃለፎም የጥበቃ አገ/ህ/ሽ/ማ

11. ዋልታ የጥበቃ የሰው ኃይልና ኮሚሽን ኃ/የተ/የግ/ማ

12. ሴፍ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ

13. አትላስ ጠቅላላ አገ/ኃ/የተ/የግ/ማ

14. ጎህ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ

ለሀገር እና ለዜጎች ሰላም እና ደህንነት ሲባል ሥራቸውን እንዲያቆሙ የተወሰነና እስከአሁን ባለው ሀገር የማተራመስ እና ሕገ-ወጥ ሥራቸው በህግ የሚጠየቁ መሆኑን ገልጿል።

ስማቸው የተገለጸው የጥበቃ ተቋማት በአስቸኳይ ሥራቸውን አቁመው ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሪፖርት እንዲያደርጉም አሳውቋል።

በተጨማሪም ማንኛውም የግልም ሆነ የመንግሥት አካል ከነዚህ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች ምንም ዓይነት ቅጥር እንዳይፈፅም የተከለከለ መሆኑን አሳስቧል።

በመጨረሻም የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎቹ ስር ተቀጥረው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ያሉ ሠራተኞችን በተመለከተ ተገቢውን ልየታ በማድረግ ማስተካከያ እስኪወሰድ ድረስ በተመደቡበት ቦታ የጥበቃ ሥራቸውን አጠናክረው እንዲሠሩ እና የሚጠብቋቸው የግል እና የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎችም በተሰጠው መግለጫ መሠረት ተገቢውን ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርጉ ሆኖ የዕለት ተዕለት ሥራቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የጦር መሣሪያ ቁጥጥርና የግል ጥበቃ ተቋማት ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ሪፖርት በማድረግ ቀጣይ በሚሰጡ የሥራ መመሪያዎች ብቻ ሊሠሩ እንደሚገባ አሳስቧል።

Address

45555 Hutchens Sq Sterling VA
Sterling, VA
20166

Telephone

+16469824943

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sebez media - ሰበዝ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Sebez media - ሰበዝ ሚዲያ:

Videos

እኛ !

ሀገራችንን ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ወሬዎችን በፍጥነት እና በትጋት ለእናንተ ለማቀበል ይንን ገጽ ከፍተናል፡፡ወዳጆቻችን ይሁኑ!

Nearby media companies


Other Media/News Companies in Sterling

Show All