Today Addis

Today Addis Digital creator, Entertainment, News Media

ህወሓት መቀሌ ከተማን ትጥሎ በመፈርጠጡ በመቀሌ ከተማ ዘረፋ አስደንጋጭ ደረጃ ላይ መድረሱ ተሰማ‼️በአሁን ሰአት መምታዩት መልኩ የትግራይ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት እየተዘረፈ ነው።
10/03/2026

ህወሓት መቀሌ ከተማን ትጥሎ በመፈርጠጡ በመቀሌ ከተማ ዘረፋ አስደንጋጭ ደረጃ ላይ መድረሱ ተሰማ‼️በአሁን ሰአት መምታዩት መልኩ የትግራይ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት እየተዘረፈ ነው።

🚨 የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል​የመልካ በሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ...
10/03/2026

🚨 የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል

​የመልካ በሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ ታዳሚዎች በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

​🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦
​የበዓሉ አከባበር ጅምር፦ የበዓሉ ታዳሚዎች ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ወደ በዓሉ ስፍራ በመፌስ የምስጋና እና የባሕል ሥነ-ሥርዓቶችን ማከናወን ጀምረዋል።

​የታዳሚዎች ተሳትፎ፦ በበዓሉ አከባበር ላይ ከተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የአባ ገዳዎች እና የደዳዎች ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ።

​የጸጥታና የእንቅስቃሴ ሁኔታ፦ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የተመደቡ የጸጥታ ኃይሎች በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች አስፈላጊውን ጥበቃ እያደረጉ ይገኛሉ።

​📌 Ankuar News Network

​ #ኢሬቻ

ወደ ኤርትራ ወስደዋቸዋል‼️ጀነራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ 5 ከፍተኛ አመራሮች በሃይል ወደ አስመራ መወሰዳቸው ተገለጸ።በመቐለ ከተማ፣ ላጪ አካባቢ ከሚገኘው «HZ» ሆቴል ታስረው የነበሩት ጀነራ...
10/03/2026

ወደ ኤርትራ ወስደዋቸዋል‼️

ጀነራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ 5 ከፍተኛ አመራሮች በሃይል ወደ አስመራ መወሰዳቸው ተገለጸ።

በመቐለ ከተማ፣ ላጪ አካባቢ ከሚገኘው «HZ» ሆቴል ታስረው የነበሩት ጀነራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ አምስት ከፍተኛ አመራሮች በሃይል ተወስደው ወደ ኤርትራ (አስመራ) መወሰዳቸው ተገለፀ

በሃይል ተወስደዋል የተባሉት ግለሰቦች፦

🚫ጀነራል ታደሰ ወረደ
🚫 ኢሳይያስ ታደሰ
🚫ተወልደ ዕምበብ
🚫ነጋሽ (ሸኾርተት)
🚫 ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር (ሓመድ ሸጠ) ናቸው።

ግለሰቦቹ በላጪ አካባቢ በሚገኘው HZ ሆቴል አንድ ክፍል ውስጥ ታስረው የቆዩ ሲሆን፣ ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ለሁለት ቀናት ያህል ዓድዋ ላይ እንዲቆዩ ተደርገው እንደነበር ታውቋል። ከዛ በመቀጠልም ወደ መቐለ HZ ሆቴል እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን፣ በትናንትናው ዕለት በሆቴሉ ዙሪያ ከፍተኛ የጸጥታ ውጥረት ሰፍኖ ውሏል።

በመጨረሻም በለሊቱ 7:30 ገደማ ታጣቂዎች የሆቴሉን በር በሃይል በመስበር፣ የታሰሩትን አመራሮች በዓዲግራት መስመር አድርገው ወደ ኤርትራ ወስደዋቸዋል ተብሏል።

ሰበር ዜና "የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰአት ከአዲስአበባ ለቃችሁ ውጡ" ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን እንዲዘጋ ወሰነች እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት አዲስአበባ የሚገኘው...
10/01/2026

ሰበር ዜና

"የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰአት ከአዲስአበባ ለቃችሁ ውጡ" ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን እንዲዘጋ ወሰነች እንዲሁም

የኢትዮጵያ መንግስት አዲስአበባ የሚገኘውን የኤርትራ ኤምባሲ ዘጋ። የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰአት ውስጥ ከአዲስአበባ ለቀው እንዲወጡ አዟል።

በአዲስ አበባ እና አካባቢው ከዛሬ ጀምሮ "በየትኛውም አካባቢና ከፍታ" በረራ የሚያካሄዱ ድሮኖችን "በመጥለፍ" እና ወደ ሌላ ቦታ በመውሰድ "የማሳረፍ" እርምጃ እንደሚወስድ የብሔራዊ መረጃና ...
09/30/2026

በአዲስ አበባ እና አካባቢው ከዛሬ ጀምሮ "በየትኛውም አካባቢና ከፍታ" በረራ የሚያካሄዱ ድሮኖችን "በመጥለፍ" እና ወደ ሌላ ቦታ በመውሰድ "የማሳረፍ" እርምጃ እንደሚወስድ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።

መስሪያ ቤቱ የድሮን አብራሪዎችን "ትክክለኛ መገኛ ቦታ በመለየት" እና "በቁጥጥር ስር በማዋል" ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድም አስጠንቅቋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጠው፤ ከዛሬ ጀምሮ "ላልተወሰነ ጊዜ" በአዲስ አበባ እና አካባቢው ማንኛውንም አይነት ድሮን ለማብረር "ፍቃድ እንደማይሰጥ" ባስታወቀበት መግለጫው ነው፡፡ ዛሬ ረቡዕ መስከረም 20፤ 2019 ማምሻውን የወጣው የመስሪያ ቤቱ መግለጫ፤ በአዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ከተሞች የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ከመከናወኑ ሁለት ቀናት በፊት የተሰጠ ነው።

በ2014 ዓ.ም የተሻሻለው የመስሪያ ቤቱ ማቋቋሚያ አዋጅ፤ "የመሪዎችን፣ የቁልፍ መሰረተ ልማቶችን እና ብሔራዊ ኩነቶችን ደህንነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የማስጠበቅ ኃላፊነት" ለአገልግሎቱ ይሰጣል። አገልግሎቱ ለድሮን በረራዎች ይሰጥ የነበረውን ፍቃድ "ላልተወሰነ ጊዜ" ያቋረጠው እና የበረራ ክልከላውን ተግባራዊ ያደረገው ይህንኑ ኃላፊነቱን ለመወጣት እንደሆነ አስታውቋል።

🙏 ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ክብሩን ይውሰድ!መስከረም 20፣ 2019 ዓ.ም.  | የተከበረው የአዲስ አበባ ሕዝብ በሰባተኛው (7ኛው) ሀገራዊ ምርጫ የሌሊት ብርድና የቀን ሐሩር ሳይበግረው መርጦ...
09/30/2026

🙏 ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ክብሩን ይውሰድ!

መስከረም 20፣ 2019 ዓ.ም.

| የተከበረው የአዲስ አበባ ሕዝብ በሰባተኛው (7ኛው) ሀገራዊ ምርጫ የሌሊት ብርድና የቀን ሐሩር ሳይበግረው መርጦን፤ እነሆ ዛሬ የሕዝብን አደራ ለመቀበል፣ በታማኝነትና በቅንነት፣ ያለ አድልዎ ለማገልገል በአዲስ አበባ ምክር ቤት ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመናል።

በቀጣይም ለሕዝባችን ቃል በገባነው መሠረት፣ ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ፣ በሥራ ፈጠራና በኪነ ጥበብ ዘርፎች ዙሪያ ከተማችንንና ኢትዮጵያውያንን በሚመጥን መልኩ፣ በየዘርፉ በቁርጠኝነትና በታማኝነት ለማገልገል እተጋለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ይባርክ! 🇪🇹

አመሰግናለሁ። 🙏🏿

ካሙዙ ካሣ

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሾሙየአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ወ/ሮ አዳነች አቤቤን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አድርጎ ሰይሟል።የአዲስ አበባ ከተማ ም...
09/30/2026

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሾሙ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ወ/ሮ አዳነች አቤቤን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አድርጎ ሰይሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደር መንግሥት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።

መስከረም 20/2019 ዓ›ም

የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ውጤት🇪🇹 ኢትዮጵያ 0-1 ሴኔጋል 🇸🇳
09/29/2026

የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ውጤት

🇪🇹 ኢትዮጵያ 0-1 ሴኔጋል 🇸🇳

በእሬቻ ዋዜማ በአድዋ ድል መታሰብያ ሙዚየም ታላቅ የቦክስ ፍልምያ ሊደረግ ነው  | የኢትዮጵያን የቦክስ ስፖርት ጥራትና ደረጃ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ታላቅ የቦክስ ውድድር በእሬቻ ...
09/28/2026

በእሬቻ ዋዜማ በአድዋ ድል መታሰብያ ሙዚየም ታላቅ የቦክስ ፍልምያ ሊደረግ ነው

| የኢትዮጵያን የቦክስ ስፖርት ጥራትና ደረጃ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ታላቅ የቦክስ ውድድር በእሬቻ ዋዜማ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።

ውድድሩ አፍሮኮ ትሬዲንግ እና ኤች.ኬ. ኢንተርቴይንመንት ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል።

በዚህ ውድድር ከፌዴራልና ከኦሮሚያ ክልል ክለቦች የተውጣጡ 16 ምርጥ ቦክሰኞች ከ48 እስከ 80 ኪሎ ግራም በሚደርሱ የክብደት ዘርፎች ፍልሚያ ያደርጋሉ።

በዚህ ውድድር የሚሳተፉት ወርቅነሽ ዋቅጅራ፣ ነጌኛ ታደሰ፣ ኮንስታብል ሳምሶን ጌታቸው እና እሱባለው ሞላ ከሳምንት በኋላ በኬንያ በሚካሄደው የአፍሪካ የቦክስ ውድድር ሀገራቸውን ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ ይሆናል።

የተወዳዳሪዎቹን ብቃት ለማሳደግ ከ3 ወራት በላይ ከፍተኛ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየው ይህ ታላቅ መድረክ፤ ዓርብ ምሽት ከ12:00 ሰዓት እስከ እኩለ ሌሊት 6:00 ሰዓት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አዳራሽ ይካሄዳል።

የመግቢያ ትኬት በአዋሽ ባንክ በኩል በቀላሉ ለመግዛት የሚያስችል አሰራር እየተመቻቸ ይገኛል ሲሉ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ፎቶ፦ ከበደ መክብብ

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

በመስከረም 3 ተዋውቀው ልክ በአንድ ዓመት ከሰባት ቀናቸው ትዳራቸውን የመሰረቱት ጥንዶች፣ አራትና አምስት ዓመት «እንጠናናለን» ለሚሉ ወጣቶች ያስተላለፉት መልዕክት! 💍ብዙ ወጣቶች "እንጠናና...
09/27/2026

በመስከረም 3 ተዋውቀው ልክ በአንድ ዓመት ከሰባት ቀናቸው ትዳራቸውን የመሰረቱት ጥንዶች፣ አራትና አምስት ዓመት «እንጠናናለን» ለሚሉ ወጣቶች ያስተላለፉት መልዕክት! 💍ብዙ ወጣቶች "እንጠናናለን" በሚል ሰበብ አራት እና አምስት ዓመታት በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ሲቆዩ ማየት የተለመደ ሆኗል። ነገር ግን የተወዳጁ መምህር መጋቢ አዲስ (ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ) እና የባለቤታቸው ወ/ሮ ሳምራዊት የጋብቻ ታሪክ ለብዙዎች ትልቅ ትምህርት የሰጠ ሆኗል።

ሁለቱ ጥንዶች የተዋወቁት ባለፈው ዓመት መስከረም 3 ቀን ሲሆን፣ ልክ በአንድ ዓመት ከሰባት ቀናቸው ትዳራቸውን በይፋ መስርተዋል። ይህን ያዩ እና ለአራት ዓመታት በፍቅር ውስጥ የቆዩ አንዳንድ ወጣቶች "አንድ ዓመት ሰውን ለማጥናት ከበቂ በላይ ነው፣ ለምን አራት ዓመት እንጠብቃለን?" በማለት ዘንድሮ ትዳር ለመያዝ እንደወሰኑ ተነግሯል።

ዶ/ር ሮዳስ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት በአጋጣሚ አልነበረም። ከዚህ ቀደም "ለምን አትመነኩስም?" አሊያም "ለምን አታገባም?" የሚሉ ብዙ ጫናዎች ነበሩባቸው። እሳቸው ግን "ድርሰቴን አግብቼ እኖራለሁ" በሚል ሃሳብ ጸንተው ነበር። ነገር ግን አምና የፍልሰታን ጾም ሱባኤ እንደጨረሱ፣ የምንኩስና ሕይወት ለእሳቸው እንዳልተፈቀደ ተረዱ። ይህ በተገለጠላቸው በጥቂት ጊዜ ውስጥ ነው እንግዲህ "የተባረከ ሰው ስጠኝ" እያለች ስትጸልይ ከነበረችው ሳምራዊት ጋር አዲስ ዓመት በገባ በመስከረም ወር የተገናኙት።

ዶክተሩ ጋብቻን ከተፈጥሮ እና ከስነ-ፈለግ ጥበብ ጋር አያይዘው ሲያብራሩት እጅግ ያስገርማል። በሳቸው እይታ ወንድ ልጅ እንደ ሰማይ እና ፀሐይ (ብርሃንና ዝናብ ሰጪ) ሲሆን፣ ሴት ደግሞ እንደ ምድር እና ጨረቃ (ተቀባይ እና አብቃይ) ናት። የሴት ልጅ የወር አበባ ዑደት እንኳን ከጨረቃ አራት ክፍሎች ጋር ቀጥታ ቁርኝት እንዳለው እና በ14ኛው ቀን ሙሉ ጨረቃ ስትወጣ በሴቶችም ማህፀን እንቁላል እንደሚወርድ በማብራራት የተፈጥሮን ድንቅ ሚስጥር አጋልጠዋል።

ሌላው ትልቁ ትምህርት ደግሞ ከማህበራዊ ሚዲያ ጫጫታ ራሳቸውን ያገለሉበት መንገድ ነው። ሰርጋቸውን ተከትሎ በቲክቶክ መንደር በባለቤታቸው ስም የሐሰት አካውንቶች ሲከፈቱ፣ ዶክተሩ ግን "የሶሻል ሚዲያ አስተያየቶችን በፍፁም አላነብም! ምክንያቱም ውዳሴው ትዕቢተኛ ያደርገኛል፣ ሃሜቱ ደግሞ ተስፋ ያስቆርጠኛል" በማለት በሥራቸው እና በትዳራቸው ላይ ብቻ ትኩረት አድርገዋል።

በመጨረሻም "እውነተኛ ፍቅር ካለ ለባል እና ሚስት ዘጠኝ እንጀራ ይበቃል" በማለት፣ አንዱ ለአንዱ እያጎረሰ ሳይታወቃቸው በፍቅር የሚበሉበት ሞቅ ያለ ትዳር እንዲኖረን መክረዋል።

የእነዚህ ጥንዶች ፈጣን እና በሳል የትዳር ጉዞ "እንጠናናለን" እያሉ ዓመታትን ለሚያጠፉ ወጣቶች ትልቅ የማንቂያ ደወል አይደለም ትላላችሁ? አስተያይታችሁን አካፍሉን! 👇✨

Address

Takoma Park, MD
20912

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Today Addis posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Today Addis:

Shortcuts

Share