07/21/2025
ከብዙ ዘመን አይሽሬ ዜማዎች ጀርባ ታላቅ ተግባር የከወኑት ሳህሌ ደጋጎ !
በ1973 ዓም ሻምበል ሳህሌ ደጋጎ ያደረገውን ቃለምልልስ ያዳምጡ https://youtu.be/dGRDrIkv_Cc
https://youtu.be/dGRDrIkv_Cc
https://youtu.be/dGRDrIkv_Cc
ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ በ1923 ዓ/ም በምዕራብ ወለጋ ልዩ ስሙ ነጆ ከተባለው ሥፍራ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በነቀምት አንደኛ ደረጃ እና በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ዘመናዊ ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ በነበረው ልዩ የውትድርና ፍቅር በቀድሞ 1ኛ ክፍለ ጦር በኋላም ማዕከላዊ ዕዝ ተብሎ በተጠራው የክ/ዘበኛ የጦር ክፍል ውስጥ በ1942 ዓ/ም ተቀጥሯል።
በነበረው ሙያዊ ብቃትና ወታደራዊ ሥነ ሥርዓት አክባሪነት ከተራ ወታደርነት በአንድ ጊዜ የሃምሳ አለቅነት ማዕረግ ማግኘት የቻለው ሣህሌ፤ በሂደት እስከ ኮሎኔል ደረጃ ደርሷል። ወደ ሙዚቃ ቀማሪነት፣ ዜማና ግጥም ደራሲነት እንደዚሁም ወደ የማዕከላዊ ዕዝ የሙዚቃ ባንድ ኃላፊነት ከመሸጋገሩ በፊት በእግረኛ ባንድ ውስጥ “ክላርኔት” የተሰኘውን የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዎች የነበረው ሣህሌ ደጋጎ፣ የሙዚቃን ትምህርት የቀሰመው ከፈረንሣዊው መምህሩ ሙሴ ኒኮ እንደሆነ ይነገራል።
ከክላርኔት በተጨማሪ “አኮርዲዮን፣ አልቶ-ሳክስ፣ ፒያኖ” የተሰኙትን የሙዚቃ መሣሪያዎችንም በብቃት ይጫወት ነበር። በጠቅል ራዲዮ ጣቢያ በአኮርዲዮን ጥዑም ዜማ ለጣቢያው አድማጮች ሲያንቆረቁሩ ከነበሩት የሙዚቃ ሰዎች መካከል ሣህሌ ደጋጎ የመጀመሪያው ነበር።
ከእነ ሻለቃ ግርማ ይህደጎ፣ ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ እና ከሻለቃ ባሻ ገብረዓብ ተፈሪ ጋር በመሆን የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራን ስም እፁብ ድንቅ በማድረጉ በኩል የበኩሉን ሚና ተጫውቷል። ግጥምና ዜማ ደራሲ ከመሆኑም ባሻገር የአጫጭር እና ረዣዥም ድራማዎች ፀሐፊ የነበረው ሣህሌ «ሁለገብ የታሪክ ማኅደር» ያሰኘውን ተግባር በሕይወት ዘመኑ አከናውኗል።
ክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ ከተጫወታቸው ሙዚቃዎች ውስጥ “ስቆ መኖር”፣ “እውነት ማሪኝ”፣ የሚሉትን ግጥሞች፣ “ዋይ ዋይ ሲሉ”፣ “ውሸት ለመናገር”፣ “ልብሽን ለአፈርሰው”፣ “ኮቱሜ”፣ የሚሉትን ዘፈኖች ግጥምና ዜማዎች የደረሰው ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ነው፡፡
ከዚህም ሌላ ለድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ “አይወጣኝም ክፉ ነገር” በሚል የዘፈነችውና በብዙኀን ዘንድ ተወዳጅነት ያለውን (“ወደመጣሁበት ምድር፣ እስክመለስባት በክብር፣ ሰውን ከማስደሰት በቀር፣ አይወጣኝም ክፉ ነገር፣ ሙዚቃውን ያቀናበረው ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ ነው።
ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ “ፍላጎቴ”፣ “ምን ነበር”፣ “ምንድነው ትዝታህ”፣ ... የተሰኙትን የብዙነሽ በቀለን ዘፈኖች ያቀናበረ ሲሆን፣ “ከንቱ ሥጋ” የሚለውንና ሌሎችንም ዘፈኖችዋን ግጥም ደርሶላታል። “አታሳየኝ ጭንቁን”፣ “የፍቅር ወጋገን”፣ “ቃልኪዳን”፣ “በብር አይጋዛም”፣ “ፍቅርህ ቀሰቀሰኝ”፣ የተሰኙትን ዜማና ግጥሞች ያዘጋጀው ሣህሌ ደጋጎ ነው፡፡ “ሰው ከተሰማራ” በተሰኘው ዘፈኗ ለምትታወቀው ለድምፃዊት መንበረ በየነ ደግሞ “እንዴት ከረማችሁ” የሚለውን ዘፈን ግጥም የደረሰው ሌ /ኮ /ል ሣህሌ ነበር።
“የቆራጡ መሪ ፍሬው ጎመራ” የተሰኘውንና ለቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ላቀነቀነችው ለድምፃዊት ውብሻው ስለሺ ደግሞ “ይህ ነው ጌትነት”፣ “የምድር ፈተና” የተሰኙትንና በ 1966 ዓ.ም የታተሙትን ዘፈኖችዋን ያቀናበረላት ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ነበር።
በዕድሜ ዘመን የኪነ ጥበብ አገልግሎት የክብር ሜዳሊያ እና የ 20 ሺህ ብር ተሸላሚ የሆነው ሣህሌ ደጋጎ፤ የ 30፣ የ20 እና የ10 ዓመት የረዥም ዘመን አገልግሎት የወርቅ፣ የብርና የነኀስ እንደዚሁም የተዋጊ ወታደርነት የደረት ዓርማ ኒሻን ተሸለሚም ነበር።
ዋይ ዋይ ሲሉ የሚለው ዘፈን የተሰራበት አጋጣሚን አስመልክቶ ሳህሌ ደጋጎ የተናገሩትን ያዳምጡ
https://youtu.be/kXMs4Hl3QNE
https://youtu.be/kXMs4Hl3QNE
https://youtu.be/kXMs4Hl3QNE
በዚህ ቃለምልልስ ላይ ሻምበል የነበሩት በኋላም ኮሎኔል የሆኑት የሙዚቃ ሊቅ ሳህሌ ደጋጎ በ1973 ዓም ከጋዜጠኛ ኃይሉ አበበ ጋር ያደረገው ቃለምልስሰ። ዋይ ዋይ ሲሉ የሚለው ጥላሁን ገሠሠ የ...