The Republic

The Republic let's be voice for voiceless peoples

07/06/2025

የካሊጉላ ክሊፓች እዚህ ፌስቡክ ላይ እያደኑኝ ተቸገርኩ፣ ዛሬም ሁለት ክሊፓች ገጠሙኝ፣ አሁን ስለአንዱ እናውራ፣ ለሁለተኛው እመለሳለሁ፣

"ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ብቻ ከExport የምታገኝው ገቢ ከ1983 እስከ 1998 (15 ዓመት ጠቅላላ ድምር) በላይ ነው፣ የአስራ-ምስት አመቱ ድምር 7.5 ቢሊየን USD ሲሆን በዚህ ዓመት ብቻ ከ8 ቢሊየን USD በላይ እናገኛለን ብለን እንጠብቃለን፣ በአንድ አመት 8 ቢሊየን ዶላር ማግኝት የምትችል ሀገር 15 ዓመት ሙሉ ምን ትሰራ ነበር ብሎ መጠየቅ ይፈልጋል፣ አዕምሮ ያስፈልጋል" ይላል ካሊጉላ አዕምሮውን በዕጣቱ እየጠነቆለ፣

በዚህ ንግግር ውስጥ አንድ ትልቅ ድንቁርና [እና] አንድ ትልቅ ወንብድና አለ፣ ከድንቁርናው እንጀምር፣

የዚህ ዓመት የውጭ ንግድ ገቢን የዛሬ 20 እና 30 ዓመት ከነበረው ገቢ ጋር ማወዳደር ትልቅ ድንቁርና ነው፣ መወዳደር ካለባቸውም በ Volume እንጂ በዶላር አይደለም፣ ለምሳሌ የዛሬ 25 ዓመት የአለም አቀፍ የቡና ገበያ ዋጋ $0.62/ pound ነበር፣ ዛሬ $4.40/ pound ነው፣ 610% ብልጫ አለው፣ የዛሬ 25 ዓመት የአለም አቀፍ የወርቅ ገበያ ዋጋ $290.25/ ounce ነው፣ ዛሬ $3,331/ ounce ነው፣ 1150% ብልጫ አለው፣ ቀለል ባለ አገላለፅ የዛሬ 25 ዓመት አንድ ኪሎ ወርቅ ተሽጦ የሚገኝው ገንዘብና ዛሬ 100 ግራም ወርቅ ተሽጦ የሚገኝው USD እኩል ነው፣ መልካም የገበያ ሁኔታ (favorable market conditions) የአንድ መንግስት ስኬት ተደርጎ የሚቆጠረው ካሊጉላ ጭንቅላት ውስጥ ብቻ ነው፣ [በነገራችን ላይ በ Volume መወዳደሩ ራሱ አግባብ ነው እያልኩ አይደለም፣ አንድ በህይወት ያለች ሀገር በትንሽ በትንሹም ቢሆን የውጭ ንግድ መጠኗን መጨመሯ ተፈጥሯዊ ነው፣] ...ወደ ውንብድና እንለፍ

ካሊጉላ ከ1983 እስከ 1998 ያለውን ዳታ የፈለገው ለውንብድና እንዲመቸው ነው፣ ለማጭበርበር ነው፣ በተጠቀሱት 15 ዓመታት ከውጭ ንግድ የተገኝ ተብሎ የሚጠቀሰው ከቡና፣ ከቅባት እህል፣ አበባ፣ ጨርቃጨርቅ ወዘተ ሽያጭ የሚገኝውን የውጭ ምንዛሬ ነበር፣ ዛሬ የኢትዮጵያ እየር መንገድ የሚስገኝው የውጭ ምንዛሬ እንደ export ተቆጥሮ ሪፖርት እየተደረገ ነው፣

በ2023 ከውጭ ንግድ የተገኝ ገቢ ተብሎ ሪፓርት የተደረገው 10.8 ቢሊየን USD ነው፣ ከዚህ ቁጥር ውስጥ እንደ ቡና፣ ሻይ፣ የቅባት እህል፣ ቆዳ፣ ወርቅ ወዘተ ተልኮ (Merchandise-Goods Exports) የተገኝው ግን 2.8 ቢሊየን USD ብቻ ነው፣ 7.4 ቢሊየን ብሩ የኢትዮጵያን አየር መንገድ ያስገኝው የውጭ ምንዛሬ ነው፣ የተባበሩት መንግስታት COMTRADE database ውስጥ ገብቶ ሊያረጋግጠው ይችላል፣

የዛሬ 10 ዓመት (i.e 2015 ዓ.ም) ከምርት ንግድ (Merchandise-Goods Exports) የተገኝው 2.91 ቢሊየን USD ነው፣ የዛሬ ሁለት ዓመት ከተገኝው የውጭ ምንዛሬ 100 ሚሊየን USD ብላጭ አለው፣ የአለም ገበያ ዋጋ ልዩነቱን ታሳቢ ካደረግን የዛሬ 10 ዓመት ከውጭ ንግድ የተገኝው ገቢ በካሊጉላ አምስት ዓመታት ከተገኝው በላይ ነው፣ አዕምሮ ያስፈልጋል ነው ያለው?

*** ይህ ሁሉ መፀሐፍ ባለበት ቦታ ድንቁርና እንደ ጎርፍ ሲወርድ ገጥሞኝ አያውቅም፣

#ካሳ

03/06/2025

ኦሮሙማ ማለት እኔነቴ ነው:: ኦሮሞነት ወላጆቼ እናቴ አባቴ ወንድሞቼ: እህቶቼ : ጎረቤቶቼ ናቸው :: ኦሮሙማ ሴቶች ልጆቼ ወንዶች ልጆቼ : አጎት አክስቴ አያት ቅድማያቴ ምንጅላቴ እኔነቴ ባጠቃላይ ቤተሰቤ ነው::

ኦሮሙማ ልጆቼ የልጆቼ ጨዋታ :ተረትና ምሳሌዬ : ሳቅና ለቅሶዬ : ምሳሌያዊ አነጋገሬ : ሂቦ ሂበካዬ : ሰፉ ና ሰርጌ : ለቅሶዬና :ስሜ ነው:: ጉዲፈቻዬ: ኢልመ ጉዲሳዬ: ኢልመ ጎሳዬ: ሴረ ጉማዬ: እርቄ : ምህረቴ ሽምግልናዬ መረባዬ ምርቃቴ :ዱዓዬ: ፀሎቴ እና ቡራኬዬ ነው::

ኦሮሙማ ቀዬና መንደሬ ነው:: ገዳ ስርዓቴ: ቦኩ ምልክቴ : አድባር አምልኮዬ ቃሉና እውነቴ ነው:

ኦሮሙማ አርሲ ጉራቲነቴ :ሲኮ መንዶነቴ : ጉጂ ጉራቲነቴ :ሰደን ቱለማነቴ: ቶርበን ኦቦነቴ: ኢቱነቴ መጨነቴ: አፍረን ቀሎነነቴ : ቦረነ ጉራቻነቴ ሰጎ ጎናነቴ : ወሎነቴ ወረቃሉነቴ : ወረባቦነቴ : ወረ ኢሉነቴ : ቦረናነቴ : የጁነቴ እስልምናዬ ክርስትናዬ: ዋቃን ቡላነቴ ነው:

ኦሮሙማ ሰብዓዊነቴ: ፍትሃዊነቴ: ሃቀኛነቴ ክብሬ እና ኩራቴ ነው:: ኦሮሞነቴ ከብቶቼ : ግመሎቼ: ፈረሶቼ የኑሮዬ መሰረት መስክ እና እርሻዬ ነው::

ኦሮሞነቴ አበየ ወይም ሞርሞር : ሃዋስ : ዋቤ: ገናሌ: ጊቤ: አንገር ደዴሳ: ባሮ ወንዜ የወንዝ ልጅነቴ ነው:: ኦሮሞነቴ ሻላ: አቢጀታ አበያ : ላቂ ሃይቆቼ ነው:: አገሬ ተራራና ወንዜ ነው

ኦሮሙማ : ጫካዎቼ : አበቦቼ : የዱር እንስሳቶቼ ዛፎቼ : ወፎቼ : ክብር ያላቸው ነብሳቴ ማርና ወተቴ የነሱ መብቶች የማከብርበት ስርዓቴ : ህጌ : ሄራ እና ሴራዬ ነው::
ኦሮሙማ ምን አለፋህ ሁለመና ሰላሜ እውነቴ እና የፍጥረት ህጌ ነው:: ህገ አልቦው ኦሮሙማን ጠላቱ አድርጎ ለማጥፋት ምሏል አሉ::

Lola karra gaye abbaa warraa guyyaan gaye.
ተብሏል ::
Maarree Arsii lameen ,Sadeen Tuulamaa , Yaa Maccaa, Boorana - Sabboo Goonaa , Ituu Humbanna, Afran Qalloo, Walloo , Gujii, , Torban Oboo Obboleeyyan too ilmaan gosaa dubbii tanaan maal jenna ree. Si balleessinaa jedhanii walii kakatanii jedhanii deebisaan teenna maal haa taatu. Wal quba haa qabaannu. Haa mari’annu

01/06/2025
26/05/2025

አንድ ዶክተር በመሠረት ሚድያ ኢሜይል በኩል ይህን አጋርቶኝ ማለፍ ከበደኝ! ይነበብ!

"ሰላም ጤና ይስጥልኝ! አንድ ሁሌ የማስበውን ነገር ላጋራችሁ፣ ይህም ምን ያክል የጤና ስርዓታችን እጅግ የወደቀ እና የተበላሸ እንደሆነ ማሳያ ነው።

እኔ በአንድ የሀገራችን ትልቅ ሆስፒታል ሬዚደንት ሀኪም ነኝ። የምንሰራቸው ቀዶ ህክምናዎች አብዛኛውን ጊዜ ረዥም ሰዓት የሚወስዱ ናቸው። አንድ ቀን ግን በጣም ረዥም ሰዓት ነበር የወሰደብን፣ ማለትም 18 ሰዓት ነበር የፈጀው። አስባችሁታል ለ18 ሰዓት ያለ እረፍት ቆመን የረባ ቁርስም ሳንበላ፣ ምሳም እራትም ሳንቀምስ ሌሊት 9 ሰዓት ነበር የወጣነው።

ከዛ ምን እንደፈለግን ታውቃላችሁ በጣም? ከምግብ ይልቅ ውሃ ! ውሃ! ግን ከየት ይገኛል በዛ ሌሊት? የትም! የሰውነታችን ፈሳሽ ስላለቀ ራሱ ከንፈራችን ተሰነጣጥቆ ነበር። እና ታካሚያችንን ወደ ICU ካስገባን በኋላ ትንሽ ጋደም እንበል ብለን ገባን ወደ ዲዩቲ ሩም። ከዛ አንድ ነገር በአእምሮዬ እየተመላለሰ አላስተኛ አለኝ። ምን ዓይነት ጨካኝ ሀገር ላይ ነን ግን? አልኩኝ።
- ካድሬውን በየስብሰባው፣ በየቢሮው 15 ደቂቃም ይሰብሰብ በየጠረጴዛው ቆሎ፣ ውሃ ብፌ ምግብ ቁርጥ ስጋ የሚያቀርብ፣ በቢራ በውስኪ የሚያራጭ እኔንና ጓደኞቼን በጠኔ የሚደፋ

- ይባሱኑ ረብጣ ረብጣ አበል የሚከፍል ለኔና ጓደኞቼ ሲሆን መቀነቱ ባዶ የሚሆን፣ ጉልበቱም የሚደክመው እና ንፉግነቱን የሚያሳየኝ ለምን ይሆን?

-ሌላ ሌላውንስ ውስጡን ለቄስ፣ በእውነት እስኪ ፍረዱኝ ጥያቄዬ የህግም ብቻ ሳይሆን የህሊና ፍርድ ይሻል።

Dr Anonymous

ፎቶ: ፋይል

22/05/2025

(መሠረት ሚድያ)- በአለም ታሪክ ወደ ጠፈር (space) የተጓዙ ሰዎች ቁጥር 721 እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ፣ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ የጠፈር ተመራማሪዎች ሲሆኑ ከቅርብ አመታት ግን ጥቂ.....

20/02/2025

ኤርትራ በአዲስ አበባ ያለውን ኤምባሲዋን እየዘጋች መሆኑ ታወቀ

(መሠረት ሚድያ)- ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ ግንኙነታቸው እየሻከረ የመጣው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግስታት የቃላት ጦርነት መጀመራቸውን ተከትሎ ኤርትራ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ኤምባሲዋን እየዘጋች መሆኑ ታውቋል።

የዛሬ ሰባት አመት ገደማ ግንኙነታቸውን ያደሱት ሁለቱ ሀገራት በትግራይ የተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት ላይ በጋራ ቆመው ቢዋጉም የፕሪቶሪያው ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ ግንኙነቱ መሻከር መጀመሩ ይታወሳል።

"ኤምባሲው ከዚህ በኋላ የአፍሪካ ህብረት ተወካዩን ይዞ ይቀጥላል፣ በኢትዮጵያ ያለውን የኤምባሲ ስታፍ ግን እያሰናበተ ነው" ያሉን አንድ የኤምባሲው ምንጫችን ሂደቱ በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የኤርትራ መንግስት የአፍሪካ ቀንድን የማተራመስ አላማ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው፣ በአስቸኳይ እንዲቆም መደረግ አለበት በማለት አልጀዚራ ላይ በቀረበ ፅሁፋቸው አስነብበው ነበር።

የኤርትራው የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ለዚህ ምላሽ የሰጡ ሲሆን የፕሬዝደንቱን አስተያየት አጣጥለው የኢትዮጵያን መንግስት የቀጠናውን ሀገራት በመተንኮስ ከሰዋል።

የኤርትራ ኤምባሲ መዘጋት መጀመርን ተከትሎ በአስመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እጣ ፈንታ እስካሁን አልታወቀም። ላለፉት ጥቂት አመታት ኤምባሲው ክፍት ቢሆንም አምባሳደር ሳይመደብበት መቆየቱም ይታወሳል።

መረጃን ከመሠረት!

20/02/2025

The chances of asteroid 2024 YR4 colliding with Earth in 2032 hit a record high. Experts expect the risk percentage to fluctuate before likely dropping to zero. Here’s why.

17/02/2025

መንግስት ንብረታቸውን ሊወስድ እየተዘጋጀ መሆኑን አቶ ልደቱ አያሌው አስታወቁ

(መሠረት ሚድያ)- ባሳለፍነው ሰኞ ጠዋት ከአሜሪካ ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ለመጓዝ በአትላንታ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቢገኙም እንዳይሳፈሩ የተደረጉት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው መንግስት ንብረታቸውን ሊወስድ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታወቁ።

ፖለቲከኛው ለበርካታ አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ተቋሟት ዛሬ በፃፉት እና ለመሠረት ሚድያ በቀጥታ ባጋሩት ደብዳቤያቸው ላይ "ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ሀገር መመለስ እንደማልችል በአንድ ስብሰባ ላይ በይፋ ተናግረዋል" ብለዋል።

አቶ ልደቱ አክለውም ወደ ሀገር ቤት እንዳይመለሱ የታገዱት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ወደ ኢትዮጵያ በሚበሩ አየር መንገዶች ጭምር መሆኑን ጠቁመዋል።

"ይህ ድርጊት የሚያሳየው የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ተፃራሪ ድምፆች ለማፈን ቁርጠኛ መሆኑን ነው። እነዚህ ድርጊቶች እየተፈፀሙ ያሉት ካለ ምንም የህግ አግባብ ስለሆነ በግዜው ካልተስተካከለ በርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ ጭምር ሊፈፀም ይችላል" በማለት በደብዳቤያቸው ላይ አስፍረዋል።

አቶ ልደቱ ከኢትዮጵያ ውጪ ሌላ ዜግነት እንደሌላቸው አፅንኦት ሰጥተው በደብዳቤያቸው ላይ ያስረዱ ሲሆን የኢትዮጵያ ህገ-መንግስትም ሆነ ሌሎች የሀገሪቱ ህጎች ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለስ እንደማይችሉ የሚገልፅ ድንጋጌ እንደሌላቸው አንስተዋል።

የአቶ ልደቱ ደብዳቤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን፣ የአፍሪካ ህብረትን፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናልን፣ ሂውማን ራይትስ ዋችን እና የአሜሪካ ኤምባሲን ጨምሮ ለ32 ድርጅቶች የተፃፈ ነው።

"ወደ ሀገሬ መሄድ ማንም ሊከለክለኝ አይችልም፣ ሀገሬ ከሄድኩ በኋላ ግን ማሰር ይችላሉ" የሚሉት ፖለቲከኛው ከአመታት በፊት ለህክምና ከሀገር ሲወጡ መንግስት ከልክሏቸው እንደነበር፣ አሁን ደግሞ ሊመለሱ ሲፈልጉ መከልከሉ እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው ባሳለፍነው ሰኞ ለመሠረት ሚድያ ተናግረው ነበር።

መረጃን ከመሠረት!

የጥናት ውጤቱ አስደንጋጭ ነው  | ዓለም አቀፉ የምግብ ፖሊሲ ምርምር ኢንስቲትዩት፣ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ተባብሮ የሠራው ጥናት ውጤት አስደንጋጭ ነው።ከኢትዮጵያ ሕዝብ ግማሹ : ከአዲስ አበባ ...
14/02/2025

የጥናት ውጤቱ አስደንጋጭ ነው

| ዓለም አቀፉ የምግብ ፖሊሲ ምርምር ኢንስቲትዩት፣ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ተባብሮ የሠራው ጥናት ውጤት አስደንጋጭ ነው።

ከኢትዮጵያ ሕዝብ ግማሹ : ከአዲስ አበባ ሕዝብ ደግሞ ሦስት አራተኛው (¾) ቫይታሚን-ዲ አጥሮታል።

ይህ አሐዝ በተለይ 13 ወር ፀሐይ ለሚጠጣ ሕዝብ ስላቅ ይመስላል።ምክንያቱም የቫይታሚን-ዲ ዋና አከፋፋይ ፀሐይ ስለሆነች።

Amharic

Latest Posts Nothing Found! Ready to publish your first post? Get started here. News Nothing Found! Ready to publish your first post? Get started here. more News World Nothing Found! Ready to publish your first post? Get started here. more World News Politics Nothing Found! Ready to publish your fir...

Jawar Mohammed said on Feb 19, 2018. We witnessed his Political prophecy
13/02/2025

Jawar Mohammed said on Feb 19, 2018.
We witnessed his Political prophecy

12/02/2025

ልጃችንን አፋልጉን

በምስሉ ላይ ምትመለከቷት ልጅ ሂክማ አብዱረሂም ትባላለች። የ9ኛ ክፍል የባሽዋም ትምህርት ቤት ተማሪ ናት። በቀን 03 ትምህርት ቤት ብላ እንደወጣች ትምህርት ቤትም አልገባችም ቤትም ተመልሳ አልመጣችም። የጠፋችበት ሰፈር አስኮ አዲስ ሰፈር እስከ ጠሮ አራት መንታ አካባቢ ነው።

እባካችሁ ያገኛችዋት ወይም የተመለከታችሁ ከታች ባሉ ስልክ ቁጥሮች ይደውሉ።
0982177757
0927185256

12/02/2025

''Karoorri 'Team Lammaa' diiguu kan jalqabame jijjiiramni dhufee aangoon Ministira Muummee eenyu harka akka gale osoo hin baramiin dura ture.

''Sababa 'nageenya isaanitiif' jedhuun namni Dr Lammaa bira, biiroo isaanii seenu calalamuu eegale. Namni isaan bira seenus dura Dr. Abiy beeksifamanii akka ta'u barreessituu isaaniitiif kallattiin kenname.''

Ka'umsi garee Team Lammaa jedhamu kana diiguu fi Lammaa qofaatti hambisuu asirraa jalqabe'' jedhu aanga'aan duraanii miseensa 'Team Lammaa' turan.

Haala itti biyyaa baafamanis BBCtti himaniiru.
https://bbc.in/42RPou9

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The Republic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to The Republic:

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share