11/08/2025
“ይሄን የመሰለ ፊት ይዤ፣ እቺን ምታክል ቂ*….ጥ” ሰሞኑን ቲክታክ ላይ ቫይራል የወጣች ወጣት ነበረች።
ትናንት በEBS 20-30 ፕሮግራም ቀርባ ያለፈችበትን የህይወት ውጣ ውረድ ስትናገር በእውነት ምን ያህል ጠንካራ ሴት እንደሆነች ተረዳሁ።
ስሟ ቤቲ፣ ውልደቷ እና እድገቷ ድሬ ደዋ( የሰሞኑ መነጋገርያ ከተማ) ነው። እናቷ በሶስት አመትዋ ጥላት ጠፋች። ከdepression, anxiety and lonely ከመሆን የተነሳ ሳታውቅው እና ሳታስበው በለጋ እድሜዋ ወደ ሱስ በቀላሉ ገባች።
እንደ ቀልድ የገባችበት ሱስ አምስት አመት ሙሉ ቆየችበት። ጤናዋን፣ ጉልበትዋን፣ ትምህርቷን እና የመሳሰሉ ነገሮችን በሱሱ ምክንያት አጣች።
እናቷን ለመፈላለግም ሞከረች፣ በመጨረሻም በወንድሟ በኩል ለእናትዋ ተደውሎ ሲነግሯት፣ “ለደህና ነገር አትደውሉም….” ብላ ስልኳን ዘጋች። እናቷ የምትኖረው አሜሪካ ሀገር ነው።(ምን አይነት ሁኔታውስጥ ሆና ልጅን የሚያህል ነገር ደህና ነገር አይደለም ብላ እንዳሰበች አንድዬ ይወቀው)
After enduring all those hardships, she ultimately triumphed over her addiction. ዛሬ ከሱሱ ከተላቀቀች አንድ አመት ሞልቶኛል ትላለች ። (እንኳን ፈጣሪ ረዳት ) ብዙ እቅዶች አሏት። ጥንካሬዋ ይገርማል። አምስት አመት ሱስ ውስጥ የነበረችውን እንደ ባከኑ አመታት ነው ምትቆጥረው፣ ነገር ግን አታማርርም እኔን ለማስተማር የመጣ ነገር ነው ትላለች።
ያሰብሽው ይሳካልሽ
ሽቅርቅር ያለች ቅዳሜ ትሁንልን 🌺🙌🏾
Via Lamrot Ejigu