Akiya Media

Akiya Media Akiya Media አኪያ ሚዲያ welcome to our YouTube Channel Subscribe now and gat more benefits.

27/07/2025
26/07/2025

ወይ ስዩም ተሾመ ሰለኮሊደሩ ጎርፍ ያለውን ስተሰሙ ... ምክንያት ወይ ምክንያት

የቀብር ስነ-ሥርዓቱ ነገ ይፈፀማል  | አንጋፋውና ታዋቂው ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን (ዶ/ር) ሐምሌ  2 ቀን 2017 ዓ.ም በሚኖርበት አሜሪካ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል።ሥርዓተ...
25/07/2025

የቀብር ስነ-ሥርዓቱ ነገ ይፈፀማል

| አንጋፋውና ታዋቂው ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን (ዶ/ር) ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በሚኖርበት አሜሪካ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል።

ሥርዓተ ቀብሩ ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ቤተሰቡ እና ወዳጆቹ በተገኙበት አራት ኪሎ በሚገኘው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈፀማል::

ቤተሰቦቹ

ነፍስን በአፀደ ገነት ያኑራት🙏

የአለም የትግል ስፖርት ኮከብ ሀልክ ሆገን 71 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!በዓለም ታላቁ የትግል ስፖርት መዝናኛ ተቋም World Wrestling Entertainment (WWE) ስማቸው ከ...
24/07/2025

የአለም የትግል ስፖርት ኮከብ ሀልክ ሆገን 71 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!

በዓለም ታላቁ የትግል ስፖርት መዝናኛ ተቋም World Wrestling Entertainment (WWE) ስማቸው ከታላላቅ አንጋፋ ግለሰቦች ጋር ከሚጠቀሱት መካከል ቴሪ ጂን ቦሌያ በቅፅል ስሙ ሀልክ ሆገን ትናንት ምሽት ሐምሌ 16, 2017 (በኢትዮጵያ አቆጣጠር) በ71 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን TMZ ዘግቧል።

* WWE ሀልክ ሆገን በ1980ዎቹ የትግል ስፖርት ኢንዱስትሪው አለም አቀፍ ተቀባይነት እንዲያገኝ እና እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።

* በ1953 በጆርጂያ የተወለዱት ሀልክ ሆገን ገና በልጅነታቸው ወደ ትግል ስፖርቱ ዓለም ገብተዋል። በ1979 የአለም የትግል ስፖርት ፌዴሬሽንን (በኋላ WWE የሆነውን) በይፋ ተቀላቅለዋል።

* ከትግል ህይወታቸው ጎን ለጎን፣ እንደ Rocky III, Mr. Nanny እና Gnomeo & Juliet ባሉ ፊልሞች ላይ በመተወን በፊልም ዓለምም ስማቸውን አስመዝግበዋል። ኤልቪስ ፕሬስሊም የሀልክ ሆገን አድናቂ እንደነበር ይነገራል።

* የኮከቦች ማኅደር: በ2005 በትግል ኢንዱስትሪ ላበረከቱት አስተዋፅኦ የWWE Hall of Fame አባል ሆነው ተመርጠዋል።

* ፖለቲካዊ ተሳትፎ: በእድሜያቸው እየገፉ ሲመጡ፣ በ2014 ወደ ፖለቲካ በመግባት ሪፐብሊካን ብሔራዊ ኮንቬንሽንን ተቀላቅለዋል። ዶናልድ ትራምፕ በ2024 ለፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ ከፍተኛ እንቅስቃሴዎችን አድርገዋል።

* ቤተሰብ: ሀልክ ሆገን በትዳር ህይወታቸው ኒክ እና ብሩክ ሆገን የተባሉ ሁለት ልጆችን አፍርተዋል።

የሞት መንስኤ TMZ እንደዘገበው ሀልክ ሆገን በፍሎሪዳ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በልብ ህመም ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

Akiya Media Meta Newsroom Hulk Hogan

ታሪኩ የሚጀምረው፣ በአንድ ትልቅ የገንዘብ ህልም እና በአንድ ደፋር የማታለል እቅድ ነበር። በመጋረጃው ጀርባ፣ ቀሲስ በላይ መኮንን እና ተባባሪዎቻቸው፣ ከአፍሪካ ህብረት የተላከ አስመስለው ያ...
24/07/2025

ታሪኩ የሚጀምረው፣ በአንድ ትልቅ የገንዘብ ህልም እና በአንድ ደፋር የማታለል እቅድ ነበር። በመጋረጃው ጀርባ፣ ቀሲስ በላይ መኮንን እና ተባባሪዎቻቸው፣ ከአፍሪካ ህብረት የተላከ አስመስለው ያዘጋጁት የ6 ሚሊዮን 50 ሺህ ዶላር የክፍያ ትዕዛዝ ሰነድ በእጃቸው ነበር። ይህ ሰነድ፣ ወደ ባንክ ገብቶ ገንዘቡን ሲቀበሉ፣ ህይወታቸውን ለዘላለም ይቀይራል ብለው ተስፋ ያደረጉበት የወርቅ ቁልፍ መስሎ ታይቷቸው ነበር። ነገር ግን፣ ያ ቁልፍ የከፈተው የሀብት በሩን ሳይሆን፣ ረጅም እና አድካሚ የፍርድ ቤት ሂደትን ነበር።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ዐቃቤ ህግ፣ ይህንን "ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል" ሲያጋልጥ፣ ጉዳዩ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ፊት ቀረበ። የህግ ፍልሚያው ሲጀመር፣ ከታሪኩ ዋና ተዋናዮች መካከል ሁለቱ ተከሳሾች ከችሎቱ በራቁበት፣ ክሳቸው ተቋርጦ፣ ታሪኩ በሶስቱ ዋና ተጠርጣሪዎች ላይ ብቻ አተኮረ፤ ቀሲስ በላይ መኮንን፣ እያሱ እንዳለ እና በረከት ሙላቱ።

ዐቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎቹን አሰማ፣ የተከሳሾቹንም የመከላከያ ምስክሮች አዳመጠ። ከረጅም የክርክር ጊዜያት በኋላ፣ የፍርድ ቤቱ መዶሻ ለመጀመሪያ ጊዜ ወረደ። 1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን፣ በችሎቱ ዳኞች ሙሉ ድምጽ ጥፋተኛ ተባሉ። ሁለቱ ተባባሪዎቻቸው ደግሞ፣ በአንድ ዳኛ የልዩነት ሀሳብ፣ በአብላጫ ድምጽ ጥፋተኝነታቸው ተረጋግጦ፣ ፍርዱ ጸና።

ቀጥሎ የቅጣት ውሳኔው መጣ። ዐቃቤ ህግ ወንጀሉ በትብብር መፈጸሙን እንደ ማክበጃ፣ ተከሳሾቹ ደግሞ የተለያዩ ማቅለያዎችን አቅርበው፣ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔውን በጥር ወር 2017 ዓ.ም. አሳለፈ። ቀሲስ በላይ መኮንን በ5 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር መቀጮ፣ እያሱ እንዳለ እና በረከት ሙላት ደግሞ እያንዳንዳቸው በ3 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር መቀጮ እንዲቀጡ ተወሰነ።

ነገር ግን ታሪኩ እዚህ ላይ አላበቃም።

ተከሳሾቹ፣ በውሳኔው ቅር በመሰኘት፣ የመጨረሻ ተስፋቸውን ሰንቀው ወደ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ ሰሚ ችሎት አመሩ። በሙስና ወንጀል “ሊፈረድብን፣ ጥፋተኛ ልንባል አይገባም" እና "ቅጣቱ ከብዶብናል" የሚሉ ሁለት ዋና ዋና የይግባኝ ነጥቦችን አቀረቡ። ዐቃቤ ህግም በበኩሉ፣ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክል እንደነበር በመግለጽ መልሱን ሰጠ።

የይግባኝ ሰሚ ችሎቱ፣ የሁለቱንም ወገን ክርክር ከመረመረ በኋላ፣ የፍርዱን የመጨረሻ ምዕራፍ ጻፈ።

በጥፋተኝነቱ ላይ፦ ችሎቱ፣ "ጥፋተኛ ልንባል አይገባም" የሚለውን የተከሳሾቹን ቁልፍ የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ አደረገው። የስር ፍርድ ቤት የሰጠው የጥፋተኝነት ፍርድ ትክክለኛ እና ሥነ-ሥርዓትን የተከተለ ነው ሲልም አጸናው። በዚህም፣ ከወንጀሉ ነጻ የመውጣት ተስፋቸው ሙሉ በሙሉ ተዘጋ።

በቅጣቱ ላይ፦ ነገር ግን፣ ችሎቱ በቅጣቱ መጠን ላይ መጠነኛ ማሻሻያ አደረገ። የቀሲስ በላይ መኮንን የ5 ዓመት እስራት ወደ 3 ዓመት ከ7 ወር ዝቅ አለ። የእያሱ እንዳለ እና የበረከት ሙላት የ3 ዓመት ከ3 ወር እስራትም፣ 3 ወር ተቀንሶላቸው 3 ዓመት እንዲሆን ተወሰነ።

በመጨረሻም፣ ከአንድ ዓመት በላይ የፈጀው የ6 ሚሊዮን ዶላሩ የማታለል ድራማ፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተቋጨ። ተከሳሾቹ ጥፋተኝነታቸው በሀገሪቱ ከፍተኛው የህግ አካል ቢረጋገጥም፣ ከመጀመሪያው ፍርድ ላይ መጠነኛ የቅጣት ቅናሽ በማግኘት የፍርድ ሂደቱ ምዕራፍ ተዘጋ።

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።
_______
በነቀሲስ በላይ ላይ የተሰጠው ፍርድ አግባብ ነው ይላሉ? አስተያየትዎን ያስፍሩ።

Akiya Media Meta Newsroom

24/07/2025

ከአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተሰጠ መግለጫ

ትላንትናው ዕለት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በአዲስ አበባ በተከሰተው ጎርፍ ዙሪያ አንዳንድ ያልተገቡ አስተያየቶች መሰጠታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው እንዳብራራው፣ ትላንትና የተከሰተው ጎርፍ ወቅቱን በጠበቀ ከባድ ዝናብ ምክንያት በወንዝ ዳርቻ ልማት ግንባታ ላይ በነበረው ጊዮን ሆቴል አካባቢ የውሃ መጠን በመጨመሩ እና ለጊዜው የተሰራለትን ግድብ ጥሶ በመውጣቱ ነው።

ይሁን እንጂ፣ አንዳንድ ግለሰቦች ሁኔታውን ያላገናዘበ እና ከእውነት የራቀ አስተያየት መስጠታቸውን ቢሮው አስታውቋል።

አዲስ አበባ የነበራትን አስቸጋሪ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት ለማሻሻል በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራ ያለውን ስራ ወደ ጎን በመተው፣ አንዳንዶች ያልተገባ ስያሜ መስጠታቸው ተገቢ እንዳልሆነም ተገልጿል።

ጥሪ ለህብረተሰቡ:-

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለመላው ህብረተሰብ እና የከተማዋ ነዋሪዎች የሚከተለውን ጥሪ አቅርቧል፦

* ወቅቱንና ከተማዋ አሁንም በበርካታ ግንባታዎች ላይ መሆኗን ከግምት ውስጥ እንድታስገቡ።

* ምንጩ ካልታወቀ የተዛባ መረጃ ራሳችሁን እንድትጠብቁ።

* ትክክለኛውንና ሚዛናዊ የሆነውን መረጃ እንድትመረምሩ።

* የኢትዮጵያ ሜቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ወቅቱን አስመልክቶ የሚሰጣቸውን ማሳሰቢያዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ራሳችሁን ከጎርፍ አደጋ እንድትጠብቁ።

የጎርፍ መከላከል ስራ እና የህብረተሰቡ ተሳትፎ
በመጨረሻም፣ ማህበረሰቡ እየጣለ ያለውን ዝናብ እና ወቅቱን እንዲሁም በከተማዋ እየተሰራ ያለውን ግንባታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣

የጎርፍ መከላከል ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ከተማው በሚያደርገው የመከላከል ስራ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ቢሮው ጠይቋል።

Via Addis Ababa City Communication

23/07/2025

አዲስ አበባ እና ክረምቱ 20 አይዲ 6 ተረኛ
ዲዛየር አለፈላት አምና ፍሎሃ ስትንሳፈፍ የተቀለደባታ ዛሬ ላይ ጠንቃቃ በመሆና እና ብዙ ክብደት ያለቸውን ነገሮች ይዛ በመንቀሳቀሱ በዚህኛው ክረምት ብዙም ለአቅመ መንሳፈፍ አልደረሰችም ።

ተረኛው ግን ታውቋል አይዲ 6 ሆኗል ።

23/07/2025

እኔ የምለው ኢሳያስ ወይም TDF የዝናብ ደመና መሰሪያውን ወስደውታል እንዴ ወይስ አሁንም እዚሁ ነው !!

23/07/2025

እንዴት አገኛቹሁት የኮሊደር ልማቱን የወደቁት የመብራት ምሶሶ ማታ ሰዎች ፈተውት ነው ።

እነዚህ ሰዎች ክፋታቸው የውሃ መተላለፊያ ቱቦዎችንም ወሰደዋል ማለት ነው !!

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Akiya Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share