
07/11/2025
የራሱን የስምንት ዓመት ህፃን ልጅ የደፈረ ተከሳሽ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ
አርባምንጭ፦ ሚያዝያ 21/2017 ዓ.ም (አ.ከ.ፖ)
የ 8 (ስምንት) ዓመት ህፃን የግብረ ሥጋ በደል በማድረስ ወንጀል የተከሰሰ ተከሳሽ በ19 (አስራ ዘጠኝ) ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱን የአ/ምንጭ ከ/አስ/ር ፖሊስ የታክቲክ ምርመራ ማስተባባሪያ ኃላፊ ኢ/ር አለቦ አዉግቾ ገልፀዋል።
ተከሳሽ ብሩክ ኃ/መስቀል ይባላል የራሱን ልጅ ሐሰት ብሩክ የሚትባል ዕድመዋ 8 ሲሆን ዕለቱና ቀኑ በማይታወቅ ጊዜ ወላጅ እናቷ ወደ ጅንካ ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ ስትሄድ ሸኝቷት ተመልሶ የገዛ ልጁን የግብረስጋ ግንኙነት ከፈፀመ ቦኃላ ለሰዉ ከነገርሽ እገልሻለሁ በማለት እያሰፈራራት ቆይቷል።
በድርግቱ ያልተፀፀተዉ ተከሳሽ በዲጋሚ ብሩክ ኃ/መስቀል በቀን 26/4/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ገደማ ይህችን ህፃን ግብረስጋ ግንኙነት አሁንም ካደረገ ቦኃላ እያስፈራራና፣እገልሻለሁ በማለት እየዛቴ ከዝያም በተጨማር ስልክ ገዝቸሽ እሰጥሻለሁ በማለት እያባበለ በፈፀመዉ በሕፃናት ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረ ሥጋ በደል በማድረስ ወንጀል ክስ ቀርቦበት መርማሪ ፖሊስ የቀረበዉን ክስ በመመርመር በሰዉና በሰነድ ማስረጃ አጣርቶ ለዐ/ህግ ክሱን ልኳል።
ዐ/ህግ የተላከዉን መዝገብ በማየት ተከሳሽ የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ ቁጥር 627/1/4፣ሀ/ የተደነገገዉን በመተላለፉ ከፍቶ ዉሳነ እንደሰጥበት ስል ለፍ/ቤት አቅርቧል።
የአ/ምንጭ ከተማ አስ/ር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዛሬ በዋለዉ ችሎት ተከሳሽን 19 ዓመት ጽኑ እስራት ዉሳነ ሰቷል።
በመጨረሻም ኢንፔክቴር አለቦ የተፈፀዉ ድርጊት እጅግ በጣም አሳፋርና ወራዳ ተግባር መሆኑን አንስቶ
እንድህ አይነት አሳፋር ድርግት የምፈጽሙ ከድርግታቸዉ እንድቆጠቡ በጥብቅ አሳስበዉ ህብረተሰቡ ህፃናትና በሴቶች ላይ የምፈፀምመዉን ጥቃቶችን አፅኖት ሰተዉ በጋራ እንድከላከሉ ጥሪዉን አስተላልፏል።
ዘገባዉ የአ/ምንጭ ከተማ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነትና ገጽታ ግንባታ ሜስተባባሪያ ነዉ !!
በጀግንነት መጠበቅ፣በሰባዓዊነት ማገልገል!!