Zena123 ZENA123 , now called ZENA123 Broadcasting Corporate FBC currently possesses high-quality audibility

08/18/2021

ሐሳብዎን ያካፍሉን zena123
በአሁኑ ወቅት የተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት የሁሉንም በር ያንኳኳ ጉዳይ ነው ማለት ይቻላል።
በተለይ በከተሞች በመኖሪያ ቤት፣ በምግብና አልባሳት ላይ ብቻ ሳይሆን እንደ ትራንስፖርት፣ ትምህርትና ጤና ባሉ ማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ ጭምር እየተፈጠረ የመጣው የዋጋ ንረት ከብዙኃኑ ሕዝብ የዕለት ገቢ ጋር ያልተመጣጠነ መሆኑን ሕብረተሰቡ በሰፊው የሚያነሳው ጉዳይ ነው።
በአቅርቦትና በፍላጎት መካከል ያለው ልዩነት ለመቀነስ መንግስት ነዳጅን ጨምሮ ስንዴ እና ዘይትን የመሳሰሉ መሠረታዊ የሚባሉ የፍጆታ ዕቃዎችን ከውጭ ቢያስገባም የዋጋ ንረቱን በሚፈለገው ልክ ውጤት አለመምጣቱ ይነገራል፡፡
ከዚሁ በተጓዳኝ ግን አላስፈላጊ የሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲባል በአንዳንድ ስግብግብ ነጋዴዎች ዕቃዎችን በመደበቅ እና የውጭ ምንዛሬ ሚዛኑን በማዛባት የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶችም ለኑሮ ውድነቱ መናር የራሱን የሆነ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡
መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የኢኮኖሚ አሻጥር ለመቆጣጠር ሕንፃና ቤቶችን የመሳሰሉ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መያዣ በማድረግ የሚሰጡ ብድሮች እንዲቆሙ በጊዚያዊነት መመሪያ አስተላልፏል፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት በዘላቂነት ለመፍታት በመንግሥት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን እንዴ ተመለከቱ? በተለይም እየታየ ያለውን የኢኮኖሚ አሻጥር ለመቅረፍ በቀጣይ ከመንግስት እና ከሕብረተሰቡ ምን ይጠበቃል ይላሉ?
ሐሳብዎን ያካፍሉን zena123

08/18/2021

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጎርፍ የተጎዱ አካባቢዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ከሰዓት በአዲስ አበባ በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ በሰው በሕይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ማለዳ ላይ በመዲናዋ የጎርፍ አደጋ ተከስቶ በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰባቸውን አከባቢዎች ጎብኝተዋል።
ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ጉዳት የተከሰተባቸውን አከባቢዎች ማለዳ ላይ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ተጎጂዎችንም ማጽናናታቸውን አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል፡፡
እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት በአደጋው የሰባት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
ሌሎች የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ወደ ሆስፒታል የማድረሱ እና የነፍስ አድን ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉም ነው የተገለፀው፡፡
ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የከተማ አስተዳደሩ እንደሚሰራ የተገለፀ ሲሆን÷ የክረምቱ ወቅት እያየለ በመምጣቱ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ አስተዳደሩ ቦታዎችን ለይቶ የጥንቃቄ ስራ ይሰራል ተብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-zena123

08/18/2021

ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች የሚገኙ ዜጎች ወደሃገራቸው ይመለሳሉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ zena123 መንግስት ከሳኡዲ አረቢያ መንግስት ጋር በመቀናጀት ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በሳኡዲ አረቢያ በእስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ዜጎች ወደሃገራቸው እንደሚመለሱ ተገለጸ፡፡
ሃገራቱ በሳምንት ሶሶት በረራዎችን በማድረግ በሳኡዲ አረቢያ የተለያዩ ማቆያ ማእከላትና እስር ቤቶች የሚገኙ ዜጎችን ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ለሃገራቸው እንዲበቁ እንደሚደረግ በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።
በሳምንት ሶስት በረራዎች በማድረግ በየሳምንቱ 1ሺህ ዜጎችን ወደሃገር እንዲገቡ የሚያደረግ ሲሆን÷ በዚህ የማስመለስ ሥራ ቅድሚያ ወደ ሃገር እንዲገቡ የሚደረጉት ሴቶች፣ ህጻናት፣ ታማሚ እና አረጋውያን ዜጎች እንደሚሆኑ ተጠቅሷል።

08/18/2021

ከሰሜን ወሎ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደሴ ከተማ የገቡ ተፈናቃዮች ሁኔታ

ደሴ ከተማ zena123
ነዋሪነታቸው ራያ አላማጣ የነበረና ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ እናት ከሦስት ልጆቻቸው ጋር ከመኖሪያ ቀያቸው ከተፈናቀሉ አራት ሳምንታት ተቆጥረዋል።

የፌደራል መንግሥት የተናጠል ተኩስ አቁም አውጆ ሠራዊቱን ከትግራይ ካስወጣ በኋላ በአላማጣ በኩል በተከፈተ ጦርነት ምክንያት ቀያቸውን ለቀው መውጣታቸውን ይናገራሉ።

ያኔ ከአላማጣ ወደ ቆቦ ነበር ሄደው ከዘመድ ጋር የተጠለሉት።

ይሁን እንጂ ብዙም ሳይቆዩ ነበር ዳግም ከቆቦ ወደ ወልዲያ የተፈናቀሉት። ወልዲያ አካባቢ ባለው የጸጥታ ስጋትም ወደ ደሴ ከተማ መሄዳቸውን ይናገራሉ።

እነዚህ ቦታዎች ለመድረስ የትራንስፖርት ችግር እንደነበር ያስታወሱት እኝህ እናት፤ የቻሉትን በመኪና ያልሆነላቸውን በእግራቸው እያቆራረጡ ደሴ እንደገቡ ገልጸዋል።

ከቤታቸው የወጡት ማቄን ጨርቄን ሳይሉ ነው። በእጃቸው ቤሳ ቤስቲን የለም።

ባለፉበት ሁሉ የከባድ መሣሪያ ተኩስ ስለነበር በሁኔታው ህጻናት ልጆቻቸው መደናገጣቸውንና አሁንም ድረስ ሌሊት እንደሚቃዡ ይናገራሉ።

"እንግዲህ ፈጣሪ ያመጣብንን እርሱ መፍትሔ ይስጠን እንጂ ሌላ ምን ይባላል? ከአጠገባችን እንደ ቀልድ የተለዩን ወንድሞቻችን፣ ጎረቤቶቻችንና ወዳጆቻችን አሉ። እኛ ተርፈን እዚህ ደርሰናል" ይላሉ።

እኝህ እናት በደሴ ከተማ በሚገኘው ዳውዶ ትምህርት ቤት ተጠልለው የዕለት እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

አዲሱ በላይ ነዋሪነቱ በወልዲያ ከተማ ቢሆንም ሰሞኑን በተፈጠረው ችግር ምክንያት ተፈናቅለው ደሴ ከገቡት መካከል አንዱ ነው።

ቆቦ ይኖሩ የነበሩ ቤተሰቦቹም ከቆቦ ተፈናቅለው ደሴ ከገቡ ሳምንት አልፏቸዋል።

ከአንድ ወር በፊት እንደገና በተቀሰቀሰው የራያ አካባቢ ግጭት ከባላ፣ ኮረም፣ አላማጣ፣ ዋጃ እና ጥሙጋ በርካታ ሰው ተፈናቅሎ ወልዲያ ከተማ ተጠልለው ነበር።

ከሦስት ሳምንት በፊት ደግሞ ጦርነቱ ወደ ቆቦ ሲስፋፋ የቆቦ እና አካባቢው ነዋሪዎች 50 ኪሎ ሜትር በእግር ተጉዘው ወልዲያ ገብተዋል።

በከተማው ከፍተኛ የሆነ ተፈናቃይ በመኖሩ ምግብ፣ መጠጥ እና መጠለያ እስከማጣት የደረሰ ችግር እንደነበር አዲሱ ይናገራል።

ግጭቱ ከራያ ወደ ወልዲያ ዙሪያ ሲስፋፋ ደግሞ የወልዲያን ነዋሪ ጨምሮ ከራያ አላማጣ፣ ከኮረም፣ ከራያ ባላ እና ከራያ ቆቦ የመጡ ተፈናቃዮችን ጨምሮ ወደ ደሴ አቅንተዋል።

ምንም እንኳን ወደ ደሴ ለመሄድ የትራንስፖርት አማራጭ ቢኖርም ከ100 ብር የማይበልጥ የነበረው ታሪፍ ከ500 እስከ 1000 ብር ስለገባ ፈተና ሆኖ እንደነበር አዲሱ ያስታውሳል።

በደሴ እና ወልዲያ መካከል ባሉ አካባቢዎች ግጭቱ ሲስፋፋ በትራንስፖርት የመሄድ አማራጭም ጠፍቶ ነበር ይላል።

በዚህ ጊዜ ጋራ እና ሸንተረሩን እያቆራረጠ ህጻናት ልጆቹን ይዞ ደሴ መግባቱን ይናገራል።

አንዳንድ የሰሜን ወሎ አካባቢዎች የጦርነት ቀጠና በመሆናቸው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ተፈናቅሎ ደሴ ከተማ ገብቷል።

በዚህም ምክንያት ደሴ ከተማ ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የተፈናቀለ ሕዝብ አለ።

ይህንን ለማስተናገድም የከተማ አስተዳደሩ አራት ትምህርት ቤቶችን ለተፈናቃዮቹ ጊዜያዊ መጠለያነት አዘጋጅቷል። እርዳታ ለማድረግም ምዝገባ እየተደረገ መሆኑን አዲሱ ተናግሯል።

ከሰሜን ወሎ የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደሴ መግባታቸው ተገለጸ
መንግሥት ሠራዊቱ በህወሓት ላይ እርምጃ እንዲወስድ 'አቅጣጫ' ማስቀመጡን ገለጸ
ረቡዕ እለት ከሰሜን ወሎ አካባቢዎች የተፈናቀሉ በርከት ያሉ አካባቢዎች ሰዎች ደሴ መግባታቸውን የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ለቢቢሲ ገልጿል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መሳይ ማሩ እንደተናገሩት ተፈናቃዮቹ አንዳንዶቹ ቤተ ዘመድ ጋር እንዲሁም መኖሪያ ቤትና ሆቴል ተከራይተው ተቀምጠዋል።

ይህንን ማድረግ ላልቻሉትና አቅም ለሌላቸው ደግሞ ትምህርት ቤቶችን ለጊዜያዊ ማረፊያነት አመቻችተው እዚያ እንዲያርፉ ለማድረግ ጥረት መደረጉን አቶ መሳይ ተናግረዋል።

ኃላፊው ከክልሉ እና ከፌደራል ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመሆኑ የዕለት እርዳታ ማቅረብ ተጀምሯል ብለዋል።

"የተፈናቃዮች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው" ያሉት ኃላፊው፤ አሁን ላይ ያለውን የተፈናቃይ ቁጥር በውል መግለጽ እንደሚቸገሩ ተናግረዋል።

በትክክል ምን ያህል ተፈናቃይ እንዳለ በእድሜና በፆታ ለማጠናቀር እየሰሩ መሆናቸውንም አቶ መሳይ አክለዋል።

ከቀናት በፊት ያነጋገርናቸው የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገ/መስቀል የተፈናቃዮቹን ቁጥር በትክክል ማወቅ ባይቻልም ከ10 እስከ 15ሺህ የሚገመት ሕዝብ እየገባ መሆኑን ተናግረው ነበር።

ደቡብ ወሎ ዞን ከዚህ ቀደም በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ ክልል የተፈፀሙ ጥቃቶችን ተከትሎ የተፈናቀሉ ሰዎችን እያስተናገደ መሆኑን ያስታወሱት አቶ መሳይ ፤ የምግብ አቅርቦት ቢኖርም አልባሳትና ምግብ ነክ ያልሆኑ አቅርቦቶች እጥረት መኖሩን ተናግረዋል።

"በዘር ሐረጋችን ብቻ ወደማናውቀው አካባቢ ለመሸሽ ተገደናል" ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ ሰዎች
"ሰው ራቁቱን ነው የመጣው። የያዘው ነገር የለም። ቁጥሩ እየጨመረ ሲሄድ የምግብ አቅርቦት ችግርም ሊኖር ይችላል" ብለዋል ኃላፊው።

በዞኑ ከዚህ ቀደም ከተለያዩ አካባቢዎች ጥቃት ሸሽተው የወጡ ከ11ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ቡድን መሪ አቶ መሐመድ ሰይድ ለቢቢሲ መግለጻቸው ይታወሳል።

የፌደራል መንግሥት የተናጠል ተኩስ አቁም አውጆ ሠራዊቱን ከትግራይ ካስወጣ በኋላ የህወሓት አማጺያን ወደ አማራ ክልል እና አፋር ክልል በመግባት ጦርነት ከፍተዋል።

ይህንንም ተከትሎ ከሁለቱም ክልሎች ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል።

ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬሴክሬታሪ ቢልለኔ ስዩም እነዚህ ተፈናቃዮች ሰብዓዊ እርዳታ ቢያስፈልጋቸውም የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረት ተነፍጓቸዋል ሲሉ ወቅሰዋል።

ይሁን እንጅ የፌደራል መንግሥት ያለውን እርዳታ እያቀረበ ሲሆን ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረግ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ጋር እየተነጋጋረ ነው ብለዋል።

08/18/2021

አብደላ ሐምዶክ ሱዳን ግዛቷን አስከብራ ከኢትዮጵያ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖራት ፍላጎት አላት አሉ

የሱዳን የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር አብደላህ ሐምዶክ
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖራት እንደምትፈልግ ነገር ግን ከወራት በፊት በወታደሮቿ ቁጥጥር ስር ያስገባችውን ኢትዮጵያ ይገባኛል የምትለውን ግዛት እንደምትጠብቅ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ወታደሮቻቸው ከወራት በፊት በቁጥጥራቸው ሥር ያስገቡትን እና ከኢትዮጵያ ጋር የሚወዛገቡበትን የድንበር አካባቢ በመጎብኘት መሠረተ ልማቶችን ሰኞ እለት ባስመረቁበት ጊዜ ነው።

የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣንት የሆኑት የወታደራዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ በአወዛጋቢው ይዞታ ውስጥ ሱዳን ያስገነባቻቸውን መሠረተ ልማቶችን መመረቃቸው ተዘግቧል።

አልፋሽካ ውስጥ በሚገኘው ዋድ ኩሊ በተባለው መንድር ውስጥ በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ ባደረጉት ንግግር አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር "ጥሩ ግንኙነት" እንዲኖራት እንደሚፈልጉ ነገር ግን ግዛቷን እንደምትጠብቅና እንደምታስከብር መግለጻቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ኡጋንዳ በአሜሪካ ጥያቄ 2ሺህ የአፍጋኒስታን ስደተኞችን ልትቀበል ነው
"ሕዝባችንን ከታወጀበት ጦርነት መከላከላችንን እንቀጥላለን" የአማራ ክልል ም/ር መስተዳድር ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር)
ሱዳን በኢትዮጵያ ሰላም ለማምጣት ጥረቷን እንደምትቀጥል ገለጸች
ኢትዮጵያና ሱዳን የግዛታቸው አካል እንደሆነ በመግለጽ ለረጅም ጊዜያት ሲነጋገሩበት የቆየው ለእርሻ ተስማማዊን የአልፋሽካ አካባቢ ከዘጠኝ ወራት በፊት የሱዳን ሠራዊት የኢትዮጵያ አርሶአደሮችን በማስወጣት በቁጥጥሩ ስር ማስገባቱ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ግዛቱ ወደነበረበት ተመልሶ ንግግር እንዲካሄድ በተደጋጋሚ ብትጠይቅም ከሱዳን በኩል ተቀባይነት ሳያገኝ ይዞታውን በማጠናከር የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ተገንብተውበታል።

የሱዳን ዜና ወኪል ሱና ጄነራል አል ቡርሐን በሥነ ሥርዓቱ ላይ በኢትዮጵያ ቁጥጥር ሥር ቆይቶ ወደ ሱዳን በተካተተው የድንበር አካባቢ መረጋጋትና ደኅንነት እንዲሰፍን እንደሚያደርጉ መናገራቸውን ዘግቧል።

ጄነራሉ ጨምረውም ሠራዊታቸውና ሕዝቡ ግዛቱ ወደ ሱዳን እንዲመለስ ላደረጉት ጥረት አድናቆታቸውን ገልጸው፤ አካባቢው ለእርሻ ተስማማሚ የሆነ ለም መሬት በመሆኑ እያንዳንዱን ስንዝር መሬት ጠብቀው እንዲያለሙ ጥሪ ማቅረባቸውን ሱና ዘግቧል።

ኢትዮጵያና ሱዳን የሚዋሰኑበት የድንበር አካባቢ ሁለቱ አገራት በይገባኛል መቋጫ ሳያገኙለት ለዘመናት የቆየ ሲሆን ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች የሚገኙበት አካባቢ ነበር።

ባለፈው ጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ የኢትዮጵያ ሠራዊት ከአካባቢው መውጣቱን ተከትሎ የሱዳን ጦር ወደግዛቱ በመግባት ኢትዮጵያውያኑን አርሶአደሮች በማፈናቀል አካባቢውን መቆጣጠራቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግሥትም ድርጊቱን በመቃወም የሱዳን ጦር ከያዛቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣና ጉዳዩ ችግሩ ቀደም ብሎ ተጀምሮ በነበረው ውይይት እንዲፈታ በተደጋጋሚ ቢጠይቅም የሱዳን መንግሥት ሳይቀበለው ቀርቷል።

08/18/2021

"ሕዝባችንን ከታወጀበት ጦርነት መከላከላችንን እንቀጥላለን" የአማራ ክልል ም/ር መስተዳድር ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር)
17 ነሐሴ 2021
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር)
የምስሉ መግለጫ,
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር)

zena123 ከአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ቆይታ አድርጓል።

ከሳምንት በፊት በተለይም የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ት ቤት "የጸጥታ ኃይሎች በህወሓት ላይ ርምጃ እንዲወስዱ አቅጣጫ ተቀምጧል" የሚል መግለጫ ከመስጠቱ በፊት የተደረገ ቃለ መጠይቅ ነው።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች መኖራቸውን የተናገሩ ሲሆን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና መገናና ብዙኃንን በወገንተኝነት ከሰዋል። ሙሉ ቃለ መጠይቁ በዚህ መልኩ ቀርቧል።

zena123፡ ጦርነቱ በስንት ግንባር ነው እየተካሄደ ያለው?

ዶ/ር ፋንታ፡ ጦርነቱ በሁሉም አማራ ክልል ከትግራይ ክልል ጋር በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች የሚደረግ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ አማራ ክልል ውስጥ ዘልቆ በመግባት ነው እየተካሄደ ያለው። በሰሜን በኩል ከጠለምት ጀምሮ እስከ አፋር ድንበር ድረስ ይዘልቃል። በብዙ መቶ ኪሎ ሜትሮች የሚሸፍን ውጊያ ነው እየተደረገ ያለው።

zena123፡ የጦርነቱን ሁኔታ እንዴት ይገልጹታል?

ዶ/ር ፋንታ፡ ህወሓት ሙሉ ወረራ ነው እያደረገብን ያለው። በሁሉም ግንባሮች ያልተገደበ ጥቃት ነው እየፈጸመ ያለው። የተናጠል ተኩስ አቁሙን በሚጻረር መልኩ ነው ጥቃቱን እየፈጸመ ያለው። ዜጎች በየቀኑ ከግጭቱና ከግድያው ለማምለጥ በገፍ እየተሰደዱ ነው።

zena123፡ አሁን ውጊያ እንዳለ ነግረውናል እና ተኩስ አቁሙ አለ ማለት እንችላለን?

ዶ/ር ፋንታ፡ መጀመሪያ መንግሥት የተኩስ አቁሙን ያደረገው በተናጠል ነበር። ነገር ግን ህወሓት ያለማቋረጥ ጥቃት ሲፈጽም እና ጭፍጨፋ ሲፈጽም ማቆሚያው የት ነው? ዜጎች በጠራራ ፀሐይ እየተጨፈጨፉ ነው። ተኩስ አቁሙ መከበር ነበረበት። እናም መንግሥት የመከላከል ሥራ ነው እየሰራ ያለው። ዜጎቻችንን እየተከላከልን ነው ያለነው። ከዚያ ያነሰም ሆነ የገፋ ነገር እያደረግን አይደለም።

ከህወሓት ጋር ስለተደረገው ወታደራዊ ስምምነት ኩምሳ ድሪባ ምን ይላል?
"በትግራይ ላይ የተጣለው ከበባ እስኪነሳ ትግላችን ይቀጥላል" አቶ ጌታቸው ረዳ
የህወሓትና የኦነግ-ሸኔ ጥምረት አዲስና አስደናቂ አይደለም፡ ቢልለኔ ስዩም
ቢቢሲ፡ ይህ አይነቱ አካሄድ ከቀጠለ የሚቀየር ነገር ይኖር ይሆን? ከህወሓት ጋር ለመደራደር?

ዶ/ር ፋንታ፡ ለውጡ እንዲመጣ የምንጠብቀው ከህወሓት በኩል ነው። የተኩስ አቁሙን ማክበር አለበት። ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ለመነጋርም ቢሆን መጀመሪያ የተኩስ አቁሙ ተከብሮ የሰላም ጊዜ መኖር አለበት። ሰዎች እየተገደሉ እና እየተጨፈጨፉ ግን ይህ ሊሆን አይችልም።

zena123 የማየት ፍላጎት ካለው በአሁኑ ወቅት እናቶች ዝናብ ላይ እየወለዱ ነው። እናም እንደሚገባኝ እንደእናንተ አይነት ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ድምጽ ላጡት ድምጽ መሆን ይገባቸዋል። ምክንያቱም አሁን ያንን እያየን አይደለምና። በእርግጥ እነዚህ ብዙኃን መገናኛዎች ድምጽ ለሚያሰሙት እና ለሚንጫጩት ብቻ ሆነዋል። ይህ ደግሞ በጣም የሚያሳዝን ድርጊት ነው።

አሁን እያወራን ባለበት ወቅት ዜጎች ያለማቋረጥ ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው። ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮችን እያስተናገድን ነው። አዲስ ባገረሸው ጦርነት ከ2 መቶ ሺህ በላይ ዜጎች ከራሳቸው የትውልድ አካባቢ ተፈናቅለዋል። ስለዚህ ውይይቱንም ቢሆን ለማድረግ የመጀመሪያውና ብቸኛው መንገድ የተጣለውን ተኩስ አቁም ማክበር ነው።

zena123፡ ህወሓት ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ የተኩስ አቁም እንደማያደርግ ተናግሯል። እናንተ ለዚህ ምላሻችሁ ምንድን ነው?

ዶ/ር ፋንታ፡ የጠየቅከኝን ጥያቄ ራስህ መልሰኸዋል። ዜጎች እየተጨፈጨፉ እና እየተፈናቀሉ ዝም ብለን ተኩስ ማቆም እንዳለብን የምታስብ አይመስለኝም። ብቸኛው መንገድ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መጀመሪያ ተኩስ አቁሙን መቀበል አለባቸው።

zena123፡ ከ200 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንዳሏችሁ ነግረውናል። ምን አይነት ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው አሁን?

ዶ/ር ፋንታ፡ ከሰብአዊ ኤጀንሲዎች ጋር እየተወያየን ነው። ለተፈናቃዮች የእርዳታ ድርጅቶች እኩል ትኩረት እየሰጡ አይደለም። ሳስተምረው ከነበረው እና ካለኝ እውቀት ጋር የሚጻረር በሰብአዊነት ላይ አድሏዊነት እያየሁ ነው።

የአማራ ክልል ተፈናቃዮች ተገቢው ሰብዓዊ እርዳታ እየደረሰላቸው አይደለም። እየቀረበ ያለው እርዳታ በቂ አይደለም። እርዳታ ከሚያቀርቡ ድርጅቶች ጋር ተነጋግረናል። ፍትሃዊ አቅርቦት አለመኖሩን አስረድተናል። ነገር ግን እስካሁን ምንም የተቀየረ ነገር የለም። ይህ እስከሚስተካከል እየጠበቅን ነው።

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር)
ቢቢሲ፡በርካታ ወጣቶች የአማራ ልዩ ኃይልን ወይም መከላከያን እየተቀላቀሉ እንደሆነ እያየን ነው። በቁጥር ምን ያህል ወጣት ሊቀላቀል ይችላል? ይህ ሁኔታስ በጦርነቱ ቅርጽ ላይ ምን አይነት ለውጥ ያመጣል?

ዶ/ር ፋንታ፡ የጠራነው ራሱን/ራሷን እንዲከላከል/እንድትከላከል ሁሉንም ሕዝባችንን ነው። ይህ ጥሪ ለእያንዳንዱ ዜጋችን ራሱን እንዲከላከል የተደረገ ጥሪ ነው። ይህ በሌሎች ላይ የታወጀ ጦርነት አይደለም። ራስን የመከላከል ጥሪ ነው። ስለዚህ ጥሪውን ለእያንዳንዱ ዜጋ ስላደረግን ይህንን ያክል ብዬ በቁጥር ልገልጽልህ አልችልም። ምናልባትም በሚሊዮኖች ሊሆን ይችላል።

zena123፡ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተለይም ደግሞ የአሜሪካ መንግሥት የአማራ ልዩ ኃይል አማራና ትግራይ በይገባኛል በሚወዛገቡበት አካካቢ [ወልቃይትና አካባቢዎቹ] ይውጡ ብለዋል። የእናንተ ምላሽ ምንድን ነው?

ዶ/ር ፋንታ፡ በዚያ ቦታ የአማራ ኃይል የሚባል የለም። ያሉት የፌደራል መንግሥት መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ክልልን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች ልዩ ኃይሎች ናቸው። በሁሉም አካባቢዎች የተሰማራው ኃይል የሚመራው በፌደራል መንግሥት ዕዝ ስር ነው።

zena123፡ ይህ ጦርነት መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። በተለይም የተለያዩ ክሶች ይቀርባሉና በዚህ ጉዳይ ላይ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚሉት ነገር አለ?

ዶ/ር ፋንታ፡ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያለኝ መልዕክት በየትኛውም ቦታ እና በማንነታቸው ሳይገደቡ የጦርነቱ አካል ላልሆኑ ነገር ግን በሂደቱ ለሚጎዱ ለሁሉም ንጹሃን ተጎጂ ዜጎች ፍትሃዊ እርዳታ ማቅረብ አለበት። የአንድን ወገን ጩኸት ብቻ በመስማት ነገሮችን ከማራገብ ይልቅ የሁሉንም አካላት ሃሳብ ማድመጥ ተገቢ ነው።

የፌደራል መንግሥት፣ የአማራ ክልል መንግሥት ሊደመጡ ይገባል። ከግጭት የሚገኝ ትርፍ የለም። ስለዚህ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የግጭቱን አንድ አካል ብቻ በመያዝና በማድመጥ ኢትዮጵያን ሊያግዛት አይችልም። አማካዩን መያዝ አለባቸው። ድምጻቸው ለማይሰማው ወገኖች ድምጽ መሆን እጅግ አስፈላጊ ነው።

የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ስለማይካድራው ጭፍጨፋ ትንፍሽ አላለም። ይህ እንደ ሰው በጣም አሳዛኝ ነው። በህወሓት ጭፍጨፋ ሰለባ ሆነው ሳለ ዝም መባላቸው በጣም ያስከፋል። በሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ዋግኽምራ እና አፋር ክልል ስለሚፈናቀሉት ዜጎች የሚሉት ነገር የለም። ይህ ምን ማለት ነው? በእውነት ለኢትዮጵያ የሚጨነቁ ከሆነ በሚሰጧቸው መግለጫዎች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው።

አንዳንድ ጊዜ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የሚሰጡ መደማደሚያዎች እጅግ አሳዛኝ ናቸው። ምክንያቱም ምንም አይነት ማጣሪያ ሳያደርጉ የራሳቸውን ድምዳሜ ይሰጣሉ። ይህ ለተጎጅዎች ሌላ ጉዳት ነው።

zena123፡ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተፈናቀሉት ከየት ከየት ነው?

ዶ/ር ፋንታ፡ በዘገባችሁ አካታችሁት እንደሆነ ባላውቅም ባለፈው መጋቢት እና ሚያዚያ በሰሜን ሸዋ ዞን እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በርካታ ሰዎች ተፈናቅለዋል፣ በምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም፣ በደቡብ ጎንደር፣ በሰሜን እና ደቡብ ወሎ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በሚነሱ ግጭቶች ምክንያት ተፈናቅለው ይገኛሉ።

በጣም አሳዛኙ ነገር ደግሞ እንዳለመታደል ሆኖ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለእነዚህ ወገኖች ድምጽ ሆኖ አያውቅም። የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በዚህ ደረጃ ለተመረጡ ወገኖች ብቻ ድምጽ መሆኑ በጣም ያሳስበኛል። ይህ ከማውቀው እና እንደመርኅ መሆን ካለበት ሎጂክ አንጻር ያፈነገጠ በመሆኑ አስጨናቂ ነው።

zena123፡ በወልቃይት አካባቢ የትግራይ ተወላጆች ተፈናቅለዋል፣ ጥቃትም ደርሶባቸዋል በተለይ ግድያ ተፈጽሞ አስከሬናቸው ተከዜ ወንዝ ላይ ተጥሏል በሚል ለሚቀርብው ክስ ምላሻችሁ ምንድን ነው?

ዶ/ር ፋንታ፡ በእንደዚህ አይነት ድራማ እና ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል የራሱን ዜጎች በመግደል ትህነግ በሚገባ የሚታወቅና የሰለጠነ ነው። እናም ይህ የድራማው እንድ አካል እንደሆነ እጠረጥራለሁ።

ባህርዳርና ጎንደር ጨምሮ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች የሰዓት እላፊ ስለመታወጁ
በትግራይ ያለው የእርዳታ አቅርቦትና ተያይዘው የሚነሱ ጉዳዮች
ከሰሜን ወሎ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደሴ የገቡ ተፈናቃዮች ሁኔታ
ቢቢሲ፡ ይህ ግጭት ከተጀመረ ዘጠኝ ወር እየሆነው ነው። እና በብዙ ዘርፎች ላይ ተጽዕኖ ነበረው። ግጭቱ በአጭር ጊዜ ሊቋጭ የሚችልበት መንገድ አለ ብለው ያምናሉ?

ዶ/ር ፋንታ፡ ለምን መፍትሔ አይኖርም? በዓለም ላይ የማይቻል ነገር የለም። የማይቻል የምናደርገው የግጭቱ ተዋንያን ነን። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በቅርበት ከሰራ እና ህወሓትን የሰላም አማራጮችን እንዲያማትር ከጠየቀ ችግሩን የማንፈታበት መንገድ ላይኖር አይችልም።

ያ ግን ሊሆን የሚችለው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን መንግሥት ሲያግዝ እና በአቅማቸው ልክ ህወሓት ላይ ጫና መፍጠር ሲችሉ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ህወሓት በአማራ፣ በአፋር እና በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ ያወጀውን ጦርነት ማቆም አለበት። ይህንንም በይፋ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ምንም ነገር እናደርጋለን እያሉን ነው።

የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግን ይህንን እየሰማ ዝምታን መርጧል። አሁን ለጊዜው የማላስታውሰው አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም እውነታውን ሰሞኑን ተናግሯል። ይህ ጥሩ ጅምር ነው። ከችግሩ የመውጫ ትክክለኛ መንገዳችን እውነት ብቻ ነው።

zena123፡ ህወሓት በቅርቡ የተኩስ አቁሙን ተቀብሎ ወደ ድርድር ይመጣል ያምናሉ?

ዶ/ር ፋንታ፡ በህወሓት ቦታ ሆኜ መናገር አልችልም። ህወሓት በየጊዜው ሃሳቡን ይቀያይራል። ይህ የራሳቸው ጉዳይ ነው።

zena123፡ ህወሓት ጦርነቱን ቢቀጥል ምን ታደርጋላችሁ?

ዶ/ር ፋንታ፡ ሕዝባችንን ከታወጀበት ጦርነት መከላከላችንን እንቀጥላለን። ያለን ብቸኛው አማራጭ እሱ ነው። በእኛ ላይ ጦርነት ማወጁን ህወሓት በይፋ ግልጽ አድርጓል ምንም እንኳ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ምንም ነገር ማለት ባይችልም።

ህወሓት ግን ኢትዮጵያን ለማፍረስ እስከ ሲዖል እንደሚሄድ ነግሮናል።ይህንን ዝም ብለን አንመለከትም። አንተስ እንደ ጋዜጠኛ በዚህ ደረጃ ሕዝባችን ላይ ጥቃት የሚፈጽምን፣ የሚያፈናቅልን እና ያልተገደበ የበቀል ፍላጎቱን ለማሟላት በደል የሚፈጽምን አካል ምን ልንለው እንድንችል ትጠይቀኛለህ? ይህንን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይገነዘባል ግን ምንም አይልም።

08/18/2021

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ግብዣ ወደ ቱርክ ሊጓዙ ነው
17 ነሐሴ 2021
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይየፎቶው ባለመብት,REUTERS
ጠቅላይ ሚንሰትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ረቡዕ ነሐሴ 12/2013 ወደ ቱርክ ለጉብኝት እንደሚጓዙ የአገሪቱ ዜና ወኪል ዘገበ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ቱርክ የሚጓዙት በአገሪቱ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ግብዣ መሆኑን የቱርክ ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬትን ጠቅሶ አናዱሉ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ከሁለት ሳምንታት በፊት ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ቱርክ ለኢትዮጵያ የትኛውንም አይነት ድጋፍ ታደርጋለች በማለት ወዳጅነታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።

ፕሬዝደንቱ ይህን ማለታቸው የተሰማው ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ በተወያዩበት ወቅት እንደነበር ተገልጾ ነበር።

ሁለቱ መሪዎች ሐምሌ 25/2013 ዓ.ም በስልክ በተወያዩበት ወቅት ቱርክ ለኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ ፕሬዝደንት ኤዶጋን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ኤርዶጋን ቱርክ ለኢትዮጵያ የትኛውንም አይነት ድጋፍ ታደርጋለች አሉ
የዶ/ር ቴድሮስን ዳግም መመረጥ የሚቃወመው ድርጅት ቀጣዩ ምርጫ ግልጽ እንዲሆን ጠየቀ
የዶ/ር ቴድሮስን ዳግም መመረጥ የሚቃወመው ድርጅት ቀጣዩ ምርጫ ግልጽ እንዲሆን ጠየቀ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በቱርክ ለምን ያህል ቀናት እንደሚቆዩ የተባለ ነገር ባይኖርም፤ ጉብኝቱ የኢትዮጵያ እና የቱርክ ዲፕሎማሲያዊ ግነኙነት ከተጀመረበት 125ኛ ዓመት ጋር መገናኘቱ ልዩ ያደርገዋል ሲል የቱርክ ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

በጉብኘቱ ወቅት ሁለቱ አገራት ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይገመግማሉ እንዲሁም ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች ይመክራሉ ተብሏል።

ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል አስካሁን የተባለ ነገር የለም።

line
ይህ በእንዲህ እንዳለ በድንበር ይገባኛል እና በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር አለመግባባት ውስጥ የምትገኘው የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን ከቀናት በፊት ወደ ቱርክ ተጉዘው ነበር።

ሱዳን ጄነራሉ ወደ ቱርክ የተጓዙት የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ ግነኙነት ለማጠናከር ነው ብላለች።

ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን በፕሬዝደንት ኤርዶጋን ግብዣ የሁለት ቀናት ጉብኝታቸውን አጠናቀው ባለፈው ዓርብ ወደ ካርቱም ከመመለሳቸው በፊት በቱርክ እና በሱዳን መካከል በርካታ ስምምነቶች እና የመግባቢያ ሰነዶችን ተፈራርመዋል።

የኃይል አቅርቦት፣ መከላከያ፣ ፋይናንስ እና መገናኛ ብዙኃን በሁለቱ አገራት መካከል ስምምነት ከተደረሰባቸው ጉዳዮች ውስጥ ተጠቃሽ መሆናቸውን አናዱሉ ዘግቦ ነበር።

line
ቱርክ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ካደረጉ አገራት መካከል አንዷ ስትሆን የጨርቃ ጨርቅ እና የኤሌክትሪክ ማስተላላፊያ ገመዶች ማምረቻዎችን ጨምሮ የቱርክ ኩባንያዎች 2.5 ቢሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ፈሰስ ማድረጋቸውን ከዚህ ቀደም የቱርኩ ዜና ወኪል አናዱሉ ዘግቧል።

ቱርክ በመካከለኛው ምሥራቅ ምጣኔ ሀብታዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ተጽእኖ ፈጣሪ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ ነች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ ፕሬዝደንት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን በቀጠናው የሚያደርጉት ጉብኝት እንደቀጠለ ሲሆን በቅርቡ ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛው ጄፈሪ ፌልትማን በፕሬዝደንት ጆ ባይደን ጥያቄ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን ግጭት በተመለከተ ለመነጋገር ዳግም ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ሮይተርስ የዜና ወኪል ከቀናት በፊት ዘግቦ ነበር።

ፌልትማን ከነሐሴ 9 እስከ 18 ወደ ኢትዮጵያ፣ ጂቡቲ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች እንደሚጓዙ እና ከየአገራቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚገናኙ የአሜሪካ መንግሥት ከቀናት በፊት አስታውቆ ነበር።

08/18/2021

የውጭ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ብድር ለመልቀቅ እያቅማሙ ነው ተባለ
ከ 1 ሰአት በፊት
አዲስ አበባ ከተማየፎቶው ባለመብት,EDUARDO SOTERAS
የምስሉ መግለጫ,
አዲስ አበባ ከተማ

ለኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ የሚባሉ የፋይናንስ ተቋማት ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ብድር ለመልቀቅ እያቅማሙ ነው።

ይህም የሆነበት ዋነኛው ምክንያት ተጨማሪ ብድር ለአገሪቱ መስጠት የመክፈል አቅሟን የበለጠ ሊያዳክም ይችላል ከሚል ስጋት ነው።

በገንዘብ ሚኒስትር አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሮይተርስ እንደተናገሩት ለምሳሌ የቻይናው ኤክዚም ባንክ እሰጣለው ብሎ የነበረውን ከፍተኛ ገንዘብ ለመልቀቅ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።

ይህም ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጵያ ከመስጠት የታቀበው የብድር መጠን 339 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይህን ያሉት የገንዘብ ሚኒስቴር የቻይና ትብብር ዳይሬክተር ደምሱ ለማ ናቸው።

ነገር ግን የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጵያ ብድር ለመልቀቅ በማቅማማት ላይ ያለ ብቸኛው የፋይናንስ ተቋም አይደለም።

ሰኔ ወር ላይ በገንዘብ ሚኒስቴር የታተመ አንድ ሰነድ እንዳመለከተው የውጭ አበዳሪዎች አስከ መጋቢት መጨረሻ ድረስ 11 ቢሊዮን ዶላር ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር።

የዓለም ባንክ አንድ አካል የሆነው የዓለም አቀፉ የልማት ትብብር ማኅበር (ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን) ለምሳሌ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ይለቃል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን ይህን እስከአሁን ተግባራዊ አላደረገም።

የወቅቱ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ተግዳሮቶች
የጥቁር ገበያው ምንዛሪ መናር በኢኮኖሚው ላይ ምን ጫና ይዞ ይመጣል?
ሚኒስቴሩ በሰነዱ ከጠቀሳቸው ሌሎች አበዳሪ ተቋሟት አንዱ ግዙፉ የዓለም የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ሲሆን ተቋሙ 2.7 ቢሊዮን ዶላር እስከ አሁን ለኢትዮጵያ አለቀቀም።

ከውጭ አበዳሪዎች ትልቅ የምትባለው ቻይና 1.4 ቢሊዮን ዶላር ብድር አልለቀቀችም። ከላይ ከተጠቀሱት አበዳሪዎች ሌላ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና ሌሎች የንግድ ባንኮች ይገኙበታል።

ይህ የውጭ አበዳሪዎች ተጨማሪ ብድር ለኢትዮጵያ ለመልቀቅ አለመፍቀዳቸው አገሪቱ ላይ እየተካሄዱ ያሉ መጠነ ሰፊ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ሊያስተጓጉል እንደሚችል ይገመታል።

በውጭ ብድር ተጠቃሚ እየሆኑ ከቆዩት ፕሮጀክቶች መካከል እርሻ፣ ትራንስፖርት፣ ኮሚዩኒኬሽን፣ አውራ ጎዳናዎች እና የባቡር ፕሮጀክቶች ይገኙበታል።

እነዚህ በድምሩ 675 ቢሊዮን ዶላር ብድር ያገኙ ፕሮጀክቶች ናቸው። ይህም እንደ አውሮፓውያኑ ከሐምሌ 2020 እስከ መጋቢት 2021 ያለውን የሚያመላክት አሐዝ ነው።

አሁን የውጭ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ገንዘብ ለማበደር ታቅበው ሁኔታውን ቆም ብለው እያጤኑት የሚገኙት አገሪቱ የብድር እፎይታን በተመለከተ በዓለም አቀፍ ደረጃ ንግግር የጀመረች በመሆኑ ነው።

ባለፈው ሐምሌ ወር የአይኤምኤፍ ቃል አቀባይ ጌሪ ራይስ በኢትዮጵያ የብድር ጉዳይ ላይ አንድ ከሚቴ በፍጥነት እንዲቋቋም ጥሪ አድርገው ነበር።

ይህም ከቡድን 20 እና ከፓሪስ ክለብ አበዳሪዎች ዘንድ ኢትዮጵያ ያቀረበችውን የብድር እፎይታ ጥያቄ እንዲመለከት ነበር።

መንግሥት የብድር መመለሻ እፎይታ ለማግኘት ንግግር መጀመሩ ስህተት አይደለም ይላሉ ባለሙያዎች።

በተለይም የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ ብዙ አገራት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸው ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ ለቢቢሲ አስተያየታቸውን የሰጡት የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ እንደሚሉት "ኢትዮጵያ ኮቪድን አልፈጠረችውም፡፡ … ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገራት የብድር እፎይታ ጊዜን መጠየቃቸው ምክንያታዊ አይደለም ማለት አልችልም" ሲሉ የኢትዮጵያን የብድር እፎይታ ጥያቄ አግባብነት ደግፈዋል።

ኢትዮጵያ ከውጭ የተበደረችው ዕዳ እስከ መጋቢት ወር ብቻ 29 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም የጥቅል አገር ውስጥ ምርት እድገት (ጂዲፒ) 27 ከመቶ የያዘ ነው።

08/16/2021

አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ህወሓት መደምሰስ አለባቸው፡- ዶ/ር ዓለሙ ስሜ
**************************
በወሎ ግንባር የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ህወሓት ለኢትዮጵያ የማይጠቅሙ በመሆናቸው መደምሰስ አለባቸው ብለዋል፡፡
የወያኔ እና ሸኔ ጥምረት ለኦሮሞና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ነው ያሉት ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ትህነግም ሸኔን በአንድ ላይ መደምሰስ አለባቸውም ነው ያሉት፡፡
የሸኔና የህወሓት ጋብቻ አዲስ ሳይሆን ህወሓት መንግሥት ሆኖም ሳለ ኦሮሞን ለማተራመስ ሲፈልግ ሸኔን ይመሩት እንደነበር ነው ያስታወሱት፡፡
አሸባሪው ህወሓት በግንባር ጀግንነት እንደሌለው የገለጹት ዶክተር ዓለሙ ለሚያሠራጨው የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ጆሮ ሳይሰጥ ህብረተሰቡ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት ወጣቶችን በሀሽሽ እያደነዘዘ እየላከ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ብዙ የአሸባሪው ታጣቂዎች እየተደመሰሱ የተሳካ ግዳጅ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ጦርነቱ በአጭር ጊዜ አልቆ ወደ ሀገር ግንባታ እንደንመለስ እንፈልጋለን ያሉት ዶ/ር ዓለሙ ሕዝቡም ልጆችን እየላከ፣ ስንቅ እያቀበለና እየተዋጋ አስደናቂ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
የሠራዊቱና የሕዝቡ ዝግጅት አሸባሪው ህወሓትን በአጭር ጊዜ ቀብሮ ሀገር ሰላም እንዲሆን የማድረግ አቅም እንዳለው መመልከታቸውንም ገልጸዋል፡፡
ለሀገር ክብር ሲሉ ቤትና ንብረት ጥለው በግንባር ላይ ያሉ ሚሊሻዎችን የልማት ሥራ ሕዝቡ እንዲሠራም ጠይቀዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡

08/16/2021

ዩኒሴፍ በአማራ ክልል ደባርቅ እና ደሴ ለሚገኙ 9 ሺህ 130 ተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ
******************
ዩኒሴፍ በአማራ ክልል ደባርቅ እና ደሴ ለሚገኙ 9 ሺህ 130 ተፈናቃዮች የምግብ፣ የጤና፣ የንፁህ መጠጥ ውኃ እና የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ በቀይ መስቀል በኩል ማድረጉን አስታውቋል።
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በአማራ ክልል ብቻ ወደ 674 ሺህ 492 የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ድርጅቱ ገልጿል።
ዩኒሴፍ በትዊተር ገጹ ባሰፈረው መልእክት፣ በተለይ ለሕፃናት የሕይወት አድን ድጋፎችን ለማድረግ እና አገልግሎቶችን ለማድረስ ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከሌሎች አጋሮች ጋር እየሠራ መሆኑንም አስታውቋል።

08/16/2021

ሐሳብዎን ያካፍሉን
እየፈፀሙት ያለውን ድርጊት በማየት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርኝነት የተፈረጁት ሸኔና ህወሓት አብሮ የመሥራት ጉዳይ አዲስ ባይሆንም እንደዚህ ህዝብን በናቀ መልኩ ግን በይፋ ይሆናል የሚል እምነት በብዙዎች ዘንድ አልነበረም፡፡
የህወሓት አገዛዝ ዘመን "ኦነግ" በሚል ታፔላ እስር ቤቶች የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የሚነገርባቸው ማዕከላት እስኪመስሉ ድረስ በኦሮሞ ተወላጆች መሞላታቸው፣ የኦሮሞ አርሶ አደሩን መሬት ለመቀራመት አዲስ ማስተር ፕላን በማርቀቅ ለዳግም ብዝበዛና ጭቆና ሲዘጋጅ በኦሮሞ ወጣቶች መስዋዕትነት ውጥኑ ሊከሽፍ መቻሉ የቅርብ ጊዜ ትውስታ መሆኑን በርካቶች ያነሳሉ::
ከዚህ በተጨማሪም በ2009 ዓ.ም ቢሾፍቱ ላይ የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ከተሰባሰበው ህዝብ በርካቶች በአሰቃቂ ሁኔታ መቀጠፋቸው፣ ከአብዲ ኢሌ የማፍያ ቡድን ጋር በመቀናጀት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኦሮሞዎች ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬ እንዲፈናቀሉ ካደረገ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ጋር በይፋ በጋራ ለመስራት በማወጅ በአሮሞ ህዝብ ስም እንቀሳቀሳለሁ በሚል ብቅ ያለው የአሸባሪው ሸኔ ግብር በርካቶችን አስገርሟል፡፡
ሸኔ ቀድሞ ሲያጥላላውና ሲንቀው ለነበረው አሸባሪው ህወሓት ያለውን ታማኝነት ማሳየቱን እንዴት ተመለከቱት? አገር ለማፍረስ የተጣመሩትን እነዚህን ኃይሎች ለማምከንስ ምን መደረግ አለበት ይላሉ?
ሐሳብዎን ያካፍሉን

08/16/2021

ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
በልዩ ልዩ የመገናኛ ብዙሃንናና ማህበራዊ ሚዲያዎች ከምሸቱ 1፡00 ሰዓት በደቡብ ጎንደር ዞን በእስቴ ወረዳ ልጫ ቀበሌ (ከእሰቴ 30 ኪሎ ሜትር ወደ አንበሳሜ ከተማ በሚወስደው መንገድ ላይ) የቀይ መስቀል አምቡላንስ ሁለት ኩንታል ብር፣ ስድስት ስናይፐር፣ ክላሽና ጥይት ይዞ ሲንቀሳቀስ እርምጃ መወሰዱን አስመልክቶ ዜና ተዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባደረገው ማጣራት ተግባሩን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አምቡላንስ ያልፈጸመዉና ድርጊቱን የፈጸመው ሌላ ተሽከርካሪና ድርጊቱን ፈጻሚዎችም በፀጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተረጋግጧል፡፡ ለበለጠ መረጃ የእስቴ ወረዳ የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤትን ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ገለልተኝነቱን ጠብቆ፣ የሁሉንም ወገኖች ዕምነት አግኝቶ በአሁኑ ወቅት በሁሉም የአገራችን ክፍሎች ሰብዓዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ መሆኑን፣ ሁሉም የሚዲያ ተቋማት እንዲያውቁና ከማህበራዊ ሚዲያ የሚያገኙትን መረጃ ከመዘገባቸው አስቀድሞ ከሚመለከተው አካል እንዲያረጋግጡ እንገልጻለን፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ዛሬም እንደትናንቱ፣ ነገም እንደዛሬው በአለቶችና በተግዳሮቶች መካከል በጽናት በመቆም ሰብዓዊ ተግባሩን ያከናውናል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት፣ አጋሮቹ፣ በጎፈቃኞቹና አባላቱ፤ እንዲሁም በግጭት አካባቢ የሚገኙ ሃይሎች ሁሉ በገለልተኝነትና ያለአድሎ ለምናከናውነው ሰብዓዊነትንና ሰብዓዊነትን ብቻ ማዕከል ላደረገ ተልዕኮአችን የዘወትር ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉልን እንጠይቃለን፡፡
በተለይም ለሰብዓዊነት ቅድሚያ በመስጠት በጎፈቃደኞቻችን፤ ሰራተኞቻችንና አምቡላንሶቻችን በሁሉም አካባቢዎች ለምናከናውነው ሰብዓዊ ተግባራችን የማህበራችን የቀይ መስቀል አርማ በአምቡላንሶቻችን ላይ በግልጽ የሚታይ መሆኑና የቀይ መስቀል አርማና መታወቂያ የያዙ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
ለሰብዓዊነት እንኖራለን፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፡፡

Address

Washington D.C., DC
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zena123 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share