01/31/2025
☞ብዙ ኃይማኖታዊያን ወላጅ አጥ ልጆችን ወይም አረጋውያንን ወይም የተቸገረን ስለመንከባከብ ይሰብካል:: የዝሙት ወይም ግድያ መጥፎነት ያስረዳል:: ይህንን የሚጠፋው ሰው አለ ብዬ አልገምትም:: የተቸገሩትን መርዳት ጥሩ መሆኑን አለማወቅ አልቸገረንም:: የተቸገሩትን የመርዳት ቢዝነስ ነው ያስቸገረው:: የዝሙት ክፋት ሳይሆን የጋብቻ ጣጣ መናር ነው ያስቸገረው:: ካገባ ልጁን እንዴት ያሳድግ? ይህንን የምናቀልበት ዘዴ ላይ እናውራ:: ከመጋባት በፊትም ከተጋቡ በሗላ መደበኛ ማማከር ይፈልጋል:: ሴትና ወንድ የተለያዩ ፍጥረቶች መሆናቸውን ያወቅሁት በጣም ቆይቼ ነው:: እንደኔ እንዴት አታስብም ብዬ መከራዋን ነበር ያበላሗት:: እሷም እንደኔ እንዴት አያስብም ብላ ቂም ይዛለች:: አንድነትን ልክ የፊዚካልና ሳይኮሎጂካል አንድነት አድርገን ነው እኮ መግባባት የተቸገርነው:: ወንዱም ሴቱም ጎሳቸው አንድ ነው:: ሰው የሚባል ዝርያ ናቸው:: Period. ፊዚካልና ኬሚካሉ ግን የሚገናኙበትና የሚለያዩበት ብዙ ነጥብ አለ:: ይህንን በመደበኛ ትምህርት ሳይቀር ቢሰጥ ጥሩ ነበር:: እኛ እኮ የጉብዝና ዕድሜያችንን የምንጨርሰው የሆነ ሀገር ካሪኩለም በመፍለጥና ተመልሶ እንደ አዲስ ኑሮን በመጀመር ነው:: እዚያና እዚህ የተበታተነ ስንትና ስንት የኢንጂነሪንግ ፎርሙላ ፈልጦ ግን የአናጺ ያህል ልምድ የለውም::
ወንድ ልጅ ከሴት ተቃውሞ አይወድም:: Appreciation ድክመቱ ነው:: ፈስህ ከለሩ ያምራል ቢባል ሁላ ይወዳል:: ግን ሽንት ቤት ለብቻህ ብትፈሳው የበለጠ ያምር ነበር እንዲባል ይፈልጋል:: ያም ሆነ ይህ ልጆቻችሁ ፊት አትፍሱ:: ውጪ ፍሬንዶቻቸው ጋር ሲጫወቱ "የአባቢን ፈስ ድምጽ በሰማኸው:: ካንተ ይበልጣል" ይባባሉባችሗል::
ስለምንድን ነበር የማወራው? በተፈጥሮ ስለምናውቀው ነገር በመንገር አታድክሙን:: How የሚለው ላይ እናተኩር:: እንዴት እናሻሽል ብለን ዘዴዎችን እያቀለልን እንሂድ::
☞Many religious people preach about caring for orphans or the elderly or the needy. They explain the evils of adultery or murder. I don't think anyone would be offended by this. We are not bothered by not knowing that helping the needy is good. It is the business of helping the needy that is the problem. It is not the evil of adultery that is the problem, but the difficulty of marriage. If he gets married, how will he raise his child? Let's talk about how to make this easier.: Before marriage and after marriage, regular counseling is needed.: I realized very late that men and women are different creatures.: I used to torment her by saying, "How can you not think like me?": And she would hold a grudge, saying, "How can you not think like me?": We have made unity in the face of the law as physical and psychological unity, and we have difficulty understanding it.: Men and women are the same race.: They are a species called humans.: Period. But there are many points where physics and chemistry meet and differ. It would be good if this were even taught in formal education. We end our youth by learning the curriculum of a country and starting a new life again. He has invented many engineering formulas scattered here and there, but he does not have the experience of a carpenter.
A boy does not like opposition from a woman. Appreciation is his weakness. He always likes it when someone says that your toilet is more beautiful. But he wants to be told that it would be more beautiful if you flushed the toilet yourself. In any case, do not flush in front of your children. When they play with their friends outside, they will tell you, "You should have heard your father's voice. He is better than you."
What was I talking about? Don't tire us by telling us about what we already know. Let's focus on the "how". Let's simplify the methods to improve.