VOA Amharic

VOA Amharic ቪኦኤ-አማርኛ ስለ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ አፍሪካ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ዓለም አቀፍ በዲጂታል፣ በራዲዮና በቴሌቪዥን ዜናና ዘገባዎችን ለአድማጭና ለተመልካች ያቀርባል።

09/15/2025

- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -
� የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሊንኮችን በመጫን ይከተሉን።
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/voaamharic
ኢንስታግራም - https://www.instagram.com/voaamharic
X - https://www.twitter.com/VOAAmharic
ዌብሳይት - https://amharic.voanews.com
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ፡- https://www.youtube.com/voaamharic
የስልክ መሥመራችን 202-205-9942 የውስጥ መሥመር 14 ነው።
� ቪኦኤ-አማርኛ ስለ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ አፍሪካ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ዓለም አቀፍ በዲጂታል፣ በራዲዮና በቴሌቪዥን ዜናና ዘገባዎችን ለአድማጭና ለተመልካች ያቀርባል።
VOA Amharic reaches our audience on digital, radio, and TV, delivering news and content about Ethiopia, Eritrea, Africa, and the United States. We will also be bringing you Health Shows, Youth Shows, Democracy Field, Women’s Shows, and Sports Shows on different days, stay tuned.

የባለ ሥልጣናት መፈታት ለደቡብ ሱዳን ውጥረት መርገብ ቁልፍ ጉዳይ ነው ተባለየደቡብ ሱዳን መንግሥት በሀገሪቱ የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ የታሰሩ ባለሥልጣናትን እንዲፈታ የምስራቅ አፍሪካ የል...
03/15/2025

የባለ ሥልጣናት መፈታት ለደቡብ ሱዳን ውጥረት መርገብ ቁልፍ ጉዳይ ነው ተባለ

የደቡብ ሱዳን መንግሥት በሀገሪቱ የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ የታሰሩ ባለሥልጣናትን እንዲፈታ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት መሪዎች ጥሪ አቅርበዋል።

የኢጋድ አባል ሀገራት ይኼንኑ የደቡብ ሱዳን ግጭት አስመልክተው ረቡዕ መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በበይነ መረብ ባደረጉት ስብሰባ የደቡብ ሱዳን መሪዎች ውጥረቱን ለማርገብ ውይይት እንዲጀምሩም ጠይቀዋል።

የደቡብ ሱዳን መንግሥት በሀገሪቱ የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ የታሰሩ ባለሥልጣናትን እንዲፈታ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት መሪዎች ጥ.....

03/14/2025

▶ በአፍሪካ የኅይል አቅርቦት ላይ ያተኮረውና በዋሽንግተን ዲሲ የተካሔደው ጉባኤ

የአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ የአፍሪካ ምኒስትሮች፣ ኢንቨስተሮች፣ የግል ገንዘብ አበዳሪዎች፣ እንዲሁም የአገልግሎትና የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ዓመታዊ ለሆነውና በአፍሪካ የኅይል አቅርቦት ላይ በሚያተኩረው ጉባኤ ላይ ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ ተገናኝተው ነበር።

“መፃኢው የአሜሪካ እና የአፍሪካ የኅይል ትብብር” በተሰኘ መሪ ቃል በተካሄደው ጉባኤ፣ በአዲሱ የትረምፕ አስተዳደር የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ የግል ኩባንያዎች የአፍሪካን የኤሌክትሪክ ኅይል ልማት፣ መሠረተ ልማት እንዲሁም የማዕድን ሃብትን በተመለከተ ያላቸውን ተሳትፎ እንደገና ለማዋቀር፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናትና የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ተወካዮች መክረዋል።

03/14/2025

▶ የልጆች ዲጂታላዊ ደኅንነት እንዴት ይጠበቅ?

የዘመናዊነት አንዱ ገጽታ የኾነው ከተማ እና ከተሜነት ሲስፋፋ፣ ኑሮን ለማሸነፍ እናትም አባትም ከቤት ውጭ ሥራ መሥራት ሲኖርባቸው፤ ሕፃናት ልጆች ገና በለጋ ዕድሜያቸው፣ በቴሌቪዥንና በእጅ ስልኮች ላይ በቀላሉ ለሚታዩ ምስሎች እና መተግበሪያዎች ተጋልጠዋል።

ኾኖም፣ ያልተገደበ የስክሪን ሰዓት አጠቃቀም፥ ለዐይን ሕመም፣ ለእንቅልፍ ዕጦት፣ ለትኩረት ማነስ፣ ለጠባይዕ ለውጥ እና አልፎ ተርፎም ለተለያዩ የአእምሮ ሕመሞች እንደሚያጋልጥ፣ የሕፃናት እድገት ባለሞያዎች ይናገራሉ።

ነዋሪነታቸውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረጉት የቴክኖሎጂ ባለሞያዋ ወሮ. ነጻነት ቦጋለ፣ ወላጆች በተለይ በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ላይ በሚያጋሯቸው የልጆቻቸው ምስሎች እና ስኬቶች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ይመክራሉ።

ወሮ. ነጻነት፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ አድርገዋል፤ ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በዶ.ር ደብረ ጽዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን ወቀሰየኢትዮጵያ መግሥት በዶ.ር ደብረ ጽዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሷል ማለቱን የሀገር ...
03/14/2025

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በዶ.ር ደብረ ጽዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን ወቀሰ

የኢትዮጵያ መግሥት በዶ.ር ደብረ ጽዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሷል ማለቱን የሀገር ውስጥ ብዙኅን መገናኛ ዘገቡ።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት፣ በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ አዲስ አበባ ለሚገኙ ዲፕሎማቶች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸው፣ ለፕሪቶሪያው ስምምነት መተግበር የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ድጋፍ መጠየቃቸውን የመንግሥት ብዙኅን መገናኛዎቹ ዘግበዋል፡፡

በዶ/ር ደብረ ጽዮን የሚመራው ቡድን ስምምነቱን ጥሷል መባሉን ማስተባበሉን በማስተባበል፣ በአንጻሩ ስምምነቱ የተጣሰው በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን ነው ሲል በተደጋጋሚ ምላሽ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ በሌላ በኩል የአፍሪካ ኅብረት፣ በክልሉ ባለው ውጥረት ተሳታፊ የሆኑ አካላት ራሳቸውን እንዲያቅቡና ችግሩ በውይይት እንዲፈታ ጠይቋል፡፡

በህወሓት የፖለቲካ አንጃዎች መካከል በተፈጠረው ሽኩቻ እጇ እንዳለበት በአቶ ጌታቸው የተከሰሰው የኤርትራ መንግሥት ክሱን አስተባብሏል።

የኢትዮጵያ መግሥት በዶ.ር ደብረ ጽዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሷል ማለቱን የሀገር ውስጥ ብዙኅን መገናኛ ዘገቡ። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የትግ....

ተመድ  የሶሪያ ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቀረበየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶሪያ ልዩ መልዕክተኛ፣ ከፕሬዝደንት ባሽር አል አሳድ ሥልጣን መወገድ ተከትሎ ባለፉት ሦስት ወራት ዐዲስ በተቀሰቀሰው...
03/14/2025

ተመድ የሶሪያ ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቀረበ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶሪያ ልዩ መልዕክተኛ፣ ከፕሬዝደንት ባሽር አል አሳድ ሥልጣን መወገድ ተከትሎ ባለፉት ሦስት ወራት ዐዲስ በተቀሰቀሰው ግጭት እየታመሰች ባለችው ሀገር ሁከቱ እንዲቆም ተማጸኑ፡፡ የሰላማዊ ዜጎች ደኅንነት እንዲጠበቅም ጥሪ አቀረቡ፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ ጌር ፔደርሰን ጥሪያቸውን ያቀረቡት፣ የዲሞክራሲ ደጋፊዎች ሀገሪቱን ለዐስርት ዓመታት ወደ ዘለቀው የርስ በርስ ጦርነት ያመራው ጸረ አሳድ ተቃውሞ የተጀመረበት 14ኛው ዓመት መታሰቢያ በሆነው በዛሬው ዕለት ነው፡፡

“የለውጥ ጥያቄ ጭካኔ የተሞላበት ከፍተኛ ብጥብጥ ገጥሞታል፣ በዘመናችን እጅግ አሰቃቂ ወደ ኾነ ግጭት አምርቷል” ያሉት ፔደርሰን “ግጭቱ ጥልቅ የሆነውን አስከፊውን የሰው ልጅ ጭካኔ አጋልጧል።” ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶሪያ ልዩ መልዕክተኛ፣ ከፕሬዝደንት ባሽር አል አሳድ ሥልጣን መወገድ ተከትሎ ባለፉት ሦስት ወራት ዐዲስ በተቀሰቀሰው ግጭት እየታመሰች ባለችው ሀገር .....

03/14/2025

🎙 ዜና እፍታ

- የኢትዮጵያ መግሥት በዶ.ር ደብረ ጽዮን የሚመራው የሕወሓት ቡድን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሷል ማለቱን የመንግሥት መገናኛ ብዙሀን ተዘገበ።

- በሙስና ተጠርጥረው ተጠርጥረው የታሰሩት የሐዋሳ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተፈረደባቸው።

- ከቻይና የሚሳይል ነዳጅ መስሪያ ቁልፍ ግብአቶችን ጭናለች ተብሎ በዜና ዘገባዎች የተጠረጠረው ሁለተኛው የኢራን ጭነት መርከብ ወደ ኢራን እያመራች መሆኑን የቪኦኤ ልዩ የትንታኔ ዘገባ አመልክቷል፡፡

✅ ቪኦኤ አማርኛን በዋትስአፕ ይከታተሉ https://whatsapp.com/channel/0029VaYrYaWDjiOTnIzDG73B

⏺️  ከቻይና የሚሳይል ነዳጅ መስሪያ ቁልፍ ግብአቶችን ጭናለች ተብላ በምዕራባዊያን የዜና ዘገባዎች የተጠረጠረችው ሁለተኛዋ የኢራን መርከብ ወደ ኢራን እያመራች መሆኑን የቪኦኤ ልዩ የትንታኔ ...
03/14/2025

⏺️ ከቻይና የሚሳይል ነዳጅ መስሪያ ቁልፍ ግብአቶችን ጭናለች ተብላ በምዕራባዊያን የዜና ዘገባዎች የተጠረጠረችው ሁለተኛዋ የኢራን መርከብ ወደ ኢራን እያመራች መሆኑን የቪኦኤ ልዩ የትንታኔ ዘገባ አመልክቷል፡፡

የመርከብ እንቅስቃሴ ክትትል ድረ-ገጾች እንደሚያሳዩት የኢራን ባንዲራ የሚያውለበልበው ጃይራን የተባለው የጭነት መርከብ፣ ከቻይና ይነሳል ተብሎ ከተጠበቀበት ጊዜ ከአንድ ወር በኋላ ዘግይቶ ባለፈው ሰኞ መነሳቱ ተጠቅሷል፡፡

በጥር እና በየካቲት ዘ ፋይናንሺያል ታይምስ፣ ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል እና ሲ ኤን ኤን ባቀረቧቸው ዘገባዎች፣ ቴህራን በሚሳይል ነዳጅ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውለውን 1,000 ሜትሪክ ቶን ኬሚካል (ሶዲየም ፐርክሎሬት) ለመጫን ከምትጠቀምባቸው ሁለት መርከቦች መካከል ጃይራን አንዱ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ከቻይና የሚሳይል ነዳጅ መስሪያ ቁልፍ ግብአቶችን ጭናለች ተብላ በምዕራባዊያን የዜና ዘገባዎች የተጠረጠረችው ሁለተኛዋ የኢራን መርከብ ወደ ኢራን እያመራች መሆኑን የቪኦኤ ልዩ የትንታ...

03/14/2025

▶️ የቆዳ ላይ ቀላል እብጠት መሰል ነገሮች እና የቆዳ ቀለምን የሚለውጡ ምልክቶች ለጤና ያሳስቡ ይኾን?

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የቆዳ ቀለምን የሚለውጡ ፣በእንግሊዝኛው አጠራር ‘ሞሎች’ በአንዳንድ ባህሎች ዘንድ እንደ ውበት ምልክት ይታያሉ። በተለይ የጥቁር ዝርያ ባላቸው ሕዝቦች ውስጥ፣ በስፋት የሚታዩና የተለመዱ ናቸው።

በአንጻሩ፣ ለጤና መታወክ ይዳርጉ ይኾን? በሚል ለጭንቀት የሚጋለጡ ወገኖች የሚሰሟቸውን ስጋቶች የሚያነሣው ጁማ ማጃንጋ፣ ለእነዚኽ እና ተያያዥ ጥያቄዎች ምላሽ ፍለጋ፣ ከናይሮቢ ኬንያ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ

አይኤምኤፍ እና ኢትዮጵያ በዋጋ ግሽበት ትንበያ ተለያዩ ትንበያዎቹ "የተለያዩ ብቻ ሳይኾኑ ከእውነታውም የራቁ ናቸው" - ባለሞያዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ)፣ በቅርቡ ስለ ኢትዮ...
03/14/2025

አይኤምኤፍ እና ኢትዮጵያ በዋጋ ግሽበት ትንበያ ተለያዩ
ትንበያዎቹ "የተለያዩ ብቻ ሳይኾኑ ከእውነታውም የራቁ ናቸው" - ባለሞያ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ)፣ በቅርቡ ስለ ኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ያወጣው ትንበያ፣ እ.ኤ.አ በ2025፣ 25 ከመቶ መድረሱን ይገልጻል፡፡ የዋጋ ንረቱ አኹን ካለበት ሁለት አኀዝ ወደ ነጠላ አኀዝ ለመውረድ እስከ 2028 ሊቆይ እንደሚችልም አይኤምኤፍ ተንብይዋል፡፡

. ትንበያዎቹ "የተለያዩ ብቻ ሳይኾኑ ከእውነታውም የራቁ ናቸው" - ባለሞያ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ)፣ በቅርቡ ስለ ኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ያወጣው ትንበያ፣ እ.ኤ.አ በ2025፣ ...

03/14/2025

▶️ የኢትዮጵያውያት ሴቶች ጥያቄ ምንድን ነው? - የአድማጭ ተመልካቾች አስተያየት
መጋቢት፥ የዓለም አቀፍ ሴቶች ወር ነው። ሴቶች ትምህርትንና ሥራን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች እኩል ዕድል እንዲያገኙ ለማብቃት በመላ ዓለም የሚደረጉ ጥረቶች፦ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በጦርነት እና በሌሎችም ሰው ሠራሽ ምክንያቶች መጓተታቸውን፣ በሴቶች ላይ አተኩረው የሚሠሩ ተቋማት ያወጧቸው ሪፖርቶች ያሳያሉ።
ዘንድሮም፣ ወርኃ መጋቢት(ማርች 8)፥ “ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ቃል በመላው ዓለም እየታሰበ ይገኛል።
በዐዲስ አበባ የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ኬኔዲ አባተ፣ በርእሰ መዲናዪቱ ጎዳናዎች ላይ ተዘዋውሮ፤ ለመኾኑ የኢትዮጵያውያት ሴቶች ጥያቄ ምንድን ነው? የሴቶች እኩልነት እንዲሰፍን ምን ቢደረግ ይበጃል? በማለት ጠይቆ ያገኘውን ምላሽ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

📷በፓኪስታን  በሽምቅ ተዋጊዎች ጥቃት የደረሰበት ባቡር ተሳፋሪዎች  የጸጥታ ሓይሎች ደርሰውላቸው ደቡብ ምዕራባዊ ባሉቺስታን ክፍለ ግዛት ማች ከተማ የሚገኝ የባቡር ጣቢያ ሲገቡ። በሁከት በሚታ...
03/14/2025

📷በፓኪስታን በሽምቅ ተዋጊዎች ጥቃት የደረሰበት ባቡር ተሳፋሪዎች የጸጥታ ሓይሎች ደርሰውላቸው ደቡብ ምዕራባዊ ባሉቺስታን ክፍለ ግዛት ማች ከተማ የሚገኝ የባቡር ጣቢያ ሲገቡ።
በሁከት በሚታመሰው ክፍለ ግዛት በታጣቂዎች የታገተው ባቡር ተሳፋሪዎች ያሳለፉትን የጭንቅ ጊዜ ለቪኦኤ በዝርዝር አውስተዋል፡፡ የፓኪስታን የጦር ሠራዊት ለበርካታ ሰዓታት ባካሄደው ታጋቾቹን የማስለቀቅ ርምጃ ሠላሳ ሦስት ሽብርተኞችን መግደሉ ተዘግቧል፡፡ የጦር ሠራዊቱ ትላንት ረቡዕ ማታ የመጨረሻውን ርምጃ ከመውሰዱ አስቀድሞ 200 የሚሆኑ መንገደኞች መለቀቃቸውን ቀደም ብለው የወጡ ሪፖርቶች አመልክተው ነበር፡፡

Address

330 Independence Avenue SW
Washington D.C., DC
20237

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when VOA Amharic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

ቪኦኤ አማርኛ

የቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ አገልግሎት በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ወደ ኢትዮጵያና ወደ ኤርትራ የራዲዮ ሥርጭቶችን ያስተላልፋል፡፡ የአማርኛ ፕሮግራም የሚሠራጨው ከአንድ መቶ ሚሊየን በላይ የሚሆን ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚኖር ሕዝብና እንዲሁም በመላ ዓለም ለሚገኙ ምንጮቻቸው ሁለቱ ሃገሮች ለሆኑ ማኅበረሰቦች ነው፡፡ አፋን ኦሮሞ ፕሮግራም የታለመው ኦሮሚያ ውስጥ ለሚኖሩ ከአጠቃላዩ የሕዝብ ቁጥር 37 ከመቶ የሚሆነውን ለሚሸፍኑ ኢትዮጵያዊያን ሲሆን ትግርኛ ፕሮግራም ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ይደመጣል፡፡