11/01/2025
ከግብፅ ኢትዮጵያ ትቀርብህ ነበር።
እኔ የፈራሁት ግብፅ ወታደራዊ ቤዝ እከፍታለሁ ብትል ብዬ ነበር፤ ግን እንደዛም አልሆነም! ምክንያቱም እዚህ ጦርነት ላይ ግብፅ እጁዋን አታስገባም! ምን አይነት ጣጣ ይዞባት እንደ ሚመጣ ታውቃለች! መጠነኛ የመድሃኒትና የጦር ድጋፍ ብታረግላት ነው።
ግብፅ ከኤርትራ ይልቅ ኢትዮጵያ እንደምጠቅማት ታውቃለች ከኤርትራ ጋር የ100 ዶላር የንግድ ስምምነት እንኳ የላቸውም! ግንኙነታቸው ፖለቲካዊ ነበር እሱም ቢሆን ሊሳካ አልቻለም።
ኢሳያስና አልሲሲ በተገናኙ በሰአታት ውስጥ የጅቡቲና የሶማሌ ፕሬዚዳንት ተገናኝተዋል። ቀጠናው ስጋት ላይ ነው። ካላበድክ በቀር ከ130 ሚሊዮን ህዝብ ጋር ልግጠም አትልም! በዚህ በኩል ደሞ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ የተባበሩት አረቦች ዝምታን መምረጣቸው ከዚህ ነገር ጀርባ እጃቸው እንዳለ ማሳያ ነው!
ኢሳያስ ከግብፅ መልስ ከኢትዮጵያ ጋር ይደራደራል ብዬ አስባለሁ። ያ ካልሆነ ግን የኢሳያስ መንግስት ይፈርስና ኤርትራ ለሁለት መከፈልዋ ወይም ድጋሚ ከኢትዮጵያ ጋር ዳግም መጠቃለሉዋ አይቀርም! አብይ አህመድ ቆቅ ነው እንዲ አይነት የሴራ ፖለቲካ እንደ ዳንቴል ሰፍቶ ነው ሚያለብሰህ።
Via Tina Bekele