01/16/2026
የሀዘን ዜና፦ ተወዳጁ የኪነጥበብ ባለሙያ ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
በኢትዮጵያ የጥበብ ዓለም ውስጥ ስመጥር እና በሁላችንም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበረው ባለሙያ ነጻነት ወርቅነህ (ነፂ) ባደረበት ድንገተኛ ከዚህ ዓለም መለየቱን በከፍተኛ ሀዘን ሰምተናል።
ነፃነት ወርቅነህ በተለይም በኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን ለበርካታ ዓመታት የሚተላለፈው በብዙ ቤቶች ዘንድ በሚወደው የቤተሰብ ጨዋታ" ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢነቱ ይታወቃል።
ከፕሮግራም አቅራቢነቱ ባሻገር፣ በበርካታ ፊልሞች ላይ ባሳየው ድንቅ የትወና ብቃቱ እና ልዩ በሆነው የሰው አክባሪነቱ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ነበረው።
የሰው ልጅ ህይወት እንዲህ ናት፤ ትላንት ማታ "ቻው" ብሎ የተለየን ሰው፣ ዛሬ በቤቱ በዛው ላይመለስ ይሄዳል ብሎ ማን ይገምታል? ነፂ የኛ ምስኪን፣ ነፂ የኛ የዋህ... እንዲህ በድንገት መለየትህ መላውን የጥበብ ቤተሰብና አድናቂዎችህን በሀዘን ሰበር አድርጎናል።
ነፃነት ወርቅነህ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት ነበር። ባበረከታቸው ስራዎችና በደግነቱ ሁልጊዜም በልባችን ሲታወስ ይኖራል።
ለባለቤቱ፣ ለልጆቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለመላው የጥበብ አፍቃሪዎች ፈጣሪ መጽናናትን እንዲሰጥልን እንመኛለን።
ነፍስህን በገነት ያኑራት!
Tigray