Kurat News ኩራት

Kurat News ኩራት Kurat NEWS-tube ኩራት ቲዩብ

የ32 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች ፤ የአዲስ አበባና የኦሮምያ የአስተዳደር ወሰን ውዝግብን እንዲፈታ የተቋቋመው ኮሚቴ ውጤታማ አልሆነም - Wazemaradio
12/27/2019
የ32 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች ፤ የአዲስ አበባና የኦሮምያ የአስተዳደር ወሰን ውዝግብን እንዲፈታ የተቋቋመው ኮሚቴ ውጤታማ አልሆነም - Wazemaradio

የ32 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች ፤ የአዲስ አበባና የኦሮምያ የአስተዳደር ወሰን ውዝግብን እንዲፈታ የተቋቋመው ኮሚቴ ውጤታማ አልሆነም - Wazemaradio

ዋዜማ ራዲዮ- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የኦሮምያ ክልልን የአስተዳደር ወሰን ውዝግብን በመፍታት እጣ ወጥቶባቸው እንዳይተላለፉ የተደረጉ የጋራ መኖርያ ቤቶችን ጉዳይ እንዲፈታ .....

12/26/2019

በደቡብ ክልል ያልተመለሱ የክልልነት ጥያቄዎችና የወላይታ ዞን ግፊት
25 December 2019
ብሩክ አብዱ
የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ በደቡብ ክልል ምክር ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2011 ዓ.ም. ተቀባይነት አግኝቶ በምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ሔለን ደበበ በተጻፈ ደብዳቤ ሕዝበ ውሳኔ ይደረግ ዘንድ፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ በቀረበ ማግሥት በርካታ የክልልነት ጥያቄዎች ከተለያዩ የክልሉ ብሔሮች ሲቀርቡ ተስተውለዋል፡፡ በጠቅላላው ከአሥር በላይ የሆኑት እነዚህ ጥያቄዎች በየብሔሮቹ የዞን ምክር ቤቶች ፀድቀው በክልል ምክር ቤት ሕዝበ ውሳኔ ከሚጠይቅ ደብዳቤ ጋር በአባሪነት የተላኩ ቢሆንም፣ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጥያቄዎችን አንስቶ በአጀንዳነት ለመወያየት ድፍረቱን አላገኘም፡፡

እነዚህ የክልል እንሁን ጥያቄዎች ለክልሉ ምክር ቤት ከቀረቡ አንድ ዓመት የሞላቸው ሲሆን፣ የአገሪቱን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ በመከተል ሕዝበ ውሳኔው እንዳይከናወን እንቅፋት አሳድረዋል ሲሉ ጥያቄዎቹን ያቀረቡት ዞኖች የክልሉን መንግሥትና ከፍተኛ ኃላፊዎቹን ሲወቅሱ ይደመጣል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዲሪ) ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 47 ንዑስ አንቀጽ 3 ሥር እንደሚደነግገው፣ በዚያው አንቀጽ ከተዘረዘሩት ዘጠኝ ክልሎች በተጨማሪ የአገሪቱ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በፈቀዱ ጊዜ የራሳቸውን ክልል ማዋቀር ይችላሉ፡፡ ይኼም በጠያቂ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች ወይም ሕዝቦች ምክር ቤት ቢያንስ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ፀድቆ ለክልል ምክር ቤት በሚቀርብ የሕዝብ ውሳኔ አስፈጻሚነት በአንድ ዓመት ውስጥ የሚከናወን እንደሆነ ሕገ መንግሥቱ ይደነግጋል፡፡ የሕዝበ ውሳኔውን ውጤት ተከትሎ የሚፈጠረው አዲስ ክልል የፌዴራሉ መንግሥት አባል ሆኖ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይቀጥላል፡፡

ሆኖም ክልሉ በአንድ ዓመት ውስጥ ይኼንን ማድረግ ባይችል የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ለማጠናከር ሥልጣንና ተግባሩን ለመዘርዝር የወጣው አዋጅ ቁጥር 251/1993 የፌዴሬሽን ምክር ቤት የብሔር፣ ብሔረሰቦች ወይም ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን በተመለከተ የሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን እንደሚኖረው በማተት፣ የክልል ምክር ቤቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ክልል የመመሥረት ጥያቄዬን አልመለሰልኝም የሚል ግን ጥያቄውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በጽሑፍ እንደሚያቀርብ በመጥቀስ፣ ‹‹ምክር ቤቱ በዚህ መልኩ በቀረቡለት ጉዳዮች ላይ በሁለት ዓመት ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፤›› ይላል፡፡

በዚህ ድንጋጌ መሠረት እስካሁን ጥያቄውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀረበ አካል ባይኖርም፣ የደቡብ ምክር ቤት ጥያቄያችንን እያጓተተብን ነው ያሉ የወላይታ ዞን ተወካዮች የሕዝቡን ጥያቄ ለማስመለስ በማለት ኮሚቴ አቋቁመው፣ ጥያቄውን ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እንዳሉ ሲገልጹ ይደመጣሉ፡፡

ይኼንን ዝግጅትና ፍላጎት የዞኑ የተለያዩ የኅብረተሰብ ተወካዮች ከሳምንት በፊት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በነበራቸው ውይይት ሲገልጹም ተስተውሏል፡፡ አንድ መቶ ያህል የወላይታ ዞን ተወካዮች የብሔሩን የክልልነት ጥያቄ በተመለከተ ለመወያየት በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት፣ በክልልነት ይመለሳሉ ተብለው የሚጠበቁ ጥያቄዎችና ይገኛሉ ተብለው የሚጠበቁ ጥቅሞችን መመለስና ማስገኘት የሚቻልባቸው አማራጮች ላይ ለመነጋገር የቀረበላቸውን ሐሳብ ውድቅ በማድረግ፣ የሕዝቡን ጥያቄ ከመመለስ ውጪ አማራጭ እንደማይኖር በማሳበብ ጥያቄው ሕገ መንግሥታዊ መንገዱን ተከትሎ የማይፈጸም ከሆነ፣ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም አስገንዝበው ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተወካዮቹ ጋር በነበራቸው ውይይት አማራጭ ሐሳቡ ላይ ለመወያየት ቢያስቡም፣ እነዚህ ጥያቄዎች መነሳት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ የክልሉ ምክር ቤት ጥያቄዎቹን በቀጥታ ከመመለስ ይልቅ አማራጮችን አይተን የሕዝቡን ጥያቄ እንፍታ በማለት ጥናት በማስጠናት መፍትሔዎችን ለመጠቆምም ሞክሯል፡፡ ሃያ አጥኚ ባለሙያዎችን ባካተተ ቡድን ተጠንቶ ይፋ የተደረገው ሰነድ በጥናቱ የተካተቱ ሰዎች የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና መሰል ጉዳዮች ከተፈቱላቸው በደቡብ ክልል መቆየትን እንደሚመርጡ ገልጿል፡፡ ስለዚህም በአንደኝነት የተቀመጠው የጥናት ምክረ ሐሳብ ክልሉን ባለበት ማቆየት የሚል ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ክልሉን ለሁለት ወይም ከአምስት ባልበለጡ የተለያዩ ክልሎች መክፈል፣ ካልሆነም የክልልነት ጥያቄዎችን ማቆየት የሚሉ ምክረ ሐሳቦችን አቅርቧል፡፡

ይኼ ጥናት በተለያዩ የክልሉ ዞኖች መርሐ ግብር ተይዞለት ምክክር የተደረገለት ቢሆንም፣ በበርካቶች ትችት የቀረበበትና ተቀባይነትን ያላገኘ ነበር፡፡ ከዚህ ባለፈም የጥናቱንና የአጥኚዎቹን ተዓማኒነትና የሙያ ብቃት የሚጠይቁ ድምፆች ተደምጠዋል፡፡

እነዚህን አማራጮች ወደ ጎን በመተው የክልልነት ጥያቄዎችን ያቀረቡ ዞኖች አሁንም እንዲፈጸምላቸው እየጠየቁ ሲሆን፣ በጥያቄዎቹ ላይ የፌዴራል መንግሥት ያለውን ትክክለኛ አቋም እንዲገልጽም ጥሪዎች ሲቀርቡበ ተደምጠዋል፡፡

የክልልነት ጥያቄያቸውን ለደቡብ ምክር ቤት ካቀረቡ ታኅሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. አንድ ዓመት የሞላቸው የወላይታ ብሔር አባላት፣ አደባባይ ወጥተው የጥያቄያቸውን መዘግየት በማውገዝ የፌደራል መንግሥት ጣልቃ በመግባት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ በቀኑ የፌደራል መንግሥት አቅጣጫ አስቀምጦ እንዲያስፈጽም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጥያቄው ከቀረበ ከአንድ ዓመት በላይ እንደሆነው በመግለጽ አግባብ አይደለም ብለው የኮነኑት አቶ ዳጋቶ፣ ይኼም የክልሉ ምክር ቤት ዝምታ ሕዝቡን አስቆጥቷል ብለዋል፡፡

ይኼንን ቁጣውን ለመግለጽ በርካታ የወላይታ ሕዝብ ዓርብ ታኅሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. አደባባይ የወጣ ሲሆን፣ በመከላከያ ጣልቃ ገብነት ሠልፉ ሳይደረግ ቀርቷል፡፡

ታኅሳስ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ይኼንን በማስመልከት መግለጫ ያወጣው የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ወሕዴግ) ‹‹የወላይታ ሕዝብ በክልል ደረጃ ለመደራጀት ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ በጠበቀ ሁኔታ ጥያቄ ከቀረበ ከዓመት በላይ ሆኗል፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤትም ለጥያቄው ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ ሳይሰጥ ከዓመት በላይ ቆይቷል፤›› በማለት ምክር ቤቱ፣ ‹‹ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 47 የሚያዘውን በመጣስ የሚፈጽመው ድርጊት የመንግሥት አካላት ሕግን ምን ያህል በድፍረት እንደሚጥሱ በጥሩ ማሳያነት ያገለግላል ማለት ይቻላል፤›› ሲል ይወቅሳል፡፡

የምክር ቤቱ ምላሽ ካለመስጠት ሐሳቡን ተቀብሎ አፅድቆታል ከማለት ሌላ ትርጉም የለውም በማለት፣ በሌላ ወገን ደግሞ ምላሽ ሳይሰጥ መቆየቱ መከልከል ማለት ነው የሚል ምንም ዓይነት የሕግ ድንጋጌ የለም ሲል ክልል መመሥረትን ምክር ቤቱ በዝምታው ተቀብሎታል ብሎ ይደመድማል፡፡ ስለዚህም፣ ‹‹የደቡብ ክልል መንግሥት ለወላይታ ዞን የክልልነት ዕውቅና ሰጥቶ በክብር እንዲሸኝ እናሳስባለን፤›› ብሏል፡፡

በወላይታ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች አንዱ የሆነው የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) የብሔሩን የክልልነት ጥያቄዎች በሚመለከት ባወጣው ጥያቄ፣ ዞኑ አፅድቆ የላከው የክልል ጥያቄ በክልሉ መንግሥት ኢሕገ መንግሥታዊ በሆነ ሕገወጥ መንገድ እንዲታይ ታግዶ ቆይቷል ሲል ይወቅሳል፡፡

ዎብን በመግለጫው፣ ‹‹ይኼ አካሄድ ሕገ መንግሥቱ ያጎናፀፈውን የሕዝቦችን የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን ሉዓላዊ መብት አደጋ ላይ በመጣል አገሪቱን ለከፍተኛ የፖለቲካና የደኅንነት ቀውስ ውስጥ የሚከት አካሄድ በመሆኑ እንዲታረም፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠረው የዎላይታ ሕዝብ ግንቦት 9 ቀን 2011 ዓ.ም. በተደረገው ሰላማዊ ሠልፍ ከመጠየቁም ባለፈም፣ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የዎላይታ ሕዝብን ለማነጋገር በመጡበት ወቅት ራስን በራስ የማስተዳደር የክልል መዋቅር ጥያቄውን በሠለጠነ መንገድ በአንድ ድምፅ አቅርቧል፤›› ብሏል፡፡

መግለጫው በመቀጠልም፣ ‹‹ለዎላይታ ሕዝብ ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ የሚሰጥ አካል በመጥፋቱ የዎላይታ ዞን ምክር ቤት ኅዳር 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ባካሄደው ጉባዔ የዎላይታ ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ሕገ መንግሥታዊ መብት መታፈኑን አውግዟል፤›› በማለት፣ የክልሉ ምክር ቤት በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ሕዝበ ውሳኔውን ማካሄድ ሳይፈልግ መቅረቱን በመጥቀስ ኮንኗል፡፡

በመሆኑም፣ ‹‹የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 47 የተቀመጠው የአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ ነገ ታኅሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. የሚጠናቀቅ በመሆኑና የዎላይታ ሕዝብ ላለፈው አንድ ዓመት ባደረገው ትግል የራሱን ዕድል በራሱ የወሰነና በግልጽ በአደባባይ የገለጸ በመሆኑ፣ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ሕጋዊ ሒደቶችን አልፎ በአስቸኳይ ዕውቅና እንዲሰጥ ንቅናቄያችን አጥብቆ ያሳስባል፤›› ብሏል፡፡

እነዚህ የክልል ጥያቄዎች ከቀረቡለት ዓመት ቢሞላም ኅዳር 20 ቀን 2012 ዓ.ም. የተሰበሰበው የክልሉ ምክር ቤት፣ የክልልነት ጥያቄዎችን በአጀንዳነት ሳይመለከት የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለሥልጣን አዋጅን፣ የሸማቾች ጥበቃ ደንብና የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ኤጀንሲ ደንብን ተመልክቶ አፅድቋል፡፡

ከወላይታ ውጪ ለክልሉ ምክር ቤት በዞን ምክር ቤቶች ፀድቀው ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል የጉራጌ ኅዳር 17 ቀን 2012 ዓ.ም.፣ የካፋ ኅዳር 26 ቀን 2012 ዓ.ም. አንድ ዓመት የሞላቸው ሲሆን፣ የሃድያ ዞን ጥያቄ ታኅሳስ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. አንድ ዓመት ይሞላዋል፡፡

እነዚህን ጥያቄዎች ሳይመለከት እያለፈ ያለው የክልሉ ምክር ቤት ፍላጎት ምን እንደሆነ በግልጽ ባይነገርም፣ በተለያዩ ውይይቶች ጥያቄዎቹን ለማስቀረት እየጣረ ላለው የክልሉ መንግሥትና የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ጊዜ ለመግዛት በማሰብ ላይ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ይደመጣሉ፡፡ ከዚህ ባለፈም ጥያቄዎቹ መመለስ ከተጀመሩ መቆሚያ ስለማይኖራቸው፣ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሲመጡ የፌዴራል መንግሥቱ በሚችለው መንገድ ባለው አቅም ይፍታው ከማለትም ይመነጫል የሚሉ አሉ፡፡

ጥያቄው ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚሄድ ከሆነም ምላሽ ለማግኘት ሁለት ዓመታትን መጠበቅ ግድ ስለሚል፣ ይኼም ለመጀመርያው ፍላጎት ጊዜ መግዣ ሊሆን ይችላል የሚሉም አልታጡም፡፡

ሪፖርተር የክልሉን አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ሔለን ደበበንና ምክትል አፈ ጉባዔውን አቶ መንግሥቱ ሻንካን ለማናገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ ይሁንና ካሁን ቀደም አፈ ጉባዔዋ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት እንደማይፈልጉ ለሪፖርተር ገልጸው ነበር፡፡

"የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ላይ የሚለወጡ ነገሮች ይኖራሉ" የጠ/ሚ የኢኮኖሚ አማካሪ
12/25/2019
"የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ላይ የሚለወጡ ነገሮች ይኖራሉ" የጠ/ሚ የኢኮኖሚ አማካሪ

"የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ላይ የሚለወጡ ነገሮች ይኖራሉ" የጠ/ሚ የኢኮኖሚ አማካሪ

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችን ከጀመረች ሁለት ዓመት ሊሆናት ነው፤ ከዚህ አንጻር አሁንም በርካታ አሳሳቢ ነገሮችና የሚነሱ ጥያቄዎች አሉ። በእነዚህ ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮ...

12/21/2019
Abbay Media

Abbay Media

የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት ሰብሳቢ እስክንድር ነጋ ከፍራንክፈርት ጀርመን

ከዚህ በታች ያለውን የ ጎ ፍንድ ሚ ሊንክ በመጫን አባይ ሚዲያን ይርዱ
https://www.gofundme.com/f/support-abbay-media?
utm_source=customer&utm_medium=copy_link&utm_campaign=p_cp+share-sheet&fbclid=IwAR3eiKDOinEFIYgsZw4ksx_EQeKLE6oLePxgRtKkqa0eakJ70UUsqZj2ndg

12/20/2019
Ethiopian Broadcasting Corporation

Ethiopian Broadcasting Corporation

#ETV ኢትዮጵያ የመጀመርያ ሳተላይቷን ልታመጥቅ መሆኗን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የቀጥታ ስርጭትን ይከታተሉ

12/18/2019

#Wolayta Diaspora Elites Bilateral Negotiations of the current situation in Ethiopia particularly Wolayta, SNNPR.
Phase #2 If the current situation esculates and the government doesn't respect the CONSTITUTIONAL RIGHTS OF PEOPLE, the following will take place:

1. All Wolayta origin European Residents are closely in touch with EUROPEAN UNION diplomatic members to brief on the pressing matters.

2. Across USA, origin of Wolayta Diaspora are preparing to hold bilateral discussion on current affairs in WOLAYTA with Senators and Congress of their State.

Address

Washington D.C., DC

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kurat News ኩራት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Nearby media companies