01/22/2025
ታላቁ ሙህር
ታላቁ መምህር
የሃገር ባለውለታ
የኛም አለኝታ
በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
#ጠባቂ #መስካሪ እውነተኛ
#አገልጋይ አባት ተቆርቋሪ
ሁሌም ስለሷ የሚጨነቁ የሚያስቡ የሚያዝኑ #የሚናገሩ
#ዝም የማይሉ
#የማይፈሩ
#ደፋር ለፍሪዎች እና #ለሌባዎች መድሃኒት የሆኑ
እንኳን ተወለዱ መምህራችን (አባታችን )
#የመኪና ድምጽ በማይሰማበት፣ የመብራት ብርሃን ባልታየበት፣የከተማ ድምቀት በማይታወቅበት በገጠሯ ትንሽ መንደር ፣ የፊደል ቅርጽ ከማያወቁ በአዕምሮ ብሩህ ከሆኑት ደገኛ ቤተሰቦች የተወለደው ፣በራሱ ዓለም የሚኖራው ፣ ከእግዚአብሔር በቀር ለሌላ ሰው እሱነቱን መግልጽ የማይወደው እሱ የመወለዱን ቀኑን ዛሬ ያስባል።
#ለአመነበት እስከ ሞት ድረስ የታመነ፣ ታይታና ማስመስል የማይሆንለት፣ ለአመነበት እውነቱን ፊት ለፊት መጋፈጥ ባህሉ ያደረገ ፣ያ ሰው ፣ሰው ሁኖ የተገለጠበትን ቀን ሲያስብ፣ ለሀገሩና ለአሳደገችው ቤተክርስቲያን ምን ሰራሁ ብሎ እራሱን ይጠይቅና ፣ ቢያንስ ከቡድንና ከግሩፕ እሳቤ ወጥቼ በገባኝ ልክ ለእውነት እኖራለሁ እያለ ቃል ይገባል።
#አርቆ አስቦ መጭውን የመተንበይ አቅሙን አዳብሮ ለነገ፣ የሚነገር ታላቅ ሥራ ባይኖረው እንኳን፣ ክፉ ስህተት ሰርቶ በሚቆጭ ታሪክ ውስጥ ላለማለፍ ይጠቀቃል።
#ለወዳጆቹ የልብ፣ ለማይወዱት ጊዜ የሌለው ማለት እነሱን እያሰበ ጊዜ የማያጠፋ ክፉን በበጎ ብቻ መመለስ የሚወድ ያ ሰው እንደ ፈረጆቹ ለመሆን ልደቴ ነው ይላል። ምቀኝነትን የማይወድ የሌሎችን ማግኘት እንደራሱ የሚቆጠር፣ ንፉግ የማይባል። ለጋስ ለመባል የሚቀረው መወለዱን እያሰበ፣ያለፈበትን ያስታውሳል።
ስትኖር የማህበረ ሰቡን ባህል አክብር የሚል መመሪያን ይጠብቃል። ለታሪክና ለባህል ልዩ ክብር አለው።
ስለሚጽፈው የማይጨነቅ እውነት መሆኑን ብቻ ለማወቅ ጥረት የሚያደርግ ፣የዚህ ሰው ለየት ያለ ጽሁፎችን በትግስት ለምታነቡ ያመሰግናል።
ጥላቻና ክፋት የሚዘሩትን ሳይታገስ፣የቤቱን አጥር አጥብቆ ያሰናብታል። ለትሁታን ያለው ክብር ታላቅ የመሆኑን ያህል፣ ለትቢተኞች መድሃኒት ነው።
#በጎረፈበት አይነጉድም። የራሱ ምልእክታ አለው። ልእልተ ወይን/ እቴጌ / የሕይወቱ ምሥጢር ናት። ከእሷ በቀር እሱን የሚረዳው የለም።
#የግል ጉዳዩን ለሰው መንገር የማይወድ፣ በእግዚአብሔር ላይ ባለው እምነት የሚመካ ፣እግዚአብሔር ከብዙ ውጣ ውረድ የጠበቀው፣ ያ ሰው ፍረጅ ልሁን ብሎ ዛሬ ልደቴ ነው አለ።
#የዚህ ሰው ፌስቡክ ጓደኞች የሆናችሁ፣ በሚያነሳው ሃሳብ ቅር የተሰኛችሁ። ከያዘው እውነት እሺ ብሎ ስለማይልቅ ባለማንበብ ተባበሩ፣ ወደ ገጼም አትምጡ እያለ የሚመክረው ጸሐፊ ፣ልደቴ ነው ሲል እሰይ ተወልድክ፣ ልንለው ነው ወይስ ተወልድክብን፣ ሁለቱንም ለማለት እድል አለን። ምክንያታዊ መሆን ብቻ በቂ ነው።
#እድሜ በቁጥር ባይሆን፣ በሥራ ቢሆን ኑሮ እንዴት ጥሩ ነበር።
ጌታ ሆይ የሚነገር ሥራ ሳላከናውን ፣ተወለደ ሞተ ከሚል የመቀብር ላይ ጽሑፍ ጠብቀኝ፣ ሳይመቼኝም ሆነ ተመችቶኝ የሚነገርና የሚጠቅም መልካም ሥራ እንድሰራ እርዳታህ አይለየኝ።
#ከመንጋ አስተሳሰብ ያራቀኝንና የጠበቁኝ መልአክ ከእኔ አትለየው። ጦርነትንና ጦርኝነትን እንድጸየፍ ያደረገኝ አስተሳስብ የምንጊዜም ሀብቴ አድርገው።
ማስመሰልንና ታይታን እንደምጸየፋቸው እንዲያውቁ አድርግልኝ። ለሰው ፊት ማዳታላትን ፣ያለ ክብሩ ማወደስን የምጠላበትን መንፈስ ከእኔ እንዳይርቅ ጠብቅልኝ።
#መልካም ስራ ሳልራ አትውሰደኝ። የመልካም ሥራ እድል ከእኔ ከራቀ ግን ተሎ ውሰደኝ።
#የሰጠኸኝ ይበቃኛል ባርክልኝ። የጎደለውን መሙላት ፣ የተዛባውን ማቅ ናት የአንተ ነውና በአንተ ላይ ያለኝ እምነት ዛሬም ነገም ያው ነው። አለቀ ከተባለ ማንነት ታላቅ ማድርግ ታውቀበታለህ ምስክርም ነኝ።
#በህማሚ ጊዜ አስታማሚ፣ አካሚና መድኃኒት አንተ ነበርክ። ሌላው ሁሉ የአንተ ወኪልና መገለጫ ነው። ስለአደረክልኝና ስለምታደርግልኝ ሁሉ በደካማ አንደበቴ ፣ኃጢአት ባበሰቆለው ሰውነቴ፣ ቅድስናን በሚናፍቀው እኔነቴ አመስግንሃለሁ።
#አንተም እንደምታወቀው እኔም እንደማስበው በቻልኩት ሁሉ እውነት ለመናገር፣ በጎ ለመሥራት ሞክሬያለሁ።
በጨመርክልኝ ዓመት ያደርኩት ይህን እንደነበር ምስክር አትሻም። መጭውንም የማደርገው እንደዚሁ ነው።
እያዳንዱ የራሱ የሆነ የእውነት ሃሳብ አለኝ በሚልበት ዓለም እንደ ቃልህ እውነት መኖር፣ ጥላቻና መገፋት ቢበዛበትም ከአንተ የሚያርቀኝ ማንም የለም።
ስለ አንተ ተንቅፈንም፣ ተጠልተንም፣ መኖር የህሊና ሠላም አለው። አንተ እውነትና የሁሉም ስለሆንክ አንተን ሳስብ ልቤ በደስታ ይሞላል።
ጌታ ሆይ ሦስት መቶ ሥልሣ አምስት ቀን ተመልሼ በዚች ቀን በዚህ መሰል ምስጋና እስከማስብህ፣ ጥበቃህ አይለኝ።
#አፌን ለምስጋና አበርታው። ከመቅደስ በር ስቆም እውነት በሆነው ቤትህ የሥጋ ድካምና ፍርሐት ከቃልህ እንዳያጎለኝ አግዘኝ። እውነትን ሳልይዝ በቤትህ እንድቆም አትፍቀድልኝ።
ማጽደቅ ባልችል እንኳን ለሰዎች መሰናከያ እንዳልሆን በቸርነት ጥላ ከልለኝ።
#ጌታ ሆይ ከትሿ ገጠር አውጥተህ ከዓለም መሪዋ ዋና ከተማ እንድኖር ያደረከኝ እኔ ማነኝ። ?
#ቃላት ለምስጋናህ አጠሩኝ፣ አመጣጤን ሳስበው የማይገለጥ መጽሐፍ ሆነብኝ።
አንተ እንደምታውቅኝ እስከ ድካሜ ቻለኝ። እኔ እንደማወቅህ በቸርነት አኑሮኝ ። አሜን አሜን አሜን።