Bilal Communication

Bilal Communication as the voice of Ethiopian Muslims, Radio Bilal intends to propagate, inform and disseminate the truth about Islam and Muslims in general and Ethiopian Musl

https://www.bbc.com/amharic/articles/clj90k01keyo
03/01/2024

https://www.bbc.com/amharic/articles/clj90k01keyo

በኢትዮጵያ አብዮት ተካሂዶ ንጉሣዊው ሥርዓት ካበቃ እነሆ 50 ዓመት ሆነው። ለሥር ነቀሉ አብዮት መከሰት ምክንያት ከሆኑት መካከል የፊውዳሉ ሥርዓት የቆመበት የመሬት ሥሪት እና የብሔር ጥ....

Thank you my dear brother Mohammed Ferej. I wanted to express my heartfelt gratitude for the beautiful poem you crafted ...
09/26/2023

Thank you my dear brother Mohammed Ferej.

I wanted to express my heartfelt gratitude for the beautiful poem you crafted on the new Neshida titled “ Nur Amba” performed by Muaz and his associates .

Your ability to capture the essence of your recent journey to Medina and your love and admiration for the Prophet Mohammed ( SAW) in poetic form is truly amazing. Your poem has touched our hearts and allowed us to share in your spiritual experience.

Thank you for sharing your talent and your heartfelt emotions through this poem.

እጅህን:ቁርጥማት :አይንካህ !

ኑር አምባ | ዋሪዳ 6 | NUR AMBA | WARIDA 6 | NEW ETHIOPIAN MENZUMA\NESHIDA | አዲስ መንዙማ\ነሺዳ_____________https://youtu.be/LO62nTfndTMhttps://youtu.be/LO62nTfndTM*****...

09/03/2022

ኃፍረተ-ቢሷ ጎንደር‼
===============
✍ በዚህ አመት እንደ ጎንደርና ወለጋ በደም የጨቀዬ ምድር፣ ስሙ የጎደፈ፣ የአሸ'ባሪዎች መፈንጪያ የሆነ፣ ተዋርዶ ያዋረደ… የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። በወርሃ ረመዿን 27ኛ ቀን ላይ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በትውልድ ከተማችን ላይ እናካሂዳለን ብለው በዝግጅት ላይ የነበሩት የጎንደር ሙስሊሞች፤ ለአመታት በነ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበና አባ ኒዩኪሌር ሙስሊም ጠልነትን በተሰበኩ መርዘኛ የጎንደር አሸ'ባሪ ክርስቲያኖች የሽብር ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።

በተፈጸመው ዘግናኝ የሽ'ብር ጥቃት ከ50 በላይ ጾመኛ ሙስሊሞች ተገድለዋል፣ ከ115+ ሙስሊሞች ለከፍተኛ አካል ጉዳት ተዳርገዋል፣ 10+ መስጅዶች ወድመዋል፣ 119+ የሙስሊሞች ንብረት በታቀደና በተቀናጀ መልኩ ተዘርፏል፤ ወድሟል።

እስካሁን ድረስ ትክክለኛዎቹ ገዳዮችና ቀስቃሾቻቸው እንደነ ዮርዳኖስ ያሉ ጽን'ፈኞች በከተማዋ በነፃነት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። ለይምሰል አንድ ሰሞን የተወሰኑት ታስረው ተፈተዋል። ይሄው ዛሬ ላይ ችግሩ የተከሰተው በቀብር ቦታ ድንበር በማስመሰልና ከኃይማኖት ግጭት ይልቅ የግለሰቦች ጸብ በማስመሰል ጉዳዩን ለማሳነስና ትኩረት እንዳይሰጠው ለማድረግ ጥረዋል።

እውነታው ግን በጎንደር ሙስሊሞች ላይ ሚያዚያ 28, 2014 E.C. ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት እስከ ደባርቅ ድረስ የተፈጸመው የሽ'ብር ጥቃት፤ ለአመታት በጽን'ፈኛ የኦርቶዶክስ ክርስትና ሰባኪዎች የተሰበከ፣ የታቀደበትና በቅንጅት የተሠራ፣ በወቅቱ የጸጥታ አካላት ድጋፍ ጭምር የነበረው፣ በጦር መሳሪያ የታገዘ አደገኛና ዘግናኝ የመስቀል ጦረኞች የሽ'ብር ጥቃት ነበር።

ባለስልጣኖቹ ይሄንን ቢሸፋፍኑትም መሬት ያለው ጥሬ ሐቅ ግን ከዚህ የዘለለ አይደለም። አሁንም እንላለን! መሸፋፈኑ ይቅርና አጥፊዎች ለፍርድ ቀርበው ተበዳዮች መካስ አለባቸው።
መሸፋፈኑ ለጊዜው ከተጠያቂነት ሊያስመልጣችሁ ቢችልም፤ የግፈደ ምድር ለሆነችው ጎንደር ታሪካዊ ጥላሸትን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚዛመት ጥላቻና በቀልን እያወረሳችኋት መሆኑን አትዘንጉ። መጥፎ አሻራ ጥላችሁ ከማለፋችሁ ይልቅ ማፍበስበሱ ይቅርና ትክክለኛውን ፍትሕ አስፍኑ።


Cc:
===
Gondar City Prosperity Party /GPP/
Ethiopian Human Rights Council
Gondar city communication
Amhara Prosperity Party /APP/
Amhara Communications
Amhara Police Commission
||
t.me/MuradTadesse

ወገኖቻችንን በግፍ የሚገድለው መንግስት ለፍርድ ይቅረብ! የፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን ዋሽንግተን ዲሲOctober 3, 2016አረመኔው የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ ዜጎቹን እየገደለ ነው።በማን አ...
10/03/2016

ወገኖቻችንን በግፍ የሚገድለው መንግስት ለፍርድ ይቅረብ!

የፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን ዋሽንግተን ዲሲ
October 3, 2016
አረመኔው የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ ዜጎቹን እየገደለ ነው።በማን አለብኝ መርህ በዘፈቀደ የሚራመደው መንግስት ከእስር እና ድብደባ (ቶርቸር)ወደ ግድያ እርምጃ ከተሸጋገረ አንድ ሙሉ ዓመት ሊያስቆጥር ነው። ከአምስት ዓመት በፊት በሙስሊሞች የተጀመረው ሰላማዊ ትግልም ሆነ የጀግናዉ የኦሮሞዉና የአማራዉ ሕዝብ ያነሳዉ የመብት ጥያቄ ሰላማዊ ምላሽ ባለማግኘቱም የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ እንቢተኝነት እንዲሸጋገር አድርጎታል።
ህዝባዊ ተቃውሞ በመላው አገሪቱ ከተሞች ውስጥ ተደጋግሞ በስፋት ተደርገዋል። የህዝብ ቅሬታን አላዳምጥም ያለው ፋሽስት መንግስት ከመቸውም በላይ አጣብቂኝ ውስጥ በመግባቱ አጥፍቶ ለመጥፋት ቆርጦ የተነሳ ይመስላል።
ህገ መንግስቱ የሚፈቅደውን መብታቸውን የጠየቁ ወገኖቻችን ሁሉ ባደባባይ በግፈኛው መንግስት እየተረሸኑ ነው። በኦጋዴን በጎንደር እንዲሁም በኦሮሚያ በአማራ እና በደቡብ ክልሎች በርካታ ወገኖቻችን በግፍ ተገድለዋል።
በተለይ በእለተ እሁድ መስከረም ሀያ አምስት ሁለት ሽህ ስምንት በአገራችን አቆጣጠር በብሾፍቱ (ድብረ ዘይት) ከተማ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተከሰተው ግድያ እና የወገኖቻችን እልቂት ተወዳዳሪ የለውም። በመቶዎች የሚቆጠሩ ወንድሞች አባቶች እናቶችን እህቶች ህፃናት ሳይቀሩ የዚህ ወንበዴ መንግስት ሰለባ ሆነው መላው የአገሪቱ ህዝብ በከፋ ሀዘን ላይ ይገኛል።
እኛም የፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን ወገኖቻችሁ በህዝባችን ላይ የደረሰው አሰቃቂ የግፍ ግድያ እጅግ በጣም አሳዝኖናል። በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ከጎናችሁ እንደምንቆም እናረጋግጣለን። ለትግላችሁ የማይቀለበስ አጋርነታችንን ለማሳወቅ እንወዳለን።
የስርዓቱ ደም ጠባቂና ታጣቂ ወታደሮች በወገኖቻችን ላይ መሳሪያ ከመተኮስ እንዲቆጠቡ ብሎም ከፋሽስት መንግስት የሚሰጠውን የግድያ ትዕዛዝ ባለማክበር ከህዝባቸው ጎን እንዲሰለፉ አጥብቀን እንመክራለን። በሽዎች ለሚቆጠሩ ንፁሀን እልቂት ተጠያቂ የሆነው የኢትዮጵያ መንግስት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ተጠያቂ እንዲሆን የአለም መንግስታትን አጥብቀን እንጠይቃለን።
በመጨረሻም የኢትዮዽያ ሕዝብ በጎሳና በሃይማኖት ሳይለያይ በአንድነት በደልን እንድንቃወም አጥብቀን እንጠይቃለን! ፈጣሪያችን አሏህ (ሱወ)በደልንና በደለኞችን ከኢትዮዽያ ምድር ያንሳልን (አሚን)!!!

ፍትሕ ለኢትዮጵያ ህዝብ
የፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን ዋሽንግተን ዲሲ

First Hijrah's Statement መሪዎቻችን በከፊል ተፈተዋል፤ትግላችን ሳያሰልስ ይቀጥላል፤የኢትዮጵያ ህዝብ ያሸንፋል። በሶስት ቀላል ጥያቄዎች የተጀመረው እልህ አስጨራሽ የሆነው የሙስሊ...
09/11/2016

First Hijrah's Statement
መሪዎቻችን በከፊል ተፈተዋል፤
ትግላችን ሳያሰልስ ይቀጥላል፤
የኢትዮጵያ ህዝብ ያሸንፋል።

በሶስት ቀላል ጥያቄዎች የተጀመረው እልህ አስጨራሽ የሆነው የሙስሊሞች ትግል በቆራጥ ታጋዮችና በጀግኖች መሪዎቻችን ጥረት እስካሁን ድረስ እንደዘለቀ ይታውቃል። በህዝብ ሙሉ ውክልና የተሰጣቸው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችን ብዙ ድብደባዎች (ቶርቸር) ሳይበግራቸው ትግሉን በቆራጥነት በመምራት ላይ ናቸው።

ሰላማዊ ትግል ምን ማለት እንደሆነ ህዝባችንን በማስተማር ብሎም አምባገነኑን የወያኔ መንግስት በማሽመድመድ ፋና ወጊ የሆነውን የትግል ስልት በተግባር አሳይተዋል። መሪዎቻችን ያለምንም ወንጀል ተከሰው ለሀይማኖት መብት እንዲሁም ለህዝባችን ነጻነት የከፈሉት መስዋዕትነት እጅግ አስደናቂ ነው። ለዚህም የከበረ ምስጋናችንን ለማበርከት እንወዳለን።

ንፁሀን መሪዎቻችን በአሸናፊነት ከእስር ቤት በመውጣታችሁ የተሰማንን ደስታ በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ሙስሊም ማህበረሰብ ስም ለመግልጽ እንወዳለን። እንኳን በህይወት ከሚወዳችሁ እና በጣም ከሚያከብራችሁ ቤተሰባችሁ እንዲሁም ህዝባችሁ ጋር አላህ በሰላም አገናኛችሁ አልሀምዱሊላህ እንላለን። አሁንም በግፈኛው ወያኔ እስር ቤት ያለምንም ወንጀል የሚሰቃዩ መሪዎቻችን ጋዜጠኞቻችን ጦማሪዎቻችን ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ እንዲፈቱ አጥብቀን እናሳስባለን።

ከአራት አመት በፊት የሙስሊሞች ትግል ሲጀመር መንግስት እንደመሪ ለህዝብ ጥያቄ ተገቢ መልስ እንደመስጠት አሸባሪ የሚል ስም በመስጠትና በመወንጀል ለማጣጣል በመሞከር ከፍተኛ ውርደት ውስጥ ገብቷል። አንዳንድ የህብረተሰቡን ክፍል ሸሪዓ ህግ ሊታወጅብህ ነው በማለት ለማስበርገግ ከፍተኛ ጥረት በመንግስት አካላት ሲደረግ ቆይቷል።

አሁን ግን ወንጀለኛው እና አሸባሪው እራሱ መንግስት ተብየው መሆኑን ሁሉም ህብረተሰብ ተገንዝቦታል። የሙስሊሙን ትግል የኢትዮጵያ ህዝብ አምኖበት በጋራ እየታገሉ ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ መብቱን እና ነፃነቱን በሰላማዊ ትግል እስከሚጎናጸፍ ድረስ ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን ማንኛውንም ድጋፍ እንደምናደርግና በቆራጥነት ከጎናችሁ እንደምንቆም ለማረጋገጥ እንወዳለን።

ትግላችን እስከ ድል ዳጃፍ ድረስ በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል።
አላህ አክበር
ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን
ዋሺንግተን ዲሲ

August 22, 2016 የህዝብን ቁጣ በሃይል መግታት እንደማይቻል ከታሪክ መማር አስተዋይነት ነዉ!!! ፈርስት ሂጅራ በአሜሪካ ከዛሬ ሃያ አመታት በፊት ሲመሰረት አንግቦ ከተነሳባቸው አላማዎ...
08/22/2016

August 22, 2016
የህዝብን ቁጣ በሃይል መግታት እንደማይቻል ከታሪክ መማር አስተዋይነት ነዉ!!!

ፈርስት ሂጅራ በአሜሪካ ከዛሬ ሃያ አመታት በፊት ሲመሰረት አንግቦ ከተነሳባቸው አላማዎች አንዱ ለኢትዮዽያ ሙስሊሞችና ብሎም ለመላው ኢትዮዽያዊ ወገናችን አጋር ለመሆንና በጎ ለመስራትም ነዉ። ታዲያ በነዚህ ባሳለፍናቸዉ አመታት በተለይ ከ1991 ለዉጥ ወዲህ እንደማንኛዉም ኢትዮዾያዊ ያገራችን የተስፋ ብርሃን ጭላንጭል እየታየን ሲጠፋ ከዛሬ ነገ ይሻላል በሚል ቆይተን ነበር። ነገር ግን አገሪቱን እያስተዳደረ ያለዉ አምባገነናዊ ስርአት ከአራት ዐመታት ወዲህ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላያ ይህ ነዉ የማይባል ህገወጥ የግፍ እርምጃ በመውሰድና በገሃድ በእምነቱ ጣልቃ በመግባት ሙስሊሙ በአገሩ ላይ ያለዉን ተስፋ ድቅድቅ ባለ ጨለማ ዉስጥ ጥሎታል።

በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ውስብስብ ሰው ሰራሽ ችግሮች እንዳሉ ይታወቃል። ከዛሬ አራት አመታት በፊት ሙስሊሙ ህብረተሰብ ለመብቱ ሲል የጀመረዉን ሰላማዊ እንቅስቃሴን አስከትሎ በአምባ ገነኖች የደረሰበት ጭፍጨፋና መከራ ዛሬ በሌላዉ ወገን ላይ በአስከፊ ሁኔታ እየደረሰ ነዉ። በተለይ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያና በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ እጅግ አስደንጋጭ እና አሳማሚ ደረጃ ላይ ደርሷል። አማራ እና ኦሮሞ ወገኖቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ በመንግስት ሀይሎች እየተገደሉ ነው።

ጭፍጨፋው በቀላሉ የሚገመት አይደለም። መጠነ ሰፊና በቁጥር በውል የማይታወቁ ወገኖች ህይወታቸውን እንደዋዛ ሰውተዋል። ደማቸው ፈሷል። አሁንም የማፈንና የመግደል ዘመቻው በሰፊው እንደቀጠለ ነው። ለጀግናዉ የኦሮሞና የአማራ ወገኖቻችን ያለንን አድናቆት ከልብ በመነጨ ምስጋና ለመግለፅ እንወዳለን። በተለይ ባደረጉትና በሚያደርጉት ትእይንተ ህዝብ ላይ የሙስሊሙን የፍትሕ ጥያቄዎችን በማንሳታቸዉ ምን ጊዜም ዉለታችሁን እንደማንረሳ እናሳዉቃለን።

የፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን አሁንም ቢሆን ከዚህ በፊት በአምባ ገነኑ የወያኔ ሰራዊት የተገደሉትን ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት እና ፍትሕ ሲሉ ህይወታቸውን የሰጡትን ሰማዕታት ሁልጊዜም በጸሎት (በዱዓዕ) እናስታውሳቸዋለን። ለሞቱለት ዓላማም ያለጥርጥር ፈለጋቸውን እንከተላለን። ለሙታን ቤተ ሰቦችም ትዕግስትን እና መጽናናትን እንመኛለን።

አሁን ባለው አስከፊ አምባገነናዊ አገዛዝ ብዙ ወገኖቻችን ማለትም የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች፤ ጋዜጠኞች፤ ጦማሪዎች፤ የሙስሊሙ ህዝብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች፤ የሀይማኖት መሪዎች፤ ምሁራን እና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እስካሁን ድረስ በእስር ቤት እየተሰቃዩ ነው። ምንም ወንጀል ያልሰሩ በአገሪቱ የሰፈነውን ጨቋኝ መንግስት በመቃወማቸውና ለሰላምና ለፍትሕ በመጮሀቸው ብቻ የታሰሩት የሀገሪቱ ውድ ልጆች በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ ድርጅታችን በጥብቅ ይጠይቃል።

የህወሀት መንግስት የሰይጣን ጥይቱን ያነጣጠረው በሁሉም ሀይማኖቶች፤ ብሄረስቦች፤ ክልሎች፤ ባጠቃላይ በሁሉም ወገኖቻችን ላይ በመሆኑ በኢትዮዽያ ላይ ፍትሕን ለማስፈር በሚደረገዉ ትግል የዜጎች ተሳትፎ ስለሚጠይቅ ክፍፍልን በመተው ድል እንድንቀዳጅ አብረን በጋራ እንድንታገል እናመላክታለን።

ለዚህ ሁሉ ግፍ ያለጥርጥር የወያኔ መንግስት አገዛዝ ተጠያቂ ነው። የስርዓቱ መሳሪያ የሆነው የታጠቀው ሰራዊት አቅፎና ተንከባክቦ ያሳደገውን ኢትዮጵያዊ ወንድሙን እህቱን አባቱን እና እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ከመግደል እንዲቆጠብ ከዚያም አልፎ መንግስትን ሳይሆን ህዝብን የማገልገል ሀላፊነት እንዳለበት አጥብቀን እንመክራለን።
ፍትሕ ለሁሉም ዜጎች!

ትግላችን ባንድነት እስከድል በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!!

አሏህ አክበር !!!

ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን
ዋሽንግተን ዲሲ

ድምፃችን ይሰማ በጎንደር ተሰማ!የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት::የወያኔ መንግስት ሐቅን ገፍትሮ ዕውነትን ደፍጥጦ ህዝብን በሃይማኖትና በጎሣ ከፋፍሎ አንድነቱን በታትኖ ...
08/05/2016

ድምፃችን ይሰማ በጎንደር ተሰማ!
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት::

የወያኔ መንግስት ሐቅን ገፍትሮ ዕውነትን ደፍጥጦ ህዝብን በሃይማኖትና በጎሣ ከፋፍሎ አንድነቱን በታትኖ አንዱን ወገን ሲገድል፣ ሲያስርና ሲያግዝ ሌላው እንዳይደርስለት በማድረግ ከአንድ ብሔር የተውጣጣ ቡድን አንግሶ ለ25 ዓመታት ያራመደው ከይሲ የግድያና የዘረፋ ዘመን የሚያከትምበት ዋዜማ ላይ መድረሱን በግላጭ ታይቷል።

መላው የአገሪቱ ሕዝብ ከሙስሊም ወገኖቹ ጎን በመሰለፍ ይህን መናጢና ጨካኝ መንግስት በጋራ እንዲታገል የኢትዮዽያ ሙስሊሞች ለ5ዓመታት የነበረው የድምፃችን ይሰማ ጥሪ በሚያስደንቅና በሚያስደምም ሁኔታ የጎንደር ህዝብ ለነፃነቱ፣ ለክብሩና ለማንነቱ ባደረገው ታሪካዊ የተቃውሞ ሠልፍ ላይ የ”ድምፃችን ይሰማ” መፈክር በማስተጋባት ከሙስሊም ወገኖቹ ጎን መሰለፉን እና ትግላቸውን መደገፉን በማያሻማ ሁኔታ በአደባባይ አውጇል። የጎንደር ህዝብ “የታሰሩት የሙስሊም ኮሚቴዎች ይፈቱ!” “ድምፃችን ይሰማ!” “በኦሮሚያ የሚደረገው የወንድሞቻችን ግድያ ይቁም! “ “ የህዝብ ጥያቄ መጠየቅ ሽብርተኝነት አይደለም!” የሚልና የኦሮሞው ታጋይ የበቀለ ገርባን ፎቶ አንግቦ በመውጣት በሙስሊሙና በኦሮሞ ሕዝብ ትግል ጎን መቆማቸው እጅግ የሚያኮራቸውና የሚያስመሰግናቸው ከመሆኑም ባሻገር ከአሁን ወዲያ በተናጠል መታገል ትርፉ ለወያኔ የጥይት እራት መሆኑን፤ አዋጩና ዘላቂው የትግል መንገድ በጋራ መታገል ብቻ መሆኑን ያረጋገጡበት መድረክ ነው።

የሙስሊሙ ህብረተሰብ አንግቦ የተነሣው የአልገዛምነትና የእምቢተኝነት መፈክር ”ድንፃችን ይሰማ! “ አሰባሳቢ የጋራ መፈክር በመሆን በአንድ ረድፍ እየተመምን የግፈኞችን ምሽግ የምንድበት ወቅት በዕውነት መቃረቡን በተስፋ ዓይን እየተመለከትነው ነው። በደልና ጭቆና በመቃወም የተነሳውን ሕዝብ ኦሮሞውን ኦነግ፣ አማራውን ግንቦት 7፣ ሙስሊሙን አሸባሪ፣ ሱማሌውን አልሸባብ፣ ጎንደሬውን የሻዕብያ ተላላኪ እያሉ ታፔላ በመለጠፍ ነጣጥሎ የመፍጀት የውሸት ፕሮፖጋንዳ ስልቻ ተቀዷል። የሙስሊሙ፣ የአማራው፣ የኦሮሞው ህዝብና ሌሎችም ታክሎበት የሚያደርጉት አንድ ወጥ የሆነ የጋራ ግንባር ትግል የወያኔ መንግስት እያነከሰ ወደ መጣበት እንዲመለስ ያደርገዋል።

የወያኔ መንግስት በጥቅምና በስልጣን አይንና ልባቸውን የዘጋባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች የዚህ መንግስት የጀርባ አጥንት በመሆን ህዝባቸውን የሚያሳስሩ፣ የሚያስደበድቡና የሚያስገድሉት አንድ ያልተገለፀላቸው ነገር ቢኖር እነዚያ ያስገደሏቸው፣ ያሳሰሯቸው፣ ያስደበደቧቸው፣ ከዚህ ግፍ ለማምለጥ አገር ጥለው በመሸሽ የባህር አሣ የበላቸው፣ በሰው ሃገር በስደተኛ ካምፕ ታጉረው የሚሰቃዩ ራሳቸውን በእሳት ያጋዩት በሙሉ ከሰማይ ላይ የተንጠባጠቡ ዘመድና ወገን የሌላቸው አለመሆናቸው ነው።

እንኳንስ የሰው ልጅ የጫካ ዛፍ እንኳ አብሮት የበቀለና ያደገ ሌላ ዛፍ አጠገቡ አለ። በዛ የጭካኔ ጎዳና ከቀጠላችሁ ግን በእናንተ የወያኔ ካድሬዎች ጠቋሚነት፣ አሳሳሪነት የጠመንጃ ቃታ ሣቢነት ደማቸው ለፈሰሰው በሙሉ ተጠያቂ ናችሁ፤ ከሕዝቡ ጋር እየኖራችሁ ነውና የትም ሆነ የት ትታወቃላችሁ፤ ትጠየቃላችሁ፤ ዋጋም ትከፍላላችሁ። ያ ደረጃ ላይ ከመድረሳቸሁ በፊት ግን አሁን የእድል በር ተከፍቶላችኋል ሕዝቡን ይቅርታ ጠይቃችሁ ወደ ትግሉ ጎራ ተቀላቀሉ።

ሌሎች በኢትዮፕዽያ ያለው የሕዝብ ጉዳይ ያገባናል ባዮች በተለይ አንዳንድ ለሙስሊሙ ህብረተሰብ እየታገልን ነው የሚሉ በሌላ በኩል ግን ሙስሊሙ በፖለቲካ መሣተፍ የለበትም፣ ድርጅታችን የወያኔን መንግስት አይቃወምም አይደግፍምም ገለልተኛ ነን የምትሉ ወንድሞቻችን በአሁኑ ሰዓት በአገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የህዝብ ጥያቄ እንዴት ነው የምታዩት?
በኦሮሚያ ከ400 በላይ ወጣቶች በወያኔ ጥይት ደማቸው ፈሷል። ከፈሰሰው የደም ጎርፍ ማዶ ቁማችሁ አሁንም ገለልተኛ ናችሁ? የጎንደር ህዝብ በወልቃይትና ጠገዴ የህይወት መስዋእት ከፍለው ግፍ በቃን ብለው በጎንደር ታይቶ የማይታወ ታቃውሞ አካሄዷል። አሁንም ገለልተኛ ናችሁ? 84 ንፁሀን ወንድሞቻችን በወህኒ ቤት ሰሌዳ ላይ ስማቸው ተለጥፎ እርምጃ ይወሰድባችኋል ተብሎ ቤተሰቦቻቸውና መላው የኢትዮትዽያ ሕዝብ በዚህ ዘግናኝ ዜና በቁጣና ሀዘን ስሜት ተውጧል። አሁንም ገለል እያላችሁ ነው ወይ?
“በደልን አለመቃወም ከበዳዮች ጋር ማበር ነው”ይባል የለ ትግሉ ወሳኝ ደረጃ ላይ የደረሰበት የቁርጥ ቀን ላይ ነን። ያለፈውን ወደኋላ ትተን በማያሻማ ሁኔታ እየተስተጋባ ያለውን የሕዝብን ፍላጎት መደገፍና ጥያቄውን በመቀበል ከሕዝባችን ጎን እንቁም። ገለልተኝነት ከአሁን ወዲያ ማክተም አለበት።
የሙስሊሙ እልህ አስጨራሽ ትግል፣ በጎንደር የታየው የአልገዛምነት ንቅናቄና እያስገመገመ በመምጣት ላይ ያለው የኦሮሞ ሕዝብ የትግል ማዕበል ዘረኛውን የወያኔ መንግስት ወደ ከርሰ መቃብር የሚኖግድበት አቋራጭ የሸርተቴና የድጥ መንገድ ያበጃጁለታል።
የጎንደር ህዝብ የሙስሊሙንና የኦሮሞውን ህዝብ በመቀላቀል ያደረጉትን የጋራና የአንድነት ጥሪ በመከተል ሌሎችም አካባቢዎች ተመሳሳይ አቋም ወስደው የሽብርና የቅሚያ ዘመን እንዲያከትም እንዲተባበሩ ጥሪ እናደርጋለን።
የኢትዮዽያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ን ቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት የኦሮሞና የጎንድር ህዝቦች የሚያደርጉትን የነፃነትና የመብት ትግል በሙሉ ልብ እንደሚደግፍ በዚህ አጋጣሚ ያረጋግጣል።


ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከድል ደጃፍ ይገሰግሳል!
አላሁ አክበር!
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት

የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት በጁላይ 15 እና 16 በዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ ጉባኤ አድርጓል። በጉባኤዉ ላይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ የሚመለከቱ ጉዳዮች ተነስተዋል፣ሁሉ...
07/25/2016

የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት በጁላይ 15 እና 16 በዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ ጉባኤ አድርጓል። በጉባኤዉ ላይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ የሚመለከቱ ጉዳዮች ተነስተዋል፣ሁሉን አቀፍ የሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ተዳሰዋል፣ በዚህ ጉባኤ ላይ የተስተዋሉት የአመለካከት ልዩነቶች ብሔራዊ መግባባትን በመፍጠር አገራዊ ፋይዳ ይኖራቸዋል ብለን እንገምታለን።ክፍል አንድ ቪዲዮን ይከታተሉ። http://youtu.be/Y1BUWoUZkk0

የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት ጉባኤ ቪዲዮ ቁጥር 4 የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት በጁላይ 15 እና 16 በዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ ጉባኤ አድርጓል። በጉባኤዉ ላይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ የሚመለከቱ ...

Address

Washington D.C., DC

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bilal Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share