11/12/2021
ሮይተር ያሰራጨው ዘገባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሰረታዊ መመሪያን ያላገናዘበ መሆኑም የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት ዜጎች ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ የቀበሌ መታውቂያ መያዝ አለባችው ቢልም ሮይተር ያወጣው ዘገባ ሰዎች በማንነታቸው ለመለየት
እንደሆነ አድርጎ የሰራው ዘገባ ከእውነታ ያራቀና አግባቡነት የሌለው መሆኑን የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል
ሮይተር በሰራው ዘገባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሰረታዊ መመሪያን ያላገናዘበና ከአዋጁ አተገባባር ጋር የሚጻረርና አግባብነት የሌለው ነው ብሏል፡፡
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዜጎች ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ የነዋሪነት መታወቂ፣ መንጃ ፍቃድና የሠራተኛ መታወቂ ሳይዙ መንከሳቀስ የተከለከለ መሆኑን መደንገጉ ይታወሳል፡፡