Gulele Radio

Gulele Radio Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gulele Radio, Radio Station, Washington D.C., DC.

Gulele Radio & Tube is the new Radio station we are going to lounge by next week Afaan Oromo and amharic lunguges polotical ,economic social media horn of Africa

በኮንትራክተር አቅም ማነስ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የታርጫ ጪዳ አስፋልት መንገድ ሥራ ተጀመረ::በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ4 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባው የ64 ነጥብ...
04/30/2025

በኮንትራክተር አቅም ማነስ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የታርጫ ጪዳ አስፋልት መንገድ ሥራ ተጀመረ::

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ4 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባው የ64 ነጥብ 8 ኪ.ሜ የታርጫ ጪዳ ሎት 3 አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

በፕሮጀክቱ ማስጀመር ሥነሥርዓት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) እና የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒን ጨምሮ የፌዴራልና ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተጀምሯል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ ከዚህ በፊት ተጀምሮ በኮንትራክተሩ አቅም ማነስ ምክንያት ተቋርጦ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ መቆየቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ የሺዋስ ዓለሙ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

ለክልሉ ህዝቦች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የታርጫ ጪዳ አስፋልት መንገድ ግንባታ ከዳውሮና ኮንታ ዞኖች ባለፈ ከአጎራባች ጅማና ወላይታ ዞኖች ጋር ያለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትስስር እንደሚያጠናክርም ተናግረዋል።

የመንገዱ መገንባት ለገበያ ልውውጥ፣ ለቱሪዝም ዕድገት፣ ለክልሉ ኢኮኖሚ መነቃቃትና ለአካባቢው ነዋሪዎች አዳዲስ ዕድሎችን የሚፈጥር እንደሆነም ተመላክቷል።

ለመንገዱ ግንባታ 4 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ከፌደራል መንግስት እንደተመደበና በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ባለቤትነት በመሳይ ኦሊ ጠቅላላ ተቋራጭና በዩኒኮን አማካሪ እንደሚሰራም ተገልጿል።

የታርጫ ጪዳ አስፋልት መንገድ በ2 ዓመት ከ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅ መገለጹንም የቢሮው ኃላፊ አመላክተዋል።

የአማራ ክልልን የማተራመስ እቅዱ የከሸፈበት ጽንፈኛ ቡድን መንግስት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሰ በማስመሰል የሀሰት መረጃ በማሰራጨት ተጠምዷል ሲሉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስ...
04/30/2025

የአማራ ክልልን የማተራመስ እቅዱ የከሸፈበት ጽንፈኛ ቡድን መንግስት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሰ በማስመሰል የሀሰት መረጃ በማሰራጨት ተጠምዷል ሲሉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ተናገሩ።

የክልሉን የጸጥታ ተቋማት መልሶ በማደረጃትና በማጠናከር ረገድ ውጤታማ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፥ ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ ይዞ የሚንቀሳቀሰው ጽንፈኛ ቡድን ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት በመፈጸም የህዝብ ጠላት መሆኑን በተግባር አሳይቷል ብለዋል፡፡

በክልሉ እየተወሰደ ካለው ህግ የማስከበር እርምጃ ጎን ለጎን ጽንፈኛ ቡድኑ የጥፋት መንገዱን እንዲተው በመንግስት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ መቅረቡን ያስታወሱት ኮሚሽነሩ፥ በርካታ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን በመቀበል ወደ ሰላማዊ ህይወት መመለሳቸውን ተናግረዋል።

በአሁን ወቅት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በተገኘው ሰላም ህብረተሰቡ ሲያነሳቸው ለቆዩ የልማትና የሰላም ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምሬት በፈጠሩ 198 የዘርፉ ተዋናዮች ላይ እርምጃ ተወሰደ*****************በኦሮሚያ ክልል በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ም...
04/30/2025

በኦሮሚያ ክልል በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምሬት በፈጠሩ 198 የዘርፉ ተዋናዮች ላይ እርምጃ ተወሰደ
*****************

በኦሮሚያ ክልል በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምሬት በፈጠሩ 198 የዘርፉ ተዋናዮች ላይ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ መንገዶችና ሎጂስቲክስ ቢሮ አስታውቋል።

ከታሪፍ በላይ ማስከፈል፣ ትርፍ መጫን፣ ከሾፌሮች ጋር ተመሳጥሮ ጉቦ መቀበል፣ ተሳፋሪውን ማንገላታት በዋናነት ከተገልጋዮች ለክልሉ መንገዶችና ሎጂስቲክስ ቢሮ የሚቀርቡ ቅሬታዎች ናቸው።

ይህን ተከትሎ የኦሮሚያ መንገዶችና ሎጂስቲክስ ቢሮ ባለፉት 3 ወራት በ198 አካላት ላይ እርምጃ መውሰዱን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ሀጂ በተለይ ለኢቢሲ ዶትስትሪም ተናግረዋል።

የሥነ-ምግባር ጥሰት በፈጸሙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችና አሽከርካሪዎች፣ የትራንስፖርት ተቆጣጣሪ ሰራተኞች፣ የትራፊክ ፖሊሶችና ሌሎች አካላት ላይ ከሥራ እስከ ማሰናበት የሚደርስ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።

ወደ ፊትም ቢሆን ከመናኸሪያ ከወጡ በኋላ የመኪና መለዋወጫ ዋጋ ጨምሯል፣ ነዳጅ ተወዷል፣ ወዘተ በማለት በሕገ-ወጥ መንገድ ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶችን ተገልጋዮች በ8556 ነጻ የስልክ መስመር ቢጠቁሙን ተመሳሳይ እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል።

እንደ ኦሮሚያ ክልል ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ክልሉ በ6 ክላስተሮች ተከፍሎ በመናኸሪያዎች ዘመናዊ የኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎት ተዘርግቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን አሰራር ተሻግረው የሚመጡ ችግሮችን ለመፍታትም የክትትልና ቁጥጥር ሥራው በመጠናከር ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ክልሉ ከተለያዩ ክልሎች ጋር የሚዋሰን እንደመሆኑ ድንበር ተሻጋሪ የትራንስፖርት ችግሮችም እንደሚያጋጥሙ የጠቆሙት ምክትል ቢሮ ኃላፊው፤ ከአዲስ አበባ ሸገር ሲቲን እና ሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎችን አቋርጠው ወደ ቡታጂራ፣ ወራቤ፣ ሆሳዕና እና ሌሎች ቦታዎች የሚጓዙ ተገልጋዮችም ቅሬታ እንደሚያሰሙ መረጃው አለን ነው ያሉት።

ችግሩን ለመፍታት ከደቡብ ክልል ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም የኦሮሚያ መንገዶችና ሎጂስቲክስ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ሀጂ ጠቁመዋል።

በመሀመድ ፊጣሞ

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት እንድትቀላቀል አሜሪካ  ድጋፍ ታደርጋለች  - የአሜሪካ የንግድ ፅ/ቤት***********************************ኢትዮጵያ የዓለም ንግ...
04/30/2025

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት እንድትቀላቀል አሜሪካ ድጋፍ ታደርጋለች - የአሜሪካ የንግድ ፅ/ቤት
***********************************

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት እንድትቀላቀል አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች።

ከ2025 የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም እና የዓለም ባንክ የጸደይ ስብሰባዎች ጎን ለጎን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በአሜሪካ የንግድ ፅ/ቤት የዓለም ንግድ ድርጅት እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ረዳት ተወካይ ከሆኑት ኒል ጄ ቤክ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት ለመቀላቀል እያደረገች ያለውን ከፍተኛ ጥረት አስመልክቶ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ አድርገዋል።

በቀጣይ ዓመት መጋቢት ወር በሚካሄደው ጉባዔ ላይ፤ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች ለማሟላት ቁርጠኛ መሆኗንም አስረድተዋል።

በአሜሪካ የንግድ ፅ/ቤት የዓለም ንግድ ድርጅት እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ረዳት ተወካይ የሆኑት ኒል ጄ ቤክ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያከናወነች ያለውን ከፍተኛ ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት እንድትቀላቀል አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ በተሳካ ሁኔታ ከዓለም አቀፉ የግብይት ሥርዓት ጋር መዋሃድ የአሜሪካ ፍላጎት መሆኑንም ገልጸዋል።

ሁለቱ ወገኖች ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በምታደርገው ጉዞ ላይ ትብብራቸውን ለመቀጠልና አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።

Gareen diyaaspooraa Oromoo guyyoota sadiif daawwannaa hojiilee misoomaa godinaalee Oromiyaa garaagara keessatti erga taa...
10/14/2024

Gareen diyaaspooraa Oromoo guyyoota sadiif daawwannaa hojiilee misoomaa godinaalee Oromiyaa garaagara keessatti erga taasisaniin booda, Waajjira Pirezidaantii MNO'tti argamuun dhimmoota garaagaraa irratti hoggantoota mootummaa waliin mari’atanii jiru.

Miseensonni diyaaspooraa kunneen, waamicha Pirezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa kabajamoo Obboo Shimmallis Abdiisaa diyaaspooraa dhalattoota Oromoof godhan fudhachuun biyyoota garaagaraa irraa kabaja ayyaana Irreechaaf gara biyyaatti kan dhufaniidha. Gareen diyaaspooraa kunis sochiilee misoomaa babal’aa naannoo Oromiyaa keessatti taasifamaa jiran kan ajaa’ibsiifataniifi kallattii hundaan deeggaruuf waadaa kan galan yoota’u, fuldurattis fayidaa biyyaafi ummataaf ittidhiyeenyaan aantummaa isaanii hojiin kan agarsiisan ta’uu ibsan.

Miseensonni hawaasa daayaaspooraa hojiilee misoomaa naannoo Oromiyaatti hojjetamaa jiran daawwataa jiruMiseensonni hawaa...
10/12/2024

Miseensonni hawaasa daayaaspooraa hojiilee misoomaa naannoo Oromiyaatti hojjetamaa jiran daawwataa jiru

Miseensonni hawaasa daayaaspooraa kunneen hanga ammaatti Warshaalee AMG hooldiing, Waldaa Aksiyoona Pirintiingii, Pabliishiingi fi Paakeejiingii Meelbaa daawwataniiru.

Guyyoota sadiifis oromiyaa keessa naanna’uun hojiilee misoomaa garaa garaa akka daawwatan ibsameera.

Hogganaan Waajjira Pirazidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa Dr. Abdulaziiz Daawud naannoo Oromiyaatti hojiileen misoomaa fayyadamummaa ummataa mirkaneessan hojjetamaa jiraachuu ibsan.

Daawwannicharratti Daareektara Daarooktareetii Hirmaannaa Daayaaspooraa Oromiyaa Obbo Amiin Jundii dabalatee angawoonni mootummaa olaanoon argamaniiru. Badhaasoo Hayileetu gabaase.

አንጋፋው የኢቲቪ ዳሬክተር አረፈ!የተቋማችን ባልደረባ እና የበርካታ ሙያዎች ባለቤት የነበሩት  አቶ ወርቁ ጋዲሳ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።አቶ ወርቁ ከዚህ በፊት በኢቴቪ በአፋን ኦሮሞ አ...
10/08/2024

አንጋፋው የኢቲቪ ዳሬክተር አረፈ!
የተቋማችን ባልደረባ እና የበርካታ ሙያዎች ባለቤት የነበሩት አቶ ወርቁ ጋዲሳ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ ወርቁ ከዚህ በፊት በኢቴቪ በአፋን ኦሮሞ አጫጭር እና ረዣዥም ድራማዎችን በመድረስ እና በዳይሬክተርነት የሚታወቁ ታላቅ ባለሙያ የነበሩ ሲሆን ህይወታቸው እስካለፈበት ድረስም በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የስቱዲዮ ዳይሬክተር በመሆን በማገልገል ላይ ነበሩ። በስራቸውም ትጉህ፣ ምስጉንና ከባልደረቦቻቸው ጋር በቅንነት የሚያገለግሉ ታላቅ ባለሙያ ነበሩ።

አቶ ወርቁ ባደረባቸው ህመም ምክነያት ማረፋቸውን ለማወቅ ችለናል።

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል።

Baga Ayyaana Irreechaa bara 2024'tiin nagaan isin gahe!እንኳን 2017 ለእሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችው!
10/04/2024

Baga Ayyaana Irreechaa bara 2024'tiin nagaan isin gahe!
እንኳን 2017 ለእሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችው!

ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ለናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ሙሉ ትግበራ በጋራ ለመንቀሳቀስ ተስማሙ*************በኒውዮርክ እየተካሄደ ካለው የ.ተ.መ.ድ. 79ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን፥...
09/22/2024

ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ለናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ሙሉ ትግበራ በጋራ ለመንቀሳቀስ ተስማሙ
*************

በኒውዮርክ እየተካሄደ ካለው የ.ተ.መ.ድ. 79ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን፥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ራምዳን ሞሀመድ አብዱላህ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ሚኒስትሮቹ ሁለቱ አገራት በናይል ተፋሰስ ፍትሃዊ እና እኩል ተጠቃሚነት ላይ ባላቸው ወጥ አቋም ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

አምባሳደር ታዬ፥ ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን በፓርላማ ማፅደቋን በማውሳት ራምዳን ሞሀመድ አብዱላህን እንኳን ደስ ያለዎት ብለዋቸዋል።

የደቡብ ሱዳን ፓርላማ ስምምነቱን በማጽደቁ የአገሪቱ ሕዝብ በናይል ተፋሰስ በፍትሀዊነት እና እኩል ተጠቃሚነት ላይ ያለውን መብት ያስከበረ መሆኑን አምባሳደር ታዬ ገልጸዋል።

በውይይቱ ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ሙሉ ትግበራ በጋራ ለመንቀሳቀስ መስማማታቸውን የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍን በፓርላማ አጽድቃ ለአፍሪካ ኀብረት ማቅረቧን ተከትሎ፤ ኡጋንዳ እ.ኤ.አ. በጥቅምት አጋማሽ የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽንን መመሥረት የሚያስችለውን ሁለተኛውን የናይል ጉባዔ ለማዘጋጀት ያሳየችውን ቁርጠኝነት መደገፏ ይታወሳል።

በአዲስ አበባ "ኢሬቻ ኤግዚቢሽንና ባዛር 2017" ዐውደ-ርዕይ ሊካሄድ ነው:-አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) "ኢሬቻ ኤግዚቢሽንና ባዛር 2017" የተሰኘ ዐውደ-ርዕይ ከመስ...
09/18/2024

በአዲስ አበባ "ኢሬቻ ኤግዚቢሽንና ባዛር 2017" ዐውደ-ርዕይ ሊካሄድ ነው:-

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) "ኢሬቻ ኤግዚቢሽንና ባዛር 2017" የተሰኘ ዐውደ-ርዕይ ከመስከረም 18 እስከ 24 ቀን 2017 በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሊካሄድ ነው፡፡

በዐውደ-ርዕዩ ላይ የፓናል ውይይቶችን ጨምሮ፣ የባሕል ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና የሙዚቃ ዝግጅቶች ይቀርባሉ፡፡

ኢሬቻ የአብሮነት ምልክት መሆኑን እና ኢኮኖሚያዊ ትሩፋቶቹን ለማስተዋወቅ ዐውደ-ርዕዩ እገዛ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

በዐውደ-ርዕዩ ከ250 ሺህ በላይ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት የብድር መጠን 2 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር መድረሱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት የብድር መጠን 2 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር መድረሱን የብሔ...
05/09/2024

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት የብድር መጠን 2 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር መድረሱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት የብድር መጠን 2 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር መድረሱን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ተናገሩ።

አይካፒታል አፍሪካ ኢንስቲትዩት ከፊንፊኔ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው 7ኛው የምስራቅ አፍሪካ አመታዊ የፋይናንስ ጉባኤ በፊንፊኔ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ፤ በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ እየተወሰዱ ያሉ የሪፎርም ስራዎችን አብራርተዋል።

ከምስራቅ አፍሪካ እንዲሁም በአህጉሩ ትስስርን ለመፍጠር፣ በዲጂታል ፋይናንስ፣ የተረጋጋ የፋይናንስ ዘርፍ ለመፍጠር፣ አካታችነት ላይ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትንም ዘርዝረዋል።

በተደራሽነት፣ በአገልግሎት ስብጥር፣ በዲጂታል ፋይናንስ ሞባይል ባንኪንግ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ በዘመናዊ ስጋት አስተዳደርና ሌሎችም አሰራሮች እያደገ መምጣቱን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉ በተደራሽነት፣ በተቀማጭ ገንዘብ፣ በአጠቃላይ የሀብት መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ስለመምጣቱም ተናግረዋል።

በ2024 መጀመሪያ የፋይናንስ ተቋማት 121 መድረሳቸውን ጠቅሰው አጠቃላይ ሀብታቸው ደግሞ 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን እንዲሁም ተቀማጭ ገንዘባቸው 2 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ብር መድረሱን ገልጸዋል።በተመሳሳይ የብድር መጠናቸውም 2 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር መድረሱንም ነው የተናገሩት።

የኢትዮጵያ መንግስት የተረጋጋ የፋይናንስ ዘርፍ ለመፍጠር ትኩረት መስጠቱን ያነሱት ገዥው በዚህም ጤናማ የፋይናንስ ዘርፍ ማስቀጠል ችሏል ብለዋል።

መንግስት ተግባራዊ እያደረጋቸው ባሉ ስትራቴጂዎች ዘርፍን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረግ፣ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ የአገልግሎት ስብጥርን ማስፋት፣ በአለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎች መሰረት መስራትና በፈጠራና ቴክኖሎጂ የታገዘ የፋይናንስ ዘርፍ እውን ለማድረግ ያስችላሉ ነው ያሉት።
ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት መደረጉ ፈጠራና ውድድርን በማፍጠን መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

በዘርፉ የተደረገው የፖሊሲ ለውጥ የውጭ ኢንቨስተሮች ገብተው እንዲሰሩ በማድረግ አዲስ ካፒታል ለማምጣትና አለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮን ለመውሰድ እንደሚያስችልም አንስተዋል።

ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ከማድረግ ጎን ለጎን የካፒታል ገበያን በማቋቋም ላይ መሆኗንም ጠቅሰዋል።
ገበያው በዚህ አመት መጨረሻ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ኢንቨስትመንት ባንክ፣ አማካሪ ድርጅቶችን ማካተት በፋይናንስ ዘርፉ አዲስ ምህዳር እንደሚፈጥር አብራርተዋል።

05/05/2024

Erga Abba Keeyna

Address

Washington D.C., DC

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gulele Radio posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gulele Radio:

Share

Category