Melkamu Abebaw Zeyini

Melkamu Abebaw Zeyini ያለዓላማ ጉዞ ከግብ አያደርስም።
ያለልፋት የሚገኝ ስኬት መጨረሻው ውድቀት ነው።

የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ__________የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ጤና ባለሙያዎች ምዝገባው በዚህ ሳምንት መጨ...
14/07/2025

የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
__________

የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ጤና ባለሙያዎች ምዝገባው በዚህ ሳምንት መጨረሻ የሚጀመር መሆኑን እያሳወቅን፤ ትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና አልፋችሁ የተመረቃችሁ ተመዛኞች ምዝገባውን ለማከናወን የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን (ቴምፖራሪ ዲግሪ፣ መታወቂያ፣ 4*3 ፎቶ) ከወዲሁ አዘጋጅታችሁ እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡
ቴምፖራሪ ዲግሪ ያልያዘ ተመዛኝ ምዝገባውን ማከናወን የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

ኤም ፖክስ
update

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia

ለCOC ተፈታኛ ጤና ተማሪዎች በሙሉ  ከ3,000+ በላይ ጥያቄዎችን በ350ብር እየገዛችሁ በደንብ ተለማመዱበት ።📍ከዚህ በፊት ለExit Exam ባዘጋጀነው ጥያቄዎች ከ 98% ተማሪዎችን ማሳለ...
29/06/2025

ለCOC ተፈታኛ ጤና ተማሪዎች በሙሉ


ከ3,000+ በላይ ጥያቄዎችን በ350ብር እየገዛችሁ በደንብ ተለማመዱበት ።

📍ከዚህ በፊት ለExit Exam ባዘጋጀነው ጥያቄዎች ከ 98% ተማሪዎችን ማሳለፍ የተቻለበት

📍አሁን ደግሞ ለCOC ያዘጋጃችኋል ተብለው የተዘጋጁ ከ 3,000+ በላይ ጥያቄዎች በመግዛት በደንብ እንዲትለማመዱ ቀርቦላችኋል።

📍ጥያቄዎቹ ፦
📌ከ 2019 -2023 ድረስ የተፈተኗቸው ፈተናዎች ናቸው
📌ፈተናው ይወጣባቸዋል ተብሎ ከሚታሰቡ አንኳር ርዕሶች ላይ በደንብ ጥያቄዎች ወተዋል Table of Content ከዚህ በታች መመልከት ትችላላችሁ።
📌Focused ተብለው የተለቀሙ ላይ በአሁኑ እንደዚህ ይጠየቃሉ ተብለው ከታሰቡ ጥያቄዎች መሀል ናቸው። እነሱ ላይ ትኩረት አድርጉባቸው
📌በተጨማሪ እያንዳንዱ ጥያቄ ከተብራራ መልስ ጋር የተዘጋጁላችሁ

📍ከዚህ በተጨማሪ Exit ከወዲሁ እነዘጋጃለን የሚትሉም ካላችሁ ለእናንተም ከ1,000+ በላይ ጥያቄዎችን ተዘጋጅቷል ከወዲህው በመግዛት ይዘጋጁ።

ለመግዛት በዚህ ቴሌግራም ያናግሩን👇👇👇
https://t.me/Melkamuabebaw

መልካም ጊዜ!

የሰዎችን ሕይወት የሚታደጉ ሐኪሞች ጥያቄ የፖለቲካ ኪሳራ በገጠማቸው ሰዎች መጠለፉ ትክክል አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ሰኔ 15፣ 2017 ዓ.ም ኢትዮጵያ ውስጥ ትክክለኛ የጤ...
22/06/2025

የሰዎችን ሕይወት የሚታደጉ ሐኪሞች ጥያቄ የፖለቲካ ኪሳራ በገጠማቸው ሰዎች መጠለፉ ትክክል አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

ሰኔ 15፣ 2017 ዓ.ም ኢትዮጵያ ውስጥ ትክክለኛ የጤና ባለሙያዎች ለምን የደመወዝ ጥያቄ አነሱ ብሎ የሚያስብ ሰው አለ ብዬ አልገምትም አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት እንዳሉት÷ የሕክምና ሙያ የተከበረ እና የሰዎችን ሕይወት የሚታደግ ነው፡፡

መንግስት እና ማሕበረሰቡም የሕክምና ባለሙያዎች ለዜጎች የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ በቅጡ እንደሚረዱ አንስተዋል፡፡

በሕክምና ባለሙያዎች የሚቀርቡ ጥያቄዎች ትክክል ሆነው ጥያቄዎች የሚቀርቡበት መንገድ ስህተት ከሆነ ግን የተፈለገውን ውጤት እንደማያስገኝ አመልክተዋል፡፡

“እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ሐኪሞች ለምን የደመወዝ ጥያቄ አነሱ ብሎ የሚያስብ ሰው አለ ብዬ አልገምትም“ ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የጤና ዘርፉን ችግር ለመፍታት ጤናማ መንገድ ካልተከተልን ችግሩ ይባባሳል እንጂ ዘላቂ መፍትሔ ማግኘት እንደማይቻል አስገንዝበዋል፡፡

በጤናው ዘርፍ የሚቀርቡ የደመወዝ፣ የጥቅማ ጥቅም፣ የቤት እና መሰል ጥያቄዎች የባለሙያዎች ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ የመፍትሄ መንገዱ ግን ከባለሙያዎች ወጥቶ በሌሎች እጅ ተጠልፏል ብለዋል፡፡

ጉዳዩ ደመወዝ ወስደው በማያውቁ ሰዎች እና መሰረታዊ አገልግሎት ሰጥተው በማያውቁ ሰዎች መጠለፉንም አብራርተዋል፡፡

እንቅልፍ አጥተው የሰዎችን ሕይወት የሚታደጉ ሐኪሞችን ትክክለኛ ጥያቄ ጉዳዩን በቅጡ የማያውቁ ሰዎች ከጠለፉትና የራሳቸው አጀንዳ ማስፈጸሚያ ካደረጉት ጉዳዩ አላማውን እንደሳተ ይቆጠራል ነው ያሉት፡፡

በዘርፉ የሚነሳውን ጥያቄ በሶስት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል አንስተው÷ ይሄም ትክክለኛ ሐኪሞች በቅንነት ኑሮ ከብዷቸው ያነሱት፣ የፖለቲካ ኪሳራ የገጠማቸው አካላት ያነሱት እና ሐኪም መሳይ ጋወን ለባሽ ፖለቲከኞች ያነሱት ጥያቄ ነው ብለዋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ሐኪም መሳይ ጋወን ለባሽ ፖለቲከኞች የትክክለኛ ሐኪሞችን ጥያቄ በመጠቀም የተከበረውን ሙያ እንዳጠለሹት አስረድተዋል፡፡

ስለሆነም መሰል ሁኔታዎችን ማጣራት እንደሚገባ ጠቁመው ÷ ለዚህም ሁሉም የጤና ባለሙያዎች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

የጤና ባለሙያዎች ጥያቄያችሁን በስሜት ሳይሆን በምክንያትና በስሌት ማስላት ስትጀምሩ ተቆንጥሮም ቢሆን ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

ሰው ለማዳን ከፍተኛ ዋጋ የሚከፍሉ ሐኪሞች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉ አውስተው÷ ለእነዚህ መሰል ሐኪሞች ለጥያቄያቸው ምላሽ ከመስጠት ባለፈ ሐውልት መቆሙን አንስተዋል፡፡

የጤና ባለሙያዎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አስገንዝበዋል፡፡

በአገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችንና የሕክምና መሣሪያዎችን ከውጭ መግዛት በሕግ ተከለከለ‼️መድኃኒቶች ወይም የሕክምና መሣሪያዎች በአገር ውስጥ አምራቾች የሚመረቱ ከሆነ በዓለም አቀፍ ግልጽ ...
05/06/2025

በአገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችንና የሕክምና መሣሪያዎችን ከውጭ መግዛት በሕግ ተከለከለ‼️

መድኃኒቶች ወይም የሕክምና መሣሪያዎች በአገር ውስጥ አምራቾች የሚመረቱ ከሆነ በዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ ከውጭ ግዥ መፈጸም ተከለከለ፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በማዕከል የሚፈጸሙ የመድኃኒቶችና የሕክምና መሣሪያዎች የግዥ አፈጻጸም መመርያ ይፋ አድርጓል፡፡
ከትናንት ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተፈጻሚ በሚሆነው መመርያ መድኃኒት ወይም የሕክምና መሣሪያ በአገር ውስጥ አምራቾች የሚመረት ከሆነ፣ በዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ ግዥ መፈጸም እንደማይቻል ይደነግጋል፡፡
መድኃኒቱ ወይም የሕክምና መሣሪያው በአገር ውስጥ አምራቾች የማይመረትም ቢሆን ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ ከሆነም፣ ከውጭ መግዛት እንደማይቻል መመርያው ይደነግጋል፡፡

ፒኤስጂ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆነ ግንቦት 23፣ 2017 ዓ.ም ፒኤስጂ ኢንተር ሚላንን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ዛሬ ምሽት በሙኒክ አል...
31/05/2025

ፒኤስጂ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

ግንቦት 23፣ 2017 ዓ.ም ፒኤስጂ ኢንተር ሚላንን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡

ዛሬ ምሽት በሙኒክ አልያንዝ አሬና ስታዲየም የተደረገውን የ2024/25 የሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ፒኤስጂ በፍጹም የበላይነት አጠናቋል።

ፒኤስጂ 5 ለ ዐ በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ባሸነፈበት የምሽቱ ጨዋታ ግቦቹን አሽራፍ ሀኪሚ፣ ዲዚሬ ዱዌ (2)፣ ክቫራስኬሊያ እና ማዩሉ አስቆጥረዋል።

በስፔናዊው አሰልጣኝ ሊውስ ኤነሪኬ የሚመራው ፒኤስጂ አስቀድሞ የሊግ-1 እና የኮፕ ዴ ፍረንስ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ የሶስትዮሽ ዋንጫን አሳክቷል።

ከአሁን በፊት በሙኒክ የተደረጉ ሁሉም የሻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ጨዋታዎች አዳዲስ ሻምፒዮኖች የነገሱበት እንደነበር ከጨዋታው አስቀድሞ በስፋት ሲነገር ቆይቷል።

ዘንድሮም በተመሳሳይ የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ የውድድሩን ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ አሳክቷል።

የምርት ጥራትን ከቦታ ጋር አቆራኝቶ የሚያስተዋውቀው ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው++++++++++++++++++++++++++የምርት ጥራትን ከቦታ ጋር አቆራኝቶ የሚያስተዋውቀው አለም አቀፉ...
31/05/2025

የምርት ጥራትን ከቦታ ጋር አቆራኝቶ የሚያስተዋውቀው ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው
++++++++++++++++++++++++++

የምርት ጥራትን ከቦታ ጋር አቆራኝቶ የሚያስተዋውቀው አለም አቀፉ የመልክዓ ምድር አመላካች ኮንፍረንስ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው።

የኢትዮጵያ አእምሯዊ መብት ጥበቃ ባለስልጣን የመልክአ ምድር አመላካች መብት ጥበቃ ስርአትን ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ተከትሎ የሚካሄደው ይህ ኮንፈረንስ በተለያዩ የተፈጥሮ ሀብቶቿ ለምትታወቀው ኢትዮጵያ የተሻለ አጋጣሚ እንደሚሆን ይጠበቃል።

በዓለም አቀፉ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ድርጅት የሚካሄደው ይህ ኮንፍረንስ፤ ግንቦት 26 እና 27 በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወልዱ ይመሰል ገልፀዋል።

በኮንፈረንሱ የዓለም አቀፉ የአእምሮአዊ መብቶች ጥበቃ ድርጅት ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ እስከ ሌሎች ዓለም አቀፍ ልዑካን እንደሚገኙበት ጠቁመዋል።

ልዑኩ በሚኖረው ቆይታ በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ገምግሞ ድጋፎችን እንደሚያደርግም በመግለጫው ተመላክቷል።

ከኮንፍረንሱ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ የምትታወቅባቸውን ምርቶች የሚያስተዋውቅ ኤግዚቢሽን እንደሚኖርም አስረድተዋል።

የመልክአ ምድር አመላካች ጥበቃ ስርአት ማለት አንድ አካባቢ ለሚታወቅበት ምርት ጥራት በግለሰብ ሳይሆን በማህበረሰብ ደረጃ እውቅና መስጠት መሆኑ ተመላክቷል።

በኢትዮጵያ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ብርቅዬ የተባለውን  ሰማያዊ ላቫ አመነጨ  | የኢትዮጵያ እሳተ ገሞራዎች ውስጥ እጅግ ብርቅዬ የሚባለውን ሰማያዊ ላቫ እየፈነጠቀ መሆኑ  እንደ ክስተት እየታየ...
28/05/2025

በኢትዮጵያ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ብርቅዬ የተባለውን ሰማያዊ ላቫ አመነጨ

| የኢትዮጵያ እሳተ ገሞራዎች ውስጥ እጅግ ብርቅዬ የሚባለውን ሰማያዊ ላቫ እየፈነጠቀ መሆኑ እንደ ክስተት እየታየ ይገኛል። ከኢንዶኔዢያ ጃቫ ግዛት ካዋ ኢጄን እሳተ ገሞራ ጋር ተመሳሳይነት አለው የተባለው ሰማያዊ ላቫው በመጀመሪያ እይታ ላቫው ከተራራው ላይ እየፈሰሰ ይመስላል፣ ነገር ግን ይህ ያልተለመደ ፍካት እንደሚታሰበው አይደለም።

"ሰማያዊ እሳት" እየተባለ የሚጠራው ይህ ክስተት በላቫ የተፈጠረ ሳይሆን ከእሳተ ገሞራው ስንጥቆች በሚወጡት የሚቃጠሉ የሰልፈር ጋዞች የሚመጣ መሆኑ ተገልጿል።

እስከ 600°C (1,100°F) የሚደርስ ሙቀት ያላቸው ትኩስ ጋዞች በአየር ውስጥ ከሚገኘው ኦክሲጅን ጋር ሲገናኙ፣ በእሳት ተያይዘው ደማቅ ሰማያዊ ነበልባል ይፈጥራሉ።

በካዋህ ኢጄን ያለው ትክክለኛው ላቫ እንደ አብዛኞቹ እሳተ ገሞራዎች የተለመደው ቀይ-ብርቱካናማ ቀለም ያለው ቢሆንም፣ የሚቃጠለው ሰልፈር ነበልባል የሚያብረቀርቅ ሰማያዊ ላቫ ምስልን የሚፈጥር ሲሆን በሌሊት ብቻ የሚታይ አስደናቂ ትዕይንት ነው ተብሏል፡፡

ኤም ፖክስ ____◾ምንነቱ! አጠቃላይ እውነታዎች!ኤም ፖክስ በሽታ በዝንጀሮ በጂነስ ኦርቶፖክስ ቫይረስ የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ሲሆን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በአካል ንክኪ ወይም በበሽታው ከ...
27/05/2025

ኤም ፖክስ

____

◾ምንነቱ! አጠቃላይ እውነታዎች!

ኤም ፖክስ በሽታ በዝንጀሮ በጂነስ ኦርቶፖክስ ቫይረስ የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ሲሆን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በአካል ንክኪ ወይም በበሽታው ከተያዙ እንስሳት ወደ ሰው ሊተላለፍ እና በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት የሚችል በሽታ ነው፡፡

◾የበሽታው ታሪካዊ ዳራ

የኤም ፖክስ ቫይረስ በዴንማርክ (1958) በዝንጀሮዎች ውስጥ የተገኘ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ልጅ ላይ የተገኘው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ነው፡፡ በቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተያዘው የዘጠኝ ወር ህጻን ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ1980 የፈንጣጣ በሽታን ማጥፋት እና የፈንጣጣ ክትባት በአለም አቀፍ ደረጃ ማብቃቱን ተከትሎ ኤም ፖክስ በመካከለኛው፣ ምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪካ ያለማቋረጥ ብቅ እያለ ይገኛል። በ2022-2023 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ተከስቷል። እንደ ሽኮኮዎች እና ጦጣዎች ያሉ የተለያዩ ትናንሽ አጥቢ እንስሳት ለበሽታው የተጋለጡ ናቸው፡፡

ከ1970 በኋላ የኤም ፖክስ በሽታ በመካከለኛው እና ምስራቅ አፍሪካ (ክላድ I) እና በምዕራብ አፍሪካ (ክላድ II) አልፎ አልፎ ተከስቷል። እ.ኤ.አ. በ 2003 በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የተከሰተው ወረርሽኝ ከውጭ ከሚገቡ የዱር እንስሳት (ክላድ II) ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ ከ2005 ጀምሮ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የተጠረጠሩ ህሙማን ሪፖርት ይደረጋሉ።

እ.ኤ.አ. በ 2017፣ የኤም ፖክስ በሽታ በናይጄሪያ እንደገና ብቅ አለ እና በመላ አገሪቱ እና ወደ ሌሎች መዳረሻዎች በሚጓዙ ሰዎች መካከል ተስፋፍቷል። እ.ኤ.አ. በ 2022 በ Clade I MPXV ምክንያት የኤም ፖክስ ወረርሽኝ በሱዳን ሪፐብሊክ ውስጥ በሚገኙ የስደተኞች ካምፖች ውስጥ ተከስቷል፡፡

◾የበሽታው ምልክቶች

ኤም ፖክስ በሽታ ቫይረሱ ካለባቸው ግለሰቦች ጋር ንክኪ ያለው ሰው የሚከተሉት ምልክቶች በሚታዩበት ወቅት ማለትም ሽፍታ፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ የራስ ምታት፣ የእጢ እብጠት፣ የቆዳ ቁስለትና ድካም፣ የጡንቻና የጀርባ ህመም ሲያስተውል በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ተገቢውን የምርመራና ህክምና አገልግሎት ማግኘት ይኖርበታል።

◾መከላከያ መንገዶች

ከላይ የተገለፁት ምልክቶች ባሉባቸው ታማሚዎች አካባቢ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎችን በመጠቀም፥ የኤም ፖክስ መሰል ሽፍታ የሚታይባቸው ሰዎች ጋር ባለመነካካት እና ታማሚዎቹ የተጠቀሙባቸውን ቁሳቁሶች፣ አልባሳትና መኝታ በአግባቡ ሳያጸዱ ባለመጠቀም፣ የግል እና የእጅ ንፅህና በመጠበቅና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ መከላከል ይቻላል።

በሽታው በቀጥታ ከሰው ወደ ሰው በንክኪ የሚተላለፍ እንደመሆኑ መጠን ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች የሚያሳይ ማንኛዉም ሰዉ በሚገኝበት ጊዜ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ሪፖርት እንዲያደርግ ወይም በ952 እና 8335 ነጻ የስልክ መስመር ጥቆማ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

በአሁኑ ወቅት ይህ በሽታ በተወሰነ ቦታ ብቻ የታየ በመሆኑ ህብረተሰባችን ሳይደናገጥ የተለመደውን አኗኗር መቀጠል የሚችል ሲሆን ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚወጣውን ወቅታዊ መረጃዎች በአግባቡ በመከታተል ራሱን እና ቤተሰቡን ከዚህ በሽታ እንዲጠብቅ እናሳስባለን።

መራራ እውነታዎች ⏸▶️⏭⏪⏩⏸▶️⏸⏸⏸⏸ምንም ነገር ለዘላለም አይቆይም፡፡ ችግሮችህ፣ የከበቡህ ሰዎች ስራህ ትዳርህና ግንኙነቶችህ ሁሉ ለጊዜዉ ነዉ፡፡ የሁሉም ነገር ፍፃሜ የሆነ ቀን ላይ ሲሆን...
17/04/2025

መራራ እውነታዎች
⏸▶️⏭⏪⏩⏸▶️⏸⏸⏸⏸
ምንም ነገር ለዘላለም አይቆይም፡፡
ችግሮችህ፣ የከበቡህ ሰዎች ስራህ ትዳርህና ግንኙነቶችህ ሁሉ ለጊዜዉ ነዉ፡፡ የሁሉም ነገር ፍፃሜ የሆነ ቀን ላይ ሲሆን ታየዋለህ፡፡ በህይወቴ ሁሉ አብረዉኝ ይኖራሉ ያልካቸዉ ነገሮች እንኳን ሳይቀሩ ሲፈረካከሱ ታያቸዋለህ።

ለሁሉም ነገር ተራ አለዉ፡፡ ሰዉን ብትጠቅም ጊዜዉን ጠብቆ አምላክህ ይከፍልሃል፡፡ ብትጎዳም እንዲሁ...በሰፈርከዉ ማንነት ጊዜዉ ሲደርስ ትሰፈራለህ

ማንም ሰዉ ስላንተ አይጨነቅም፡፡ 20% ፐርሰንቱ ብቻ ስላንተ ሲጨነቁ እነሱም የቅርብ ጓደኞችህና ቤተሰቦችህ መሆናቸዉን አትዘንጋ። 80 ፐርሰንቱ ግን ኑር አትኑር አንዳች ቅንጣት ስላንተ አያስቡም፡፡ ችግሮችህን ለነዚህ ለ 80% ፐርሰንት መናገር እራስህን ማባከን ነዉ ምክንያቱም ችግርህ ለነሱ ምናቸዉም አይደለምና! የራሳቸዉ ጉዳይ ብቻ ያሳስባቸዋልና ቆጠብ በል።

ሰዎች በህይወትህ ይመጣሉ ደግሞም ይሄዳሉ፡፡ አንድ ቀን ለብቻህ ሰዉ በሌለበት ልትሞት ትችላለህና ሰዎችን አትደገፍ።

ከ5-6 የልብ የምትላቸዉ ሰዎች በቀር ፌስቡክ ላይ ያሉት የጓደኛ ጋጋታ ምንም አይጠቅሙህም፡፡ ብትሞት እንኳ ቀብርህ ላይ የማይመጡ ብዙዎች መሆናቸዉን እወቅ።

የስራ አለቃህ እንድታድግና የተሻለ ቦታ እንድትይዝ ሊመኝ ይችላል ግን መቼም እንድትበልጠዉ አይፈልግም፡፡ ምንም ሽልማትና ጭብጨባ ቢበዛልህ ከሱ እንደምትበልጥ ካሰበ አንተን ለመገፍተር ወደ ኋላ አይልም ።

98 % ፐርሰንቱ ሰዉ መቼ እንደተወለድክ እንኳን አያዉቅም 2 % ፐርሰንቱ መቼም እነማን እንደሆኑ መገመት አያቅትህም ፡፡ ካላመንከኝ ሞክረህ እየዉ!

የዉሸት ጓደኞችህ የተሻለ ህይወት እንድትመራ በፍጹም አይፈልጉም፡፡ ነገሮች መልካም ሲሆኑ የሚሰበሰቡ ሰዎች ሊያስገርምህ አይገባም አንድ ቀን ህልምህ 'ወለም' ብሎ ካዩ እጃቸዉን ቀስረዉ ይስቁብሃል፡፡ የዛኔ ያልሳቁብህን የልብ ጓደኞችህ አድርጋቸዉ።

ገንዘብ ያለዉና ፀዳ ብሎ የሚመላለስ ሰውን ብዙዎች ሲያከብሩት ትመለከተዋለህ፡፡ የማያዉቅህ እንኳን ቢሆን ፀዳ ካልክበት ሊያከብርህ ሲዳዳዉ ታየዋለህ።

ለሰዎች ምክር መስጠት በጣም ቀላል ነዉ ነገር ግን ምክርን ወደተግባር መቀየር ከባዱና አስቸጋሪዉ ነገር ነዉ፡፡ አንዳንዴ ሰዉን ካለበት ማጥ ለማዉጣት ካሰብክ ከምክር በላይ የሆነ ስብዕና ሊኖርህ ይገባል፡፡

አንድ ውሸታም ጓደኛህ ከ 100 ጠላትህ ጋር እኩል ጥፋት ያደርሳል፡፡ ጠላቶችህን ተከታተላቸዉ ጓደኞችህን ደግሞ በጣም ተከታተላቸዉ።

ነገሮች መልካም እንዲሆኑና እንዲሳኩ ያለ የሌለ ጥረትህን አድርገህ ሳይሳካልህ ቀርቶ ይሆናል፡፡ ይህ ያንተ ደካማነት ሳይሆን ህይወት እንዲህ አይነት ገፅታም ስላላት ነገሩን ተቀበለዉ፡፡

ለመወደድ ልዩ ሰዉና ሁሉንም ሞካሪ መሆን አይጠበቅህም ፡፡ እንዳንዴ ሰዉ ሁሉ ባይወድህ እንኳን ይህ ምንም ማለት እንዳልሆነ ተረዳ፡፡ በሰዎች መጠላትንም ቀለል አድርገህ ዉሰደዉ ምክንያቱም እንዴት እራስህን ማሳደግ እንዳለብህ ማጤን ወሳኙ ነገር ሲሆን የሰዎችን ስሜት እያዳመጥክ ከፍና ዝቅ እያልክ መኖር አይጠበቅብህም፡፡

የራስህ አስተሳስብ ይኖርሃል፡፡ ሌሎችም እንዲሁ...ሰዎች በሀሳብህ አለመስማማታቸዉ አንተነትህ ላይ የሚያመጣዉ ነገር የለም፡፡ ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን አስተሳሰብ ረጋግጠህ አትዉጣ፡፡ የሰዎችን ሃሳብ አክብር ሰዎችም ሃሳብህን እንዲያከብሩ አድርግ።

ሰዎች ስለ ደስታ አጋነዉ ሲያወሩ ትሰማ ይሆናል፡፡ በአጭሩ ደስታ ማለት ስሜትህ ሳይሆን አእምሮህ ያለበት ሁኔታ ነዉ፡፡ ደስተኛ ሆነህ በሰዎች ልትጎዳ ትችላለህ።

ይቺ አለም የምትፈልግህ ጠቃሚ ነገር አንተ ጋር እንዳለ ስታምን ብቻ ነዉ፡፡ ባጠቃላይ አለም እራስ ወዳድ ናት።

የብርቱካን ተመስገን ሕጋዊ የጋብቻ ውል◾️"ባለቤት አለኝ፤ አሁን እንዴት ነው ከባለቤቴ ጋር ሰላም የምናገኘው መተማመንስ የሚኖረን?" - ብርቱካን ተመስገንሀሰተኛ ድራማ የተሠራባት ብርቱካን ተ...
28/03/2025

የብርቱካን ተመስገን ሕጋዊ የጋብቻ ውል

◾️"ባለቤት አለኝ፤ አሁን እንዴት ነው ከባለቤቴ ጋር ሰላም የምናገኘው መተማመንስ የሚኖረን?" - ብርቱካን ተመስገን

ሀሰተኛ ድራማ የተሠራባት ብርቱካን ተመስገን ቤተሰቦቻቸው ጋር ሄደው በአካባቢው ባህል መሰረት ትዳር እንደመሰረተች ራሷም ባለቤቷም ምሥክርነት ሰጥተዋል።

በጋብቻዋም የሁለት ዓመት ልጅ እንዳፈራች እና በመልካም ሁኔታ ስትኖር እንደነበር ጎረቤቶቿን ጨምሮ ሁሉም ምሥክርነት ሰጥተዋል።

ብርቱካን ከመዓዛ መሐመድ ጋር በስልክ ባደረገችው ንግግር ያስጨነቃት እንዴት ከባለቤቷ ጋር ተመልሳ እንደምትኖር ነው።

ባሏን ያገባቸው በድንግልና እንደሆነ የምታወሳው ብርቱካን፤ አሁን እንዴት ባሏ የድሮ ማንነቷን እንደሚቀበል እና ቀጣይ ምን ዓይነት ሕይወት ሊኖራት እንደሚችል ትጠይቃለች።

ይህን ሁሉ እንድትጠይቅ ያደረጋት ጉዳይን የሚያረጋግጠው የጋብቻዋ ሁኔታ በምሥክር ወረቀት የተረጋገጠ እንደሆነ መረጃ ተገኝቷል።

ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆነው ከወሳኝ ኩነት ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም የተሰጣቸው የጋብቻ ምሥክር ወረቀት ነው።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251114670303

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Melkamu Abebaw Zeyini posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share