NT NEWS ETHIOPIA

NT NEWS ETHIOPIA NT NEWS ETHIOPIA የዜና ድህረ-ገፅ ሲሆን ወቅታዊ፤ ሃገራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ዜናዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በታማኝነት የሚያቀርብ ፕላት ፎርም ነው ።

Tetelestai - ተፈፀመ " እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። "( ትንቢተ ኢሳያስ 5...
04/19/2025

Tetelestai - ተፈፀመ

" እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። "
( ትንቢተ ኢሳያስ 53-5 )

የሶማሌላንድን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ አሸነፉየዋደኒ ፓርቲ እጩ ሆነው የቀረቡት አብዲራህማን ኢሮ ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እንዳሸነፉ የምርጫ...
11/19/2024

የሶማሌላንድን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ አሸነፉ

የዋደኒ ፓርቲ እጩ ሆነው የቀረቡት አብዲራህማን ኢሮ ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እንዳሸነፉ የምርጫ ኮሚሽኑ ዛሬ አሳውቋል።

በስድስተኛው የሶማሌላንድ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ሆነው የቀረቡት መሃመድ አብዱላሂ ኢሮ ኘሬዝደንት ሙሴ ቢሂን በከፍተኛ ድምፅ ብልጫ አሸንፈዋል።

የሶማሌላንድ ምርጫ ኮሚሽን ባወጣው ሪፓርት አብዱላሂ ኢሮ 63.9በመቶ ድምፅ አግኝተዋል። የሃገሪቱ ኘሬዝደንት ሙሴ ቢሂ ደግሞ 34.8 በመቶ ማግኘታቸው ታውቋል።

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ብድር ሰጠችበአለም አዲስ አገር ለሆነችው ደቡብ ሱዳን የተሰጠው ብድር በሁለቱ አገራት መካከል አገናኝ ለሚሆን መንገድ ግንባታ የሚውል ነው።የአራት አመት እፎይታ...
11/05/2024

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ብድር ሰጠች

በአለም አዲስ አገር ለሆነችው ደቡብ ሱዳን የተሰጠው ብድር በሁለቱ አገራት መካከል አገናኝ ለሚሆን መንገድ ግንባታ የሚውል ነው።

የአራት አመት እፎይታ ኖሮት በ10 አመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቀው ብድር ከ738 ሚሊየን ዶላር በላይ ነው።

በደቡብ ሱዳን ድንበር ውስጥ የሚገነባው 220 ኪሜ መንገድ በኢትዮጵያ ተቋራጮች እና አማካሪዎች እንዲከናወን በሁለቱ አገራት ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል።

የብድር አመላለሱም በካሽ እና በድፍድፍ ነዳጅ እንደሚሆን ነው የተጠቀሰው ሲል ካፒታል አስነብቧል።

Facebook.com/ntnewsethiopia

ገዳ 🤔
08/03/2024

ገዳ 🤔

Breaking news,     ትረምፕ ምርጫ ቅሰቀሳ ላይ እያለ ከደቂቃዎች በፊት በመድረኩ ላይ የጥይት ድምጽ በመሰማቱ በፍጥነት በጠባቂዎቻቸው ከመድረኩ እንዲወርዱ ተደርገዋል:: የተተኮሰው ጥ...
07/14/2024

Breaking news,

ትረምፕ ምርጫ ቅሰቀሳ ላይ እያለ ከደቂቃዎች በፊት በመድረኩ ላይ የጥይት ድምጽ በመሰማቱ በፍጥነት በጠባቂዎቻቸው ከመድረኩ እንዲወርዱ ተደርገዋል:: የተተኮሰው ጥይቅት ይሁን ተቀጣጣይ ነገር ጆሯቸው አካባቢ እንደመታቸውና እንደደማ ተንቀሳቃሽ ምስሉ ያሳያል::

በትራምፕ ላይ የተኮሰ ሰው ህይወቱ አልፏል:: ግለሰቡን ፖሊስ ተኩሶ ይምታው እራሱን ያጥፋ ግን እስካሁን መረጃዎች አልወጡም:: BBC ግለሰቡ መሞቱን ብቻ ዘግቧል::

ከደቂቃዎች በፊት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያሉ ሲተኮስባቸው የሚታይበትን ቪዲዮ ላይ ፡ ትራምፕ ጆሯቸው አካባቢ በመጠኑ የደማ ነገር ይታያል ። እና የሚገርመው ምንድነው ? የፀጥታ ሀይሎች ትራንፕን ከበው ሲወስዷቸው ፡ በእናሸንፋለን ምልክት እጃቸውን ጨብጠው ለደጋፊዎቻቸው ያሳዩ ነበር ። ...
እንደውም. . በቀጥታ ታርጌት ከሆኑት ከሳቸው ይልቅ በአካባቢው የነበረው ሰው ደንግጧል ። .........
በዚህ በዛሬው የፔንስልቫንያ ጥቃት ፡ የግድያ ሙከራውን ያደረገው ሰውና ፡ የሌላ የአንድ ሰላማዊ ሰው ህይወት እንዳለፈ እየተነገረ ነው ።

ሕወሓት "በልዩ ሁኔታ" በፓርቲነት እንዲመዘገብ የፍትሕ ሚኒስቴር ጠየቀሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) "ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመጽ ተግባሩን በማቆም፤ ሕገ መንግሥታዊ ዴሞክራሲያዊ...
06/28/2024

ሕወሓት "በልዩ ሁኔታ" በፓርቲነት እንዲመዘገብ የፍትሕ ሚኒስቴር ጠየቀ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) "ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመጽ ተግባሩን በማቆም፤ ሕገ መንግሥታዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ የተስማማ በመሆኑ በልዩ ሁኔታ" መመዝገብ እንዲችል ፍትሕ ሚኒስቴር ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ጠየቀ።
በፍትሕ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞትዮስ ፊርማ ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተጻፈው ደብዳቤ "በልዩ ሁኔታ የፖለቲካ ፓርቲ ምዝገባን ይመለከታል" የሚል ርእስ የተሰጠው ሲሆን ደብዳቤው ለቦርዱ መድረሱን ከተቋሙ ለማረጋገጥ ችለናል።
ፍትሕ ሚኒስቴር ጥያቄውን ያቀረበው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ጉባኤው አሻሽሎ ያፀደቀውን የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ሥነ ምግባር አዋጅን መሠረት አድርጎ ስለመሆኑ ለምርጫ ቦርድ በተፃፈው ደብዳቤ ተጠቅሷል።
ዘገባው የሰለሞን ሙጨ ነው ።

©DW AMHARIC

በቴሌግራም እና በፌስቡክ ይከታተሉን ።

ቴሌግራም
https://t.me/ntnewsethiopia
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/ntnewsethiopia

06/21/2024



ጎረቤት ኬንያ ታቃውሞ እየናጣት ነው።

መንግሥት በታክስ ላይ ጭማሪ ሊያደርግ ማቀዱን ተከትሎ በተለይም ወጣቱ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥቷል።

ከወጣቶቹ ሰልፍ ጋራ በተያያዘ ትላንት አንድ ሰው #ተገድሏል፡፡

ግድያው የተፈጸመው በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ነው ተብሏል።

ዛሬም በናይሮቢና የተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ ሲካሄድ ውሏል።

ተቃዋሚዎቹ በሚቀጥለው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሔድ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራታቸው ተነግሯል።

ይህ በኬንያ ወጣቶች መሪነት የተነሳው እና ባለፈው ማክሰኞ በናይሮቢ ከተማ ተጀምሮ በመላው አገሪቱ የተሰራጨው ተቃውሞ በመጭው ማክሰኞ ብሔራዊ የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል።

ተቃዋሚዎቹ ለምን አደባባይ ወጡ ?

ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ደስተኛ አይደሉም።

አካሄዳቸውም ለብዙ ኬንያውያን ኑሯቸውን አስቸጋሪ ማድረጉን ይገልጻሉ።

በተለይም መንግሥት አሁን ያዘጋጀው የታክስ ጭማሪ ረቂቅ አዋጅ የህዝቡን ኑሮ የሚያመሰቃቅል እንደሆነ በመግለጽ እየተቃወሙ ነው።

የታክስ ጭማሪውን በመቃወም ለወራት በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሲደረግ ቆይቶ ነው ወደ ተቃውሞ ሰልፍ የተቀየረው።

የኬንያ መንግሥት ምን ይላል ?

መንግሥት የታክስ ጭማሪ ሊያደርግ ያቀደው ብድር ለመክፈል እና ለልማት ሥራዎች እንደሆነ ገልጿል።

ተቃውሞውን ተከትሎ ከረቂቅ አዋጁ ላይ የተወሰኑትን እንደሚተው ቢያስታውቅም ተቃውሞው ግን ዛሬም ቀጥሏል።

የታክስ ጭማሪው ምን ላይ ነው ?

መንግሥት በያዘው እቅድ የታክስ ጭማሪው በተለያዩ ሸቀጦች ላይ የሚደረግ ነው።

በነዳጅ ላይ ሊጨመር የታሰበው 9 ሺልንግ ሲሆን ጭማሪው ለፈረሱ መንገዶች መጠገኛ እንደሚሆን የአዋጁ አርቃቂዎች አስታውቀዋል።

መንግስት በተጨማሪ አካባቢን ለመጠበቅ በሚል ታክስ ለመጣል ያቀደ ሲሆን ይህም ደግሞ የፕላስቲ ውጤቶች የሚያስከትሉትን ብከላ ለመከላከል እንደሆነ አስታውቋል።

ብሔራዊ ሸንጎው ረቂቅ አዋጁን ሚቀጥለው ሳምንት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ለተቃውሞ የወጡት ኬንያውያን ግን በተቃውሟቸው እንደሚገፉበት አስታውቀዋል።





©tikvahethiopia

በቴሌግራም እና በፌስቡክ ይከታተሉን ።

ቴሌግራም
https://t.me/ntnewsethiopia
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/ntnewsethiopia

የኬንያ መንግስት ሊጥለው ያሰበውን ቀረጥ ለመቃወም አደባባይ የወጡ ዜጎች ጉዳት ደረሰባቸው ። የኬንያ መንግስት ሊጥለው ያሰበውን ቀረጥ ተከትሎ ለተቃውሞ አደባባይ ከወጡ ሰዎች መካከል 200 ሰ...
06/21/2024

የኬንያ መንግስት ሊጥለው ያሰበውን ቀረጥ ለመቃወም አደባባይ የወጡ ዜጎች ጉዳት ደረሰባቸው ።

የኬንያ መንግስት ሊጥለው ያሰበውን ቀረጥ ተከትሎ ለተቃውሞ አደባባይ ከወጡ ሰዎች መካከል 200 ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው 100 ሰዎች ታስረዋል።

በቅርቡ ኬንያ 2.7 ቢሊየን ዳላር ከቀረጥ ለማግኘት ያለመ የታክስ ረቂቅ ይፋ አድርጋ ነበር።

ከሰሞኑ በጉዳዩ ዙሪያ ተቃውሞ መበራከቱን ተከትሎ ፓርላማው በረቂቅ የፋይናንስ ሕጉ ላይ እየተወየየ ነበር፤ ነገር ግን ተቃውሞዎች ሊበርዱ አልቻሉም።

ማክሰኞ ዕለት የተጀመረው የአደባባይ ተቃውሞ ተጠናክሮ በመቀጠሉ የተወሰኑ ቀረጦችን መንግሥት አንስቷል።

ፖሊስ በፓርላማ አቅራቢያ ላይ ለተቃውሞ በተሰበሰቡ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ እና ውሃ በመርጨትም ለመበተን ሞክሯል።

በኬናዊያን ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው የቀረጥ ረቂቅ በሀገሪቱ ፓርላማ የመጀመሪያ ዙር ያለፈ ሲሆን ማክሰኞ ሕግ ሆኖ ለማፅደቅ ድምጽ ይሰጥበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የኬኒያ ዋና ከተማ በሆነችው ናይሮቢ ዛሬ በነበረው ተቃውሞ ፖሊስ በተኮሰው አስለቃሽ ጭስ ከ200 ሰዎች በላይ ጉዳት ሲደርስባቸው 6 ሰዎች ሲያመልጡ የመኪና አደጋ አጋጥሞቸዋል። 5 ሰዎች ደግሞ በጥይት ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸውን አልጃዚራ ዘግቧል።

በቴሌግራም እና በፌስቡክ ይከታተሉን ።

ቴሌግራም
https://t.me/ntnewsethiopia
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/ntnewsethiopia

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሲታወስ...አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ተወልዶ ያደገው ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ አንድ መቶ ኪሎ ሜትሮች ርቃ በምተገኘው አምቦ ከተማ ውስጥ ነው።እናቱ ወይዘሮ ጉደቱ ሆራ፣...
06/21/2024

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሲታወስ...

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ተወልዶ ያደገው ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ አንድ መቶ ኪሎ ሜትሮች ርቃ በምተገኘው አምቦ ከተማ ውስጥ ነው።

እናቱ ወይዘሮ ጉደቱ ሆራ፣ ሃጫሉ ከልጅነቱ ታሪክን መስማትና የመንገርና ዝንባሌውንና ችሎታውን ጠንቅቀው ተረድተውት ስለነበር ከመጀመሪያው አንስቶ ያበረታቱት እንደነበር በተደጋጋሚ ሃጫሉ ያስታውሳል።

አባቱ አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ደግሞ ልጃቸው ሃጫሉ በትምህርቱ ዓለም ገፍቶ ዶክተር ወይም የዩኒቨርሲቲተ መምህር እንዲሆንላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው።
ሃጫሉ ግን ገና ከልጅነቱ ጀምሮ በፍቅሯ ለወደቀላት ሙዚቃ ነበር መላው ትኩረቱ። በአስራዎቹ እድሜው ላይ እያለ እንኳን የበርካቶችን ስሜት የሚኮረኩሩ ሙዚቃዎችን ይጫወት ነበር።
ሃጫሉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለ በ1995 ዓ.ም የ17 ዓመት ታዳጊ እንዳለ ታስሮ ለአምስት ዓመታት አምቦ በሚገኘው እስር ቤት አሳልፏል።

ፖለቲካዊ መልዕክት ያላቸውና ተወዳጅ የኦሮሞ የትግል ሙዚቃዎችን ማቀንቀኑን እንዲያቆም ለማድረግ መታሰሩን ሃጫሉ ይናገራል።
ነገር ግን መታሰሩ እንደውም ይበልጥ በሥራው እንዲገፋበትና በሰዎች ላይ የሚደርሰውን ግፍ እና ጭቆና የበለጠ እንዲገባው ማድረጉን በአንድ ወቅት ተናግሮ ነበር።
በእስር ላይ ሳለም ነበር የሙዚቃ ግጥሞችን ዜማዎችን መጻፍ የጀመረው። ከአምስት ዓመታት በኋላ ሲለቀቅ የደረሰበትን በደል ለመቃወምና ለሚሊየኖች ድምጽ ለመሆን ወስኖ እንደወጣ ይናገራል ሃጫሉ።
በአጭር ጊዜም በኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ዘንድ ብቻ ሳይሆን በመላዋ አገሪቱ ተወዳጅ የሆነለትን 'ሰኚ ሞቲ' የተሰኘውን አልበሙ አቀረበ። የዚህ የሙዚቃ ስብስብ አብዛኛዎቹ ግጥሞችና ዜማዎች ሃጫሉ በእስር ላይ እያለ የሰራቸው እንደነበሩ ይነገራል።
በወቅቱ በሃያዎቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል ውስጥ የነበረው ሃጫሉም በዚህ አልበሙ በተለይ ደግሞ የአልበሙ መጠሪያ በነበረው ሙዚቃው ቋንቋውን በማይችሉ ሰዎች ዘንድም ታዋቂነትን ለማትረፍ ችሎ ነበር።

ከጥቂት ዓመት በኋላም ወደ አሜሪካ የሙዚቃ ሥራዎቹን ለማቅረብ በሄደበት ጊዜ ሁለተኛውንና "ዋኤ ኬኛ" አልያም "የእኛ ነገር" የሚል ትርጉም ያለውን አልበሙን ለቀቀ።
በወቅቱ አልበሙ አማዞን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ በመሸጥ ከፍተኛ ትኩረትን አግኝቶ የነበረ ሲሆን፤ የሃጫሉ ተወዳጅነትም የበለጠ እየተጠናከረ መጣ።
ሃጫሉ እንደሚለው "ሙዚቃ ለእኔ ህይወቴ ነው። ውስጤ ነው ያለው። የሕዝቤን የአኗኗር ዘዬ የማሳውቅበት፣ የሆዴን የምገልጽበት ነው። ሙዚቃ ሁሉ ነገሬ ነው፤ ዘመድም ጠላትም ያፈራሁበት።"
ሃጫሉ ተወዳጅ የሆኑ የኦሮሞ የሙዚቃ ስልቶችን ከዘመናዊው ሙዚቃ ጋር በማጣመር በሚያቀርባቸው ሥራዎቹ ብዙዎችን ጆሮና ቀልብ ለመማረክ አስችሎታል። በአገሪቱ የሚገኙ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎችም ሙዚቃዎቹን በተደጋጋሚ በማጫወታቸው በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ዘንድ አድናቆትን ማግኘት ችሏል።
ከሦስት ዓመት በፊት በአገሪቱ ተቀስቅሶ ከነበረው ጸረ መንግሥት ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ በነበረው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ወቅት የሃጫሉ ያወጣው 'ማለን ጂራ' የተሰኘው ነጠላ ሙዚቃው ከፍተኛ ተወዳጅነትን ከማትረፍ አልፎ የእንቅስቃሴው መነቃቂያ ሆኖ ነበር።

ሃጫሉ የመንግሥት ባለስልጣናት በሚገኙባቸውና በቀጥታ በቴሌቪዥን በሚቀርቡ በትልልቅ የሙዚቃ መድረኮች ላይ በመገኘት ሙዚቃዎቹን በሚያቀርብበት ጊዜ ያለፍርሃት የሚሰማውን ፖለቲካዊ ጉዳዮችንም በማቅረብ በድፍረቱ ይታወቃል።
ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት የነበረው የ36 ዓመቱ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሰኞ ሰኔ 22/2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ በተፈጸመበት ጥቃት ህይወቱ ያለፈ ሲሆን ከህልፈቱ ቡኋላም በህይወት በነበረበት ጊዜ ጀምሮ ነገር ግን ያልጨረሰውን አልበም ወዳጆቹ እና ቤተሰቡ በማስጨረስ ' ማልመሊሳ ' የሚል መጠርያ ያለውን አልበም ማበርከት ተችሏል አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ የ ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱ ፖለቲካ የገባው ድንቅ የጥበብ ሰው እና የሰብዐዊ መብት ተሟጋች ነበር ።

በቴሌግራም እና በፌስቡክ ይከታተሉን ።

ቴሌግራም
https://t.me/ntnewsethiopia
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/ntnewsethiopia

ደቡብ ኮርያ ዩክሬንን በጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ መሞከር ማሰቧ ትልቅ ስህተት ነው ሲሉ ፑቲን አስጠነቀቁ ቭላድሚር ፑቲን ደቡብ ኮሪያ ዩክሬንን በጦር መሳሪያ የምታስታጥቅ ከሆነ "ትልቅ ስህተት"...
06/21/2024

ደቡብ ኮርያ ዩክሬንን በጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ መሞከር ማሰቧ ትልቅ ስህተት ነው ሲሉ ፑቲን አስጠነቀቁ

ቭላድሚር ፑቲን ደቡብ ኮሪያ ዩክሬንን በጦር መሳሪያ የምታስታጥቅ ከሆነ "ትልቅ ስህተት" እንደምትሰራ አስጠንቅቀዋል። ፑቲን ይህንን አስተያየት የሰጡት ሴኡል እንዲህ ያለውን እንቅስቃሴ እያደረገች ነው ካለ በኋላ ሲሆን ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ በሁለቱም ሀገራት ላይ "ጥቃት" በሚፈጠርበት ጊዜ እርስ በርስ ለመረዳዳት የደረሱበትን አዲስ ስምምነት የአፀፋ ምላሽ ነው።ሴኡል ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ለማቅረብ ከወሰነች ሩሲያ “አሁን ያለውን የደቡብ ኮሪያን አመራር ሊያስደስት የማይችል ውሳኔ ታደርጋለች” ሲሉ ፑቲን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

የሩሲያው መሪ በቬትናም ውስጥ ንግግር ያደረጉት በፒዮንግያንግ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ ሲሆን ብዙም ሳይቆይ ከሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር የጋራ መከላከያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ደቡብ ኮርያ ቀደም ሲል ስምምነቱን ለብሄራዊ ደህንነቷ አስጊ ነው በማለት አውግዛ የነበረ ሲሆን የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ቻንግ ሆ ጂን ሀገራቸው "ለዩክሬን የምትሰጠውን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ጉዳይ እንደገና ለማየት ማቀዷን" ተናግረዋል። የፑቲንን አስተያየት ተከትሎ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንታዊ ፅህፈት ቤት አርብ እንዳስታወቀው ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ለማቅረብ የተለያዩ አማራጮችን እንደሚያስብ ሩሲያ የምታደርገው እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረተ ነው ብሏል።

በደቡብ ኮሪያ የሚገኘውን የሩስያ አምባሳደርን ሴኦል በማስጠራት ተቃውሞ እንደምታሰማ ዮንሃፕ የዜና ወኪል ስማቸውን ያልተጠቀሰውን የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ደቡብ ኮሪያ ለዩክሬን ሰብአዊ እርዳታ እና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ብትሰጥም ሀገራትን በጦርነት አለማስታጠቅ ይፋዊ ፖሊሲ አላት። በዚህም እስካሁን ገዳይ መሳሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነችም። አንዳንዶች በሩሲያ እና በሰሜን ኮርያ መካከል ያለው ጥልቅ ወታደራዊ ትብብር ደቡብ ኮርያ አካሄዱን እንደገና እንድታስብበት እያደረጋት ይገኛል ብለዋል። ተንታኞች ቀደም ሲል ዩክሬን የፑቲንን የሰሜን ኮርያ ጉብኝት በደቡብ ኮርያ ላይ ግፊት ለመጨመር እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል ።

በጉብኝቱ ወቅት ኪም ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ወረራ “ሙሉ ድጋፍ” ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ሩሲያ የሰሜን ኮሪያ ሚሳኤሎችን በዩክሬን እያሰማራች መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች እየጨመሩ መጥተዋል። በዛሬው እለት የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ የሩስያ እና የሰሜን ኮሪያ ስምምነትን በመመዘን በክልሉ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የሚጨነቅ ማንኛውንም ሀገር ሊያሳስብ ይገባል ብለዋል። አክለውም ስምምነቱ “ምንም የሚያስደንቅ አይደለም” ሲሉ ዩናይትድ ስቴትስ ስለ ሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ግንኙነት ለብዙ ወራት ስታስጠነቅቅ መቆየቷን ገልፀዋል።

በቴሌግራም እና በፌስቡክ ይከታተሉን ።

ቴሌግራም
https://t.me/ntnewsethiopia
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/ntnewsethiopia

ፑቲን የምስራቅ እስያ ሁለተኛ ጉብኝታቸውን በቬትናም አድርገዋልየሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በምስራቅ እስያ  ሁለተኛው የሆነውን ጉብኝታቸው ለማድረግ በቬትናም ዋና ከተማ ሃኖይ ተገኝተዋ...
06/20/2024

ፑቲን የምስራቅ እስያ ሁለተኛ ጉብኝታቸውን በቬትናም አድርገዋል

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በምስራቅ እስያ ሁለተኛው የሆነውን ጉብኝታቸው ለማድረግ በቬትናም ዋና ከተማ ሃኖይ ተገኝተዋል።

ፕሬዝዳንት ፑቲን ወደ ሰሜን ኮሪያ እና ቬትናም ያደረጉት ጉብኝታቸው ሩሲያ በዚህ አካባቢ ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ማሳያ ተደርጎ እየተወሰደ ነው።

አሜሪካ ጉብኝቱን ለፕሬዚዳንት ፑቲን በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስተዋወቅ ዕደል መስጠቱን ወቅሳለች።

የቬትናም ከሩሲያ ግንኙነት ጅማሮ በ1950ዎቹ በሰሜን ቬትናም ውስጥ ለነበረው የኮሚኒስት መንግስት በሶቪየት ኅብረት በተሰጠው ወሳኝ ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ የተጀመረ እና ብዙ አስርት ዓመታትን የተሻገረ ነው።

በቴሌግራም እና በፌስቡክ ይከታተሉን ።

ቴሌግራም
https://t.me/ntnewsethiopia
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/ntnewsethiopia

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ በመባል ተሸለመ ።የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2024፣ የአፍሪካ ምርጥ የበ...
06/20/2024

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ በመባል ተሸለመ ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2024፣ የአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ (Best Entertainment Award in Africa) እና የአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ ገመድ ዓልባ ኢንተርኔት አገልግሎት (Best Wi-Fi Award in Africa) ዘርፍ ሽልማት ወስዷል።

ይህ በ “Airline Passenger Experience Association” (APEX) የመንገደኞችን ድምፅ መሰረት በማድረግ ለአየር መንገዶች ዕውቅና የሚሰጥበት መድረክ በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሽልማቶች አንዱ ሲሆን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ አየር መንገዶች ለሚያቀርቡት የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ዕውቅና የሚሰጥበት ነው።

TELEGRAM :- t.me/ntnewsethiopia
FACEBOOK :- NT NEWS ETHIOPIA

Address

Washington D.C., DC

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when NT NEWS ETHIOPIA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to NT NEWS ETHIOPIA:

Share