
09/28/2025
ቡታጅራ ምን ተፈጠረ?‼
ትናንት ምሽት ቡታጅራ ከተማ አጋጥሞ የነበረው ቃውሞ ዛሬ በአንፃራዊነት መብረዱ ተሰምቷል።
ትናንት በከተማዋ ተቀስቅሶ የነበረው ተቃውሞ መነሻ ምክንያት በመስቃን ወረዳ እንቦር ቀበሌ ይተዳደርበት የነበረው የስናኖ ሴራ የተባለ አካባቢን የዞኑ አስፈፃሚዎች "የእንቦር ቀበሌ አይደለም ፣ የዶቢ ቀበሌ ነው።" ብለው በመወሰናቸው መሆኑን የደረሰኝ ጥቆማ ያመለክታል።
"ለመቼውም ቢሆን ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል። በጎጥ ህዝብን ማበጣበጥ ተገቢ አይደለም።" ሲሉ አስተያዬታቸውን ያጋሩ የከተማዋ ነዋሪዎች አልጠፉም።
ነዋሪዎቹ የሰለጠነው አለም በዞንና በወረዳ አይደለም በአንድ ቤት ግድግዳ የአገር ድንበሩን በሀሳብ መስመር እያካለለ ተከባብሮና ተደማምጦ ሲኖር፣ በእኛ ሀገር ደግሞ ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁናቴ በማንነት ላይ ያተኮረ መሳሳብና "የእኔ" ባይነት ለመግነኑ መዋቅሩ ራሱን ሊፈትሽ ይገባልም ነው ያሉት።
👉ፔጃችንን ላይክ እና ፎሎው በማድርግ ቤተሰብ እንሁን!🙏
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ👇
https://t.me/zumra_tube