ድምፀ ተዋሕዶ - Voice of Tewahido - VoT

ድምፀ ተዋሕዶ - Voice of Tewahido - VoT ድምፀ ተዋሕዶ - Voice of Tewahedo በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚያተኩሩ መረጃዎችን የምንሰጥበት ነው፡፡

የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በእያንዳንዳችን እጅ ነው!ሥርዐት ጠብቀን የምንማጸናቸው አባቶች ድምጻችንን ለመስማት የተዘጋጁ አይመስሉም። ከሚሞቱላቸው ልጆቻቸው ይልቅ ማዕበል የሚያናውጠውን የፖለቲካ ...
06/05/2023

የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በእያንዳንዳችን እጅ ነው!

ሥርዐት ጠብቀን የምንማጸናቸው አባቶች ድምጻችንን ለመስማት የተዘጋጁ አይመስሉም። ከሚሞቱላቸው ልጆቻቸው ይልቅ ማዕበል የሚያናውጠውን የፖለቲካ ትርፍ ለማዳመጥ ጆሯቸውን አዘንብለዋል። ከገዳማውያን ይልቅ ብሔርተኞችን ተቀብለዋል። ከዋልድባ እስከ ማኅበረ ሥላሴ፣ ከጣና ቂርቆስ እስከ ደብረ ሊባኖስ የተማጸኑ ድምጾች ቦታ አጥተዋል። አባቶች የጀመሩት ኢቀኖናዊ አካሄድ ቤተ ክርስቲያንን የሚደፋፈር ቅጽሯን የሚያፈርስ ነው። ከነዮዲት፣ ከነግራኝ እና ከውጭ ጠላቶች ጥፋት ቀጥሎ የሚመጣው ቀኖናዊ ጥሰት በታሪክ ተመዝግቦ የሚቀመጥ የታሪካችን ጠባሳ ሆኗል።
ምንም እንኳን መፍትሔው እየከረረ እና እየጠነከረ ቢሄድም እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ይህንን ሕገ ወጥ ሹመት መከላከላችንን እንቀጥላለን። ተቃውሟችንን እና ድምፃችንን ንቀው ፖለቲካዊ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳትን በሚያካሂዱ አካላት ግን እጃችን መጠንከሩ ልባችንም መጨከኑ የግድ ነው። ቤተ ክርስቲያን በውጭ ኃይሎች ስትደፈር ከሞትን በውስጥ ፖለቲከኞች መሠረቷ ሲናጋ ዝም እንል ዘንድ አይገባንምና። ቤተ ክርስቲያን በሁላችን እጅ ናት እና አጥብቀን እንያዛት።

ድምፀ ተዋሕዶ
https://t.me/onesinod

ዜና መጻሕፍትሚያዝያ 14 ቀን 2015 ዓ.ም (አዲስ አበባ)በመልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ ሰይፉ (አባ ሕፃን) የተጻፈው መጽሐፍ ተመረቀ። ነቅዐ ሕይወት የተረኘው እና በመልአከ ሕይ...
22/04/2023

ዜና መጻሕፍት
ሚያዝያ 14 ቀን 2015 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

በመልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ ሰይፉ (አባ ሕፃን) የተጻፈው መጽሐፍ ተመረቀ። ነቅዐ ሕይወት የተረኘው እና በመልአከ ሕይወት አባ ገብረ ኢየሱስ የተደረሰው መጽሐፍ ዛሬ በቦሌ መድኃኔዓለም መመረቁን የድምፀ ተዋሕዶ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ በርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና ምእመናን ተገኝተዋል።
ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል በተደረገው መፈንቅ ሲኖዶስ ፊት ለፊት ወጥተው በዕንባ ጭምር በመጋፈጣቸው ከመንሥት ኃይሎች በርካታ ማስፈራሪያዎች ደርሰውባቸዋል። በዚህም ምክንያት መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው በጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ በአንድ ጠባብ ክፍል እንዲኖሩ ተገደዋል። አባ ገብረ ኢየሱስ (አባ ሕፃን) ነቅዐ ሕይወትን በዚሁ ጠባብ ክፍል ውስጥ ከገቡ በኋላ እንደጻፉት የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

ድምፀ ተዋሕዶ - VoT
https://t.me/onesinod

ለመላው ኦርቶዶክሳውያን እና አፍቃሬ ኦሮቶዶክሳውያን እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ!
15/04/2023

ለመላው ኦርቶዶክሳውያን እና አፍቃሬ ኦሮቶዶክሳውያን እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ!

አስደሳች መረጃ በዛሬው ዕለት ሦስት ሙስሊሞች ልጅነትን አግኝተዋል። በዛሬው ዕለት ከእውየተኛዋ መንገድ ጋር ሳይገናኙ በእስልምና ቁራኛ ውስጥ ተይዘው የነበሩ ሦስት ሙስሊሞች ተጠምቀው ተቀላቅለ...
05/04/2023

አስደሳች መረጃ

በዛሬው ዕለት ሦስት ሙስሊሞች ልጅነትን አግኝተዋል። በዛሬው ዕለት ከእውየተኛዋ መንገድ ጋር ሳይገናኙ በእስልምና ቁራኛ ውስጥ ተይዘው የነበሩ ሦስት ሙስሊሞች ተጠምቀው ተቀላቅለውናል። ሙስሊሞቹ ተምረው ለመጠመቅ ፈቃደኝነታቸውን ካሳዩበት ዕለት ጀምሮ ለ2 ዓመታት ከአንድ ወር ትምህርተ ክርስትና ሲወስዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ገብረ ኢየሱስ፣ ገብረ እግዚአብሔር እና ወለተ ኢየሱስ ተብለው እውነኛዋን መንገድ አግኝተዋል።
ሁለቱ ተማሪዎች በመሆናቸው ራሳቸውን እስከሚችሉ ድረስ ሙሉ ወጫቸው በቅን ኦርቶዶክሳውያን የሚሸፈን ይሆናል።
ማንነታቸውን እና ዝርዝር ጉዳዮችን ለደኅንነታቸው ሲባል አልፈናል።
ድምፀ ተዋሕዶ

You can view and join right away.

ዛሬ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለት ነው። እንኳን አደረሳችሁ።ስለ ሕማማችን ታመመ፤ ስለ ሐጢአታችን መተላለፍን ተቀበለ። ስለ እኛ ሞተ። በኋላም ከሙታን ተለይቶ ተነሣ!...
05/04/2023

ዛሬ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለት ነው። እንኳን አደረሳችሁ።
ስለ ሕማማችን ታመመ፤ ስለ ሐጢአታችን መተላለፍን ተቀበለ። ስለ እኛ ሞተ። በኋላም ከሙታን ተለይቶ ተነሣ!

ድምፀ ተዋሕዶን በቴሌግራም ይቀላቀሉ
https://t.me/onesinod

በውስጥ መስመር ስለ ፓስተር ቢኒያም ትክክለኛ መረጃ ስጡን ባላችሁን መሠረት አጣርተናል። ፓስተር ቢኒያም መድረክ ላይ ቆሞ ክርስትና ስሜ ፍቅረ ኢየሱስ ይባል ነበር አለ እንጂ አሁን ተጠምቄ ፍ...
03/04/2023

በውስጥ መስመር ስለ ፓስተር ቢኒያም ትክክለኛ መረጃ ስጡን ባላችሁን መሠረት አጣርተናል። ፓስተር ቢኒያም መድረክ ላይ ቆሞ ክርስትና ስሜ ፍቅረ ኢየሱስ ይባል ነበር አለ እንጂ አሁን ተጠምቄ ፍቅረ ኢየሱስ ተብያለሁ አላለም። በመሆኑም ተጠመቀ የሚባለው ዜና የተሳሳተ ነው።

በቴሌግራም ይጎብኙን
https://t.me/onesinod

እኒህ ካህን በድንጋይ ተወግረው ሲገደሉ ባለቤታቸውን እና ልጆቻቸውን ማቋቋም ትንሹ የቤተ ክህነት ድርሻ ነበር። ነገር ግን ለቀብራቸው እንኳን ተገቢው ክብር አለመሰጠቱ አነጋጋሪ ብቻ ሳይሆን አ...
01/04/2023

እኒህ ካህን በድንጋይ ተወግረው ሲገደሉ ባለቤታቸውን እና ልጆቻቸውን ማቋቋም ትንሹ የቤተ ክህነት ድርሻ ነበር። ነገር ግን ለቀብራቸው እንኳን ተገቢው ክብር አለመሰጠቱ አነጋጋሪ ብቻ ሳይሆን አሳሳቢም ነው።
እስቲ ፍረዱ። ተቀጥቅጠው የተገደሉት አዲስ አበባ የው። የተቀበሩትም አዲስ አበባ ነው። ታዲያ ቢያንስ እንኳን ለሰማዕትነታቸው ክብር በቀብራቸው ተገኝቶ ክቡር አስከሬናቸውን የሸኜ አባት እንዴት ጠፋ? ከብፁዓን አባቶቻችን መካከል ቢያንስ አንድ ሰው እንዴት ሳይገኝ ቀረ? ፍርዱን ለእናንተ ትተናል። ብፁዓን አባቶቻችንም (በተለይ በቀብራቸው ቀን 5 ኪሎ መንበረ ፓትርያርክ የነበራችሁ) ራሳችሁን ጠይቁ። የአባቶች ትግል ወንበራቸው ሲነካ ብቻ ነው የሚሉ ተቺዎች እውነት አላቸው ብለን ለመቀበል እንዳንገደድ እንሰጋለን።
ከእኒህ ሰማዕት በላይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የለም!

ድምፀ ተዋሕዶ
ቴሌግራም
https://t.me/onesinod

ሰላም!ዛሬ ከምሽቱ 1፡00 ሰአት ጀምሮ በዘመቻ መልክ የሚለቀቁ 7 ቪድዮዎች አሉን፣👉 7ቱንም በየ 5 ደቂቃው ልዩነት በኢንፎርማል/የግል እና ደጋ ፊ ፌስቡክ ገፃችን ፤ 7ቱንም በትዊተር ገፃች...
30/03/2023

ሰላም!

ዛሬ ከምሽቱ 1፡00 ሰአት ጀምሮ በዘመቻ መልክ የሚለቀቁ 7 ቪድዮዎች አሉን፣
👉 7ቱንም በየ 5 ደቂቃው ልዩነት በኢንፎርማል/የግል እና ደጋ ፊ ፌስቡክ ገፃችን ፤ 7ቱንም በትዊተር ገፃችን ፤ 7ቱንም በቲክቶክ አካዉንቶቻችን እንለጥፋለን!
👉ሁሉንም ቪድዮ ሁሉም አመራር እና የሚድያ ሰራዊቱ ይለጥፈው!
👉 በሁሉም ቪድዮ ላይ "ጥበብን ከብልሃት ጋር የተቸረ መሪ❗️" የሚል መልዕክት አብሮ ይለጠፋል!
👉 የዘመቻውን ተሳትፎ በየማህበራዊ መሰረቱ ለዘሪሁን እንደተለመደው እስከ ጠዋት 2:3ዐ ይላካል!
👉መልዕክቱን እንልካለን በፍጥነት ሰራዊቱ ይዘጋጅ!

በርቱ❗️
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #
(ከላይ የላክንላችሁ መልእክት ከብልጽግና ፓርቲ ለብልጽግና የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት በውስጥ መስመር የተላከላቸው ነው። ቪዲዮዎቹ እንደደረሱን እናቀርባለን)
ቪዲዮዎቹን በቴሌግራም ቻናላችን ያገኛሉ።
https://t.me/onesinod

ምዕራፍ አንድ ድራማ በዚህ ተጠናቋል!=========የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በመግለጫው አሳወ...
30/03/2023

ምዕራፍ አንድ ድራማ በዚህ ተጠናቋል!
=========
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በመግለጫው አሳወቀ።

ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ማዕረግ እንዲጠሩም ገልጿል።

በዚህ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብለው እንደሚጠሩና ወደ ነበረ የአባትነት ኃላፊነታቸው የሚመለሱ ሲሆን በይቅርታ የተመለሱት በቁጥር 20ዎቹ መነኮሳትም ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው የክህነት አገልግሎት እንዲያገለግሉ ሆኖ በምንኩስና ስማቸው እንዲጠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

የድምፀ ተዋሕዶን ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ።
https://t.me/onesinod

ሃይማኖት አልባ ባለማተቦችድምፀ ተዋሕዶበትናንትናው ዕለት በነበረው የፓርላማ ስብሰባ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ መጠየቅ እና መከራከር የቻለ ጠንካራ ሰው አለማየት አሳ...
29/03/2023

ሃይማኖት አልባ ባለማተቦች
ድምፀ ተዋሕዶ
በትናንትናው ዕለት በነበረው የፓርላማ ስብሰባ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ መጠየቅ እና መከራከር የቻለ ጠንካራ ሰው አለማየት አሳዛኝ ነው። በፓርላማው ውስጥ ብዙ ባለማተቦች ቢኖሩም መስቀሉን በአንገታቸው እንጂ በልባቸው አለማሠራቸውን አሳይተውናል።
ለምሳሌ በመንፈሳዊ ተቋሞቻችን ሳይቀር ትልልቅ ሓላፊነቶች ላይ የነበሩ ሰዎች ጸጥ ረጭ ብለዋል። የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ዝምታ አሳዛኝ እና አስደንጋጭ ከሆነ ቆይቷል። በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ እስከ ሥራ አመራርነት ሥልጣን የነበረው አቶ ባያብል ሙላቴም የፓርላማው አባል ነው። አቶ ባያብልም ቢሆን በዚህ ጭንቅ ሰአት በፓርላማው ውስጥ የቤተ ክርስቲያኗን ድምፅ ለማሰማት አለመድፈሩ ያሳዝናል።
መንፈሳዊ መድረክ ላይ ዕንባ እያፈሰሱ ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሲሉ የነበሩ ሁሉ የመንግሥትን ሥልጣን ሲቆናጠጡ "ስቅሎ ስቅሎ" እያሉ አይተናቸዋል። በፓርላማ ውስጥ ካሉ ኦርቶዶክሳውያን ቢያንስ አንድ ደፋር፣ እውነተኛ እና የቤተ ክርስቲያን መገፋት የሚያንገበግበው ሰው መጥፋቱ የቤት ሥራችን ብዙ እንደሆነ አመላካች ነው።

ድምፀ ተዋሕዶን ቴሌግራም ቻናል ይጎብኙ!
https://t.me/onesinod

አዲስ መረጃ""""""""""""መጋቢት ፲፱/ ፳፻፲፭ ዓ.ም ድምፀ ተዋሕዶከቤተክርስቲያን በውግዘት የተለዩ 17 የቀድሞ አባቶች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በተደረሰው ስምም...
28/03/2023

አዲስ መረጃ
""""""""""""
መጋቢት ፲፱/ ፳፻፲፭ ዓ.ም
ድምፀ ተዋሕዶ

ከቤተክርስቲያን በውግዘት የተለዩ 17 የቀድሞ አባቶች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በተደረሰው ስምምነት መሰረት 10ሩን የስምምነት ነጥቦች መቀበልላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር አስገብተዋል።

ደብዳቤውን ያስገቡት 17 ሲሆኑ አንዱ ወደ ጸበል መሄዳቸውን ገልጸው ደብዳቤአቸውን በተወካይ አስገብተዋል። በጥቅሉ ደብዳቤ ያስገቡት18 ሲሆኑ ቀሪዎቹ 6 የቀድሞ አባቶች በህመም ምክንያት እንዳልተገኙ በዛሬው ዕለት የተገኙት የቀድሞ አባቶች ገልጸው በቅርብ ጊዜ ቀሪዎቹ ግለሰቦች ማመልከቻቸውን ይዘው እንደሚመጡ ገልጸዋል።

ምንጭ፡ የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
https://t.me/onesinod

የአቡነ አረጋዊ አሳዛኝ አሟሟት (ክፍል ፩)አቡነ አረጋዊ ታመው አልጋ ላይ ከመዋላቸው አስቀድሞ ምንም አይነት የሕመም ምልክት እንዳልነበረባቸው ታውቋል። ጤንነታቸውንም በየጊዜው "ቸክ" የሚዪደ...
27/03/2023

የአቡነ አረጋዊ አሳዛኝ አሟሟት (ክፍል ፩)

አቡነ አረጋዊ ታመው አልጋ ላይ ከመዋላቸው አስቀድሞ ምንም አይነት የሕመም ምልክት እንዳልነበረባቸው ታውቋል። ጤንነታቸውንም በየጊዜው "ቸክ" የሚዪደርጉ ጥንቁቅ አባት ነበሩ። በሥርዐተ ቀብራቸው ቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ "የብፁዕ አቡነ አረጋዊ አሟሟት ግራ ያጋባል፤ ታመው አልጋ ላይ ከመዋላቸው በፊት ምንም ዓይነት የሕመም ምልክት አልነበረባቸውም። ብቻ ምክንያቱ ይለያይ እንጂ ተጠርተው ሂደዋል" ማለታቸው በብፁዕነታቸው ሞት ላይ አንዳች የተቀነባበረ ጉዳይ እንዳለ ማሳያ ነው።
1, ብፁዕነታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ታመው ኮሪያ ሆስፒታል እንዲገቡ ከተደረገ በኋላ በኮሪያ ሆስፒታል ሕክምና ሳያገኙ ተሰቃይተዋል። ይኸውም ከቤተ ክህነት በጀት እንዳይለቀቅ ሴራ በመጠንሰሱ ነው። አባታችን ከቤተ ክህነት የሕክምና በጀት ባለመለቀቁ ሕይወታቸው አስጊ ሲሆን የኮሪያ ሆስፒታል ሠራተኞች እና ወዳጆቻቸው ገንዘብ አዋጥተው የኮሪያ ሆስፒታል ሕክምናው ተጀመረ። (ይህንን እውነት ከኮሪያ ሆስፒታል ሐኪሞች ማረጋገጥ ይቻላል። በአቡነ አረጋዊ ልክ ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ ያሉ አባት ለምን የሕክምና ወጭ ተከለከሉ?
2, ከብዙ ቢሮክራሲ በኋላ ውለው አድረው በጀቱ ሲለቀቅ የኮሪያ ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ውጭ ሂደው እንዲታከሙ አዘዙ። በዚህም መሠረት ብፁዕ አባታችን ደክመው በአውሮፕላን አንቡላንስ ውስጥ ሰው ሠራሽ መተንፈሻ ተገጥሞላቸው አንቡላንሱ ወደ ውጭ መብረር ጀመረ። በርካታ ሰአታትን ሲጓዝ የቆየው አንቡላንስ ግን ለሕክምና ወደሚሄድበት ሀገር በሚደርስበት ሰአት ተመልሶ አዲስ አበባ ዐረፈ። ይህ ለምን ሆነ ተብሎ ሲጠየቅ ብልሽት ገጥሞት ነው የሚል ምክንያት ተሰጠው። አባታችን ይበልጥ እየተዳከሙ መጡ። ከቀናት በኋላም ተበላሸ የተባለው አቡላንስ ሳይጠገን ብፁዕነታቸውን ይዞ ወደ ውጭ ሄደ። ይህ ለምን ሆነ? ይቀጥላል....

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/onesinod

Address

England
Bu Dang
2129

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ድምፀ ተዋሕዶ - Voice of Tewahido - VoT posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share