በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል በመቀላቀል
https://t.me/aac_pshrdb
ያለዎትን ሀሳብ አስተያት እንዲሁም ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ

22/07/2025

ሀሙስ ምሽት 2 ሰዓት ይጠብቁን

ቢሮው በአደረጃጀት ማሻሻያ ጥናት አተገባበር ላይ ከክ/ከተማ እና ከወረዳ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ።።።።።።።።ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፤  ሐምሌ 15 ቀን 2017ዓ.ምየአዲስ አበባ ከተማ አስተ...
22/07/2025

ቢሮው በአደረጃጀት ማሻሻያ ጥናት አተገባበር ላይ ከክ/ከተማ እና ከወረዳ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ
።።።።።።።።
ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፤ ሐምሌ 15 ቀን 2017ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በአደረጃጀት ማሻሻያ ጥናት ላይ ከክ/ከተማ እና ከወረዳ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

የአደረጃጀት ማሻሻያ ጥናቱ መነሻ ከተማ አስተዳደሩ ባለው ሀብት ሊያሰራ የሚያስችል መዋቅራዊ አደረጃጀት እና የሰው ሀይል አደረጃጀት ከማሻሻል አንፃር እና በወረዳዎች ላይ የሚስተዋለውን የተለጠጠ መዋቅር ለማሻሻል እንዲቻል የጥናቱ መነሻ መሆኑ ተገልፃል፡፡

በዚህ መሰረት የዓደረጃጀት ማሻሻያ ጥናቱ ዓላማ በወረዳዎች በስፋት የሚስተዋለውን አስተዳደራዊ ወጪዎች በማሻሻል ለዘላቂ ልማት፣ ለካፒታል ፕሮጀክት፣ ለስራ እድል ፈጠራ፣ ለሰራተኛ አቅም ግንባታ እንዲውል በማድረግ አደረጃጀቶችን በማሻሻል ውጤታማነቱን ለማረጋገጥ እንዲቻል መሆኑን ተገልጻል፡፡

በአደረጃጀት ማሻሻያው ሂደት ላይ የሚከናወኑ ተግባራት ምን መምሰል እንደሚገባቸውና የጥናቱ ተግባራዊነት ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር እንደተናገሩት የአደረጃጀት ማሻሻያ ቢደርግባቸው የተባሉ ተቋማት ጋር መረጃ ተወስዶ በጥናቱን የተመላከተ መሆኑን ገልጸው በተመላከተው መሰረት ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር ክፍተት የሚታይባቸውን የወረዳ ፅ/ቤቶች በቀረበው መነሻነት ወደ ክ/ከተማ ለማምጣት እንዲቻል በሰፊው ውይይት ሲደረግ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

የተቋማት የአደረጃጀት ማሻሻያው በየቦታው የሚታየውን የሰው ሀይል እጥረት ከመፍታቱ ባሻገር ሊያሰራ የሚያስችል የመዋቅራዊ አደረጃጀት ስርዓት ለመዘርጋት እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771711638

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል፦ HTTPS://T.ME/AAC_PSHRDB

👍👍👍 ኢንስታግራም :- HTTPS://WWW.INSTAGRAM.COM/P/DDEO-REOK-Y/?IGSH=YZLJYTK1ODG3ZG==

👍👍👍ቲክቶክ፦ HTTPS://VM.TIKTOK.COM/ZMHU7WUET/

👍👍👍 ዌብ ሳይት ፦ HTTP://WWW.PSHRDB.GOV.ET/

በቢሮው ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚካሄደው አብሮነት ለለውጥ መርሀግብር የሶስተኛ ምዕራፍ መርሀግብር ተካሄደ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፤ ሐምሌ 14 ቀን 2017ዓ.ም የአዲስ ...
21/07/2025

በቢሮው ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚካሄደው አብሮነት ለለውጥ መርሀግብር የሶስተኛ ምዕራፍ መርሀግብር ተካሄደ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፤ ሐምሌ 14 ቀን 2017ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ተኛአስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚያካሄደው አብሮነት ለለውጥ መርሀግብር የሶስተኛ ምዕራፍ የሀያ ሁለተኛው ዙር ፕሮግራሙን የቢሮው አመራርና ሰራተኞች በተገኙበት አካሂዷል፡፡

በእለቱም የእውቀት ሽግግር እና የህይወት ልምዳቸውን ያካፈሉት በቢሮ የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ደፋር " ለብልፅግና ንቃ" በሚል ሀሳብ ላይ የእውቀት ሽግግራቸውን ያካፈሉ ሲሆን የብልፅግና አስተሳሰብ ነፃነትን የሚፈልግ የአስተሳሰብ ውቅር የአዕምሮ ዝግጁነት ነው ብለዋል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771711638

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል፦ HTTPS://T.ME/AAC_PSHRDB

👍👍👍 ኢንስታግራም :- HTTPS://WWW.INSTAGRAM.COM/P/DDEO-REOK-Y/?IGSH=YZLJYTK1ODG3ZG==

👍👍👍ቲክቶክ፦ HTTPS://VM.TIKTOK.COM/ZMHU7WUET/

👍👍👍 ዌብ ሳይት ፦ HTTP://WWW.PSHRDB.GOV.ET/

ከተማችን አዲስ አበባን የሚመጥን  ኮሙኒኬሽን ሥራዎች በላቀ ብቃት እንደምንገነባ አንጠራጠርም ! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት እና ...
21/07/2025

ከተማችን አዲስ አበባን የሚመጥን ኮሙኒኬሽን ሥራዎች በላቀ ብቃት እንደምንገነባ አንጠራጠርም !

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት እና ክፍለ ከተሞች ዕውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል። ቢሮችን የከተማዋን ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ ለህብረተሰቡ መረጃ በፍጥነት እንዲደርስ በማድረግ በኩል ላሳየው ላቅ ያለ አፈጻጸም የተሽከርካሪ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

ጠንካራ የኮሙኒኬሽን ስርዓት በመዘርጋት ህዝባችን ብቁ በከተማው ሁለንተናዊ እቅስቃሴ ተሳታፊ እንዲሆን ጥራት ያለው መረጃ በመስጠት ለከተማችን ሁለተናዊ ፈጣን እድገት አሁንም በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን።

"አምና በስኬት ላይ ነበርን፤ዘንድሮም በስኬት ላይ ሆነናል፤ወደፊትም በስኬት ላይ ስኬት እየተጎናፀፍን ለከተማችን ሁለተናዊ ፈጣን እድገት በመረጃው ዘርፍ መስራታችንን እንቀጥላለን፡፡

ይህ እንዲሳካ ላደረጋችሁ በየደረጃው የምትገኙ የኮሙኒኬሽን አመራሮች ፣ስራተኞች እና የማህበረሰብ አንቂዎች በሙሉ ድሉ የእናንተም ነውና በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2017 በጀት ዓመት የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን በመስራት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቢሮዎች፣ ተቋማት፣ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች እውቅናና ሽልማት ማበርከታ...
21/07/2025

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2017 በጀት ዓመት የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን በመስራት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቢሮዎች፣ ተቋማት፣ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች እውቅናና ሽልማት ማበርከታቸውን ገለጹ
።።።።።።።።።።።።
ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2017 በጀት ዓመት የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን በመስራት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቢሮዎች፣ ተቋማት፣ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች እውቅናና ሽልማት አበርክተናል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

በዚሁም መሰረት፦

የካቢኔ አባል ከሆኑ ቢሮዎች፦

1ኛ. የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
2ኛ. ሠላምና ፀጥታ ቢሮ
3ኛ ፋይናንስ ቢሮ
4ኛ. ትምህርት ቢሮ
5ኛ. ኮሚኒዩኬሽን ቢሮ

ከክፍለ ከተሞች፦

1ኛ. ቦሌ
2ኛ. አቃቂ ቃሊቲ እና ለሚ ኩራ
3ኛ. ኮልፌ ቀራኒዮ

የካቢኔ አባል ካልሆኑ ተቋማት፦

1ኛ. የደንብ ማስከበር ባለስልጣን
2ኛ. የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን
3ኛ. የመንገዶች ባለስልጣን
4ኛ. የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት ኤጀንሲ
5ኛ. የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ሲሆኑ፤ እንዲሁም 33 ወረዳዎች ተሸላሚ ሆነዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እውቅናና ሽልማቱ የሁሉም አመራር፣ በየደረጃው ያሉ ባለሞያዎች፣ የባለድርሻ አካላት እና አብሮን ለሰራዉ ህዝባችን የተሰጠ ሲሆን ይህም ይበልጥ ሰርተን የህዝባችንን የመልማት ፍላጎት የምናሳካበት እንጂ የሚያዘናጋን አይደለም ብለዋል።

በመሆኑም፤ እውቅናው በቀጣይ በጀት ዓመት አልቀን በመስራት የህዝባችንን ተጠቃሚነት እንድናረጋግጥ ትልቅ አደራም ጭምር ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አብረን አቀድን ፣ አብረን ሰርተን፣ አብረን ውጤቱን አምጥተናል ! ባለፉት ቀናት ስናካሂድ የነበረው የከተማችን የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት አ...
20/07/2025

አብረን አቀድን ፣ አብረን ሰርተን፣ አብረን ውጤቱን አምጥተናል !

ባለፉት ቀናት ስናካሂድ የነበረው የከተማችን የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት አጠናቅቀናል።

በግምገማችንም የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶችን በማላቅ እና የተለዩ ድክመቶችን በማረም በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ተግባብተናል ።

ከተማችን በሁሉም ዘርፍ ለነዋሪዎቿ ምቹ ፣ ሀገራዊና አህጉራዊ ብሎም አለምአ ቀፋዊ ሚናዋን በብቃት የምትወጣ ፤ ስሟና ግብሯ የተናበበ ከተማ እንድትሆን የጀመርነዉን ልማት በጥራት፣ በስፋትና በፍጥነት አጠናክረን እንደምንቀጥል ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ጤናዉ የተጠበቀ ፣ አካሉ የዳበረ አመራር ለምናልመዉ ብልፅግና ወሳኝ ነዉ። ዛሬ ማለዳ  መላዉ አመራራችን  ከ2017 አመታዊ የስራ ግምገማችን እና እቅድ ዉይይት ጎን ለጎን የማስ ስፓርት አከና...
20/07/2025

ጤናዉ የተጠበቀ ፣ አካሉ የዳበረ አመራር ለምናልመዉ ብልፅግና ወሳኝ ነዉ።
ዛሬ ማለዳ መላዉ አመራራችን ከ2017 አመታዊ የስራ ግምገማችን እና እቅድ ዉይይት ጎን ለጎን የማስ ስፓርት አከናዉነናል ።

በትጋት ወደ ስኬት!
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን!ዛሬ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ማካሄድ ጀምረናል።የ2017 በጀት ዓመት ከመቼውም የበለጠ ስኬት ያስ...
19/07/2025

የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን!

ዛሬ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ማካሄድ ጀምረናል።

የ2017 በጀት ዓመት ከመቼውም የበለጠ ስኬት ያስመዘገብንበት ነው ፤ የእቅድ አፈፃፀማችን 95 በመቶ ተሳክቷል።

መዲናችንን ለሀገር ክብር የምትመጥን፣ እንደ ስሟ “ውብ አበባ" ለማድረግ በኮሪደር ልማት፣ በከተማ መልሶ ማልማት እና በወንዞች ዳርቻ ልማት ስራዎች፤ በስራ እድል ፈጠራ እና የገቢ እቅድን በማሳካትና ያገኘነውን ገቢ በቁጠባና ብክነትን በማስወገድ ለዘላቂ ልማትና ድህነት ቅነሳ በማዋል ዙሪያ በተከናወኑ ስራዎች አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግበናል።

በሁሉም ስራዎቻችን ውስጥ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ቀጣይነትን ያረጋገጥንበት፣ የበጀት ጉድለትን በህብረተሰብ ተሳትፎና በጐ አገልግሎት እየሞላን ከህዝብ ጋር ተቀራርበን በመስራት ውጤታማ የሆንበት በጀት ዓመት ነው።
ለነዚህ ሁሉ ስኬቶች አብራችሁን የለፋችሁ፣ ከራሳችሁ በላይ ህዝባችንን ያስቀደማችሁ የከተማችን ነዋሪዎች እና የደከማችሁና ውጤት ያስመዘገባችሁ አመራሮቻችንን እና ሰራተኞቻችንን ከልብ እናመሰግናችኋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ

ቢሮው በከተማ አስተዳደሩ ምዘና ከሚመለከታቸው ሴክተር ተቋማት ጋር በቅንጂት በመሆን የ2017በጀት ዓመት የአፈፃፀም ምዘና አዳሄደ።።።።።።።።።።ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፤ ሐምሌ 11  2017ዓ.ም...
18/07/2025

ቢሮው በከተማ አስተዳደሩ ምዘና ከሚመለከታቸው ሴክተር ተቋማት ጋር በቅንጂት በመሆን የ2017በጀት ዓመት የአፈፃፀም ምዘና አዳሄደ
።።።።።።።።።።
ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፤ ሐምሌ 11 2017ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከፕላንና ልማት ቢሮ ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት ከተውጣጡ የምዘና ኮሚቴ አባላት ጋር በጋራ በመሆን የቢሮውን የ2017በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ምዘና አካሂዷል።

ምዘናውም በዋናነት የእቅድ ዝግጂት እና የKPI አፈፃፀም ፣ የአመራሩ የስራ አሰራር ስርዓት ፣ አዳዲስ ኢንሼቲቭ ስራዎች ፣ ሰው ተኮር ተግባር አፈፃፀም ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል እርካታን ማሳደግ አንፃር እና ምቹ የስራ ከባቢ መፍጠር አንፃር እንዲሁም መሰል ተግባራት ላይ ትኩረት በማድረግ ተካሂዷል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771711638

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል፦ HTTPS://T.ME/AAC_PSHRDB

👍👍👍 ኢንስታግራም :- HTTPS://WWW.INSTAGRAM.COM/P/DDEO-REOK-Y/?IGSH=YZLJYTK1ODG3ZG==

👍👍👍ቲክቶክ፦ HTTPS://VM.TIKTOK.COM/ZMHU7WUET/

👍👍👍 ዌብ ሳይት ፦ HTTP://WWW.PSHRDB.GOV.ET/

18/07/2025
ትምህርት ቤት ትውልድ የሚቀረፅበት ማዕከል በመሆኑ መንግስት  ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ  እየሰራ መሆኑ ተገለፀ::በቦሌ ክፍለ ከተማ በመንግሥት እና በማህበረሰብ ተሳትፎ የተገነቡ ማስፋፊያ የተደረ...
18/07/2025

ትምህርት ቤት ትውልድ የሚቀረፅበት ማዕከል በመሆኑ መንግስት ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ::

በቦሌ ክፍለ ከተማ በመንግሥት እና በማህበረሰብ ተሳትፎ የተገነቡ ማስፋፊያ የተደረገላቸው ትምህርት ቤቶች ተመርቀዋል።

በምረቃ መርሀግብር ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር )ትምህርት ቤት ትውልድ የሚቅረጽበት እና ሀገርን የሚገነባበት ማዕከል በመሆኑ የትምህርት ቤት ግንባታና ማስፋፊያ ላይ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራን ነው ብለዋል።

ፕሮጀክቶቹ መጪው ትውልድ በአካል ፣ በስነልቦና ፣ በእውቀት እና በክህሎት ብቁ እንዲሆኑ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ለትምህርት ዘርፉ በተሰጠው ትኩረት ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረው፣ ለአብነትም ትምህርት በፈረቃ ይሰጡ የነበሩ ትምህርት ቤቶች መቀነስ መቻሉንና ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር ምቹ እንዲሆኑ መደረጉን አንስተዋል፡፡

የቦሌ ክፍለ ዋና ስራ አስፈፃሚ እሸቱ ለማ (ዶ/ር) የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ እና ማስፋፊያ ጥራት ያለው ትምህርት ለትውልድ ለመስጠት እንድሁም የተማሪ የክፍል ጥምርታ ደረጃን የሚያስጠብቅ እና የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳደግ የክፍለ ከተማው አስተዳደር በስፋት ሲሰራ መቆየቱን አውስተው፣ “ዛሬ የተመረቁት ፕሮጀክቶችም ይህንን ግብ ለማሳካትና የኅብረተሰቡን የትምህርት ቤት ተደራሽነት ጥያቄ ለመመለስ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ” ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቶቹ የታለመላቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ የትምህርት ባለድርሻ አካላትና ኅብረተሰቡ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለው ተናግረዋል፡፡

ከለውጡ ወዲህ የህዝብን ጥያቄ የሚመልሱ በርካታ ፕሮጀክቶች መሰራታቸውን ጠቅሰው ለትምህርት ዘርፉ በተሰጠው ትኩረትም መሻሻሎች መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

ትምህርት ቤት ትውልድ የሚቀረፅበት ማዕከል በመሆኑ መንግስት  ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ  እየሰራ መሆኑ ተገለፀ በቦሌ ክፍለ ከተማ በመንግሥት እና በማህበረሰብ ተሳትፎ የተገነቡ ማስፋፊያ የተደረገ...
18/07/2025

ትምህርት ቤት ትውልድ የሚቀረፅበት ማዕከል በመሆኑ መንግስት ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ

በቦሌ ክፍለ ከተማ በመንግሥት እና በማህበረሰብ ተሳትፎ የተገነቡ ማስፋፊያ የተደረገላቸው ትምህርት ቤቶች ተመርቀዋል።

በምረቃ መርሀግብር ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር )ትምህርት ቤት ትውልድ የሚቅረጽበት እና ሀገርን የሚገነባበት ማዕከል በመሆኑ የትምህርት ቤት ግንባታና ማስፋፊያ ላይ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራን ነው ብለዋል።

ፕሮጀክቶቹ መጪው ትውልድ በአካል ፣ በስነልቦና ፣ በእውቀት እና በክህሎት ብቁ እንዲሆኑ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ለትምህርት ዘርፉ በተሰጠው ትኩረት ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረው፣ ለአብነትም ትምህርት በፈረቃ ይሰጡ የነበሩ ትምህርት ቤቶች መቀነስ መቻሉንና ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር ምቹ እንዲሆኑ መደረጉን አንስተዋል፡፡

የቦሌ ክፍለ ዋና ስራ አስፈፃሚ እሸቱ ለማ (ዶ/ር) የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ እና ማስፋፊያ ጥራት ያለው ትምህርት ለትውልድ ለመስጠት እና የተማሪ የክፍል ጥምርታ ደረጃን የሚያስጠብቅ ነው ብለዋል።

ከለውጡ ወዲህ የህዝብን ጥያቄ የሚመልሱ በርካታ ፕሮጀክቶች መሰራታቸውን ጠቅሰው ለትምህርት ዘርፉ በተሰጠው ትኩረትም መሻሻሎች መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share