
26/06/2025
19🕯🕯🕯
መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ! አናንያን፣አዛርያን፣ሚሳኤልን ከሚነድ እሳት እንዳወጣሃቸው እኛንም ልጆችህን ከሚያስፈራን የሚያስጨንቀን ነገር ሁሉ ጠብቀን፣ ከገባንበት እሳት አውጣን አሜን!
በችግራችን ጊዜ ከሰው አለቃ ይልቅ የመላእክት አለቃ ከእሳት ከመከራ የሚያወጣው ቅዱስ ገብርኤል ይድረስልን።
የታመንክ የልብ ወዳጅ
የምህረት አማላጅ
አንተ ነህ ገብርኤል
የምትቆም በቅድም እግዚአብሔር
የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ረድኤት በረከት ምልጃ ፀሎት አይለየን ከክፉ ነገር ሁሉ ይታደገን 💒❤️