25/07/2025
~~~~~~~~√√√√√
ለመምህር ፈንታሁን ዋቄ
wakie
//
እየውለዎት ትግሉን መደገፍ ይቻላል፤ በትግሉ ውስጥ ግን ገብቶ ብይን ለመስጠት መንቀሳቀስ ግልፅ ጣልቃ ገብነት ነው። የአማራ ብሄርተኝነት እርሰዎ እንደሚሉት ወይም እንደሌሎቹ የአውሬ ብሄርተኝነት አይደለም። የአባቶቻችንን ስነ-ልቦና እናስቀጥላለን እንጅ ከስሪታችን የምናፈገፍገው አይኖርም። ፓለቲካ የጋራ ጉዳይ ነው። የጋራ ካልሆነ ፓለቲካ ሊሆን አይችልም። ይሄ ማለት አይደለም አማራ ህዝብ ውስጥ ያለ ሃይማኖት እና ሌሎች መገለጫወች ቀርቶ የሌላውንም ክብር በሚሰጥ መልኩ የሚኬድበት ነው። ብዙ ጉዳዮች እንደ ትናንት አይደሉም። ዛሬ በአንድ በሚወጣ ቃል ብቻ የቀጣይ ፍላጎት እና እቅድ በቀላሉ በማሽን( AI) የሚታወቅበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው። አንድ የተለመደ ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ላይ ችክ ብሎ የግድ እንዲህ ካልሆነ የሚባል አካሄድ የለምም አይሰራምም!
ይሄ ትግል ሰፊ መስዕዋትነት እየተከፈለበት ያለ ነው። በዚህ ወቅት ጠላት ላይ በመረባረብ ሌሎች ጉዳዮችን በሌላ መልክ መሄድ ይቻል ነበር።
አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነትን የተቃወምነው ወደ ፊትም እስከ ጥግ የምንታገለው ትናንት በብዓዴን ውስጥ ጉዳይ እንኳን ህውሃት ገብታ እያዘዘች እያንዳንዳችንን እንደ ህዝብ ከባድ መስዕዋትነት ከፍለናል። በዚያም አላበቃም አብይ አህመድ ብዓዴንን ራሴ እያዘዝኩ ካልመራሁ የአማራ ኢሊት ገብቶ ከስልጣኔ ያስወግደኛል ብሎ ስለፈራ ራሱ መሪወችን እነ ዶ/ር አምባቸውን በጀነራሉ በኩል ጀነራሉን ደግሞ ራሱ በቀጥታ ገድሎ ይሄው ትናንት ከህውሃት ጋር ዛሬ ደግሞ ከእኛ ጋር ይሄን ከባድ መስዕዋትነት እያሰከፈለን ያለው ለዚህ ነው ይሄ ጦርነትም የሃገርን ህልውና የሚፈታተን እንደሆነም ማሰብ ተገቢ ነው። በፓለቲካው ረገድ ትግሉን የጀመሩ መሪወች #ስለትናንት በቂ እውቀት፣ #ስለ ዛሬንሰፊ መረዳት #ስለ ነገም የመተምበይ ብቻ ሳይሆን ነገን የመበየን አቅም ያላቸው መሪወች ስላለን ምንም ጣልቃ ገብቶ እንዲህ አስቡ ተብሎ ምሪት አያሻቸውም።
ለዚህም ነው ውስጣዊ ጣልቃ ገብነትን አምርን የምንፀየፍ እስከ መጨረሻው የምንታገለው!
አሁን በተረዳሁዎት መሠረት ሰፊ የአካሄድ ችግር እንዳለብወት እና ለቀና ነገር እየታገሉ የሚሄዱበት ግን ታጋዮችን የማጠልሸት ፣መጠራጠርን የመዝራት ለጠላት የበለጠ አመቺ ሁኔታን የሚፈጠር እጅግ ያልተሰላ አካሄድ ነው! እርሰዎ የእኛ የህይወት እና የመንፈስ አስተማሪያችን፣ በቤተክርስቲያናችንም ውስጥ በምርምር ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ ምሁር ነዎት እኔ በግሌ አከብረወታለሁ። የፓለተካ አካሄደዎ ግን Idealism የበዛበት ይባስም ብሎ ጠላት የሚፈልገውን ምንም የሃሳብ ዝምድና ሳይኖርወት እየፈፀሙለት መስሎ እየተሰማኝ ነው።
ደግሞም እንዲህ ዓይነት ያልተገባ በመረጃ ያልተረጋገጠ speculation እርስወን በማይመጥን መልኩ በተለይ ከሁሉም አቅጣጫ እሳት በሚወርድባቸው በአማራ ፋኖ በጎጃም መሪወች ላይ አጀንዳ የሚያስቀይራቸው አካል/ግለሰብ አለ" ብሎ ጥርጣሬን መፍጠር ተገቢ አይደለም።
በሌሎች በኀልዮት ጉዳዮች ላይ ሃሳብወትን ለመሸጥ የሚያቀርቧቸው ትንተናወችን እኛም የምናዳምጣቸው ናቸው። ጣልቃ ገብነት ሆነ ያለ ሚናችን ግን በውስጥ ጉዳያችን ገብቶ መፈትፈትን ግን ፈፅሞ አንታገስም!
እደግመዋለሁ እስከመጨረሻ እንታገላለን!
ከአክብሮት ጋር!
Bezabih Belachew