
08/15/2025
በታርጫ አጠቃላይ ሆስፒታል ከሚከሰቱ የሞት ሁኔቶች የእናቶች ሞት በልዩነት በሆስፒታሉ የእናቶች ሞት ቅኝት እና ምላሽ ቡድን( MDSR team) በጥልቀት እንደምገመገግም የሆስፒታሉ ሜድካል ዳይሬክተር ዶ/ር አስራት ጌርሾንገልጸዋል።
በሆስፒታሉ በ2017 በጀት ዓመት 2200 እናቶች የወሊድ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን በበጀት ዓመቱ እሰከ ስኔ 30/ 2017 ድረስ ምንም የእናቶች ሞት አልተመዘገበም ነበር ። 2017 በጀት ዓ/ም ከወለዱ እናቶች 532 በኦፕራሲዮን የወለዱ ስሆን፡ 16 እናቶች ማህጸን በምጥ ምክንያት መፈንዳት (uterine rupture) ምክንያት ዉስብስብ ቀዶ ህክምና ተደርጎላቸዋል ።
በተጨማሪም 187 እናቶች በወሊድ ጊዜ ደም አስፈልጓቸው የተሰጣቸው ስሆን፡ 68 እናቶች የሞት አፋፍ ላይ(maternal near miss) እና 48 እናቶች ከወልድ በኋላ ማያቋርጥ መድማት (PPH) ኖሯቸዉ ከፍተኛ ህክምና ተደርጎላቸው መትረፋቸውን የክፍሉ አስተባባሪ ዶ/ር ወንድማገኘሁ ሲሳይ ገልጸዋል። ከወሊድ ጋር በተያያዘ 8 እናቶች ወደ ከፍተኛ ህክምና ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ሪፈር ተደርገዋል።
የተለያዩ የማህጸን ችግሮች ያሉባቸው 2336 እናቶች ተኝተዉ የታከሙ ስሆን ከእነዚህ ዉስጥ 386 እናቶች ከፍተኛ የማህጸን ቄዶ ህክምና እና ለ100 እናቶች የነጻ የማህጸን ዉልቃት ቄዶ ህክምና መደረጉን ዶ/ር ወንድማገኝ ጨምረው ገልጸዋል ።
በሆስፒታሉ በቅርብ ወራት ተጨማር የማህፀን እና ፅንስ ስፐሻሊስት ሀኪም የተቀጠረ ስሆን በእናቶች ክፍል በአሁኑ ሰዓት 1 subspecialist ፡1 specialist ፡1 የድንገተኛ ቄዶ ጥገና ፡ 28 አዋላጅ ነርስ ፡ 5 ስክረብ ነርስ ፡ 3 ጠቅላላ ሀክሞች፡5 አነስቴዥያ ባለሙያዎች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የሆስፒታሉ ሰራ አስክያጅ አቶ ያዕቆብ ሌንጫ ገልጸዋል ።
በክልሉ የእናቶች ህክምና አገልግሎት በሰብስፔሻሊት የምሰጥበት ብቸኛ ሆስፒታል መሆኑ ይታወቃል ። በሆስፒታሉ በቅርብ ቀን የተከሰተውን የአንዲት እናት ሞት የሆስፒታሉ እናቶች ሞት ቅኝት እና ምላሽ ቡድን ከእለቱ ተረኛ ባለሙያዎች ጋር ጥልቅ ውይይት እና ግምገማ ማድረጋቸውን ዶ/ር ወንድማገኘሁ ጨምረው ገልጸዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ የእናት ሞት እንዳይከሰት በሆስፒታሉ ባለሞያዎች አቅም መደረግ ያለበትን ሁሉ ለማድረግ መስማማታቸውን ገልጸዋል።
አንዳንድ ቡድኖች የምስክን እናቶች ሞት ለፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ እና የተቋሙን እና የባለሞያዎችን ስም ለማጠልሸት የምሄዱት አካሄድ መሬት ላይ ያለዉን እውነት የማይገለጽ መሆኑን ዳይረክተሩ ዶ/ር አስራት ገልጸዋል።
ህብረተሰቡ እንደዚህ አይነት ነገር ስከሰት መጠየቁ በሆስፒታሉ እና ባለሙያዎች ያላዉን አመነታ እና ባለቤትነት የሚያሳይ ስለሆነ በቅንነት እንደምቀበሉት ገልፀዋል። በሆስፒታሉ ለወሊድ የሚመጡ እናቶች ሁሉም በሚባል ደረጃ በስፔሻሊሴት ሀኪሞች እንደምታዩ እና ባለፈዉ ዓመት የእናቶች ህክምና ቡድኑ በሳምንት 2 ቀን በዓመት 104 ቀን በየቀኑ የተሰሩ ስራዎች እና ክስተቶችእየገመገሙ መምጣታቸውን አሳውቀዋል ።
ሆስፒታሉ ከ12 ወረዳዎች እና አጎራባች ዞኖች የሚመጡ ዉስብስብ የጤና ችግር ያለባቸውን እናቶች ተቀብሎ የምያስተናግድ መሆኑን በመገንዘብ የተለያዩ አካላት ድጋፍ እንድያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።
በተለይ በዝናብ ወቅት አብዛኛው የወረዳ መንገዶች የመዘጋጋት ሁኔታ እናቶች ዘግይተው ደክመዉ እንድደርሱ ምክንያት እንደሆነ ጠቅሰው የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ደም በመለገስ ጭምር ህይወት የማዳን ስራ እየሰሩ መሆኑ ይታወቃል።
(ታርጫ አጠቃላይ ሆስፒታል)