ከደራሲያን አለም ፔጅ

  • Home
  • ከደራሲያን አለም ፔጅ

ከደራሲያን አለም ፔጅ ማንበብ "ሙሉ" ሰው ያደርጋል
(268)

ወዳጀ  #ማጉረምረሙን ተውና  ፈጣሪህን  አመስግን >>>ፈተና ከገጠመህ ፀልይ እንጂ  #አታጉርምርም ፈጣሪ ሁሌም ታላቅ ነውና>>> ትልቅ አምላክ እንጅ ትልቅ እሚባል ችግር የለም።     "የም...
25/09/2025

ወዳጀ #ማጉረምረሙን ተውና ፈጣሪህን አመስግን

>>>ፈተና ከገጠመህ ፀልይ እንጂ #አታጉርምርም ፈጣሪ ሁሌም ታላቅ ነውና

>>> ትልቅ አምላክ እንጅ ትልቅ እሚባል ችግር የለም።

"የምታመልከው አምላክ በነገሮች ሁሉ ላይ #የበላይ እንደሆነ "አትዘንጋ።

🟣 ወዳጄ ሆይ ለህሊናህ እርፍት ለልብህ ደስታን ከፈለክ ሁልጊዜ #መልካም ሰው ሁን መልካምነት ለራስ ነው።
" በልባችን መልካምነት ካለ እንኳን የተርፈን ያለችንን እንካፈላታለን"

🟣 ሁሌም ጥሩ ነገር እናድርግ ምክንያቱም ከክፋት #ደግነት ትልቅ ዋጋ አለውና።

✳ ደግነት አንድ ቀን መልሶ ይከፍላል መልካምነት ለራስ ነውና
🚺 መልካም ሰው መልካም ሂወትን ያገኛል
🚹 መልካም ወንድ መልካም ሚስትን ያገኛል
🚺 መልካም ሴት መልካም ባልን ታገኛለች
🚹 መልካም ሰው መልካም ልጆችን ያገኛል
🚺 መልካም ሰው ደስታን ያገኛል
🚹 መልካም ሰው ሰላምን ያገኛል
🚺 መልካም ሰው ፍቅርን ያውቃል
🚹 መልካም ሰው መልካም ነገርን ያገኛል
🚺
" ታዲያ " #መልካም ሰው መሆንን የማይፈልግ ማነው??
#ፈጣሪ መልካም ሰው እንድንሆን ይርዳን። አሜን

ከዚህ ቀጥሎ በአዲስ ትረካ እንመጣለን ይጠብቁን

ከደራሲያን አለም ፔጅ

አንዱ ቃለመጠይቅ ላይ     የቴዲ አፍሮን ዘፈን_____“ማር ሲገባ ገዳም፣ ድንጋይ ተንተርሶ፣ጧፉም እንደመናኝ፣ እዩት ቢጫ ለብሶ”የሚለዉን የቴዲ አፍሮን ስንኝ “ይህን ቅኔ የፈታ እኔ ሸልማለ...
24/09/2025

አንዱ ቃለመጠይቅ ላይ
የቴዲ አፍሮን ዘፈን_____

“ማር ሲገባ ገዳም፣ ድንጋይ ተንተርሶ፣
ጧፉም እንደመናኝ፣ እዩት ቢጫ ለብሶ”

የሚለዉን የቴዲ አፍሮን ስንኝ “ይህን ቅኔ የፈታ እኔ ሸልማለሁ። ይሄ ሁለቱ መስመር ብቻ አርባ ዘፈን ይወጣዋል …ወዘተ” ብሎ ሲያበቃ …
”እኔ ልፍታዉ? ልፍታዉ?” ብሎ ጀመረ።
ምን የቅኔ ማዕበል ሊያወርድብን ነዉ ብዬ አፌን ከፍቼ ስጠብቅ…

“ማር ሲገባ ገዳም፣ የሚለዉ ‘ጧፍ’ ነዉ። ‘ድንጋይ ተንተርሶ’ የሚለዉ ደግሞ ጧፉ እናቶች ሲሸጡት ድንጋይ ላይ አንተርሰዉ ነዉ። ‘ጧፉም እንደመናኝ፣ እዩት ቢጫ ለብሶ’ የሚለዉ ደግሞ ያዉ ጧፍ ቢጫ አይደል መቅደስ ዉስጥ ሲገባ? ልክ እናንተ እንደለበሳችሁት” ብሎ በራሱ የቅኔ አፈታት ፈቶት አረፈ 😂

“ብላሽ!” አለ ሰዉየዉ
ዘ_ይገርም እኮ ነው

F,t

አስቂኝ 😂እውነተኛ ታሪክሳራ እባላለሁ ልጅ እያለሁ አብረን መርካቶ ያደግን ታየች የምትባል የልብ ጓደኛ ነበረችኝ። የሆነ ጊዜ ላይ ራጉኤል ጋር የነበረው የአባቷ ጨርቃ ጨርቅ ሱቅ በጣም ታዋቂ ...
23/09/2025

አስቂኝ 😂እውነተኛ ታሪክ

ሳራ እባላለሁ ልጅ እያለሁ አብረን መርካቶ ያደግን ታየች የምትባል የልብ ጓደኛ ነበረችኝ።
የሆነ ጊዜ ላይ ራጉኤል ጋር የነበረው የአባቷ ጨርቃ ጨርቅ ሱቅ በጣም ታዋቂ ሆነ።
ከዛ ብዙም ሳይቆይ አለፈላቸውና መርካቶን ለቀው ኦልድ ኤርፖርት የሚባል ሰፈር ቤት ሰርተው ገቡ።
እኔ እዛው መርካቶ ጭቃ ላይ እየተራገጥኩ አንበጣ ሳባርር ታየች ቢኪኒ የሚባል ጡት ማስያዣ ተገዝቶላት መዋኝት ተማረች።
አልፎ አልፎ ቤታቸው ስጋበዝ ምቾቷ ይጋባል።

የእማማ ራድያ የሽንት ቤት ፍሳሽ በግቢዬ የሚያልፈው እኔ፣ 😂
የእነ ታየች ግቢ ውስጥ ያለው ጋርደን ላይ ተንጋልዬ መጽሐፍ እያነበብኩ ስታይ፣ አይ ውበት።
አመሻሽ ላይ ወደ መርኬ ለመመለስ ገብሬል ጋር ያለው ታክሲ ውስጥ ስገባ፣ መጽሐፌን ጭብጥ እድርጌ ይዤ ከሰፊው ህዝብ ጋር ስገፋፋ😂፣
ጎበዝ ለካስ ምቾት ይተንናል!።

ጥቂት አመታት አልፈው እኔ በ"ክልክል" አጥር ውስጥ፣ ፍቅርኛ መያዝ በማይፈቀድልኝ አስተዳደግ ውስጥ ስዳክር

😂ታየች ሳምሶን የሚባል እንደሷ
በምቾት የሚንሳፈፍ የከንፈር ወዳጅ ያዘች። ህልምና መጽሐፍን የሰጠኝ እግዚያር ግን ደግ ነው። አሁን ደሞ ቸርነቱ በዝቶ የእኔ ከንፈር እንኳ በእውን ባይሳም የጓደዬ የታየች ከንፍር ሲሳም ሊያሳየኝ! እሱ ምን ይሳነዋል!

አንድ ቅዳሜ ታየች ደወልችልኝና ግራ የሚያጋባ ጥያቄ ሰነዘርች።
"ቲጂዬ ዋና ትችያለሽ?😂".. ከሳምሶን ጋር ጊዮን ሆቴል ሊዋኙ ተቀጣጥረው ኖሮ አብሬያቸው እንድዝናና መጋበዝዋ ነበር።
ምቾቷ አሳውሯት ነው እንጂ የት ነው እኔ መርካቶ ውስጥ ዋና የምማረው? ታደለች የምትቸረችረው የከሰል ሐይቅ ውስጥ?
ወይስ ወ/ሮ የሻረግ ጠላ ቤት ያለው #ማሰሮ ውስጥ? ታየች ፌዝ ተማረች።
ታየች ዋና ተማረች። ከመርካቶ ቦይ በኮንጎ ጫማ ተንደርድራ በቢኪኒ ጊዮን ሆቴል የውሃ ገንዳ ውስጥ ተጠመቀች።

እሁድ ጠዋት የከንፈር ወዳጆቹን አጅቤ እነሱ ሊዋኙ
እኔ ፎጣ ልጠብቅ 😂ጊዮን ሆቴል ደረስን።

ጁስና ኬክ ታዞልኝ እነሱ ውሃ ውስጥ ሲንሳፈፉ እኔ በእነሱ አለም ውስጥ ስንሳፈፍ፣ እንሱ በአራት ነጥብ የታጠሩ ደማቅ አርፍተ ነገሮች።
እኔ ገና ያልተብራራው ተከፍቶ ያልተዘጋ ቅንፍ። ውሃ ሲረጫጩ ደስ ሲሉ።
ይጎነታተላሉ። ኦ ቢኪኒዋ! አረንጓዴ ባለአበባ። ሳምሶን ከጀርባዋ ቆሞ እሷ ጸጉሯን ወደ ላይ ሰብስባ የላላውን የብኪኒዋን ገመድ እያሰረላት ሲጠጋት እሷ እየሳቀች ከወሲብ እንፋሎቱ ስትሸሽ። ሲያስቀኑ። በቀረብልኝ በጥቂት ደቂቃዎች ነው ኬኩንም ጁሱንም የሰለቀጥኩት። እንዲህ ያለው ምግብ በነጻ ሲገኝ ሰጪው ሃሳቡን ሳይቀይር ቶሎ ማውደሙ ከልምድ የመጣ ነው። የመርካቶ ቅደም ተከተሉ መጀመርያ ረሃብ ማስታገስ ከዛ ስለ ታየች የከንፈር ዕጣ ፈንታ ማሰላሰል።

በጨረፍታ እያየኋቸው ደስታቸው ተጋባብኝ። ያሽካካሉ። ፊታቸው ያብረቀርቃል። ሳምሶን ብዙ ሳምሶኖች ቢሆን፣ እኔን ጎትቶ ውሃ ውስጥ የሚያጠልቀኝ ሌላ ሳምሶን ከዚህኛው ላይ ተቆርሶ ቢመጣ። ሮዝ ቢኪኒ ቢኖረኝ። የብኪኒዬ ገመድ ቢላላ፣ ሳምሶን ሊያስርልኝ ቢጠጋኝ፣ በወሲብ እንፋሎቱ እጠመቅ ነበር። መጣበቅ፣ መጠመቅ፣ አንድ መሆን። ታየች ለምን ሸሸች?

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ያላሰብኩት ክስተት ተፈጠረ። ታየች እየተጣደፈች ከገንዳው ስትወጣ አየኋት። ፊቷ ላይ ብስጭቷ ይነበባል። ዞር ብዬ ሳምሶንን ቃኝሁት። ግራ ገብቶት ፈዞ ያያታል። አጠገቤ ስትደርስ በፍጥነት ፎጣዋን አንስታ ገላዋን እያደራረቀች "ቲጂ ቶሎ መሄድ አለብን ተነሽ" ብላኝ ሳትጠብቀኝ ወደ ልብስ መቀየሪያው ክፍል አመራች። "ይህ ቀዥቃዣ ወሲባም ምን አድርጓት ይሆን?" ብዬ እያሰላሰልኩ ተከተልኳት። ለባብሳ ወደ ታክሲ ስናመራ የሳምሶን አብሮን አለመሆን ግራ እንደገባኝ ስታውቅ "የኔ እና የእርሱ ነገር አብቅቷል" ብላ በረጅሙ ተነፈሰች።

እንዴ? ይህ የተመቸው ቦንቦሊኖ የመሰለ ልጅ፣ ለመላው የመርካቶ ኮረዳ ኬክና ጁስ የመግዛት አቅም ያለው ሳቂታው የሃብታም ልጅ፣ ቢኪኒዋን ወሲብ በተሞላበት ርህራሔ ያሰረላት ስሱ ሳምሶን ምን አድርጓት ይሆን? ልምድ ያካበቱ የሚመስሉ ከንፈሮች እንዲሁ በዋዛ ሊቀሩ?
"ምን እንዳደረገ ታውቂያለሽ?" አለች እየተብከነከነች። "የውሃው ገንዳ ውስጥ፣ እዛ የምንዋኝበት ገንዳ ውስጥ፣ አፍንጫውን ጨምቆ፣ በሃይል እንፍፍፍፍፍ ብሎ ንፍጡን ስቦ ካወጣ በኋላ እዛው ውሃ ውስጥ አይወረውረው
😂😂😂
መሰለሽ? ከዛ ደሞ እጁን መለቃለቁ! አይኑን ማየት አልፈልግም" ብላ አስረግጣ ነገረችኝ።

ወንድሜ ሆይ፣

የታየች #መስፈርት ግልጽ ነው። መርሴዲስ ቢኖርህ፣ ተጫዋች፣ አማላይ፣ ሳቂታ አፍቃሪ ብትሆን፣ ነገር ግን ንፍጥህን በየቦታው የምታዝረከርክ ከሆነ፣

ከታየች ጋር እድል አይኖርህም። የህዋ ተመርማሪ ብትሆን፣ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ብትሆን፣ ምን አለፋህ የሮም ከተማን የቆረቆርከው መሃንዲስ አንተ ብትሆን፣ ግን ህዝብ የሚዋኝበትን የውሃ ገንዳ በንፍጥህ የምትበክል ዝርክርክ ከሆንክ የታየች አጸያየፍ ከእግዚያር ፍጥረት ሁሉ የረቀቀ ነው። 😂😂

የታየች መጨረሻ ግን ምን ይሆን 😂

T S

ከደራሲያን አለም ፔጅ

23/09/2025

ለናተ የማይረሳ ትዝታ የቱ ነው ??
ወርቃማው ዘመን 239
ከደራሲያን አለም ፔጅ

አጭር እውነተኛ  #ታሪክ..እሷ ለእኔ እኔ ለእሷ ብቻ ያለን ይመስል ነው የምንፋቀረው በእርግጥ እኔ ያለ እሷ ቤተሰብም ጓደኛም የለኝም ቤተሰቤ አለሜ እሷ ናት። ወይን እያደረ እንደሚጥመው እየ...
22/09/2025

አጭር እውነተኛ #ታሪክ
..እሷ ለእኔ እኔ ለእሷ ብቻ ያለን ይመስል ነው የምንፋቀረው
በእርግጥ እኔ ያለ እሷ ቤተሰብም ጓደኛም የለኝም ቤተሰቤ አለሜ እሷ ናት።
ወይን እያደረ እንደሚጥመው እየናፈቁ ያላገኙት ሰው ሞት ሲከርም እንደሚበረታ ሀዘን የእኔናየእሷም ፍቅር በየሰከንዱ ነበር #የሚጨምር።
እኔ የቀን ሰራተኛ ምንም የሌለኝ ምስኪን ስሆን እሷ ደግሞ የሀብታም የከበርቴ ልጅ ናት ነገር ግን ማነሴን አሳይታኝ አታውቅም ከእነ ጉድለቴ ተቀብላኝ ከእነ ድክመቴ አፍቅራኝ ነበር የምትኖረው።
ከጊዜያት በሗላ ግን ሁሉም ነገር ተለወጠ የምወዳት ፍቅሬ በእኔ ላይ መጨከን እና መቆጣት አመጣች።

የቀን ሰራተኛ ጉልበቱ ዝሎ እና ደክሞነውና ወደ ቤቱ የሚገባው እኔም የዛለውን ሰውነቴን እየጎተትኩ ነበር ፍቅሬ የደወለችው "ላገኝህ እፈልጋለሁ ከቦታችን ቁጭ ብዬ እየጠበኩህ ነው" ስልኩ ተዘጋ።

ስጎትተው የነበረው ሰውነቴ ቀለለኝ ድካሜ ተነነ...ወይ ፍቅር..❤
መድሀኒት እኮ ናት ስከንፍ ካለችኝ ቦታ ተገኘሁ። ፀዳል የመሰለው ፊቷ በሀዘን ጠቁሮ የውብ አይኖቿ ነፀብራቅ በእንባ ፈዘው ችምችም ጥርሶቿ በከንፈሯ ተሸፍኖ ጉም ያጠላበት ሰማይ መስላለች።
ስሜቷን ሳትነገረኝ ተረበሽኩ ከፋኝ መከፋቱ ግን ለእሷ ልቤን አልጠቀመውም እንደ እናቴ ሳይሆን እናቴ ናት የምላት ፍቅሬ"አንተ ደሀ ነህ! ለቤተሰቤ ክብር አትመጥንም.እኔም ብሆን ሀብታም ዘናጭ ወንድ ነው የምፈልገው" ብላ የብስጭት እሳት ጭራብኝ መላ ሰውነቴን አነደደችው
"ደግመህ ወደ እኔ እንዳትመጣ መመለስ ከፈለክ ህይወትህን ቀይር ያለበለዚያ አባትዬ ሙት እጠላሀለሁ" ብላ በደጉ ጊዜ ፍቅርን አውርተን ፍቅርን ሰርተን ፍቅር ሸምነን በፍቅር ባበድንበት ጊዜ ያደረኩላትን የብር ቀለበት ፊቴ ወርውራ በእንባ ጥላኝ ሄደች።
😢
....አይኖቼ እንባን ሰጣት አንደበቴም ቃልን ነፈጋት ቀን ጎደለ ፀሐዬ በእሷ ቃል ጠለቀች ጨረቃም በደመና ውስጥ ሰረገች የገባችልኝ የእምነት ቃል እንደ ሸክላ ተሰበረ
ከእኔ ፍቅሯ እንደ ጉም ተነነ ድህነቴ ብቸኝነቴ አስጠቃኝ እናቴ ብትሆን ግን....
ከመቅፅበት የብስጭት እሳቱ ከስሞ የእልህ እሳት ተያያዘ ውስጤ ወኔን ሰነቀ።
ገንዘብ ለማግኘት ተጨማሪ ስራ እና ትምህርት ጀመርኩኝ መቼ ካሰብኩት እንደምደርስ አላውቅም ግን ፍቅሬን ልበቀላት ሰው ሆኜ ላሳያት በየቀኑ እጓጓለሁ።

ናፍቆቷ ሳያንገላታኝ ወደ ልቤ ሰማይ እየበረርኩ አስታግሳለሁ።
ፍቅሯ ሲርበኝ ደግሞ አይኔን ከድኜ አያታለሁ በልቤ ስላኖርኳት ከእኔ ጋር እንደ ሆነች አስብ ነበር ግን አዝኜባታለሁ ለዚህም ይቅር የምላት እንዴት እንደሆነ እያቀድኩ ነው....
ከአመታት በሗላ በህይወቴ ትልቅ ለውጥ መጣ በድርጅት የሃላፊነት ቦታ ላይ ተቀመጥኩ።

አልባበሴም ተቀየረ ፈላጊዎቼ አክባሪዎቹ እጅግ በዙ ስለእኔ ሁሉም ጠያቂ ሆነ እኔ ግን ፍቅሬን ላገኛት ወደ ድሮ ሰፈሯ ሲሄድ ለቀዋል ተብዬ አዲስ አድራሻቸውን ተቀብዬ ወደዛው ሳቀና ከበርቴ እናት እና አባቷን አየኋቸው ደስ አለኝ....
ስታየኝ ምን ትለኝ ይሆን እያልኩ አዕምሮዬን እያስጨነኩ ተከተልኳቸው እናት እና አባቷን ለመሸኘት የመኪናዬን ክላክስ አሰማኋቸው እናቷ ያውቁኛል እና ሲያዩኝ ደነገጡ "ልሸኛቹ" አልኳቸው እና ወደ መኪናው አስገብቼ መንዳት ጀመርኩኝ እናቷ ያውቁኛል "ምን ሁነው ነው" አልኳቸው እሳቸውም "ልጄን ጠላሀት?" አሉኝ "ለምን" አልኳቸው ለዘላለም ነዋ በእሷ ፍቅር የቆረብኩት.......
ከመቃብር ስፍራ ስንደርስ መኪናውን አስቆሙኝ እና እንድከተላቸው ነግረውኝ ወደ ስፍራው ገቡ ከሰውነት አካሌ አንዳች ነገር ተቆርጦ ሲወድቅ ታወቀኝ ያየሁትን ማመን አቃተኝ የኔዋ እናትይ

በደም ካንሰር ሞታ አየኋት ለካ እንደዛ የጨከነችብኝ በእሷ ሞት እንዳልጎዳ እንድጠላት እና ሰው እንዳላጣ እና ሰነፍ ድሀ ሆኜ እንዳልቀር ነው ፍቅሯን አርቃብኝ የጠገነችኝ...❤ወይ ፍቅር.....ሞታ ሰው አደረገችኝ ራሷን ዝቅ አድርጋ በፍቅር ከፍ አደረገችኝ..የምወደው ፍቅሯ በፍቅር ሰራኝ.ለእሷ በመታመኔ ሽልማቴ ንፁህ ፍቅር ነበር የማይለወጥ ...እና እንዴት ከድሮ በላይ አላፈቅራት.......

💕ምን ትጠብቃለህ ወንድሜ? ታፈቅራታለህ? ትናፍቅሀለች?

👉 ደስታህን ሁሌም ንገራት😍 ጊዜህን ሰጥተሀት ፍቅርህን አሳያት ከማንም ጋር አታነፃፅራት

21/09/2025

EB's ኢሊባቡር ያፈረቻቸው
ከግብፅ የጎል ናዳ ያተረፈን በረኛችን አቡኪ ና የአፍሬማ እጩ_........

ሶስቱ  #የሚያሙ እውነታዎች!1.  ለረጅም ጊዜ ትክክልና እውነት እንደሆነ ያመንነውና የተከተልነው አመለካከት ስህተት እንደሆነ ወደማወቅ መምጣት … ያማል!፡፡2.  ለረጅም ጊዜ እንደሚወደንና ...
18/09/2025

ሶስቱ #የሚያሙ እውነታዎች!

1. ለረጅም ጊዜ ትክክልና እውነት እንደሆነ ያመንነውና የተከተልነው አመለካከት ስህተት እንደሆነ ወደማወቅ መምጣት … ያማል!፡፡

2. ለረጅም ጊዜ እንደሚወደንና እንደሚቀበለን አምነን የነበረው ሰው እንደማይወደንና እንደማይቀበለን ወደማወቅ መምጣት … ያማል!፡፡

3. ለረጅም ጊዜ ገንዘባችንን፣ ጊዜያችንንና ስሜታችንን በማስተባበር የሰራንለት ነገር እንደማያዋጣና እንደማያዛልቅ ወደማወቅ መምጣ … ያማል!፡፡

እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ሁለንተናችንን እንዳባከኑብን፣ ከሁኔታዎቹና ከሰዎቹ አንጻር የዘረጋነው የወደፊት እቅድ ገደል እንደገባ እና ሕይወታችን ባዶ እንደሆነ ሊሰማን ይችላል፡፡

#መፍትሄ ማድረግ የምንችለው . . .

1. መረጋጋትና ስሜትን ረገብ ማድረግ

2. እውነታውን ለመቀበል ራስን ማዘጋጀትና በክህደት አለም ውስጥ አለቆየት

3. ለሁኔታው ምን አይነት ምላሽ መስጠት እንዳለብንና የወደፊታችንን እንዴት ማቀድ እንዳብን በሚገባ ማሰብና የሰዎችን እገዛ መቀበል፡፡

አይዟችሁ! ሁሉም ነገር ያልፋል! ሁሉም ነገር ይታለፋል!

Eyob

Follow me Amare Lake

ከደራሲያን አለም ፔጅ

በቅርብ ቀን በአዲስ ትረካ ይጠብቁን

የኢትዮጵያ ፊልሞች  #ኩራት የሆኑት ......👉የወንዶች ጉዳይ ፣ሎሚ ለሽታ፣ጉዲፈቻ፣👉የነገን አልወልድም፣ ስርየት፣ኒሻን ሌሎችም ብዙ ብዙ ብዬ ብዙ ታላላቅ ፊልሞችን መጥራት ይቻላል የኢትዮጵያ...
15/09/2025

የኢትዮጵያ ፊልሞች #ኩራት የሆኑት ......

👉የወንዶች ጉዳይ ፣ሎሚ ለሽታ፣ጉዲፈቻ፣
👉የነገን አልወልድም፣ ስርየት፣ኒሻን ሌሎችም ብዙ ብዙ ብዬ ብዙ ታላላቅ ፊልሞችን መጥራት ይቻላል የኢትዮጵያ ፊልም የወረደ ነዉ አይረባም ብዬ አልተችም... ምንም ችግሮች ቢኖሩበትም የብዙዎቻችን እዚህ ሙያ ዉስጥ መነሻ ፊልም ማየት ነዉና ብዙ በታሪክ በዝግጅት አስገራሚ የሆኑ ፊልሞች አሉ የኢንዱስትሪዉ መቀዛቀዝ እና የባለሙያዉ ኤጎ መኖር የሁላችንም ጠንክሮ ፊልሞቻችን ላይ አለመስራት እንጂ ባለዉ የሰዉ ሀይል ብዙ ፊልሞችን ማምረት በቻልን ነበር ቢሆንም እነዚህ ፊልሞች በበጀት ወይም በተለያዩ ነገሮች አነስ ተደርገዉ ተሰሩ እንጂ በትልቅ በጀት ታግዘዉ ቢሰሩ አለምአቀፍ ደረጃን የሚያገኙ እና ሀገራችንን የሚያስጠሩ ድንቅ እና ምርጥ ኦርጂኛል የኢትዮጵያ ስታንዳርድ ኩራት ፊልሞች ይሆኑ ነበር.....!!

እናተ ምርጥ ፊልም የምትሉት ኮሜንት ???

   18//ራሄል በወላጆቿ ቤት ከመዋኛ ገንዳ አጠገብ ከእናትና አባቷ ጋር ተቀምጣ የጥዋት ፀሀይ እየሞቀች ነው፡፡ ፀጋ   ‹‹ አበባ ስጪኝ?››ስትል እህቷን ጠየቀች፡፡ራሄል ከተቀመጠችበት ተነ...
15/09/2025



18

//
ራሄል በወላጆቿ ቤት ከመዋኛ ገንዳ አጠገብ ከእናትና አባቷ ጋር ተቀምጣ የጥዋት ፀሀይ እየሞቀች ነው፡፡
ፀጋ ‹‹ አበባ ስጪኝ?››ስትል እህቷን ጠየቀች፡፡

ራሄል ከተቀመጠችበት ተነሳችና የፀሐይ መነፅሯን ወደ ጭንቅላቷ ገፋ በማድረግ እህቷ የፈለገችውን አበባ ቀነጠሰችና በትናንሽ እጆቾ ውስጥ አስቀመጠችላት…ፀጋ በደስታ ፈነጠዘች፡፡
ሮቤል እና አዲሷ ረዳት የፋውንዴሽኑን ስራ ከአሰበችው በላይ በጥሩ ብቃት እየመሩላት እንደሆነ ለሁለት ቀን ወደቢሮ ተመልሳ ባደረገችው የስራ ግምገማ መረዳት ችላለች፡፡
…እህቷን ለማስታመም በሆስፒታል ባሳለፈቻቸው አስር ቀናት ውስጥ ምንም የጎደለ እና ሳይሰራ የተወዘፈ ስራ አልነበረም…እና አሁንም ለሌላ አንድ ሰምንት ታናሽ እህቷ በደንብ እስክታገግም አብራት እንድትሆንና ቀለል ያሉ ስራዎችን እዛው እቤት ሆና እንድትሰራ ፈቅደውላት እሷም ተስማምታ ወላጇቾ ቤት ነው ያለችው፡፡

‹‹ኤሊ እመጣለሁ ያለው መቼ ነው?››ወ.ሮ ትርሀስ መጽሃፏቸውን ከጎኗቸው ባለ የመስታወት ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ራሄልን ጠየቋት።

‹‹ከሶስት እስከ አራት ሰዓት እመጣለሁ ነበር ያለው ፡፡ ››መለሰች…ጸጋ ራሷ ቀጥፋ የሰጠቻትን አበባ ፀጉሯ መካከል ሻጠችላት…ራሄል በፈገግታ እህቷን ወደራሷ ሳበችና ጉንጮን በመሳም‹‹ትንሿ እህቴ ..እንዲህ ስላሳመርሺኝ አመሰግናለው››አለቻት፡፡
በዛው ቅፅበት ወደግዙፉ ግቢ እየቀረበ የሚመጣ የመኪና ድምፅ ተሰማ ፡፡

‹‹የምትጠብቂው ጓደኛሽ አለ እንዴ?››አቶ ቸርነት ጠየቁ፡፡

‹‹ አይ አይመስለኝም?››ራሄል እርግጠኛ ባለመሆን ጠየቀች፡፡

‹‹እንግዲያው አለም መጥታ ማንነቱን እስክታሳውቀን እንጠብቅ ?››በማለት እናቷ ሳቁ።

አለም ወዲያው እየተፍለቀለቀች መጣች…‹‹ራሄል ነይ እንግዳሽን ተቀበይ››

‹‹ማን ነው?››

‹‹አትንገሪያት ተብያለው…እራስሽ መጥተሸ እይው››አለችና ወደኪችኗ ተመለሰች፡፡

ራሄል.‹‹ማነው በወላጆቼ ቤት ከእኔ ጋር እንዲህ አይነት ጫወታ ለመጫወት የደፈረው?››በማለት ተነስታ ፀጋን ይዛ ሄደች።ራሄል እና ፀጋ ወደ ግቢው የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ሲሄዴ ኤሊ ወደ ውስጥ ሲገባ ተመለከቱት ።ራሄል እንዳየችው በውስጧ የደስታ ማዕበል አጥለቀለቃት።

ባለመኪና ስትጠብቅ ባለሞተር ሰው በማየቷ ተደንቃ ‹‹ሄይ፣ እንዴት እዚህ ደረስክ? የሞተር ሳይክልህን ድምፅ አልሰማሁም።››አለችው…

ዔሊ ጎንበስ ብሎ በቀስታ ሳማት እና ፀጋን አንስቶ ካቀፋት በኃላ‹‹ሌላ አይነት የመጓጓዣ ዘዴ ነው የተጠቀምኩት.››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ሞተርህ ተበላሸች እንዴ ?›› አለችና አይኖቾን ወደመኪና ማቆሚያ አዞረች ከእሷ ቀይ መኪና አጠገብ የቆመ ባለ ሰማያዊ ቀለም መኪና እያየች ግራ ተገባች።

‹‹ ያን መኪና ከማን ነው የተዋሰከው? ወንድምህ እንደዚህ አይነት መኪና የለውም።››

ዔሊ ተነፈሰ። ‹‹እነሆ፣ ወ.ሮ ራሄል ሞተሬን ሸጥኩት።››

ራሄል መኪናዋን በድጋሜ ተመለከተች፣ ‹‹ሞተር ሳይክልህን አስወገድከው !አየህ እኔ ስለ አንተ የምወደው ያን ነው ። ቆንጆ እና ፈጣን ተማሪ ነህ….ግን ለምን?››

…‹‹ደህና፣ በአንድ ወቅት አንድ ሰው እንዴት አንድ ኃላፊነት የሚሰማው ለዛውም የህፃናት ሀኪም የሆነ ሰው ሞተር ሳይክል ይነዳል ? የሚል ጥያቄ ጠየቀኝ። እና ለእሱ መልስ ለመስጠት ብዬ ነው መኪና የገዛሁት፡፡››

ራሄል ወደ መኪናው ሄዳ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ትንሽ ነካችው፣ ከዚያም ወደ ዔሊ ተመለሰች፣ ››

‹‹አስደንቀኸኛል ››አለችው

‹‹ስለሞተር ሳይክሎች ያለሽን ስሜት ስለማውቅ እናም የፍራቻሽም ምክንያት በከፊል ትክክል መሆኑን ስላመንኩበት ነው...››

እዛው የሳሎኑ በረንዳ ላይ ካሉ ወንበሮች አንዱን እንዲቀመጥ ሳበችለት ፀጋን በክንዱ እንዳቀፈ ተቀመጠ….ከጎኑ ሌላ ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡

ከዛ ሳታስበውና ምንም ሳትዘጋጅበት ትልቅ ቁም ነገር ከአንደበቱ አፈትልኮ ወጣ ‹‹ይህን ሁሉ በትክክለኛው መንገድ ይፋ ማድረግ ፈልጌ ነው …ራሄል፣ ላገባሽ እፈልጋለሁ።››አላት፡፡

ጆሮዎቾን ማመን አልቻለችም…ልቧን ደረቷን ሰንጥቆ እንዳይወጣ የፈራች ይመስል ደግፋ ያዘችው ። በውስጧ የሚንተከተከው ደስታ እና ፍቅር እና ምስጋና መውጫ ለማግኘት እየሞከሩ በአንደበቷ ላይ ተንገዋለሉ….ማልቀስ ብቻ ነው የቻለችው፡፡

‹‹ሄይ እኔ ያን ያህል መጥፎ ነገር አልተናገርኩም….ለምን ታለቅሻለሽ?››

‹‹በጣም ደስ ብሎኝ ነው…..››ስትል በለሆሳሳ መለሰችለት፡፡‹‹እወድሀለሁ ኤሊ›› ወደ እሱ ተሳበችና ጉንጩን ሳመችው..ታፋው ላይ የተቀመጠችው ፀጋ በደስታ እጆቿን እያጨበጨበች በሳቅ ተንከተከተች። የእሷ ሳቅና ደስታ ወደ እነሱም ተጋባ፡፡

‹‹መጀመሪያ ዝም ብዬ ለአንቺ ምንም ሳልነገርሽ ወደቤተሰቦችሽ ሽማግሌ ለመላክ አቅጄነበር …››

‹‹እንዴ የእኔን ሀሳብ ሳታውቅ ሽማግሌ ልከህ እምቢ ብልህስ?››

‹‹ያው ምን አደርጋለው የተሰበረ ልቤን ይዤ የብቸኝነት ኑሮዬን ቀጥላለዋ !!››ብሎ ትከሻውን ነቀነቀ።ራሄል ጣቷን ከንፈሩ ላይ አድርጋ ሳቀች።

‹‹ ስለነርከኝ ደስ ብሎኛል፣ደግሞ ስትነግረኝ ፀጋ በመሀከላችን መገኘት በመቻሏ ደስታዋ ድርብ ሆኗል … ለነገሩ እኛን አንድ ያደረገች እሷ ነበረች.››

‹‹እሺ ስላልሽኝ ደስ ብሎኛል…:በዚህ ምክንያት በህይወቴ ለሆነው ነገር እግዚአብሔርን በየቀኑ አመሰግነዋለሁ:: በአንቺ ምክንያት ህይወቴ መሉ ሆኗል››

‹‹አንተ ስጦታዬ ነህ ኤሊ ›› አለችና አቀፈችው።

‹‹አሁን እናትና አባትሽን እንፈልግ።››

ተስማሙና …ተያይዘው በአረንጓዴ ተክሎች ወደተሸፈነው ግዙፉ ጊቢ ተያይዘው እየተሳሰቁ ሄዱ፡፡

ደ/ር ኤልያስ ዛሬ ምን አልባትም በህይወቱ ፍፁም የሆነ ደስታ የተሰደሰተበት ቀን ስለሆነ ስሜቱን መቆጣጠር አቅቷት ጥንቅቅ ብሎ ባለቀ ውብ ቤቱ ውስጥ ከክፍል ክፍል እየተመላለሰ እንደህፃን እየቧረቀ ነው፡፡ስልኩን አነሳና ደወለ…፡፡ከአራት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡

‹‹ውድ ባለቤቴ እንዴት አለሽልኝ››

‹‹አንተ ያንን ቃል መጠቀም የምትችለው እኮ ሰማንያ ፈርመህ ቤትህ ስታስገባኝ ነው››አለችው እየሳቀች፡፡፡

‹‹ያው በይው..ዜናውን አልሰማሽም እንዴ…..?ሽማግሌዎቼ እኮ ወላጆችሽ ልጃቸውን ሊሰጡኝ በደስታ መስማማታቸውን አሁን ነግረውኝ በደስታ እያበድኩ ነው፡፡››

‹‹ከአንተ ቀድሜ ሰማሁ…ምነው ይከለክሉኛል ብለህ አስበህ ነበር እንዴ?››

‹‹እንዴ ምን ይታወቃል…..ምን አልባት ቅድሞ እደጅ እየጠና ያለ ብረት መዝጊያ አማች ኖሮ ሀሳባቸው ወደእሱ ቢያጋድልስ?››

‹‹እሱስ እውነትህን ነው …ለአሁኑ ግን ተርፈሀል››

‹‹እኔም መትረፍ የምፈልገው ለአሁኑ ብቻ ነው…የማገባው አንዴ ብቻ እኮ ነው…››ተሳሳቁ፡፡

‹‹እና ይሄንን ደስታ አብረን ማክበር የለብንም ትያለሽ…?››

‹‹አንተ ..ከአሁን ወዲህ እኮ እስከሰርጌ ቀን ድረስ ልታየኝ አይገባም…››

‹‹እንደዛ ከሆነማ ሰርጉን ነገውኑ ደግስ በይኛ››

‹‹አዎ ..ያን ያህል ከቸኮልክ አድርገው››
‹‹እሺ..አስበብበታለው..እውነት ግን በጣም ላገኝሽ ፈልጌለሁ…››

እሷም ከአንደበቷ አውጥታ አትናረው እንጂ በጣም ልታገኘው ፈልጋለች፡፡‹‹ ይቻላል..የትና መቼ?፡፡››

‹‹ምሳ ልጋብዝሽ …ሰባት ሰዓት ስካይ ላይት እንገናኝ፡፡››

‹‹ሰባት ሰዓት ..አሁን እኮ አራት ተኩል ሆኖል…..ለመዘጋጃጀት በቂ ጊዜ አይኖረኝም፡፡››

‹‹አንቺ ደግሞ..እንደውም ምንም መዘገጃጀት አያስፈልግሽም… እዛ ሆስፒታል በነበርሽበት ጊዜ ያለምንም ዝግጅት ምን እንደምትመስዬ እኮ አውቃለው…ለእኔ ብለሽ ለመቆነጃጀት ከሁለት ሰዓት በላይ ማጥፋት የለብሽም…ከዛሬ ወዲህ ባልሽ ነኝ፡፡ማለቴ ለጊዜው እጮኛሽ ነኝ..ግን ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፡፡››

‹‹‹ይሁንልህ እሺ…..ግን ቅር ካላለህ አንድነገር ልጠይቅህ ››

‹‹ምን ጠይቂኝ››

‹‹ጸጋን ይዣት ብመጣ ቅር ይልሀል?››

‹‹አረ በፍፅም ..እንደውም በተቃራኒው ደስ ነው የሚለኝ …እሷ ከመጀመሪያው ጀምሮ የፍቅራችን ብቸኛ ምስክር ነበረች..ዛሬ መገኘት ይገባታል….ጫጉላ ቀናችን ላይ አብራን ወደመኝታ ትግባ እንዳትይ እንጂ ለዛሬው ደስ ይለኛል››

ስለጫጉላ ሲያወራ እፍረትም ሙቀትም ተሰማት‹‹አንተ ምን እያልክ ነው..?በል ቸው››ብላ ስልኩን ዘጋች፡፡

እሱም ወዲያው ወደሻወር ቤት ገባና ሰውነቱን በፍጥነት ተለቃለቀ…ከዛ ፂሙን ላጨ…ሙሉ ሱፍ ለበሰና ዝንጥ አለ…፡፡ለመውጣት ዝግጁ ሆነ…፡፡ሰዓቱን ሲያይ 5 .ከሩብ ይላል….ከራሄልና ከፀጋ ጋር ወደሚገናኝበት ቀጠሮ ከመሄዱ በፊት ማግኘት የሚገባው አንድ ሰው አለ…ከአመት በፊት በሆስፒታል አብራው ትሰራ የነበረች የህጻናት ሀኪም ነች ትናንትና ደውላ ላገኝህ እፍልጋለው ያለችው፡፡ለዚህች ዶ/ር የስራ ባለደረባው ነበር…ያለፈውን አንድ አመት ተጨማሪ ትምህርት እድል አግኝታ ኖሩዌይ ነበር ያሳለፈችው፡፡አሁንም ለሁለት ሰምንት ረፍት እንደመጣች እና መመለሻዋ እንደደረሰ እናም ከመሄዶ በፊት አንድ እቃ ልትሰጠው እንደምትፈልግ ነግራው ነው እግረመንገዱን ሊያገኛት የወሰነው፡፡

ሀያ ሁለት ነበር ቀጠሮቸው…እሷም ቸኩላ ስነበረ ቀጥታ ወደጉዳዩ ነበር የገባችው፡፡አንድ የታጠፈ ነጭ ፖስታ አውጥታ እጁ ላይ አደረገች፡፡ግራ ገብቶትም ደንግጦም‹‹ምንድነው ሲል?››ጠየቃት፡፡

‹‹ትዝ ይልሀል ከመሄዴ በፊት አብረን የምንከታተላት አንድ ታማሚ ልጅ ነበረች…እናቷ ከአንተ ጋር ትግባባለች…እንደውም የልጅነት ጓደኛዬ ነበረች ብለሀኛል››

‹‹ኦኬ ትክክል ነሽ..ስለፀጋ ነው…ማለቴ የዛን ጊዜ ስሟ ትሁት ነበር..ስለእሷ ነው የምታወሪው››

‹‹አዎ ስለእሷ ነው…ለመሆኑ እንዴት ነች…?አሁንም በህይወት አለች?››

‹‹አዎ በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ ነች…ግን ፖስታው ምን እንደሆነ አልገባኝም››

‹‹ፖስታውማ እናትዬው እዛ ሆስፒታል ውስጥ ህጻኗን ጥላ ከመሄዶ በፊት ይህንን ፖስታ ለአንተ እንድሰጥ አደራ ብላ ሰጥታኝ ..ነበር….እርግጥ በወቅቱ ልጇን ጥላ እንደምትሄድ አልገመትኩም እና እሺ ብዬ ተቀበልኮት….ግን በዛው ሰሞን አንተም ለሆነ ስራ ወደክፍለሀገር ወጥተህ ነበር..እኔም ውጭ ለመሄድ በጣም እየተዋከብኩ ስለነበረ እቤቴ ወስጄ እንደቀልድ እንዳስቀመጥኩት እረሳሁት እና ሳልሰጥህ ሄድኩ ..በቀደም ነው የድሮ ወረቀቶቼን ሳስተካክል ድንገት አገኘሁት..አድራሻውን ሳነብ ትዝ አለኝ….መጀመሪያ አፍሬ እንደተረሳ ልተወው ነበር›..በኃላ ሳስበው ግን ምን አልባት በጣም አስፈላጊ ነገር ቢሆንስ ብዬ…አይኔን በጨው አጥቤ አግኝቼ ልሰጥህ ወሰንኩ….ይቅርታ እሺ››

‹‹አረ ችግር ለውም…ያው ልጄን አደራ..ተከታተላት ምናምን የሚል መልዕክት ነው የሚሆነው….ያንን ደግሞ እሷ ባትለኝም አደርገዋለው››በማለት ፖስታውን ኪሱ ውስጥ ከተተና ከእሷ ተሰናብቶ መኪናው ወደ እስካይ ላይት አዞረ፡፡

ከቀጠሯቸው 10 ደቂቃ ቀድሞ ነበር የደረሰው፡፡ ወንበር ይዞ በጉጉት ይጠብቃቸው ጀመር..፡፡ድንገት ፖስታው ትዝ አለው፡፡ አወጣና አየው…፡፡ከጀርባው ለማከበርህ ደ/ር ኤልያስ ከፅጌረዳ ይላል፡፡
እነ ራሄል እስኪመጡ ቀዶ ሊያነበው ፈለገ…መቅደድ ከመጀመሩ በፊት ፖስታውን ጠራጴዛው ላይ አስቀምጦ ስልኩን ከኪሱ አወጣና ተመለከተው…ራሄል ነች፡፡አነሳው፡፡

‹‹እሺ የእኔ ፍቅር››

‹‹ቀድመንህ ደርሰናል መሰለኝ››

‹‹አረ እንዴት ተደርጎ…››አለና ያለበትን ቦታ ነገራቸውና እስኪያዩት ቆሞ ጠበቃቸው…. ራሄልን ሲያያት ልቡ ትርክክ አለ….ወደፊት ተራምዶ ፀጋን ከእቅፏ ተቀበለና..ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙ…. ወደ ጠረጴዛቸው ሄደው ተቀመጡ….ምሳ ታዘዘ እና እስኪመጣ ሞቅ ያለጫወታ ጀመሩ…..ራሄል ድንገት ፊት ለፊቷ የተቀመጠ ፖስታ አየችና በመገረም አነሳችና አየችው…፡፡

‹‹ፅጌረዳ ማን ነች?››ኮስተርተር አለች፡፡

‹‹ቀናሽ እንዴ?››

‹‹በኢንተርኔት ዘመን ፖስታ በምትልክልህ ሴት እንዴት ብዬ ነው የምቀናው?››

‹‹በፖስታው አድራሻ ላይ የተጠቀሰችው ፅጌረዳ ማለት የፀጋ እናት እንደሆነችና ፖስታው ከተፃፈ ከአመት በኃላ እንዴት እንዳገኘው… በእንግሊዘኛ ነገራት››ይሄንን ያደረገው ፀጋ ፊት ስለእናቷ በምትሰማው ቋንቋ ለማውራት ስላልደፈረ ነው፡፡

‹‹እና..አልተከፈተም እኮ››

‹‹አዎ…አሁን ስለፀጋ እኔን ብቻ ሳይሆን አንቺንም ስለሚመለከት አብረን እናነበዋለን››

‹‹እርግጠኛ ነህ?››

‹‹ አዎ እርግጠኛ ነኝ››

‹‹እና እናንብበዋ››ብላ ልትቀደው ስትዘጋጅ፡፡

‹‹አይ …ይሄንን ጊዜያችንማ ለሌላ ጉዳይ አንጠቀምበትም…››ብሎ ፖስታውን ከእጇ ተቀበለና ከጎኗ ካለው ወንበር ላይ የተቀመጠው የራሷ ቦርሳ ውስጥ ከተተው፡፡

‹‹በቃ አንቺ ጋር ይሁንና ..ሰሞኑን አንድ ላይ ሆነን እናነበዋለን፡፡››ተስማማች…ምሳ ቀረበላቸው በሉ…ከዛ ወጥተው ወደአለም ሲኒማ ጎራ አሉና ፊልም አዩ….አሪፍና ጣፋጭ ቀን አሳለፉ….

ራሄል ደስ የሚል ቀን ብታሳልፍም ድክም ብሎታል…ገና ሁለት ሰዓት ሳይሆን ነው መተኛት እንደምትፈልግ ለወላጆቾ ተናግራና እነሱን ተሰናብታ ወደመኝታ ክፍሏ የገባቸው…የለሊት ልብሷን ቀይራ ለመተኛት አልጋዋ ላይ ከወጣች በኃላ ….የፀጋ እናት ፃፈች ተባለው ደብዳቤ ትዝ አላት….፡፡ለምን እንደሆነ ባታውቅም ውስጡ ያለውን ደብዳቤ ማንበብ ፈልጋለች….ግን ኤልያስ አብረን እናነበዋለን ነው ያለው..እራሷን ገሰጸች እና ተኛች፡፡እንቅልፍ ሊወስዳት ግን አልቻለችም…መልሳ ተነሳችና ከአልጋው ወርዳ ከቦርሳዋ ውስጥ ያለውን ፖስታ አወጣችና ወደአልጋዋ ተመለሰች….ቀደደችውና ውስጡ ያለውን ደብዳቤ አወጣችው…ማንበብ ጀመረች፡፡.

ኤሊ ይሄንን ደብዳቤ ለመጻፍ ለበርካታ ቀናት ከራሴ ጋር ስሟገት ነበር..ብዙ ቀን መፃፍ ጀምሬ ወረቀቱን ቀድጄ ጥያለው…በመጨረሻ ግን ለልጄ ስል ማድረግ እንዳለብኝ ውስጤ ስላመነ አድርጌዋለው፡፡

ኤሊ አንተ የልጅነት የሰፈር ጎደኛዬ ነህ…በጣም እወድሀለው…እርግጥ አውቃለው አንተም በጣም ትወደኛለህ..የእኔ ግን ከዛ ያለፈ ነው..አፈቅርህ ነበር…ሀይስኩል እያለን ህልሜ ወደፊት አንተን ማግባት ነበር…ከአንተ ልጅ መውለድ ነበር…አውቃለው ለአንተ ጓደኛህ ብቻ ነኝ….በእኔ ልብ ውስጥ ያለው መዝሙር ግን ሌላ ነበር….እና ምን ሆነ አንተ አሪፍ ውጤት አምጥተህ ዩኒቨርሲቲ ስትገባ እኔ ወድቄ ሰፈር ቀረሁ..እንደዛም ሆኖ በአንተ ደስተኛ ነበርኩ…እሱ ለሁለታችንም ይበቃል አልኩ…በአንተ ዲግሪ እኔ የራሴን ወደፊት ኑሮ አቀድኩ….ከአንተ ጋር የምሰራውን ቤት አለምኩ…ግን ህይወት ወራጅ ወንዝ ብቻ ሳትሆን ደራሽ ጎርፍ ጭምር ነችና…ሳላስበው ካልሆኑ ልጆች ጋር ገጠምኩ..ድህነቴና የቤተሰቦቼ የገንዘብ አቅም ደካማነት አንዳንድ ያልሆኑ ስራዎችን እንድሰራ አስገደደኝ..

አንተ ዶክተር ሆነህ ተመርቀህ ስትመጣ እኔ የሶስት አመት የሽርሙጥና ልምድ ነበረኝ..ያ ደግሞ በድብቅ ሳደርገው የቆየሁት ሳይሆን ሀገር ዘመድ ያንተም ቤተሰቦች ጭምር የሚያውቁት መራር ሀቅ ነበር፡፡እና በዛ ቆይታ ስለአንተ ያለኝን ህልም ገድዬው ነበር….እና ተመርቀህ መጣህ…በጣም ደስ አለኝ..የቁጭት እንባ አለቀስኩ…፡፡ አረሳሀኝም..አልተጠየፍከኝም…ቤታችሁ በተዘጋጀ የምረቃት ዝግጅት ላይ አፈላልገህ የምሰራበት ብና-ቤት ድረስ መጥተህ ጋበዝከኝ፡፡ለአንተ ስል የሰፈር ሰዎችን አይን ..ችዬ የቤተሰቦችህን ምን ይሉኛል እያልኩ እየተሸማቀቅኩ መጣሁ..ጥሩና ደስ የሚል ዝግጅት ነበር፡፡

ራሄል የምታነበውን ነገር ማመን አልቻለችም…..በጣም አጎጊና አስፈሪ ሆነባት….ማንበቧን ቀጠለች፡፡

…ከዛ መደዋወል አልፎ አልፎ መገናኘትም ጀመርን፡፡ትዝ ይልሀል ስራ ከያዝክ ከሁለት አመት በኃላ ሚዜ የሆንክበት የዶ/ር ሰለሞን ሰርግ ላይ ጋበዝከኝ….ደስ አለኝና መጣሁ…አሪፍ ሰርግ ነበር..አንተም በጣም ደስ ብሎህ ነበር…ያለወትሮህ በጣም ጥተህ ነበር… እኩለ ሊሊት ላይ ከሰርጉ ቤት ደግፌህ ተያይዘን ወጣን…ሆቴል አልጋ ያዝኩልህና እንድታርፍ አድርጌ ወደቤቴ ልሄድ ስል ትንሽ አጣጪን አልከኝ..ተው ይበቃሀል ብልህም አልሰማሀኝም..እንደውም ሶፋ ላይ ተኛለው አንቺ አልጋው ላይ ትተኚያለሽ…በለሊት ወዴትም አትሄጂም አልከኝ፡፡ከዛ ተስማማውና እዛው እልጋ ክፍል ውስጥ መጠጥ አዘን መጠጣት ጀመርን…ፈርቼ ነበር…ለእኔ ሳይሆን ለአንተ ነበር የፈራሁት…ከዛ እንዴት እንደሆነ አላውቅም መሳሳም ጀመርን… ሁሉም ነገር ሆነ …ካዛ በኃላ ነፍስህን አታውቅም ነበር…በውድቅት ለሊት ቁጭ ብዬ አሰብኩ…ጥዋት የተፈጠረውን ስታውቅ በጣም እንደምትበሳጭ አሰብኩ..ሁለተኛ ስሬ እንዳትደርሺ እንደምትለኝ እርግጠኛ ሆንኩ…ሳልመው የኖርኩትን ፍቅርህን ማግኘት ባልችልም ጓደኛነትህን ማጣት እንደሌለብኝ ወሰንኩ፡፡

ሁሉን ነገር አፀዳደው..ያወለቅከውን ፓንትና ሱሪህን በየተራ እንደምንም ብዬ መልሼ አደረኩልህ…ቀበቶህን ሳይቀር አሰርኩልህ፡፡ከዛ በስነ-ስርአት አልጋው ላይ አስተኛውህ… የራሴንም ልብስ ሙሉ በሙሉ ለብሼ አልጋ ልብሱን ተከናንቤ ሶፋ ላይ በመተኛት ስጨነቅና ስፀልይ ነጋ….ጥዋት ስትነቃ አይን አይንህን ሳይ ነበር…እግዜር የተመሰገነ ይሁን አንተ ምን እንደተፈጠረ አላወቅክም..ምንም የተቀየረ ነገር አልነበረም..ከዛ ጓደኝነታችን እንደነበረ ቀጠለ፡፡ደስ አለኝ…ከሁለት ወር በኃላ ሌላ መዘዝ መጣብኝ ..ማርገዜን አወቅኩ..ምን ላድርግ ..ከአንተ ጋር መተኛት ለአንት ማርገዝ ለእኔ የልጅነት ህልሜ ነበር እናም መደስት ነበረብኝ..ግን በዚህ አይነት ሁኔታ ላይ እያለው የሚሆን እንዳልሆነ አውቃለው…አንተ ለእኔ አዝነህ ልጅቷን ብትቀበል እንኳን ወላጆችህ ምን ይሉሀል….?ቤተሰቦችህ ምን ያህል ሀይማኖተኛ እና የተከበሩ ሰዎች እንደሆኑ አውቃለው..በአንተ ምን ያህል እንደሚኮሩብህ በደንብ አውቃለው…እና አንተ በማታውቀው ጉዳይ እንዴት እንዲያዝኑብህ ላድርግ…?ወሰንኩ…ትሁትን ላስወርዳት ወሰንኩ፡፡ብዙ መድሀኒት ተጋትኩ..እሷ ግን ጠንካራ ታጋይ ነበረች..አልወጣም አለች…በመጨረሻ የራሱ ጉዳይ ብዬ ተውኳት.. ተወለደች.. በእርግዝናዬ ወቅትም ሆነ ከወለድኩ በኃላ ከጎኔ ነበርክ…አባቷን ብዙ ጊዜ ጠይቀሀኝ ዋሽቼህ ነበር…እና እስከመጨረሻውም ላልነግርህ ነበር እቅዴ፡፡ ግን…ከስድስተ ወሯት በኃላ ታመመች… ሙሉ በሙሉ ሆስፒታል ገባች…ሳያት ህመሟ ቀጣይነት ያለውና ምናልባትም የእድሜ ልኳ እንደሆነ ተረዳው…እኔ ጋር ብትሆን ምን ላደርግላት እችላለው? ..እንዴት ልንከባከባትና እንዴት ላሳክማት እችላለሁ..?አሰብኩ..ከዛ ለአንተ እወነቱን ለመናገር ወሰንኩ፣ግን ያው ፊት ለፊትህ ተቀምጬ አይኖችህን እያየው ይሄንን ዜና ልነግርህ አልችልም..ያለኝ ምርጫ ይሄንን ደብዳቤ ፅፌ እኔ ከአካባቢው ከተሰወርኩ በኃላ እንዲደርስህ ማድረግ ነው፡፡

አንተ የትሁት አባት ነህ…ከፈለክ ዲ.ኤን.ኤ ማስመርመር ትችልህ..እኔ ማንም ሊያገኘኝ ወደማይችለው ቦታ ሄጄያለው ..ማለት ከሀገር ውጭ ነው ሄድኩት..መቼም አልመለስም….ልጅህን ወላጆችህን በሆነ መንገድ አሳምነህ ለእነሱ ብትሰጣቸው ደስ ይለኛል..እነሱ ልጅን ለማሳደግ ፍላጎቱም ፍቅሩም፣፣ ብሩም አላቸው…ብቻ የራስህ ልጅ ነች…በፈለከው መንገድ አሳድጋት፡፡
ጽጌረዳ ነኝ…..እስከመጨረሻው ደህና ሁንልኝ፡፡

ራሄል ወረቀቱን ጨመደደች ከእሷ አርቃ ወረወረችው….ከአልጋዋ ወረደችና የወለል ምንጣፉ ላይ እየተንከባለለች እስኪደክማት አለቀሰች…‹‹እሺ አሁን ምድነው የማደርገው?››እራሷን ጠየቀች፡፡‹‹‹ኤልያስ ይሄ ደብዳቤ ሲደርሰው ምንድነው የሚሆነው?››የዚህን መልስ መገመት አልቻለችም፡፡ለመረጋጋት እና ወደአልጋዋ ለመመለስ ከሁለት ሰዓት በላይ ነው የወሰደባት፡፡
ካዛ እስከንጋቱ አስራ አንድ ሰዓት ድረስ ስትገለባበጥና ስታስብ ነበር ያሰበችው፡፡
መጨረሻ የነገሩን ጥሩ ጎን ማየት ቻለች..በተለይ ለፀጋ አባት ማግኘቷ ደስ አላት.ኤልያስ አባቷ ሆነ ማለት ደግሞ እሷም እናቷ ሆነች ማለት ነው፡፡
ይሄን ስታስብ ውስጧ ደስ ሚል ስሜት ወረራት፡፡
ግን ኤልያስስ ዜናውን በእንደዚህ አይነት መንገድ ይቀበለዋል…
በእፍረት አንገቱን ደፍቶ ቢጠፋባትስ …?‹‹አልመጥንሽም…ጋብቻው ይቅር ቢላትስ?
››ስቅጥጥ አላት.ደግሞ ኤልያስ ምን ያህል ስሜታዊ ሰው እንደሆነ ስለምታውቅ አያደርገውም ብላ በእርግጠኝነት ልትተማመንበት አልቻለችም
…እና አንድ ውሳኔ ወሰነች፡፡
አንደኛ ሰርጋቸውን ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ እንዲደረግ ማድረግ፡፡
ሁለተኛ ደግሞ ሰርጋቸው ተደግሶ ባል እና ሚስት ተብለው አንድ ቤት ተጠቃለው እስኪገቡ ድረስ ይሄንን ፀጋ ልጁ እንደሆነች የሚገልፀውን ደብዳቤ እንዳያገኘው ማድረግ፡፡
እነዚህን ውሳኔዎች ከወሰነች በኃላ ነው የተወሰነ መረጋጋት ስለተሰማት እንቅልፍ የወሰዳት፡፡

ውድ አንባቢያን ከዚህ በታች ያለውን የትረካው አጨራረስ እናት እንድትጨርሱት አድርገነዋል !

ትረካ ለመፃፍ ምን ያህል ውስብስብ እንደሆነ እንድትረዱት እና የእናንተ የትረካ አረዳድ ምን ያህል እንደሆነ #እንድንረዳ የተተወ የ 10 መስመር ቦታ ነው



#ተፈፀመ

ትረካውን ካጨራረሱ ውጭ እንዴት አያችሁት ??

ኮሜንት ??

ቀጣይ በሌላ ትረካ እስክንገናኝ መልካም ቆይታ ይሁንላችሁ

ከደራሲያን አለም ፔጅ
Firaw Kiya

ወዳጀ  #አታጉረምርም ፈጣሪህን ብቻ አመስግን >>>ፈተና ከገጠመህ ፀልይ እንጂ አታጉርምርም ፈጣሪ ሁሌም ታላቅ ነውና>>> ትልቅ አምላክ እንጅ ትልቅ እሚባል ችግር የለም።     "የምታመልከው...
15/09/2025

ወዳጀ #አታጉረምርም ፈጣሪህን ብቻ አመስግን

>>>ፈተና ከገጠመህ ፀልይ እንጂ አታጉርምርም ፈጣሪ ሁሌም ታላቅ ነውና

>>> ትልቅ አምላክ እንጅ ትልቅ እሚባል ችግር የለም።

"የምታመልከው አምላክ በነገሮች ሁሉ ላይ የበላይ እንደሆነ "አትዘንጋ።

🟣 ወዳጄ ሆይ ለህሊናህ እርፍት ለልብህ ደስታን ከፈለክ ሁልጊዜ መልካም ሰው ሁን መልካምነት ለራስ ነው።
" በልባችን መልካምነት ካለ እንኳን የተርፈን ያለችንን እንካፈላታለን"

🟣 ሁሌም ጥሩ ነገር እናድርግ ምክንያቱም ከክፋት ደግነት ትልቅ ዋጋ አለውና።

🚹 ደግነት አንድ ቀን መልሶ ይከፍላል መልካምነት ለራስ ነውና
🚺 መልካም ሰው መልካም ሂወትን ያገኛል
🚹 መልካም ወንድ መልካም ሚስትን ያገኛል
🚺 መልካም ሴት መልካም ባልን ታገኛለች
🚹 መልካም ሰው መልካም ልጆችን ያገኛል
🚺 መልካም ሰው ደስታን ያገኛል
🚹 መልካም ሰው ሰላምን ያገኛል
🚺 መልካም ሰው ፍቅርን ያውቃል
🚹 መልካም ሰው መልካም ነገርን ያገኛል
🚺
" ታዲያ " #መልካም ሰው መሆንን የማይፈልግ ማነው??
#ፈጣሪ መልካም ሰው እንድንሆን ይርዳን። አሜን

ከዚህ ቀጥሎ ውርስ የመጨረሻው ክፍል #ትረካ ይቀጥላል
ከደራሲያን አለም ፔጅ

ወዳጅ  #አታጉረምርም ፈጣሪህን ብቻ አመስግን >>>ፈተና ከገጠመህ ፀልይ እንጂ አታጉርምርም ፈጣሪ ሁሌም ታላቅ ነውና>>> ትልቅ አምላክ እንጅ ትልቅ እሚባል ችግር የለም።     "የምታመልከው...
15/09/2025

ወዳጅ #አታጉረምርም ፈጣሪህን ብቻ አመስግን

>>>ፈተና ከገጠመህ ፀልይ እንጂ አታጉርምርም ፈጣሪ ሁሌም ታላቅ ነውና

>>> ትልቅ አምላክ እንጅ ትልቅ እሚባል ችግር የለም።

"የምታመልከው አምላክ በነገሮች ሁሉ ላይ የበላይ እንደሆነ "አትዘንጋ።

🟣 ወዳጄ ሆይ ለህሊናህ እርፍት ለልብህ ደስታን ከፈለክ ሁልጊዜ መልካም ሰው ሁን መልካምነት ለራስ ነው።
" በልባችን መልካምነት ካለ እንኳን የተርፈን ያለችንን እንካፈላታለን"

🟣 ሁሌም ጥሩ ነገር እናድርግ ምክንያቱም ከክፋት ደግነት ትልቅ ዋጋ አለውና።

🚹 ደግነት አንድ ቀን መልሶ ይከፍላል መልካምነት ለራስ ነውና
🚺 መልካም ሰው መልካም ሂወትን ያገኛል
🚹 መልካም ወንድ መልካም ሚስትን ያገኛል
🚺 መልካም ሴት መልካም ባልን ታገኛለች
🚹 መልካም ሰው መልካም ልጆችን ያገኛል
🚺 መልካም ሰው ደስታን ያገኛል
🚹 መልካም ሰው ሰላምን ያገኛል
🚺 መልካም ሰው ፍቅርን ያውቃል
🚹 መልካም ሰው መልካም ነገርን ያገኛል
🚺
" ታዲያ " #መልካም ሰው መሆንን የማይፈልግ ማነው??
#ፈጣሪ መልካም ሰው እንድንሆን ይርዳን። አሜን

ከዚህ ቀጥሎ ውርስ የመጨረሻው #ትረካ ይቀጥላል
ከደራሲያን አለም ፔጅ

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ከደራሲያን አለም ፔጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share