ነጋሪት ሚዲያ

  • Home
  • ነጋሪት ሚዲያ

ነጋሪት ሚዲያ news & media web

24/06/2025

ሼር

22/06/2025

ሰኔ 15 Black day

21/06/2025

አርበኛ ሳሙኤል ባለዕድል

አንድ አማራ አንድ ዓላማ፦

የአማራ ብሔርተኝነት እና አማራነት አንድ የመዳኛ መንገዳች ነው።በቁጥር ብዙ አማራዎች ቢኖሩም አማራነት ግን አንድ ነው።
ለየትኛውም አማራ በአማራነት እና በአማራ ብሔርተኝነት ሥር አንድ ወንድም ነው።
ከየትኛውም አማራ ለአማራው ሌላው ከቀረበው ግን ወይም ይቀርበኛል ብሎ ካሰበ ግን ባንዳነት በደሙ በውስጡ አለ ማለት ነው።
1983 ዓ.ም. አማራ ነን በሚሉ ፀረ አማራወች ተወክለን ትግሉን አሳልፈን ሰጥተን ህዝባችን የመከራ ማዕበል ሲወርድበት 27 ዓመት አለፈ።
2008 ዓ.ም. ጀምሮ በነበረው የሥርዓት ለውጥ እንቅስቃሴም እዛው ውስጥ ያሉ የሥርዓቱን አገልጋዮች የአማራ ተወካይ አድርገን ትግላችን አሽጠን ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተዳረግን።

ትግሉም የስርዓት ለውጥ ሳይሆን የመንግሥት ለውጥ ብቻ ሆነና አሁንን ወለደ።በዚህ መንገድ ሥጋ ለብሶ የመጣው የአሁኑ የአማራ መከራ እጅግ የከፋ መሆኑ ለማንም የተሠወረ አይደለም።
አሁንስ ለስንተኛ ጊዜ ትግል አሳልፈን ሰጥተን ሕዝባችን ለስቃይ እንድንዳርገው ተብሎ ይሆን አማራን ወዲያና ወዲህ አሰልፈን ጠላትን ሳይሆን ትግሉን ለመክፈል እየተሠራ ያለው?
የግላዊ እሳቤ መሪወች ፍላጎት በሚድያ ተደግፎና ተጀቡኖ ወደታጋዩ እና ወደሕዝቡ እንዳይጋባ በጣም እሠጋለሁ።

በትግሉ ሜዳ ያለውም ሆነ በጽኑ ደጋፊነት ያለው የትኛውም አማራ እገሌ የተባለ የሰፈሬ አለቃ ምን ይፈልጋል? ሳይሆን ትግሉ ምን ይፈልጋል? ብሎ የማሰብ አቅም ላይ ካልደረሰና ጆሮ ያገኘ ተናጋሪ የሚወዛውዘው ከሆነ የትግሉ መርገምት ነው።
አማራን ካለበት የህልውና ሥጋት ከፍ የሚደርገው አሻጋሪ ሀሳብ እንጅ ጭብጨባ ብቻ አይደለም።
ማንኛውም አማራ ለአማራ ያስፈልገዋል።በመርህ ላይ ቁመን የትግል መዳረሻችንን ስናስብ ሰው ከሰው የተለየ አይደለም።
ሁሉም አማራ ቁርጥ ሀላፊነት ከተሰማው ስለሚናገረውም ስለሚፀፈውም ከተጠነቀቀ ለምድ የለበሱ ፀረአማሮችን መለየት ይከብዳል የሚል እምነት የለኝም።
የትኛውንም ፅሑፍም ሆነ ንግግር ስንመለከት ከዚህ ሀሳብ የሚያተርፈዉ ማነው? አማራው? ወይስ ለፀረ አማራው? የሚል ማንጠሪያ መመዘኛን ማስቀመጥ ካልቻልን የጠላቶቻችን አጃቢወች ሁነን እራሳችን ለማስገደል መሳሪያ አቃባይ መሆናችን አይቀሬ ነው።
ከዚህ በፊትም እንደ ገለጽነው አማራው አንድ ግልፅ የመዳኛ መንገድ አለው።
አማራው ሥሁት በሮችን ለይቶ እሱም እንደአማራ በእንድነት ቆሞ የሥርዓት ለውጥ ማምጣት ሲችል ብቻ ነው።
አማራን እንደ አማራ ሊያኖር ለሚችል ለሥር ነቀል የሥርዓት ለውጥ ትግል እንጂ ለጥገናዊ ለውጥ አልወጣንም።
የሥርዓት ለውጡን ማምጣት የሚቻለውም ፀረ አማራነትን እና አማራ ጠልነትን የሕይወትም የትግልም መርህ አድርገው ከሚሠሩ አካላት ጋር አብሮ በመቆም ሳይሆን ለስልጣንም ለጥቅምም ሳይስገበገቡ እራስን ወጣሁለት ለምንለው ዓላማም ሆነ ህዝብ አሳልፈን በመስጠትና ከሁሉም አማራነትን በውል ከተረዱ የአማራ ታጋዮች ጋር በአንድነት፤ አማራ ጠል ካልሆኑ ሥርዓቱን ከሚታገሉ ከሁሉም የኢትዮጵያ ኃይሎች ጋር በኅብረት በመሥራት ነው ብየ አምናለሁ።

በተለይ ማኅበራዊ ሚድያ ላይ ትግሉን በተመለከተ የምትሠሩ ወገኖች ሀገር፣ፍትህ፣ለውጥ ብሎ የተነሣውን ኃይል በፉክክር ስሜት መንደርና ጎጥ ላይ ለመቸንከር ባለማወቅም በተሰላ መንገድም የምትሔዱበትን ጥበትን የማላመድ ተግባር ብታቆሙ መልካም ነው።
የጎንደር አማራ አለ፤የወሎ አማራ አለ፤የሸዋም የጎጃምም አማራ አለ፤ እነኝህ መጠርያ የክፍለሀገር ስያሜወች እንጅ ማንነት አይደሉም።
ማንነታችን አማራነታችን መታገያችን አማራዊ ብሔርተኝነታችን ነውና።
ሀገር ብለን ወጥተ

20/06/2025

ሰበር መረጃ - ወልቃይት

ህወሀት በብልፅግና አጋዥነትና መንገድ ጠራጊነት ወልቃይትን ዳግም ለመዉረር ዝግጅቷን ጨርሷ ጦሯን ወደ ተከዜ አስጠግታለች።

18/06/2025

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ወሎ ቤተ-አማራ ቀጠና የተሰጠ መግለጫ!

የአማራ ሕዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ እንደ ሰው በሕይወት የመኖር አደጋ የደቀነበትን ኦህዴድ ብልጽግና መሩን አገዛዝ ለመገርሰስ የሞት የሽረት ትግል እያደረገ ይገኛል፤ በዚህ በጦርነቱ፤ በአውደ ውጊያ፣ በፖለቲካ፣ በሚዲያ እና በዲፕሎማሲ እንዲንኮታኮት የማድረግ አመርቂ ሥራ ተሰርቷል፤ እየተሰራም ይገኛል።

በአውደ ውጊያ፣ በፖለቲካ፣ በሚዲያ እና በዲፕሎማሲ የሽንፈት ጽዋ የተከናነበው የብልጽግና አገዛዝ የአማራ ሕዝብን የከዱና ከትግል ሜዳ የራቁ ፋኖ መሳዮችን በመሰብሰብ ባይሳካለትም ከላይ በጠቀስናቸው መንገድ ማሸነፍ ያቃተውን የፋኖን ኃይል "ፋኖን ከሕዝብ መነጠል፤ በመቀጠል ደምስሶ ማጥፋት" በሚል ስትራቴጅ ነድፎ ከዘረፈው የሃገርና የህዝብ ሃብት ከፍተኛ በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ስንገልፀው የነበረ እውነት ነው።

ከሰሞኑም በመቀሌ ሰማዕታት ሀውልት ስር "የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር አባል" በሚል የተለቀቀውን ምስል እኛ ተመልክተናል። እነዚህ ልጆች በመጀመሪያ አሁን ላይ የዚህ የገለጹት አባል አለመሆናቸውንና ትግል ክደው ከወጡ አንድ አመት በላይ እንደሆናቸው እየገለጽን፤ አገዛዙ በተለይ በጌታቸው ረዳ አማካኝነት በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርቦ ማሳካት ያልቻለውን ፕሮፓጋንዳ ትግል ከድተው ወደ አገዛዙ የገቡትን ልጆች በመሰብሰብ ተከታታይነት ያለው ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን መግለጽ እንፈልጋለን።

ለሕዝባችን ማስተላለፍ የምንፈልገው ነገር አገዛዙ በሁሉም ግንባሮች የሽንፈት ጽዋ እየቀመሠ መሆኑን ተረድታችሁ ይሄን የደረሰበትን ሽንፈት በፕሮፓጋንዳ ለመቀልበስ እየተራወጠ መሆኑን በመገንዘብ፤ በቀጣይ መሠል ፕሮፓጋንዳዎችን ሊሰራ እንደሚችል ማስታወስ እንፈልጋለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ሰኔ 11/2017 ዓ.ም

17/06/2025

ሰበር ዜና!

ጀኔራል አያና ቱራ ላይመለስ ተሸኘ
በጎንደር ጎርጎራ በተከሰከሰችው ሄሊኮፍተር ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዶ ለህክምና ወደ ጦር ሀይሎች ሆስፒታል ተወስዶ ለማትረፍ እርብርብ ቢያደርጉም እስትንፋሱን ማስቀጠል ባለመቻላቸው አገዛዙ ቤት እለቅሶውና ዋይታው ደርቷል።

የአገዛዙ ደንገጡር አሽከር እና ሎሌ ሁኖ የአማራን ህዝብ ሲጨፈጭፍና ሲያስጨፈጭፍ ፣ ስቃይ እና መከራ፣ ሲያደርስ ኑሮ አሁን ላይ የግፍ ፅዋው ሞልቶ በመፍሰሱ ጀኔራል አያና ቱራ በርግጠኝነት ከአሁን በኃላ ህዝባችን ላይ መከራና ስቃይ አያደርስም ምክንያቱም ምሽቱን አፈር በልቷል። ጀኔራል ተብየው ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ እስካሁን ድረስ የመንግስት ቀኝ እጅና ተላላኪ በመሆን የአገዛዙ ታማኝ ተብሎ ቤተመንግስት ባሉ ሰዎች የሚታመን ሌባና ዘራፊ ጭምርም ነበር ።

በሄሊኮፕተር አደጋው ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ካሜራ ባለሙያ አቶ ብዙአየሁ ብርሃኑ መሞቱን የመንግስት ሚዲያዎች የዘገቡ ቢሆንም የሌሎች ሙትና ቁስለኞች ፖለቲካው ላይ ከፍተኛ ስብራትና ውርደት ስለሚያመጡ በከፍተኛ ሚስጢር እንዲያዙ ትዛዝ የወረደ ቢሆንም ከፋኖ መረጃ ክፍላችን ማምለጥ ባለመቻላቸው የተነሳ የጀኔራል አያና ቱራ ሞትን ነፃነት ፈላጊው ህዝባችን በኩራት እናበስራለን ።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ጎንደር ቀጠና ዳግማዊ ቴዎድሮስ (5ኛ) ኮር የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ )

15/06/2025

! አፉብሐ
ጎርጎራ የጀግኖቹ ጎራ💪💪💪
በጎንደር ጎርጎራ በፋኖ በትር ተመትቶ ሄሊኮፍተር ወድቋል!!

14/06/2025

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ወሎ ቀጠና የልጅ እያሱ ኮር ጥልቅና መሠረታዊ የስራ ግምገማ አደረገ፡፡

አፋብኃ በወሎ ቀጠና የልጅ እያሱ ኮር ከ 06/10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ባደረገው የኮር አመራር የስራ ግምገማ የነበሩትን ችግሮች በመቅረፍ በአዲስ አስተሳሰብ እና በአዲስ የትግል ወኔ ኮሩን ወደ ተሻለ የትግል ምዕራፍ ለማሸጋገር ጥልቅ ግምገማ በማድረግ እና የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ እንዲሁም ቃል በመገባባት ግምገማው ተጠናቋል።

ይህን የስራ የግምገማ ሂደት በበላይነት የመሩት የአማራ ፋኖ በወሎ ቤተ አምሓራ የዘመቻ መምሪያ ኃላፊው አርበኛ በለጠ ሽጋው ሲሆኑ ግምገማው ጠንከር ያለ እና እያንድ አንዱ የኮር አመራር ያለበትን ችግር ነቅሶ በመነጋገር ድክመታቸውን እንዲያርሙ እና ጥንካሬያቸውን እንድያስቀጥሉ ከቤቱም ከመድረክ መሪዎችም አቅጣጫ የተሰጠ ሲሆን ይህን የተሰጠ አቅጣጫ በአግባቡ ለማይወጡ የኮሩ አመራሮች ድርጅቱ ባወረደው የስነ ምግባር ደንብ መመሪያ መሠረት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ስብሰባውን ሲመሩት የነበሩት የድርጅቱ የዘመቻ መምሪያ ሀላፊ አርበኛ በለጠ ሸጋው ጠንከር ያለ ትዕዛዝ እና አቅጣጫ ሠጥተዋል።

በተለይ ትግሉን ለመጥለፍ የመንግስትን ተልዕኮ ለማስፈፀም የተሰገሰጉ ሰርጎ ገቦችን በመመንጠር የማያዳግም እርምጃ መውሰድ አማራጭ የሌለው ቁልፍ መፍትሄ መሆኑን ቤቱም ከመድረክ ላይ የነበሩ የድርጅቱ አመራሮች በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል።

በመድረክ ሲንሸራሸሩ የነበሩ ጥልቅ ሃሳቦች ድርጅቱ ብሎም ኮሩ ላይ ያሉ ስትራቴጂክ አመራራሮች የሀሳብ ድህነት የሌለባቸው የትግሉን ሁኔታ በአግባቡ የተረዱ እና ቁጭ ብሎ በመነጋገር ችግሮችን ከመፍታት አንፃር ጥልቅ የሆነ የፖለቲካ እይታ ያላቸው መሪዎች እንዳሉ የታየበት እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ጠቁመዋል፡፡

ይሁንና የነበረው መድረክ የተከሰቱ ችግሮችን ትኩረት በመስጠት በምንም አይነት ሁኔታ አለባብሶ መሄድ በድርጅቱ ቦታ የሌለው መሆኑን እና የተጀመረው የፋኖ የትግል መስመር እምርታው በውትድርናው እና ነፍጥ ባነገበው ኀይል ላይ ህልውናውን ተስፋ ያደረገ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካው እና በመድረክ አያያዝም ጭምር ከፍተኛ ለውጥን ያሳየ መድረክ ነበር።

መድረኩ ሲጠናቀቅም የልጅ እያሱ ኮር ከፍተኛ አመራሮች እና የአማራ ፋኖ በወሎ ቤተ-አማሓራ አመራሮች በአንድ ላይ በመሆን የተጀመረውን የህልውና ትግል በማጠናከር የብልፅግናን ሰው በላ ስርዓት ፀሐይ ሙሉ በሙሉ እንዲጠልቅበት የማድረግ ሀላፊነታቸውን አጠናክረው እንደሚፈፅሙ በአንድ ድምፅ ተማምለው ተስማምተዋል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ወሎ ቀጠና የልጅ እያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ሰኔ 7/2017 ዓ.ም

13/06/2025

ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!!

//

የምንከፍለው ውድ የሕይወት መስዋዕትነት ትግላችንን ይበልጥ የሚያጠናክረው ነው!!

//

ሰኔ 6፣ 2017 ዓ.ም.።

//

በሰሜን ወሎ ዞን፣ በዋድላ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ ቆማ በተባለ ቦታ የአማራ ፋኖ ወሎ ቤተአምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ፣ በሰኔ 5 ቀን፣ 2017 ዓ.ም እስከ አፍንጫው ከታጠቀ የአገዛዙ ጥምር እግረኛ ጦር ጋር ባደረገው ከባድ ውጊያ በጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ አድርሷል።

በአውደ ውጊያው በርካታ አምቡላንሶች የጠላትን ቁስለኛ እና አስከሬን ወደ ጋሸና ከተማ እና በአካባቢው ወደሚገኙ የጤና ተቋማት ያሸሹ ቢሆንም፣ አስከሬናቸው ያልተነሳ የመከላከያ እና የአድማ በታኝ አባላትን ህዝቡ በሚታወቀው ጨዋነቱ ቀብሯቸዋል።

ከሟቾች መታወቂያ መረዳት እንደተቻለው፣ ከተደመሰሱት መካከል የሻለቃ ማዕረግ ያላቸው እና የአገዛዙ መስመራዊ መኮንኖች እንዳሉበት ተረጋግጧል።

በዚህ አወደ ውጊያ፣ ከወገን በኩል እንደወትሮው ሁሉ ለአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል የሰማዕትነት ፅዋ የተከፈለ ሲሆን፡-

1. አርበኛ ደምስ ይመር፣
2. አርበኛ ኮራ ደርቤ እና
3. አርበኛ ጌታቸው አሻግሬ

ለሕዝባቸው፣ ለዓላማቸው እና ለድርጅታቸው በክብርና በጀግንነት ተሰውተዋል።

የእነዚህ ውድ አርበኞች መስዋዕትነት የተነሳንለትን የህልውና ትግል ይበልጥ አጠናክረን እንድንቀጥል የትግል ስንቅ እና አደራ ይሆነናል።

የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግሉን በፋኖ አደረጃጀት በባዶ እጁ አስጀምሮ አሁን ያለበት ከፍታ ላይ ያደረሰው በርካታ ጠምዝማዛ መንገዶችን እያለፈ ነው፡፡ በዚህ ጉዞው ከውጭ ብቻ ሳይሆን ከውስጥም በእሳት እየተፈተነ፤ አያሌ የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ነው።

ይህ ሁሉ የመጨረሻውን የነጻነት ፍሬ ይበልጥ የሚያጣፍጠው እንጂ፣ አገዛዙ እንደሚመኘው ትግሉን ወደኋላ የሚጎትተው አይደለም።

ፋኖ ሕዝብ ነውና ማንም ሊያሸንፈው ስለማይችል፣ ትግላችን ከመቼውም ግዜ በላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ ለድልም ይበቃል።

ሁሌም መሃሪ የሆነው ፈጣሪ፣ የሰማዕታቱን የአርበኛ ደምስ ይመር፣ የአርበኛ ኮራ ደርቤ እና የአርበኛ ጌታቸው አሻግሬ ነፍስ በአፀደ ገነት እንዲያኖርልን እና ወዳጅ ዘመዶቻቸውን እንዲያፅናናልን እንመኛለን።

ክብር ለሰማዕታት !!

ድል ለአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት !!

ድል ለአማራ ሕዝብ !!

ድል ለኢትዮጰያ ሕዝብ !!

ሰኔ 6 2017 ዓ. ም።

11/06/2025

የግዳጁ ሰልፍና የባህርዳር ህዝብ

የብልጽግናው አገዛዝ የባህርዳርን ህዝብ “ፋኖን አውግዙ” በሚል በግዳጅ ሰልፍ እያሰናዳ ነው

የአብይ አህመድ አገዛዝ የአማራን ህዝብ ከፋኖ በተቃራኒው ለማሰለፍ በርካታ ዶክመንተሪዎችን ሰርቷል ፣ ሰልፎችን አዘጋጅቷል ፣ በፋኖ ስም ዘራፊዎችን አሰማርቷል፡፡
ሆኖም የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆቹንና የህልውና ታጋዮቹን ጠንቅቆ ስለሚረዳ በየአቅጣጫው ከልጆቹ ጎን ተሰልፎ ዘልቋል፡፡
ታዲያ ብልጽግና አሁንም በዚህ የማስገደድ ተግባሩ ቀጥሎ በክልሉ መቀመጫ ባህርዳር ከተማ ህዝቡ ፋኖን አውግዞ ሰልፍ እንዲወጣ በሆድ አደር ካድሬዎቹ በኩል እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡
ያረጀ እና ያፈጀ የሀሰት ዶክመንታሪ እና ዘገባ በመስራት አልሳካለት ያለው የብልፅግና አገዛዝ አሁንም በባህርዳር ከተማ ህዝቡን ለተቃውሞ ሰልፍ በማስገደድ በየቀበሌው የኮታ ድልድል መስጠቱን እና ከተለያዩ ቦታወች የሐይማኖት አባቶችን አስገድዶ ማስመጣቱን መረጃዎች ደርሰውናል፡፡
ፋኖን ለማውገዝ የሃይማኖት አባቶችን ከፊት ለማስቀደም የሚጥረው ይህ አገዛዝ ከምንም በላይ ደግሞ እምነትን እያጠፋ ፣ የእምነት ተቋማትን እያወደመ ያለ ስርዓት እንደሆነ ይታወቃል።
ነገር ግን የሐይማኖት አባቶችን እና የተለያዩ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን ነጠላ በማልበስ ቤተክርስቲያን ፋኖን አወገዘች ለማለት እንደሆነ ተደርሶበታል፡፡
ስለዚህም በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸምኩት ያለውን የዘር ማጥፋት ለመደበቅ የደግፉኝ ሲል ሰልፍ ተጠርቷል ።
“በመሆኑም በዚህ ሰልፍ ላይ የምትገኙ የምታስተባብሩ ለአማራ ነፃነት ሲባል በዱር በገደሉ በተሰውት ጎዶቻችን ደም እና አጥንት ላይ እንደመቀለድ ስለሆነ በዚህ ቀን ለሚደርሱ ማንኛውም አይነት ጉዳቶች ፋኖ ሀላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን እያሳወቅን ሁሉም ሰው ባለመገኘት የትግሉ ተባባሪ እንዲሆን” ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል የአንደኛ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ሃብታሙ የሱፍ ገልጿል፡፡
በአውደ ውጊያ መረጃ ደግሞ ጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክፍለጦር የአብይ አህመድን ወታደር እንደቅጠል አርግፎታል ሲል ክፍለጦሩ አሳውቋል፡፡
ትናንት ሰከላ ግሽ አባይ ከተማ ድንጋይ ገበጣ እና ሳንግብ ቤተክርስቲያን መሸጎ የነበረው ሀይል ላይ አፋብኃ ጎጃም ቀጠና ጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክፍለ ጦር ግዮን ብርጌድ ከንጋቱ 11:00 ላይ መብረቃዊ ጥቃት ሰንዝረውበታል።
በዚህ አውደ ውጊያ ሰከላ ግሽ አባይ ከተማ ሳንግብ ቀበሌ ላይ 3 የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ ድንጋይ ገበጣ ላይ ደግሞ 4ቱ ተገድለዋል፡፡
እንዲሁም የበላይ ዘለቀ 8ኛ ክፍለጦር በትናንትናው እለት በሸበል በረንታ ወረዳ የዕዱኃ ከተማ መሽጎ የሚገኘው የአገዛዙ ሀይል ወረጎና አካባቢ ሲንቀሳቀስ በፋኖ ተመትቶ ፓትሮሉ ከጥቅም ውጭ ሆኖበታል፡፡ 5 የአገዛዙ ወታደር ሲገደል 8 የሚሆነው ደግሞ ቆስሏል፡፡
በሌላ መረጃ ትናንት ሰኔ 3/2017 ዓ.ም አንድ መቶ መሪ የመከላከያ አባል የነበረ ከኮርክ ከተማ እና ሁለት ምሊሻዎች ከየላምገጂ ከተማ በመውጣት የአፋብኃ በጎጃም ቀጠና የሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክፍለ ጦር የአብራጂት ብርጌድን ተቀላቅለዋል።
በተመሳሳይ አሥርአለቃ አዲሴ ቸሬ እና ሃምሳአለቃ ታደሰ የተባሉ የአገዛዙ ወታደራዊ አመራሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው አባሎቻቸውን እንደያዙ አፋብኃ በጎጃም ቀጠና 1ኛ ክ/ጦር ስር የሚገኘውን ኮረኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድን ተቀላቅለዋል፡፡

04/06/2025

✊✊🔥🔥🔥
ጎንደር ከተማ ከንጋት ጀምሮ አፋብኃ ጎንደር ቀጠና ፭ ኮር ከፍተኛ ው*ጊያ እየተደረገ ይገኛል በኤርፖርት ፣ በጠዳ በተለያዮ አቅጣጫ ፋኖ ወደ ከተማ እየገባ ነው

ጎንደር ከተማ ዙሪያ ማክሰኝት ከተማ በፋኖ እጅ ገብታለች 70 የግፍ እስረኞች ነፃ ወተዋል

አዲስ ዘመን ጠ*ላት እየተለበለበ ነው

✊✊✊✊

03/06/2025

እስክንድርና መከታው ፋኖዎችን ማጋዳደላቸውን ቀጥለውበታል #ፋኖ #ዜና

ልብን የሚሰብር አሳዛኝ ነገር ሰማሁ:: የነእስክድር ጦር ከፍተኛ ሃይል አሰባስበው በከሰም ክፍለ ጦር ላይብ ውጊያ ለመክፈት ሃይላቸውን አቅርበዋል:: ምን አልባትም በሰአታት ውስጥ ክፍተኛ ውጊያ ሊቀሰቀስ ይችላል::

አገዛዙ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በከሰም የመከላከያ ሙሉ ኮር አሰማርቶ ነበር ሲዋጋ የነበረው:: የከሰም ክፍለ ጦር ፋኖዎችም በጀግንነት በአገዛዙ ጦር ላይ ብዙ ኪሳራ አድርሰዋል::

ቀላል ውጊያ አልነበረም ሲያደርጉ የነበሩት:: የከሰም ክፍለ ጦር ተዳክሟል: ጥይት ጨርሰዋል በሚል ከሰምን በነርሱ ስር በሃይል ለማድረግ ነው እነመከታው ማሞ የተንቀሳቀሱት::

ይሄንንም ለማዘናጋት: ትክረት ለማስቀየር ቀድም ሲል በደብረ ብርሃን እካባቢ: የተደረገ የድሮን ጥቃትን ተከትሎ: የአማራ ፋኖ ፋኖ በሸዋ ፋኖዌች ላይ ጉዳት ሲደርስ: ድንገተኛ ጥቃት አድርገው ያፈኗቸውን የአፋብሃ የሸዋ ቀጠና የተወሰኑ አመራሮች: አስገድደው አስተያየት እንዲሰጡ አድርገዋቸዋል:: ልክ ጋሽ ተስፋዬ መካሻን እንዳደረጉ:: ወያኔዎች: ብልፅግናዎች አስገድደው ያሰሯቸውን በቴሌቭዥን ያቀርቡ እንደነበረው:

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ነጋሪት ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share