Halaba media network

Halaba media network public page

ዛሬ ስራ የጀመረው የመሶብ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ አገልግሎት፣ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማህበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው። ለአገልግሎት የተደራጀው አ...
22/04/2026

ዛሬ ስራ የጀመረው የመሶብ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ አገልግሎት፣ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማህበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው። ለአገልግሎት የተደራጀው አውቶቡስ ሙሉ ቁሳቁስ የተሟላለትና ራሱን የቻለ የአገልግሎት ማዕከል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ቀልጣፋና አስተማማኝ አሰራርን ለማረጋገጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና ስርዓቶችን አቀናጅቶ የያዘ ነው።

‎አውቶቡሱ የአገልግሎት ፍሰቱን የሚያደራጅ የሰልፍ ማስተናገጃ ስርዓት ያለው ሲሆን፣ የተለያዩ የክፍያ አማራጮችንም አካቷል። ለአገልግሎቱ የሚያስፈልገውን ኃይል በከፊል ከ8 ኪሎ ዋት የፀሐይ ብርሃን የሚያገኝ ሲሆን፤ አስተማማኝ ኢንተርኔትም ተገጥሞለታል።

‎ በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጡን ደህንነትና ግልፅነትን ለመከታተል ካሜራዎች ተገጥመውለታል። መፍትሔ አምጪ ሆኖ የተዘጋጀው የፈጠራ ውጤትና ተንቀሳቃሽ ክፍል፤ ከስምንት የተለያዩ የመንግስት ተቋማት የሚገኙ የሚከተሉትን ወሳኝ አገልግሎቶች ይሰጣል፦

‎• አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) መስጠት
‎• የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ማደስ
‎• ለመንጃ ፈቃድ የሚያስፈልግ የህክምና ምርመራ ማድረግ
‎• የነዋሪነት መታወቂያ ማደስና የልደት ምዝገባ
‎• የመንጃ ፈቃድ መስጠትና የተሽከርካሪ ታርጋ ማደስ
‎• የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የመንገድ ፈንድ ክፍያን ማከናወን
‎• የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባና የመረጃ እርማት
‎• በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የሚሰጥ የቅድመ ክፍያ የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን ይሰጣል።

‎በአጠቃላይ ይህ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ የስምንት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ላይ በማቀናጀት፣ ዜጎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ወይም የተለያዩ ቢሮዎችን ማንኳኳት ሳያስፈልጋቸው ምቹ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ መፍትሄ ይሰጣል።

"ፍትህ ለአክሱም ሙስሊሞች""የሙስሊሞች ጉዳይ ያላሳሰበው ከእኛ አይደለም" ረሱል (ሰ ዐ ወ)የአክሱም ሙስሊም ማህበረሰብ እንደተለመደው ሃይማኖታዊ ግዴታው ዛሬ የጁምአ ሰላት ይሰግዳል። የመንግ...
21/04/2026

"ፍትህ ለአክሱም ሙስሊሞች"
"የሙስሊሞች ጉዳይ ያላሳሰበው ከእኛ አይደለም" ረሱል (ሰ ዐ ወ)
የአክሱም ሙስሊም ማህበረሰብ እንደተለመደው ሃይማኖታዊ ግዴታው ዛሬ የጁምአ ሰላት ይሰግዳል።

የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ኢሰብአዊ ከሆኑ የከተማ ወንበዴዎችና ጽንፈኞች ጥቃት ሊከላከሉት ይገባል!

የጀግና አቀባበል ቀኑ እየደረሰ ነው! ዝግጁ🏆 ይዘን ድርብ ድል
21/04/2026

የጀግና አቀባበል ቀኑ እየደረሰ ነው! ዝግጁ
🏆 ይዘን ድርብ ድል

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፊጥር በዓል በጤና እና በደስታ አደረሳችሁ! አደረሰን!! 🕋✨​ያለፈው የረመዳን ወር የሰላም፣ የዱዓ እና የፍቅር እንደነበረው ሁሉ፤ ይህም የኢድ በዓል በቤታችን...
20/03/2026

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፊጥር በዓል በጤና እና በደስታ አደረሳችሁ! አደረሰን!! 🕋✨
​ያለፈው የረመዳን ወር የሰላም፣ የዱዓ እና የፍቅር እንደነበረው ሁሉ፤ ይህም የኢድ በዓል በቤታችን እጥፍ ድርብ ደስታን፣ በልባችን ደግሞ የማይጠፋ የኢማን ኑር ይሙላው። 🤲 ሰላሙንና ፍቅሩን ይለግሰን።
​አላህ ጾማችንን፣ ሶላታችንንና ዱዓችንን ተቀብሎ ለሚቀጥለው ዓመትም በሰላም ያድርሰን። 🌼✨
​ኢድ ሙባረክ! 🎉🌙

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፊጥር በዓል በጤና እና በደስታ አደረሳችሁ! አደረሰን!! 🕋✨

​ያለፈው የረመዳን ወር የሰላም፣ የዱዓ፣ የፍቅርና የኢባዳ እንደነበረው ሁሉ፤ ይህም የኢድ በዓል በቤታችን እጥፍ ድርብ ደስታን፣ በልባችን ደግሞ የማይጠፋ የኢማን ኑር ይሙላው። 🤲 አላህ ከልባችን ፍርሃቱን፣ ከቤታችን ደግሞ በረከቱን አይንፈገን፤ ሰላሙንና ፍቅሩን በሁላችንም ላይ ይለግሰን፣ከተራቡት ሳይሆን ከፆሙት ጋር የድርገን
🌙☪️
​አላህ ጾማችንን፣ ሶላታችንን፣ ዱዓችንንና መልካም ስራችንን ሁሉ ተቀብሎ ለሚቀጥለው ዓመትም በሰላም፣ በጤና እና በበጎ ስራ ያድርሰን። 🕌🤲

​ኢድ ሙባረክ! 🎉🌙

03/03/2026
ያ ረቢ.!!🤲 በዚህ ረመዳን ወንጀላቸው ሙሉ ለሙሉ ከተማረላቸው፣ ከእሳት ቅጣትም ነጃ ካወጣሃቸው ባሮችህ መድበን።🤲🤲አሚንንን🤲🤲🤲
03/03/2026

ያ ረቢ.!!🤲 በዚህ ረመዳን ወንጀላቸው ሙሉ ለሙሉ ከተማረላቸው፣ ከእሳት ቅጣትም ነጃ ካወጣሃቸው ባሮችህ መድበን።🤲🤲

አሚንንን🤲🤲🤲

The Halaba Sera Festival is now open, and we take great pleasure in extending an invitation to you from around the world...
09/01/2026

The Halaba Sera Festival is now open, and we take great pleasure in extending an invitation to you from around the world.🌍

"በራስ አቅም የተሰሩ ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች የሚመረቁበት የዘንድሮ የሀላባ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል ልዩ ነው" - ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴንታህሳስ 29/2018 "በራስ አቅም የተሰሩ ...
09/01/2026

"በራስ አቅም የተሰሩ ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች የሚመረቁበት የዘንድሮ የሀላባ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል ልዩ ነው" - ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን

ታህሳስ 29/2018 "በራስ አቅም የተሰሩ ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች የሚመረቁበት የዘንድሮ የሀላባ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል ልዩ ነው" ሲሉም የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን ገለጹ።

በዚህ ወቅትም የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን እንደገለጹት የሀላባ ብሄረሰብ የማንነት መገለጫ የሆነው የሴራ በዓል "ሴራ በዓለችን በህብር የመቻል አቅም ማሳያችን" በሚል መሪ ቃል የሚከበረው በዓል እንኳን ደረሳችሁ ብለዋል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሀላባ ህዝብ ተሳትፎ እየተገነባ የሚገኘው የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ የመጀመሪያ ፌዝ፣ በዞኑ ካፒታል በጀት የተገነባው የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት ህንጻ ግንባታና ሌሎች በከተማ የተሰሩ ትላልቅ ልማት ፕሮጀክቶች እንደሚመረቁ ገልጸዋል።

ሴራ ባህላችን በከበሩ ስናከብር የበለጣ አንድነታችንና አብሮነታችን በማጠናከር የዞናችንን አስተማማኝ የልማት፣ አንድነታችንና ሰላም ይበልጥ ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የሴራ በዓል በሀላባ ብሔረሰብ ዘንድሮ እጅግ የተለየ ስፍራ የለውና አሮጌውን ዓመት በመሸኘት አዲሱን ዓመት የምንቀበልበት አዲስ ዘመን አቆጣጠር (የዘመን መለወጫ) የሚጀምርበት እንደሆነ ተናግረዋል።

በሀላቢሳ አቆጣጠር የሀላባ ሴራ በዓል (መንገሳ) የአዲስ ዓመት ዘመን መለወጫ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በውስጡ በርካታ መልዕክቶችና ትርጉም መኖራቸውን ገልጸዋል።

ወቅቱ ግርዘኞች የግርዘት ስነ-ስርዓታቸውን አጠናቀው ከልጅነት ወደ ወጣትነት (ሀላፊነት) የሚሸጋገሩበት፣ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ለትዳር የሚተጫጩበት፣ 2 ጥንዶች ጋብቻ ስነ-ስርዓቶች ሰርጋቸውን የሚከናወኑበት እና የተጣለ የሚታረቅበት ወቅት መሆኑን ጠቁመዋል።

በተለይ መንገሳ በየዓመቱ በታህሳስ ወር የሚከሰት የሀላባ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ አርሶ አደሩ ለዓመት ያለፈበት አዝመራ ወደ የቤቱ የሚያስገባበት እና ቀድሞ ሰብስቦ ጨርሶ የእፎይታ ጊዜውን የሚያጣጥምበት እና ለሁለተኛ አመት ዝግጅት የሚያደርግበት ወር መሆኑን አቶ ሙህዲን ሁሴን ተናግረዋል።

የሀላባ ሴራ ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋና ስነ-ጥበባዊ እሴቶች አጉልቶ በማደራጀት ለቀጣይ ትውልድ በማስተላለፍ ማንነቱን ጠብቆና አክብሮ እንዲኖር ማስቻል እንደሚገባ ገልጸዋል።

የዘንድሮው የሀላባ ሴራ በዓል ከድሮም እየተከበረ የመጣ ነው ያሉት አቶ ሙህዲን ሁሴን።

የሀላባ ሴራ በዓል ነባርና ጠቃሚ ባህላዊ እሴቶችን ሳይበረዙ ባህሉን ጠብቆ በማንነቱ የሚኮራ፣ የሚያከብር፣ ለማንነቱ የሚቆረቆርና የሚጠብቅ እንዲሁም ባህሉ ለልማት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር፣ ባህሉን የሚወድና የሚያፈቅር የወጣቱ ዜጋ መፍጠር እንዳለበት ገልጸዋል።

ሴራ ባህላችን በህልና ትውፊትታችን ለዓለም የሚናሳይበት ዕለት በመሆኑ ዘንድሮ አመት እንደዞናችን ከወትሮ በተለየ መልኩ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቅን እንገኛለን ሲሉም ተናግረዋል።

ሴራ የሀላባ ማኅበረሰብ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቹን ጠብቆ የማቆየቱ ምስጢር፣ ተከባብሮና ተደጋግፎ የመኖር ባህሉ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ ጥንካሬና ተምሳሌትነቱ ሁሉ የሚገለጽበት ነው ብለዋል።

የበዓሉ አከባበር ወጣቱ ማሕበረሰብ ከአያት ቅድመ-አያቶቹ የወረሰውን የማንነት ዕሴቱን ጠብቆ እንዲያስቀጥል ትልቅ ሚና እንዳለውም ጠቁመዋል።

የዘንድሮው የሀላባ ሴራ በዓል በሀገር ውስጥ በአዲስ አበባና በክልላችን ፖለቲካ አስተዳደር መቀመጫ በሆሳዕና ከተማ፣ እና ከሀገር ውጭ በዱባይ፤ በአሜሪካ፣ በደቡብ አፍሪካ ከወትሮው በተለያ መልኩ በከበሩን ጠቁመዋል።

በዞን ደረጃ በሚከበረው ሴራ በዓል ከሀገር ውጪ በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያ፣ በሀገርው ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የክብር እንግዶችና የሀገር መሪዎች በበዓሉ እንደሚታደም ገልጸዋል።

ለመላው በሀገር ውስጥና ውጪ ለሚገኙ የብሄረሰቡ ተወላጆችና ወዳጆች ለበዓሉ እንኳን አደረሳችሁ ሲሉም ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሀላባ ዞን ኮሚኒኬሽን

ጥር 3 ቀን የሀላባ ዘመን መለወጫ 'ሴራ' በዓል የሚከበርባት የሀላባ ቁሊቶ ከተማ የምሽት ገጽታ (በምሥል) :-
09/01/2026

ጥር 3 ቀን የሀላባ ዘመን መለወጫ 'ሴራ' በዓል የሚከበርባት የሀላባ ቁሊቶ ከተማ የምሽት ገጽታ (በምሥል) :-

09/01/2026
09/01/2026

Address

Cape Town
TVCHANNEL

Telephone

+27680000576

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Halaba media network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category