21/04/2022
ኢኬ መረጃ ኢትዮጵያ
ያልታደለች ሐገር
የደቡብ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ተፈሪ አባተ ፦
" በሳውላ በውሃ ሃብት ልማት ፅ/ ቤት ውስጥ የውሃ ተቋም ግንባታ እንዲደረግ ከክልሉ የተላከውን ሃብት በመውሰድ የፕሮጀክት ማናጀር/ የውሃ ፕሮጀክት ፅ/ቤቱ ኃላፊ የራሱን ቤተሰብ ባለቤቱንና ሌሎች አካላት በማህበር እንደተደራጁ በማድረግ ከ5 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ሃብት መዝብሮ አካባቢውን በመልቀቅ አዲስ አበባ በመግባት የግል ድርጅት በማቋቋም ሲንቀሳቀስ የፋይናንስ ኦዲተሮች በመሄድ ኦዲት በማደርግ ለፍ/ቤት ቀርቦ ኦዲቱ ተገቢ መሆኑንና ጉድለቱ በመረጋገጡ ይህን በዋናነት የሰራው አካል በ9 ዓመት እና 50 ሺህ ብር ቅጣት፤ ባለቤቱ 8 ዓመት እና ተመሳሳይ የገንዘብ ቅጣት፤ ያስተባበሩ የመሩ ፣ አጠቃላይ ለብክነቱ ተዋናይ ናቸው የተባሉ የማናጅመንት አካላት እያንዳዳቸው 5 ዓመት የጎፋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ እንዲያሳልፍ ተደርጓል"
" በሃዲያ ዞን በአንዳንድ ወረዳዎች ላይ ከባንክ ጋር በመመሳጠር አንድ 6,500 ደሞዝተኛ የሆነ አንድ 0 በመጨመር 65,000 ብር ደሞዝ በባንክ ሲተላለፍለት እንደነበር እንዲሁም ደግሞ 130 ሺ ብር ደሞዝ በወር የሚከፈለው ሰው በማግኘት ግለሰቦቹንም ባንኩ ውስጥም የሚያስተዳድሩት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ገንዘቡ ተመላሽ እንዲሆን እያተሰራ ነው "
" በከምባታ ዞን ወረዳዎች ውስጥ በሌሉ ሰዎች ስም በገዛ ቤተሰብ ስም በባንክ አካውንት ደሞዝ በየወሩ የማስገባት ድርጊት በጥቆማ ተደርሶ ሰዎቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል "
" በሃላባ ዞን የፅህፈት ቤት ኃላፊ ከኃላፊነት ተነስተሻል ስትባል ወዲያው ባንክ ቤት በመሄድ ወደ ግለሰብ አካውን 700 ሺ ብር እንዲዞር በማድረግ ከባንክ ለማውጣት ስትል እርምጃ በመውሰድ፣ተባባሪዎችን በማሰር ሃብቱን ወደመንግስት ካዛና እንዲመለስ ተደርጓል "
https://t.me/EKMEDchannel