26/04/2025
የማያዛልቃችሁን ሰው ለዩ!
ከሚከተሉት ባህሪያት ቢያንስ አንዱን የምታዩባቸው ሰዎች ምናልባት ብዙም የማያዛልቋችሁና አንድ ቀን ለስሜት ጉዳት አጋልጠው የሚሰጧችሁ አይነት ሰዎች እንደሆኑ ጠርጥሩ፡፡
• ራሳችሁንም ሆነ ያላችሁን ነገር በነፃ ስላቀረባችሁላቸው፣ ልክ እንደ ርካሽ የሚቆጥሩና የማያመሰግኑ ሰዎች፡፡
• በዓላማችሁና ለማደግ በምታደርጉት የየእለት ጥረት የሚያላግጡና የሚያሾፉ ሰዎች፡፡
• እየጠፉና እየቆዩ ለአንድ ነገር አማራጭ ሲያጡና ያንን ነገር ከእናንተ ብቻ እንደሚያገኙ ሲያውቁ ብቻ የሚፈልጓችሁ ሰዎች፡፡
• እናንተንና ወዳጅነታችሁን ሳይሆን የእናንተንና ያላችሁን ነገር ብቻ የሚፈልጉ ሰዎች፡፡
• በፍጹም የማያምኗችሁ ሰዎች፡፡
• ስህተታችሁን እየቆጠሩ የሚወቅሷችሁና በፍጹም ይቅር የማይሏችሁ ሰዎች፡፡
• ስህተታቸው እንዳይገኝባቸው እናንተን አሳልፈው የሚሰጡ ሰዎች፡፡
• ሰዎችን ለእናንተ የሚያሙና ስለሰው ክፉን የሚያወሩላችሁ ሰዎች፡፡
• እናንተ የጀመራችሁትን ነገር እነሱ እንደጀመሩት አድርገው ለማሳየት የሚጣጣሩ ሰዎች፡፡
• ለእነሱ መኖር፣ መስጠትና መልካም ነገር ማድረግ፣ ልክ እንደ ግዴታችሁ አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች፡፡
(ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)