Alfredo

Alfredo Alfredo Advisory | Unconditional Servant. We’re empowering minds and businesses through counseling, coaching, consulting, and global advisory services.

10/09/2026
 #ጸሎትህ ያልተመለሰው... ጭጭ ስላላልክ ቢሆንስ?በጸሎትና መንፈሳዊ ሕግ መርህ መሠረት፣ የተመኘኸውን ነገር እንደተሳካ አድርገህ በውስጥህ ከተቀበልከው በኋላ ለሰዎች አለመናገሩ ለስኬቱ እጅግ...
06/09/2026

#ጸሎትህ ያልተመለሰው... ጭጭ ስላላልክ ቢሆንስ?
በጸሎትና መንፈሳዊ ሕግ መርህ መሠረት፣ የተመኘኸውን ነገር እንደተሳካ አድርገህ በውስጥህ ከተቀበልከው በኋላ ለሰዎች አለመናገሩ ለስኬቱ እጅግ ወሳኝ ይመስለኛል፤ ምክንያቱም፦

1. የውጭ ተጽዕኖ እና መጠራጠርን ይከላከላል፦ ነገሩ በውስጥህ ገና በምናብ ደረጃ የተፈጠረ እንቡጥ እውነታ ነው። ይህንን ገና በዓይን ያልታየ እውነታ ለጓደኞችህ ስታወራ ሊጠራጠሩ ወይም ሊያፌዙ ይችላሉ። የነሱ መጠራጠር ደግሞ ያገኘኸውን ውስጣዊ እርጋታና እምነት (Indifference) ይሸረሽረዋል።

2. የውስጥ ኃይልህን (Energy) ያባክናል፦ አንድን ነገር አስቀድሞ ለሰዎች ማውራት አእምሮህ ነገሩ እንደተፈጸመ አድርጎ የፈጠረውን ከፍተኛ ውስጣዊ ኃይል (Subconscious focus) በንግግር እንዲተን ያደርገዋል።

3. የእውነተኛ “ግድ የለሽነት” (Indifference) ምልክት ዝምታ ነው፦ አንድ ነገር በእርግጥ በእጅህ እንዳለ ካመንክ፣ ለሰዎች ለማስረዳት አትጣደፍም። ለምሳሌ በእጅህ ላይ ላለ ስልክ “ስልክ አለኝ” ብለህ እንደማታወራው ሁሉ፣ የጸሎትህን ፍጻሜ ከተቀበልከው ለሰዎች የማውራት ፍላጎትህ ይቀንሳል።

ምን ማድረግ አለብህ?
~ ምስጢርህን ጠብቅ፦ ፍጻሜው በሚታየው ዓለም እስኪገለጥ ድረስ በውስጥህ ያዘው።
~ በውስጣዊ ስሜትህ ብቻ ኑር፦ ማውራት ባማረህ ቁጥር ወደ ውስጥህ ተመለስና ያንን የስኬት ስሜት በጸጥታ ደግመህ ተለማመደው።
~ ተግባርህ እንጂ ቃልህ አይናገር፦ ውጤቱ ሲመጣ አንተ ሳትናገር ውጤቱ እራሱ ይናገራል።

ስለዚህ፣ አእምሯዊና መንፈሳዊ ጥንካሬህን ለመጠበቅ ዝም ማለት ለጸሎትህ መመለስ ከሁሉ በላይ ይጠቅምሃል ባይ ነኝ። የእናተው አልፍሬዶ

አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። ማቴዎስ 6:6

መልካም ሰንበት ይሁንላችሁ💐❤️🙏

 #እውነተኛ ዋስትናየኑሮ ውድነት፣ ውዝፍ እዳዎች እና ስለነገ እርግጠኛ አለመሆን ሁልጊዜ ወደ አእምሯችን የሚያመጣው አንድ የሐሰት መልእክት አለ፦ “አይበቃችሁም፣ ያንሳችኋል፣ አትሻገሩትም!” ...
30/08/2026

#እውነተኛ ዋስትና
የኑሮ ውድነት፣ ውዝፍ እዳዎች እና ስለነገ እርግጠኛ አለመሆን ሁልጊዜ ወደ አእምሯችን የሚያመጣው አንድ የሐሰት መልእክት አለ፦ “አይበቃችሁም፣ ያንሳችኋል፣ አትሻገሩትም!” የሚል። የሚያኖረን ስራችን ብቻ እንደሆነና ምንጫችን ጉልበታችን እንዲሁም እውቀታችን እንደሆነ ሊያሳምነን ይዳዳዋል።
ነገር ግን የሁሉ ነገር ባለቤት የሆነው ፈጣሪ የሚነግረን እውነት ይለያል፦
“ብሩም የእኔ ነው፤ ወርቁም የእኔ ነው፤ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር!” ሐጌ 2:8

የሕይወታችን ዋስትና የሚለካው ባከማቸነው ንብረት መጠን ሳይሆን፣ ማለቂያ የሌለው ሀብት ባለው ፈጣሪ አምላካችን አቅርቦት ላይ ነው!

💡 5ቱ ወርቃማ መመሪያዎች፡
1. በእጥረት ጊዜ ➔ መታመናችንንና ተስፋችንን በእግዚአብሔር ላይ እናድርግ!
2. ሲያትረፈርፈን ➔ትህትና እንላበስ!
3. መንገዶች ሲዘጉ ➔በጸሎት እንትጋ!
4. በረከት ሲፈስ ➔ ምስጋናችንን ሙሉ በሙሉ ለእርሱ እንስጥ!
5. ለሌሎች ስናካፍል ➔ ያለ ስግብግብነት በቅን ልብ እንስጥ!

እነዚህ ከላይ የጠከስኳቸው ሁኔታዎች በሁሉም ሰው ሕይወት ውስጥ አቀሬ ናቸው። ወቅታቸውን ጠብቀው እየተፈራረቁ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ይከሰታሉ።

ቁሳቁስን ከማሳደድ ይልቅ የሀብት ሁሉ ምንጭ የሆነውን እግዚአብሔርን እንከተል! የተሰጠንን በጥበብ እያስተዳደርን፣ በታማኝነት እንሥራ። ሁኔታዎች ቢቀያየሩም እግዚአብሔር ሁሌም ታማኝ ነው!

“እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ... ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።”
ማቴዎስ 6:31-33

መልካም ሰንበት ይሁንላችሁ💐❤️🙏

SundayInspiration GodsPromises

 #ቢዚ ነኝማንም ሰው «ቢዚ ነኝ» ለማለት ካልፈለገ በቀር እውነት ሥራ አይበዛበትም። ይህ ደግሞ እጅግ በጣም የተወጣጠረ ጊዜና ብዙ ሃላፊነት ያለባቸው ሰዎች ጭራሽ ራሳቸውን በእንዲህ ዓይነት ...
23/08/2026

#ቢዚ ነኝ
ማንም ሰው «ቢዚ ነኝ» ለማለት ካልፈለገ በቀር እውነት ሥራ አይበዛበትም። ይህ ደግሞ እጅግ በጣም የተወጣጠረ ጊዜና ብዙ ሃላፊነት ያለባቸው ሰዎች ጭራሽ ራሳቸውን በእንዲህ ዓይነት መንገድ እንደማይገልጹ በማየት ማወቅ ይቻላል። ነገርየዉ ጥቅምም ጉዳትም ቢኖረውም ብዙ አማራጭ በበዛበት በዚህ ዘመን ግን ጉዳቱ ያመዝናል ባይ ነኝ።
ምክንያቱም፦

1. ድክመት ነው። ብዙ ሰው «ቢዚ ነኝ» ሲል በጣም የሰራና እራሱን ያዋደደ ይመስለዋል። ነገሩ የተገላቢጦሽ ነው። ይልቁንም ለሌሎች ሰዎች ጊዜውን ወይም ስራውን እንዴት ማስተዳደር እንዳለበት እንደማያውቅ ያሳያል።

2. «ቢዚ ነኝ» ማለት በሰወች ዘንድ በጣም ተፈላጊ ወይም አስፈላጊ እንደሆንን አጋኖ በማሳየት፤ በቀላሉ የማይሞከር ወይም የማይገኝ ሰው አስመስሎ ያቀርበናል።

3. በተጨማሪም እጃችን ላይ ባለው ተግባርና ስራ (3D) ላይ ብቻ እንድናተኩር በማድረግ ጭንቀት ውስጥ ይከተናል።

4. ⁠በእርግጥ «ቢዚ ነኝ» ማለት በህይወታችን ከማንፈልገው ነገር ራሳችንን የምናርቅበት ትልቁ መንገድ በመሆን ሊያገለግል ይችላል።
አባቶቻችን፤ «ከልብ ካለቀሱ እንባ ግድ አይልም» እንዲሉ ነው ነገሩ።

«ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይም በታች ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።»
መክብብ 3:1

በአልፍሬዶ አድቫይዘሪ
የምክር አገልግሎት ከፈለጉ ይጻፉልን!

በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ትላላችሁ? ሀሳባችሁን ኮመንት ላይ አጋሩን።

#ቢዚነኝ #የአመራርክህሎት #የአእምሮጤንነት

ይህ ምግብ ምንድነው እስቲ ገምቱ?
22/08/2026

ይህ ምግብ ምንድነው እስቲ ገምቱ?

Address

Johannesburg

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 12:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alfredo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Alfredo:

Shortcuts

Share