Ethio Southafrica/ ኢትዮ ሳውዝ አፍሪካ መልቲ ሚዲያ

Ethio Southafrica/ ኢትዮ ሳውዝ አፍሪካ መልቲ ሚዲያ Ethio-South Africa Multimedia is based in South Africa.

We are devoted to broadcast news and analysis on socio-political, economic, education issues as well as top quality entertainment & sport.

27/03/2024
27/03/2024

በደቡብ አፍሪካ የአሲድ ጥቃት የደረሰበት ቡሩኬ እና ቤተሰቦቹ ከኮሚኒቲ አመራር ጋር በመሆን በብሩኬ ስም የሚጭበረበረውን አካውንት በመቃወም እና ወቅታዊ እርዳታ ለብሩኬ የሚያስፈልገውም ትክክለኛውን መረጃን በደቡብ አፍሪካ የተዋቅውረው ኮሚቴ መግለጫ ሰተዋል ብሩኬም በራሱ አንደበት ያስተላለፈው መልእት ይከታተሉ

ጓዳችን ወንዴ ወደ ሀገረ አሜሪካ በቅርቡ የመጡትን ልጆቹንና ቤተሰቡን ናፍቆቱን ሳይጠግብ በደረሰበት ህመም ምክንያት ይችን አለም ተለይቶ ወደማይቀርበት ወደፈጣሪው ሄዷል ወንዴ ሰው አክባሪና እ...
13/08/2023

ጓዳችን ወንዴ ወደ ሀገረ አሜሪካ በቅርቡ የመጡትን ልጆቹንና ቤተሰቡን ናፍቆቱን ሳይጠግብ በደረሰበት ህመም ምክንያት ይችን አለም ተለይቶ ወደማይቀርበት ወደፈጣሪው ሄዷል ወንዴ ሰው አክባሪና እጅግ ትሁት ሰው ነበር ለቀብር ማስፈጸሚያው ይህን ጎፈንድ በማድረግ ወገናዊ ሀላፊነታችንን እንወጣ

አቶ ወንድወሰን ጌታቸው ጫካ ቀደም ብሎ ይኖርበት ከነበረበት ደቡብ አፍሪካ ወደ አገረ አሜሪካ በ 2015 በመምጣት በቨ… Elisabeth Getachew needs your support for ለአቶ ወንድወሰን ጌታቸው ጫካ የቀብር ስነ ስ...

12/08/2023

የሀዘን መግለጫ

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያውያ አባት አቶ ወንድወሰን ጌታቸው በሞት ተለየን

አቶ ወንድወሰን ጌታቸው ጫካ የስደት ህይወትን ከተቀላቀለ ወዲህ ብዙም ሳይቆይ እ/ኤ/አ በ2001 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ወደ ነጻነቷ ምድር ደቡብ አፍሪካ ገባ::

በደቡብ አፍሪካ መኖር በጀመረበት ወቅት ከእርሱ ቀደም ብለዉ ከተሰደዱ ኢትዮጵያዊያንጋር ተቀላቀለ:: ከዚያን ግዜ ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋሻና መከታ በመሆን ማንም በማንም እንዳይጠቃ ማንም ማንንም እንዳይበድል ሲያግዝ የኖረ የህዝብ አለኝታ ሲሆን ዛሬ ሐበሻዉ ማሕበረሰብ እየሰራ ለሚኖርበት የንግድ ስፍራ መከበር ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመሆን አለኝታነቱን ያሳየ የስደት በረከታችን ነበር።

ወንደሰን ጌታቸው ጫካ እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 2001 በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ መኖር እንደ ጀመረ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ማህበር አባል በመሆን በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ
ማህበራዊ እና ባህላዊ እሴቶች ላይ በንቃት በመሳተፍ የወያኔ የዘር ፖለቲካን ጭቆናን እና ከፋፍሎ የመግዛት ፖሊሲዎችን በመቃወም በተለይም በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚፈፀሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በማጋለጥ አሉታዊ ተፅእኖ መፍጠር የቻለ ጀግና ነዉ።

ለኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ማህበር በደቡብ አፍሪካ በምክትል ሊቀመንበርና በምክትል ጸሐፊነት እና በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴነት እንዲሁም በህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ላይ እንዲያገለግል የተጣለበትን ሐላፊነት ግምት ዉስጥ በማስገባት ህዝባዊነቱን በተግባር አሳይቷል::
በደቡብ አፍሪካ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ( ዲፓርትመንት ኦፍ ሆም አፊርስ) ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የስደተኝነት መስፈርትን አያሟሉም በማለት አቋም በያዘበት ወቅት ላይ
ግምባር ቀደም ተሰላፊ በመሆን የሚመለከተዉ አካል ውሳኔውን እንዲያጥፍና ኢትዮጵያዊያን የስደተኝነት መብታችን እንዲከበር ጉልህ ሚና ተጫውቷል።
በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት
የአለም አቀፍ ዘላቂ እና አስተማማኝ የእድገት ጉባኤ ላይ የወያኔ ኢህአድግ ሰባዊ መብት ጥሰትን ለማጋለጥ ስደተኛዉ ማህበረሰብ ያዘጋጀዉን ሰላማዊ ሰልፍ ተገን ባደረገ መልኩ
የወያኔ መንግስት አስተባባሪዎችን በሀሰት በመክሰስ ሂድቱን ለማደናቀፍ የሞከረዉን ሴራ እንዲከሽፍ ከ 2000 በላይ ስደተኞችን በማስተባበር ለዓለም አቀፉ መሀበረሰብ
የወያኔን የሰብአዊ መብት ጥሰት ጸሀይ እንዲሞቀዉ ታላቅ ተግባር አከናውኗል።
እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2004 በኢትዮጵያ አስራ አምስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ውህደት በፈፀሙበት ወቅት የህብረቱ ሊቀመንበር የሆኑትን ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በደቡብ
አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተጋብዘዉ በክብር በተገኙበት ወቅት በተከፈተዉ ብሔራዊ አጀንዳ ላይ በመሳተፍ ታሪክ የሚዘክረው ተሳትፎ አድርጓል።
እ.ኤ.አ. በ 2005 ምርጫ 97 ዓ/ም በሐገራችን ኢትዮጵያ በተደረገዉ ምርጫ ምክንያት ዉጤቱን በተቃወሙ ንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመዉን ኢፍትሀዊ እልቂት አምርሮ በመቃወም ጉዳዩ ለሚመለከታቸዉ ተቀማጭነታቸው ደቡብ አፍሪካ ለሆኑ የአለም አቀፍ ተቋማት ቅሬታ ለማሰማት ስደተኛዉን መሀበረሰብ በማስተባበር እና
ጥሪዉን በማሰማት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የንጹሐን ዜጎች ድምጽ በመሆን ታላቅ ድርሻ ተወጥቷል።

ወንድወሰን ጌታቸው ጫካ ከዚህ ተጨማሪ ማህበረሰባችንን በማስተባበር በታዋቂው የነፃነት ታጋይ እና የአፍሪካ አባት የኔልሰን ማንዴላ አለም አቀፍ ቀንን ምክንያት በማድረግ ከሀውቴን የጤና ቢሮ ( ሄልዝ ዲፓርትመንት ) ጋር በመተባበር ለኦሬንጅ ፋርም የህፃናት ማሳደጊያ
እንዲሁም በአልበርተን የአካለ ስንኩላን ህፃናት ማሳደጊያና ማስተማሪያ ተቋም በማገዝና እና በየአመቱ የሚደረገውን እርዳታ በማስተባበር ደረጃ የበኩሉን ጥረት በማድረጉ በደቡብ አፍሪካ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ከደቡብ እፍሪካ ዜጎች እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ አካላት ታላቅ ምስጋና እና እውቅና እንድናገኝ ታላቅ ሚና ተጫውቷል።

ብዙዎች ሲጨነቁና ሲቸገሩ ገንዘብ በማሰባሰብ እና በማገዝ የማይደክመዉ በኢትዮጵያ ያለአግባብ በግዞት ለታፈኑ የህሊና እስረኞች ባገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ ከመጮኽ እልፎ ለወገኑ ተቆርቋሪ ጠንካራ እና ታታሪ ቤተሰቡን የሚወድና
ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን ሰዉ የተባለ ሁሉን የሚወድ በማህበራዊ ህይወቱ ውስጥ ተቆርቋሪና ተፅኖ ፈጣሪ ባሕሉን ሃይማኖቱን ባንዲራዉን አክባሪ እጀ ሰፊ ጀግና ነበር።

ለቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ, ለትግል አጋሮቹ እንዲሁም ለመላዉ ነጻነት ፈላጊ ኢትዮጵያዉዊያን
ሁሉ መፅናናትን እና ብርታን እንዲሰጥልን እየተመኘን የወንድማችን ነፍስ በአጸደ ገነቱ
እንዲያኖርልን ፈጣሪያችንን እንማጸናለን::

ከ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር አባላት

መልካም ዜና ከተባበሩት ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ማህበር ደቡብ አፍሪካ
02/05/2023

መልካም ዜና ከተባበሩት ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ማህበር ደቡብ አፍሪካ

Address

Johannesburg
2091

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Southafrica/ ኢትዮ ሳውዝ አፍሪካ መልቲ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Ethio South Africa MultiMedia

Ethio-South Africa Multimedia is based in South Africa. It aims to provide eye-opening information to the Ethiopian community. We are devoted to broadcast news and analysis on socio-political, economic, education issues as well as top quality entertainments and sports. COMMENT, LIKE, SHARE AND SUBSCRIBE TO INTERACT WITH ALL OUR SOCIAL MEDIA PLATFORMS. FACEBOOK: www.ethiosouthafrica.oc.za@ethiosouthafricamultimedia" rel="ugc" target="_blank">www.ethiosouthafrica.oc.za@ethiosouthafricamultimedia TWITTER: @EthSAMultimedia https://twitter.com/EthSAMultimedia YouTube:https://www.youtube.com/channel/UCSsTPi3wGdcP4blILdBYFaA