14/03/2025
ዳግማዊ መንግሥቱ ኃይለማርያም የሆነው አቢይ አሕመድ በኤርትራ ላይ ጦርነት ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የአደባባይ ሃቅ ነው። እውነት ለመናገር [የግዴታ] ካልሆነ በስተቀር የኤርትራ መንግሥት ከአቢይ ጋር ለመዋጋት ፍላጎት የለውም። ነገር ግን፥ አቢይ ወረራ እስከፈፀመበት ድረስ "አማራጭ" ስለሌለው ራሱን ለመከላከል ይዋጋል። የኤርትራ መንግሥት የሚዋጋው ግን ብቻውን አይደለም።
የኤርትራ መንግሥት አቢይ አሕመድ የቃጣበትን ወረራ ለመመከት የግዴታ ብቻውን ሳይሆን በራሱ አቢይ ላይ ያኮረፈውን የሕወሓት ታጣቂ ክንፍ ይዞ ነው። ይኼ [የኤርትራ መንግሥትና የወያኔ ጥምረት] ጊዜያዊም ቢሆን ለኢሳያስ አማራጭ ስለሌለው እንደ plan B ተጠቅሞ መዋጋቱ አይቀሬ ነው።
እዚህ የኃይል አሰላለፍ ላይ ግን ማለትም አቢይ አሕመድ ከኢሳያስና ደብረጽዮን ጥምረት ጋር ሲገጥሙ ውጤቱ እንዲህ በቀላሉ የሚገመት አይደለም። ምናልባትም የኃይል መመጣጠን ስለሚኖር ቶሎ አሸናፊ ላይኖር ይችላል። ከየራሳቸው አቢይና ኢሳያስ (ደብረጽዮን) ባሻገር የአረቡ ክፍልም በተዘዋዋሪ በሁለቱ ሐገሮች ጎራ ተሰልፎ እንደሚያዋጋ ሐቅ ነው። ሳዑዲዓረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች፣ ቃጣር፣ ግብፅና መሰል ሌሎች ፀረ-ኢትዮጵያ ሐገራት ይሳተፉበታል።
በእኔ አተያይ አቢይ ጦርነቱን ቢፈልገውም የኢሳያስ-ደብረጽዮን ጥምረት ወታደራዊ አሰላለፍ የኃይል ሚዛን ስለሚቀይር ምናልባትም ጦርነቱ የማይደረግበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል። አቢይ [በአሰብ] ጉዳይ ከኤርትራ ጋር ሊዋጋ የነበረውን አጀንዳ ለጊዜው አጥፎ ቅድሚያ ወያኔን ለማጥፋት ሊዋጋ ይችል ይሆናል። ግን ደግሞ "ከወያኔ መጥፋት በኋላ አማራውስ" የሚለው ጥያቄ እንደሚመጣበት ሃቅ ነው። ምክንያቱም የኦሮሞ ኃይል በአማራ ጉዳይ የስልጣን ማስጠበቂያው ወያኔ ነው። [እንበልና] ወያኔን ገሸሽ ካደረገ በኋላ ቀጥሎ ወደ ኤርትራ መሄዱ አይቀሬ ነው። ነገር ግን [ነቄው] ኢሳያስ አፈወርቂ የአቢይን አካሄድ ስለሚያውቅ ቀድሞ ወያኔ survive እንዲያደርግ ሊረዳው ይችላል። ምክንያቱም ወያኔን ከጨረሰ በኋላ ወደ ኤርትራ እንደሚሄድ ስለሚያውቅ።
ሌላው ደግሞ፥ ምናልባትም አቢይ ወያኔ ላይ ጦርነት ቢከፍት ጦርነቱ ከመጠናቀቁ በፊት ኢሳያስ የአሰብ ወደብን ቀድሞ ለአረቦች ሊያከራየው ይችላል።